tgindex
አብዱ ሰመድ || ᗩᗷᗞᑌᔑᗴᗰᗴᗞ

አብዱ ሰመድ || ᗩᗷᗞᑌᔑᗴᗰᗴᗞ

Статистика
@Ilellah1арабский

{ إِنَّ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ سَیَجۡعَلُ لَهُمُ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وُدࣰّا } • • • እነዚያ ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ አልረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል • • •

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
449
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
210
22 постов
Вовлечённость
46,8%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
49
1/48двое суток
56
1/72трое суток
60

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • ሲራ እያዳመጥኩ ሸይኻችን አድሀም ስለ አይሁዶች ያወራው አንድ ታሪክ በጣም አስገርሞኛል ። ከክርስቶስ ልደት ሰባ አመት በፊት የሮሙ ቀይሰር እየሩሳሌምን ወሮ ነበር ። በወቅቱ በቁድስ ይኖሩ የነበሩት አይሁዶች ነበሩ ። ከበባው ለአምስት ወራት ከዘለቀ በኃላ አይሁዶቹ እጃቸውን ይሰጣሉ ። የሮሙ ቀይሰርም አንድ ትዕዛዝ ያውጃል ። ይሀውም እያንዳንዱ አይሁዳዊ አባወራ : ሚስትና ልጆቹን እንዲሁም በህይወት ካሉ አባትና እናቱን ጭምር እ ን ዲ ገ ድ ል ያዛል ። በምትኩም እነሱን እንደማይገላቸው ቃል ይገባላቸዋል ። አስገራሚው ነገር‹የቀይሰሩ ትዕዛዝ ሳይሆን የነሱ ያለማቅማማት መፈፀም ነው› ይላል ሸይኽ ። ራሳቸውን ለማዳን የታዘዙትን ፈፀሙ ። ወላጆቻቸውን ሚስቶቻቸውን ልጆቻቸውን ሰውተው ነፍሳቸውን ነፃ አወጡ ። ይሄን ታሪክ ሳዳምጥ ገዛዊያን ምን አይነት ሰዎችን እየተጋፈጡ እንደሆነ ነበር እያሰብኩ የነበረው .....

  • ኢስላም የቤተሰብ ስርዐትን አስመልክቶ ቋሚና የማይቀር ህግ አለው ። ይህ ህግና ስርዐት ከእስልምና ሰዋቢቶች ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋ በትዳር ጎጆ ውስጥ ሲጣመር ኢስላም ለነዚህ ሁለት ሸሪኮች የየራሳቸውን ኃላፊነት ሠጥቷቸዋል ። ይህ የኃላፊነት ክፍፍል ባዩሎጂካል ተፈጥሮኣቸውን እና ሳይኮሎጂካል ስሪታቸውን መሰረት ያደረገ ነው ። እነዚህ ሁለት የተለያዩ ፆታዎች በአንድ ጎጆ ውስጥ ተመሳሳይ ሚና ሊኖራቸው አይችልም ። ወንድ ልጅ ቤቱ ያመጣትን ሴት የመቀለብ የማልበስ ፣ የመንከባከብ እና የሚያስፈልጋትን ነገር ሁሉ የማሟላት ኃላፊነት አለበት ። ልጆቹንም እንደዛው ። ይህን ቤተሰባዊ ግዴታውን ለመወጣት በየዕለቱ ሰርቶ መግባት ይኖርበታል ። ከዚህም ውጪ ወንድ ልጅ ማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይም ከፊት ተሰላፊ ነው ። እነዚህን ከግንዛቤ በማስገባት ኢስላም ባሎችን ቀዋም/መሪ/አስተዳሳሪ እንዲሆኑ አድርጓል ። ይሄ ከላይ እንዳነሳሁት ቤት የሚቆምበት መሰረታዊና የማይሻር የአላህ ድንጋጌ ነው ። ሚስት ደግሞ ይህን ኃላፊነቱን በአግባቡ ለሚወጣው ባለቤቷ እንደ መሪነት ላለበት ኃላፊነት ቀናኢና ታዛዥ (ቃኒታህ) መሆን ይገባታል ። በዚህ ሂደት ባለቤቷ ቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ላሉበት ማህበራዊ ኃላፊነቶች አጋዥ ትሆናለች ፣ እራሷንም ሆነ የሱንም ሚልኮች ትጠብቃለች ። እነዚህ ሷሊሃት የሚባሉ ሚስቶች መገለጫዎች ናቸው ። ይህን እንደ አስል/መሰረት ከተቀበልን ፣ ከአንዳንድ ተጨባጮች አንፃርና አሁን ካለንበት የኑሮ ሁኔታ አንፃር ሚስት ኑሮኣቸውን ለማሻሻልና ባለቤቷንም ለመርዳት ወይም በገንዘብ እራሷን ለመቻል ወጥታ ሀላል ብትከስብና በገንዘቧ ብትነግድ የሚከለክላት ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው ፣ ባልም እንዲሁ ቤት ውስጥ ባሉ ስራዎች በቅንነት ሚስቱን ቢያግዝ የመልካምነቱ መገለጫ ነው .........ልጆቿን በቅርበት እየተከታተለች በእናትነት እቅፏ ስር አድርጋ በተርቢያ ብታሳድጋቸውና እሷም ሆነች ልጆቹ ችግር ሚባል ሳይነካቸው ተቀማጥለው እንዲኖሩ እሱ ብቻ ወጥቶ ቢለፋ የተሻለና መሰረት ከመሆኑ ጋ ማለት ነው ። የሞራል ልዕልና ያለውን ማህበረሰብ ለመገንባት ከፈለግን ሚናዎች ሊደበላለቁ አይገባም ። እኛ እንደ ኢስላም ቁርዐን ያስቀመጥልን መስመር አለ የቤተሰብ ህይወት ላይ ደግሞ ምርጥ ሞዴል አለልን ። ሴት እናት ሆና ሚስት ሆና እህትና አክስት ሆና ስላላት ሁቁቆች ማንም ሊያስተምረን አይችልም ። ከሁሉም የሚያብቃቃ በጣም በቂ የሆነ አስተምህሮ አለን !!!

  • ከሶስቲ ሺ ዓመታት በፊት የነበሩት ነብዩላህ ሱለይማን አሁን በ20ኛው ክ/ዘመን ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ሁሉ ብዙ ርቀው ያለፉ ይመስለኛል ። የመን የሚገኝን ትልቅ ዙፋን በአይን ብልጭታ ፍጥነት እንዲመጣ ማድረግ (ያሀን የሚያክል ዙፋን በspeed of light ነው የመጣላቸው ማለት እንችላለን) ፣ ሁድሁድ የምትባለዋ ወፍ የምትሰራላቸው የ intelligence ስራ ፣ ለቢልቂስ የገነቡት አስገራሚ ቤተ መንግሥት ( ከውስጥ ዥረት የሚፈስበትና የላይ ንጣፉ መስታወት የሆነ )  ፣ ንፋስ የሁለት ወር መንገድን በጥቂት ሰኣታት የሚያደርሳቸው ነገር ( በኛ ዘመን ጄት በሉት) ፣ የምድርን ውብ ማዕድናት ከየብስም ከባህርም ያለገደብ መጠቀም መቻላቸው (Mining) .....  ሱረቱል አን-ነምል ተፍሲር   ከሸይኻችን እያዳመጥን የተከተበ  🙂

  • አብደላህ ሩሽዲ እንደሚለው ገዛህ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ለሙስሊሙ ወይም ለዓረቡ ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ህዝብ ውርደት ነው ። በዚህ ልክ መጠለያ ድንኳን ውስጥ እየኖሩ ያሉ ያልታጠቁ ህዝቦች ላይ : በዘመናዊ ቦምቦች Massacre እየተፈፀመ የዓለም ህዝብ ይሄን ነውር አለማስቆሙ በቶሎም ይሁን ዘግይቶ ዋጋውን ይከፍላል/እንከፍላለን ❗️ ገዛህ ተረስታለች/ረስተናታል - عفا الله عنا 😔 (ምስሉ የዛሬ ነው)

  • የጀላሉ አድ-ዲን አስ-ሱዩጢ ተርጀማ በጥቂቱ ሸይኽ ሙሐመድ ሃሚዲን

  • ዑምራ የሄዱ ሰዎች ስለመዲና የሚያወሩት ነገር ለየት ይላል ። ሁሉም በሚባል ደረጃ ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው የማያውቅ እጅግ የተለየ ስሜት እንደተሰማቸው ፣ የሚገርም ሰኪና እንዳገኙና ይህ ነው ተብሎ የማይገለፅ ነገር ከተማው እንዳለው ይናገራሉ ። እርግጥ ይሄ ሁሉ አያስደንቅም : አላወቁም እንዴ ? ከተማውኮ ለሰማይና ለምድር የከበዱት ፣ ከአዋቂና ጥበበኛው ጌታ ቁርዐንን የተሰጡት ፣ የፍጡራን ሁሉ አማላጅ የሆኑት አሽረፉ ኸልቂላህ ክቡር ገላ ያረፈበትኮ ነው ። እንዴት ነው ታዲያ ሰኪና ማያገኙት ? እንዴት ነው በደስታ የማይሰክሩት ? እንዴት ነው አይናቸው ማያነባው ? እንዴት ነው Emotional ማይሆኑት ? إنها مدينة رسول الله ﷺ 💚

  • የተከበረ እውቀት በንጹሑ ቀልብ ውስጥ እንዴት ወደ "ጨለማ" ተቀየረ? ☆☆☆ ​በጥንታዊቷ ደማስቆ መተላለፊያዎችና በታሪካዊዎቹ ረዋሒያ እና አሽረፊያ መድረሳዎች ግንብ መካከል፣ አል-ኢማም አል-ነወዊ (631–676 ሂ) የተባሉ ታላቅ ዓሊም ይኖሩ ነበር። አል-ነወዊ ተራ ተማሪ አልነበሩም፤ የእውቀት ጥማት በደም ስሮቻቸው ውስጥ ይወራጭ ነበር። ከሌሊቱም ሆነ ከቀኑ አንዲትም ሴኮንድ ቢሆን ያለ ንባብ፣ ያለ ድርሰት ወይም ያለ ማሰላሰል አያሳልፉም ነበር። ​ሆኖም ግን፣ ወደ ታላቅነትና አላህን ወደ መፍራት የሚያመራው መንገድ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለም፤ አንዳንዴም የግራ መጋባት እሾሆች ያጋጥሙታል። ​በእውቀት ፍለጋቸው መጀመሪያ ላይ፣ በወጣቱ አል-ነወዊ ልብ ውስጥ ለሕክምና እውቀት ድንገተኛ ፍላጎት አደረ። የኢብኑ ሲናን "አል-ቃኑን" የተሰኘ ገናና መጽሐፍ ገዝተው፣ ወደ ምስጢራቱ ለመጥለቅ ቆረጡ። ነገር ግን ትልቁ ገጠመኝ ጽሐፉ ገጾች ላይ ሳይሆን፣ መጽሐፉ በነፍሳቸው መስተዋት ላይ ባጠላው ድንገተኛ ጥላ ላይ ነበር! ​ኢማም አል-ነወዊ በገዛ አንደበታቸው ገልጸውታል እንዲህ በማለት፡- ​"عَلِقَ ببالي الاشتغالُ بالطب، فاشتريتُ كتاب(القانون) وعزمتُ على الاشتغال فيه، فأظلمَ عليّ قلبي، ومضت عليّ أيامٌ لا أقدرُ على الاشتغال بشيء، ففكرتُ في أمري: من أين دخل عليّ هذا؟ فألهمني اللهُ أن الاشتغال بالطب هو السبب، فبعتُ 'القانون' في الحال، وأنار قلبي ورجعت إلى ما كنت عليه." ​(በልቤ ውስጥ የሕክምናን ትምህርት የመማር ፍላጎት አደረ፤ በመሆኑም (አል-ቃኑን)የተሰኘውን መጽሐፍ ገዝቼ በእርሱ ለመጠመድ ወሰንኩ። በዚህም ምክንያት ልቤ ጨለመብኝ፣ ምንም ነገር መስራት የማልችልባቸው ቀናትም አለፉ። ከዚያም "ይህ ነገር ከየት ገባብኝ?" ብዬ አሰላሰልኩ። አላህም ሕክምናን መማሬ ምክንያቱ እንደሆነ ገለጠልኝ፤ ወዲያውኑ (አል-ቃኑን)የተሰኘውን መጽሐፍ ሸጥኩት፣ ልቤም በራ፣ ወደነበርኩበትም ተመለስኩ!) ​የሕክምና እውቀት — ያለ ምንም ጥርጥር — የሰውን ልጅ ሕይወት ከሚታደጉ እጅግ የተቀደሱ ጥበቦች አንዱ ነው። እንደውም ኢማሙ አል_ዘሀቢ (ሲየር አዕላም አል-ኑበላእ ላይ እንደጠቀሱት ታላቁ ኢማም አሽ-ሻፊዒይም፡- "የእውቀት ግማሽ!" በማለት ለህክምና አክብሮታቸውን ገልጸዋል። ታዲያ ይህ የከበረ ጥበብ በኢማሙ አል-ነወዊ ልብ ውስጥ እንዴት የግራ መጋባትና የጨለማ መንስኤ ሊሆን ቻለ? ​መልሱ የሕክምናን ጥበብ በማሳነስ ውስጥ አይደለም፤ ይልቁንም በሰው ልጅ ነፍስ ምስጢር፣ በትኩረት ህግ እና አላህ እያንዳንዱን ባሪያው ለተገቢው ተልዕኮ የመረጠበት ጥበብ (ተውፊቅ) ውስጥ እንጂ:: ​ 📍አል-ነወዊ በዲን እውቀት ውስጥ እውነተኛ አሻራ ማሳረፍ ሙሉ ትኩረትን እንደሚጠይቅ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። እንደ ሕክምና ያለ ሰፊና ሙሉ ጊዜን የሚጠይቅ ትምህርት ውስጥ መግባት ደግሞ ከእስልምና እውቀቶች መስመር ጋር መጋጨቱና በሁለት ግዙፍ ዓለማት መካከል መበታተኑ አይቀሬ ነበር። መበታተን ደግሞ የእንቅስቃሴን ፍጥነት የሚገታ፣ የእውቀትንም ብርሃን የሚያጠፋ የመጀመሪያው አደጋ ነው። ​ ​📍አንድ ሰው አላህ ለእርሱ ከተመደበለት ትክክለኛ የሕይወት መስመር ሲወጣ በነፍሱ ውስጥ የሚፈጠረውን የጭንቀትና ምቾት የመንሳት ምልክት ያሳያል። የጠራች ነፍስ ከትክክለኛው ምህዋሯ በጥቂቱም ቢሆን ስትወጣ ወዲያውኑ የባዕድነትና የጨለማ ስሜት ይሰማታል። ​ ​📍እንደ ኢብኑ ሲና ድርሰቶች ያሉ የጥንት የሕክምና መጻሕፍት፣ በሕክምና ተግባርና በጥንታውያን የግሪክ ፍልስፍና የተቀላቀሉ ነበር። ኢማሙ አል-ነወዊ በእነዚያ ፍልስፍናዊ ጥልቅ አስተሳሰቦች ውስጥ በሐዲሥና በፊቅህ እውቀቶች ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን ንጹሕ አእምሮ የሚያደፈርስ ሆኖ አግኝተውታል። ​ ​📍የኢማሙ አል-ነወዊ ገጠመኝ መንገድ ብቻውን የቆመ ክስተት አይደለም፤ ቃላትና የጽሑፍ ሀሳቦች በታላላቅ ዑለሞችና ደራሲያን ላይ እንኳ ሳይቀር አሉታዊ የሆነ ከፍተኛ ተጽእኖ የማሳደር አቅም አላቸው። ​ሶሪያዊው ታላቁ ዓሊም፣ ደራሲና አሰላሳይ ሸይኽ ዐሊ አል-ጠንጣዊ (1327–1420 ሂ) በወጣትነታቸው ከሩሲያ ልብወለዶች አንዱን አንብበው በነፍሳቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮባቸው እንደነበር ገልጸዋል። ​እርሳቸው በጻፉት "አል-ዚክረያት" መጽሐፋቸው ላይ የሚከተለውን ብለዋል፡- ​"كادت تُؤثّر في ديني، وتُفْسِد فِكْري، لولا أنْ أنقذني اللهُ مِن شَرِّها.." ​(አላህ ከክፋቱ ባይጠብቀኝ ኖሮ በሃይማኖቴ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድርና አስተሳሰቤን ልያበላሽብኝ ምንም አልቀረውም ነበር..) ​ሸይኽ አል-ጠበንጣዊ ትልቅ ዐሊም እና የበሰለ ደራሲ ሆነው ሳለ ስለ አንድ ልብወለድ ይህንን ተናግረዋል! ታዲያ የመንፈስ ጥንካሬውም ሆነ የእውቀት መሠረቱ አነስተኛ የሆነ ተራ ሰው በራሱ አእምሮ ላይ ውድቀትንና የሐሳብ ጥፋትን አይፈራምን? ​ የአል-ነወዊ ከኢብኑ ሲና መጽሐፍ ጋር የነበራቸው ታሪክ እና የጠንጣዊ በልብወለዶች ላይ የነበራቸው ልምድ ታሪካዊ ወሬዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ በህይወት ውስጥ አሻራን የመተውና አእምሮን ከመጥፎ ሐሳብ የመጠበቅ ታላቅ መመሪያ ናቸው፡: አንዳንዴ ሀሳቡ ማራኪ፣ ፕሮጀክቱ የተከበረ፣ ሙያውም የላቀ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አላህ ለአንተ ከመደበልህ ተልዕኮህና ከእውነተኛ ፍላጎትህ ጋር ላይጣጣም ይችላል። አዲስ እርምጃ ወይም ንባብ ፍላጎትህን እንዳጠፋው፣ ወይም በልብህ ውስጥ ጥርጣሬንና ጨለማን እንዳሳደረብህ ካወቅህ ወዲያውኑ ቁም እና አካሄድህን መርምር፤ አካል እንደሚታመመው ሁሉ ቀልብም በባዕድ ሐሳቦች ይታመማል። በነወዊ አቋም ውስጥ ትልቁ ነገር ልባቸው ብርሃኑን ይመልስ ዘንድ መጽሐፉን ወዲያውኑ ለመሸጥ የወሰዱት ፈጣንና ቆራጥ ውሳኔ ነው፤ በጠንጣዊ ልምድ ውስጥም ቢሆን ወደ ንባብ ከመግባት በፊት ባለሙያዎችን ማማከር አስፈላጊ መሆኑን ማሳሰባቸው ነው። ​ኢማሙ አል-ነወዊ በ45 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት የ"አል-ቃኑን" መጽሐፍን ባይተዉ ኖሮ፣ ምናልባት ታሪክ ሌላ አንድ ጎበዝ ሐኪም ያገኝ ነበር፤ ነገር ግን ህዝበ ሙስሊሙን ከ "ሪያዱ አስ-ሷሊሒን" ከ "አል-አርበዒን አል-ነወዊያ" እና ከ "አል-ሚንሃጅ" የመጨረሻ ሀብቶች ያጎድል ነበር። አል-ነወዊ ተልዕኮአቸውን ስላወቁ፣ ብርሃናቸው የት እንዳለ ስተረዱ፣ እና ለልባቸው የሚበጀውን ስለለዩ በዘመናት መካከል የብዙዎችን መንፈስና አእምሮ ፈውሰዋል! አላህ ይጠብቀን! © Nesru Khedir/ነስሩ ኸድር

  • «ሶሻል ሚዲያ ሳይመጣ በፊት ሞኝን ቤተሰቦቹ ብቻ ነበር የሚያውቁት» ይላሉ ሸይኽ ዓዲል ። ምንም አይነት የታወቀ የኢልም ሰነድ የሌለው ፣ ከእከሌ ሸይኽ ላይ ነው ኢልም የያዘው ወይም እከሌ ሸይኽ ናቸው ኢጃዛ የሰጡት ተብሎ የሚነገር የእውቀት ውርስ የሌለው አንድ ወጣት ግለሰብ ጀርመን ተቀምጦ .... ለእስልምና ባበረከቱት አስተዋፅኦ ዑማው በጅምላ የተቀበላቸው ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶችን እንደ ቀልድ ከእስልምና እና ከሱና ያስወጣቸዋል ። ይህን ለማድረግ ካሜራ ማስተካከልና ማይክ Adjust ማድረግ ብቻ ነው የሚጠበቅበት ። ከዛ ፕሮቶኮሉን ጠብቆ ይመጣና ኢማም አቢ ሀኒፋ ሙብተዲእ ናቸው ነወዊ አላህን ሳያውቁ ነው የሞቱት 😥 ጀላሉ አድ-ዲን አስ-ሱዩጢ ከእስልምና ምንም ድርሻ የላቸውም እያለ ታላላቅ አኢማዎችን ቀለል አድርጎ ይዘልፋል ። ጭራሽ ለዚህ የጅህልና ተግባሩ አላህን ምስክር ያደርጋል ። ሰውዬው ካለፉትም በዘመናችን ካሉትም ዑለሞች የሚቀረው የለም ፣ ሁሉንም ካልሀየስኩ ሁሉንም ካልተቸው የሚል ደረቅ ሞጋች ነው። በጣም አሳዛኙ የሱ እንዲህ ድንበር ማለፍ አይደለም ፣ ይህን ሰው ከቁም ነገር ቆጥረው የሚከቱሉና ጭራሽ እንደ ትልቅ ዓሊም የሚመለከቱ ብዙ ግለሰቦች መኖራቸው ይበልጥ አሳሳቢ ነው ። መሰል ታፊህ ሰዎች እንደ ቁድዋ መያዛቸው ከቂያማ ምልክቶች አንዱ መሆኑ ብናውቅም በዚህ ልክ ግን ዲፋዕ የሚያደርግለት ተከታይ ማፍራቱ አስገራሚ ነው ። አኢማዎቻችን በየዘመናቸው እስልምና ከነ መስደሩ ተጠብቆ እንዲቆይ የራሳቸውን ድርሻ ተወጥተው ከአላህ ጋ ተገናኝተዋል የማንም ተራ ግለሰብ ተነስቶ ስላንቋሸሻቸው ከክብራቸው ላይ የሚቀነስ ምንም ነገር የለም ፣ እነሱ ፀሀይ ናቸው በየዘመኑ ማብራታቸውን ይቀጥላሉ ።።።።

  • ከምድር ስር የተወለደ ታላቅነት ​(የ አል-መብሱጥ ኪታብ ታሪክ) ​☆☆☆ ​በታሪክ ውስጥ ስለ ጽናትና እውቀት ብዙ ተጽፏል፤ ነገር ግን ከአስቸጋሪ መከራና የጭቆና ጨለማ ውስጥ ተወልደው ዓለምን ያበሩ ሥራዎች ጥቂት ናቸው። ከእነዚህ ድንቅ የታሪክ ክስተቶች መካከል ደግሞ የእስልምና የህግ ሳይንስ (ኡሱል አል-ፊቅህ) ሊቅ የሆኑት እና በ483 ሂጅሪያ ላይ ያረፉት ኢማም አል-ሰርدረኽሲ ያዘጋጁት "አል-መብሱጥ" ኪታብ ታሪክ ነው። የዚህ 30 ቅጽ ያለው ግዙፍ መጽሐፍ የአጻጻፍ ታሪክ እጅግ አስደናቂና ልብ የሚነካ ነው። ​አዘጋጁ ኢማም አል-ሰረኽሲ የታወቁ ዓሊም ነበሩ። የ"ኦዝጀንድ" ከተማ ገዥ ያወጣውን ኢ-ፍትሐዊ አዋጅ ተቃውመው እውነትን በመናገራቸው ገዢው ተቆጣ። የእርሳቸውን ድምጽ ለማጥፋት ወደ አንድ ጥልቅና ጨለማ ጉድጓድ (ምድር ቤት) እንዲጣሉ አደረገ። ​በጉድጓዱ ውስጥ ምንም ዓይነት መብራት፣ መጽሐፍ፣ ወረቀት ወይም ብዕር አልነበረም። ነገር ግን የታማኝ ተማሪዎቻቸው ፍቅርና የራሳቸው የላቀ የማስታወስ ብቃት ተአምር ሠራ! ተማሪዎቻቸው በየቀኑ በጉድጓዱ አፍ ዙሪያ ይሰበሰባሉ። ኢማም አል-ሰረኽኸሲ ከስር ሆነው በቃላቸው ዒልሙን ይነግሯቸዋል፣ ተማሪዎቹ ከላይ ሆነው ቃል በቃል ከሸይኻቸው የሚሰሙትን ይጽፉ ነበር። ​ኢማም አል-ሰረኽሲ በዚህ የጉድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያሳለፉትን መከራና የደረሰባቸውን ግፍ "አል-መብሱጥ" በተሰኘው መጽሐፋቸው በበርካታ ክፍሎች ላይ ገልጸውታል። በወቅቱ የስሜታቸውን ጥልቀት በሚያሳይ መልኩ ያስመዘገቧቸው እነዚህ ልብ የሚነኩ ቃላት ከጁምዓና ከጀማዓ ሰላት መራቃቸውን፣ ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸውን እና በጉድጓዱ ውስጥ በሰንሰለት ታስረው ያሳለፉትን መከራ በግልጽ ይገልጻሉ። ​ለምሳሌ የአንዱን ክፍል ማብራሪያ ሲጨርሱ እንዲህ ብለው ነበር፡- ​«ይህ ማጠቃለያ ከወዳጅ ዘመድ መጠየቅ ከተከለከለው፣ ከሰላማዊ ኑሮ ከተገለለውና በጉድጓዱ ጥልቀት ውስጥ በእንባ ከተዘፈቀው እስረኛ የቀረበ ነው...» ​ኢማም አል-ሰረኽሲ በዚያ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በመጽናት "አል-መብሱጥ" የተሰኘውን ባለ 30 ሙጀለድ ኪታብ አጠናቀቁ። በመጨረሻም ከእስር ሲወጡ፣ አካልና ነፃነት ቢታሰሩም እውነተኛ ቁርጠኝነትን ግን ጨለማ እንደማይገድበው አስመስክረው አልፈዋል። ​አላህ ሰፊውን እዝነቱን ያውርድላቸው፤ በዚያ አስቸጋሪ የጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ሆነው ለኡማው ያበረከቱትን ታላቅ የእውቀት ገጸ-በረከት ይቀበላቸው © Nesru Khedir/ነስሩ ኸድር

  • «አነስ ኢብኑ ማሊክ ዘንድ ነበርን ፣ የነብዩ ውኃ መጠጫ እቃ እንዲመጣለት አዘዘ ፣ በውስጡም ውሀ ተደረገልንና ተሰጠን ከውኃውም ጠጣን ፣ በፊታችን እና በአናታችን ላይም አፈሰስን ፣ በነብዩም ﷺ ላይ ሰላዋት አወረድን » ታቢዒዩ ሀጃጅ ኢብኑ ሀሳን ሙስነድ ኢማም አህመድ مترجم اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد 💚

  • ከምዕራባዊያን ጋ ያለብን ችግር የእስልምና ሳይሆን የፊጥራ ነው ይላል ዐብዱልዐዚዝ አጥ-ጠሪፊ ። ምዕራባዊውን በቁሳዊ እድገት ብቻ የመሰረቱት ስልጣኔ ከተፈጥሮኣዊ እሴቶች ጋ ጭምር እያላተማቸው ሸይጧን በነርሱ ላይ «...አዛቸውምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ...» ብሎ የዛተውን እንዲፈፅም ፍፁም ታዛዡ ሆነውለታል ። ፆታ ያስቀይራሉ ፣ በሰርጀሪ ተፈጥሮኣቸውን ይለውጣሉ ፣ ተመሳሳይ Genders ይጋባሉ ። ይሄን ኢ-ተፈጥሮኣዊ ስራቸውን ደግሞ ስልጣኔ አድርገው እንዲያስቡ ኢብሊስ እኩይ ተግባሮቻቸውን ሸልሞ አቅርቦላቸዋል ። አሳዛኙ ነገር መሰል ሙንከሮች በጣም ኢንቲሻር ከመሆናቸው ብዛት እንደ ሙንከር ራሱ እንዳይቆጠሩ እየሆኑ መምጣቱ ነው ። የሰው ልጅ በራሱ ላይ በሚያደርገው ነገር ሌሎችን እስካልጎዳ ድረስ ነፃ ነው የሚለው ሊበራል አመለካከታቸው ለብዙ ፈሳዶች በር መክፈቻ ሆኗቸዋል ፣ እውነታው ግን የሰው ልጅ ራሱን አላስገኘም ፣ በእናቱ ማህፀን ውስጥ ያለሱ ድርሻ በሚፈልገው ቅርፅ ያስገኘው አምላክ አለው ። ይህ አምላክ ከዘረጋው ተፈጥሮኣዊ ስርዐት ውጪ ለመጓዝ መሞከር መልሶ የሚጎዳው ከስርዐቱ ያፈነገጠውን አካል ነው ።

  • ስፔን ታላቁ ሙጃሂድ ጧሪቅ ቢን ዚያድ የከፈታት ታላቋ አንደሉስ (ያሁኗ ስፔን) ከወርቃማ ታሪካችን ውስጥ ትጠቀሳለች። ያሁኗን ስፔን ማዕከል አድርጎ ለ800 ዓመታት የዘለቀው ይህ ኢስላማዊ ስርዐት አሁን ላለቺዋ አውሮፓ ቁሳዊ ስልጣኔ ትልቅ አበርክቶ እንደነበረው ይነገራል ። በሳይንስ በስነፅሁፍ በኪነ ህንፃ የተራቀቁ ምሁራን መፍለቂያ ነበረች አንደሉስ ። ቁርጡባ ፣ ገርናጣህ ኢሽቢሊያ ፣ ጡለይጢላ .....እነዚህ ግዛቶች አሁን ድረስ በስፔን ያሉና ያን ውብ ዘመን የሚያስታውሱን ቅርሶች ናቸው ። አስገራሚው ነገር አሀን ድረስ በስፔን ምድር የዚህ ኢስላማዊ ስልጣኔ ህያው አሻራዎች መኖራቸው ነው ። የመስኖ ስርዐቶች ፣ የተራቀቁና ያሁን ምህድስናን የሚያስንቁ ግንባታዎች ( የቁርጡባ መስጂድና በሴቪያ የሚገኘው ቤተ መንግስት ተጠቃሽ ናቸው) ፣ የሚያማምሩ የዜማ ስልቶች ወዘተ አሁን ድረስ አሻራቸው ያሉ የአንደሉስ ስልጣኔ ቅሪቶች ናቸው ። ከዚህም ውጪ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት መፍለቂያም ነበረች - ታላቁ ሙፈሲር ቁርጢቢ ፣ ኢብኑ ዐረቢ ፣ አቡ ሀያን ፣ ኢብኑ ዐጢያህ እና መሰል ዑለማኦች መገኛ ነበረች አንደሉስ ። ኋላ ላይ የእርስ በእርስ የስልጣን ሽኩቻ ከውጪ ኃይሎች ወረራ ጋ ተደምሮ ይህን ግዙፍ ስልጣኔ ከጣሉት በኃላ አውሮፓ ላይ ኢስላማዊ ስርዐት ዳግም አልተነሳም ። ለወደፊቱ ግን ሮም እንደምትከፈት የሚገልፁ ትንቢታዊ ሀዲሶችን መሰረት አድርገን ካወራን ወይ بالسلاح والسنان ካልሆነም ቢል ቀለሚ ወልቡርሀን ኢውሮፕ እንደምትከፈት መናገር እንችላለን - إن شاء الله

  • አንድ ታዋቂ ሙስሊም ግለሰብ ‹ኢስላማዊ ስርዐትን በኛ ሀገር ደረጃ ማሰብ ቅዠትና እውርነት ነው ብሎ ፅፎ ተመለከተን ............ እስልምናን ከኢስላማዊ ስርዐት ነጥለን መመልከት አንችልም ። እስልምና መሬት ላይ ወርዶ የሚተገበር ኃይማኖት ነው ። እስልምና ዲን እና ደውላ ነው ። ያ ሁሉ የቁርዐን አንቀፆች ላይ የተዘረዘሩ የአላህ ህግጋቶች እንድንቀራቸው ሳይሆን መሬት ላይ አውርደን እንድንተገብራቸው ነው የወረዱት ። ፉቀሃዎችም ዐብረል ቁሩን እነዛን ሁሉ የአህካም ኪታቦችን በዝርዝር ያሰናዱት እንዲነበቡ ሳይሆን እንዲተገበሩ ነው ። ኢስላማዊ የፖለቲካ ስርዐት ከሌለ አላህ እንድንፋርድባቸው ያወረዳቸው ህጎቹ የሚተገበርበት ግራውንድ አይኖርም ። ኢስላማዊ ስርዐት እንዲኖር ማሰብ እውርነትና ቅዠት አይደለም ፣ ይልቅ ዓለማችን ከገባበት ኃላ ቀርነትና የበደል ስርዐት የሚወጣበት ብቸኛ መፍትሔ ነው ። ኢስላማዊ ስርዐት ዘመናዊውን ዓለም የቀደመና ለሁሉም ዘመንና ቦታ የሚስማማ ነው ። ማህበራዊ ፍትሕ የሚሰፍነው ፣ በዜጎች መካከል እውነተኛ የሀብት ክፍፍል የሚፈጠረው ፣ የሰዎች (ዲን ሀብት ዐቅል ገንዘብ ክብር) የሚጠበቀው የአላህ ህግ ምድር ላይ ሲተገበር ብቻ ነው ። ሰነፍ ሆነን ይህንን የአላህን ፍላጎት ማስፈፀም ቢሳነን ማሰባችንንም እንደ ቅዠት መቁጠር ‹ላ ኢላሀ ኢለላህ'ን ካለመረዳት የሚመጣ የዐቂዳ ኸለል አድርጌ ነው ምቆጥረው። ላ ኢለላህ ኢለላህ በሁሉም ምድራዊ ስርዐቶች ላይ የታወጀ ታላቅ አብዮት ነው ። ላ ኢላሀ ኢለላህ አላህን ማምለክ ብቻ ሳይሆን ፍርድንም ለርሱ ብቻ ማድረግ ነው ። እንደ ስትራቴጂ አቋምን መሸሸግ ወይም መሰረቱ ላይ ስምምነትን ገልፆ አካሄድ ላይ የተሻለ የሚሉትን መንገድ መጠቆም ወይም ከነጭራሹ ዝምም ማለት አንድ ነገር ነው ፣ በጥቅሉ ግን ኢስላማዊ ስርዐት አሁን ላለንበት ዘመን እንደማይበጅ ወይም መተግበር የማይቻል አድርጎ ማሰብ በፍፁም ልክ አይደለም !!!

  • ወጣት ወይም ታዳጊ ሆናቹ ሶሻል ሚዲያ ላይ ዲናዊ መልዕክት ምታጋሩን ወንድምና እህቶች በተለይ ታዋቂ የሆናቹ - ከተቻለ በእድሜ የበሰለ ሙርሺድ/መንገድ አመላካች ቢኖራችሁ ጥሩ ነው 😊

  • ገንዘብ ቢኖረኝ ይሄን አደርጋለው ... ብለን ምንመኛቸው ነፍ ነገሮች አሉ ። ሞዴላቸው ሌተስት የሆኑ መኪናዎች ፣ የተንጣለሉ ቪላዎች ፣ ውድ ዋጋ የሚያወጡ አልባሳት ፣ ጌጣጌጦች ምናምን ... አዎ አላህ ሀብት ቢሰጠንና እነዚህ ነገሮች ቢኖሩን ኖርማል ነው ። ነገር ግን ሀብት እንዲኖረን ስንመኝ ትልቁ ግባችን ይሄ ከሆነ የቃሩን መንገድ ላይ ነን ። ቃሩን አምሳያ የሌለውን ሀብት አላህ ለግሶት ነበር ግና የተሰጠውን ፀጋ መጋጌጫ ብቻ አደረገው ። ዳኢዎችም መጥተው «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ» ብለው መከሩት ። አላህ የሰጠውን ድልብ ሀብት ወደ አላህ መቃረቢያ እንዲያደርገው ገሰፁት ። ዱኒያ መጣቀሚያ ነችና ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታውን እንዳይረሳ ግና ዋና የትኩረት ማዕከሉ አኸራን እንዲያደርግ ነገሩት ። የቃሩን ልብ በዱኒያ ፍቅር ታውሮ ስለነበር እነዚህ መዋኢዞች አልጠቀሙትም አላህም ከነሀብቱ አሰጠመው ። ትዕዛዙ የሚለው ከነዱኒያም ድርሻህን አትርሳ ነበር እኛ ግን ዋናው ትኩረታችን ዱኒያ ላይ ሆኖ ከአኸራ ድርሻችሁን አትርሱ የተባልን ይመስል ቀጣዩ ዓለም ሰከንደሪ ጉዳያችን ነው ። እነዚህን ነው አላህ ‹ሙሪዲል ሀያቲ አድ-ዱኒያ› የቅርቢቱ ዓለም ፈላጊዎች እያለ የሚወቅሳቸው - نعوذ بالله ። ሀብትን የሚሹት ሀብታም መሆን የሚፈልጉት የዱኒያ ጌጣጌጥን ብቻ ፈልገው ነው ። [ሱረቱል ቀሰስ ተፍሲር እያዳመጥኩ የተከተበ]

  • በየቀኑ ስለሚከሰት ስለማናስተውለው እንጂ የቀንና ሌት መፈራረቅ እጅግ አስገራሚ ከሆኑ የአላህ ተዐምራቶች አንዱ ነው ። ከሰዐታት በፊት በብርሀን አድምቃን የነበረቺው ፀሀይ ተሰውራብን ፅልመት ውስጥ ገብተናል ። ቁርዐኑ «ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ ከእርሱ ላይ ቀንን እንገፍፋለን፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ» እንዳለው በጨለማ ውስጥ እንገኛለን ። የሚደንቀው ነገር በተመሳሳይ ሰዐት ሌላ አካባቢ ደግሞ ፅልመታቸው ተወግዶላቸው በፀሀይ ፍካት ብርሀን ውስጥ የሚገቡ ሀገሮች አሉ ። እኛን ፅልመት ውስጥ የከተተን አምላክ ለሌሎች ደግሞ ብርሀን እያፈነጠቀላቸው ነው ። አስከትሎም ከነሱ ብርሀንን ወስዶ መልሶ ለኛ ይለግሰናል ። ቀኑን ለሀረካ ለሊቱን ለሰከን አድርጎ ይሄን አስደናቂ ስራ ያለምንም መዛነፍ በየሰዐቱ በመላው ምድራችን በቁድራው ይከውናል ። በእርግጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች በዚህ የአላህ ድንቅ ስራ ውስጥ ትልቅ ተዐምር አለ ። الله 💚 [ተራ የሰዎችን የእጅ ስራ ለማድነቅ ቃላት ምናዥጎደጉድ ሰዎች የአላህን አስገራሚ የቁድራው መገለጫዎች ማስተንተንና እርሱን ማወደስ ልምዳችን ሊሆን ይገባል ]

  • ገ ዛ ህ የቲም ነች ሰይዱና ኸድር ከነቢ ሙሳ ጋ በነበራቸው ጉዞ ላይ የየቲሞችን ቤት አቃንተውላቸው እንደነበር ይታወቃል ። ለዛ ድርጊታቸውም ያስቀመጡት ሪዝን ጌታቸው ከችሮታው ሊያጣቅማቸው ፈልጎ እንደሆነ ለነብዩላህ ሙሳ እንደገለፁላቸው ሱረቱል ከህፍ ይነግረናል ። ለሰፊናው መሸንቆር ‹ፈለግኩኝ› ለህፃኑ ግድያ ደግሞ «ፈለግን» ነበር ያሉት ፣ ለየቲሞቹ ጊዜ ግን فَأَرَادَ رَبُّكَ «ጌታህ ፈለገ» ነበር ያሉት ። የየቲሞችን ጉዳይ ኃላፊነት የሚወስደው እራሱ አላህ ነው ፣ ገ ዛህ የቲም ናት ። ምንም እንኳን አባት ሊሆኗት የሚገቡ ሰዎች ኸዝል ቢያደርጓትም ሰሚና ተመልካቹ አይተዋትም ።

  • ሐዲስ ዘግይቶ የመሰነዱ ጉዳይ እውነታ ○●○●○ ሐዲስ የተጻፈው ነቢዩ ﷺ ካለፉ ከ200 ዓመታት በኋላ ነው" የሚል ክርክር ሲነሳ እየሰማን ነው:: ይህ ትችት "በመጻፍ" እና "በመጽሐፍ መልክ በምዕራፍ ከፋፍሎ በማተም" መካከል ያለውን ግዙፍ ልዩነት ካለማወቅ (ወይም ሆን ብሎ ከማድበስበስ) የመጣ ነው:: ሐዲስ መጻፍ የተጀመረው ከ200 ዓመት በኋላ ሳይሆን፣ ገና በነቢዩ ﷺ ሕይወት ዘመን በሰሐባዎች እጅ ነው። ነቢዩ ﷺ መጀመሪያ ላይ ከቁርኣን ጋር እንዳይቀላቀል በመስጋት ሐዲስ መጻፍን ከልክለው የነበረ ቢሆንም፣ ከጊዜ በኋላ ግን ቁርኣን በደንብ ሲለይ ሐዲስን መጻፍ ፈቅደዋል። ታላቁ ሰሐባ ዐብዱላህ ቢን ዐምር ኢብን አል-ዓስ (ረ.ዐ) ነቢዩ ﷺ የተናገሩትን ሁሉ ይጽፍ ነበር። ቁረይሾች "ነቢዩ ሰው ናቸው፣ በደስታም በቁጣም ይናገራሉ፤ እንዴት ሁሉንም ትጽፋለህ?" አሉት። እርሱም ለነቢዩ ﷺ ነገራቸው። ነቢዩም ﷺ ወደ አፋቸው በመጠቆም፦ "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነው አላህ እምላለሁ ከዚህ (ከአፌ) እውነት እንጂ ሌላ አይወጣም" አሉት። ይህ ስብስብ (الصادقة ) ይባላል። ኢማም አል-ቡኻሪ እንዳስተላለፉት፣ ዐሊይ (ረ.ዐ) በሰይፋቸው ላይ የታሰረች አንዲት የተጻፈች ጥቅልል ሰነድ (ሰሒፋህ) ነበረቻቸው። ስለ ምን እንደሚያወራ ሲጠየቁ፦ ስለ ካሳ ሕግጋት ፣ ስለ እስረኞች ፍቺና መሰል የሸሪዓ ድንጋጌዎች በነቢዩ ﷺ ትዕዛዝ የተጻፈ መሆኑን ተናግረዋል። ከ 30_100 አመተ ሂጅራ ዘመን ሐዲሦች በሰፊው የተጻፉባቸው በርካታ ማስታወሻዎች ነበሩ። ዶ/ር ሙስጠፋ አል-አዕዞሚ በጥናታቸው እንዳረጋገጡት፣ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ብቻ ሐዲሥ የጻፉ ከ50 በላይ ሰሐባዎች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ታቢዒዮች ነበሩ። የሀማም ኢብን ሙነቢህ ሰነድ በታሪክ ውስጥ የኦሬንታሊስቶችን አፍ ሙሉ በሙሉ የዘጋ ትልቅ ግኝት ነው። ታቢዒዩ ሀማም ኢብን ሙነቢህ ከታላቁ ሰሐባ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) የሰማቸውን 138 ሐዲሦች በአንድ ማስታወሻ ላይ ጽፎ ነበር። ይህ ሰነድ የተጻፈው 60 ዓ.ሂ አካባቢ ነው (ማለትም ነቢዩ ካለፉ ከ40 ዓመታት በኋላ ብቻ!) ይህ የሀማም ስብስብ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በብራና ተገኝቶ ሲታተም እና በ250 ዓመተ ሂጅራ ከተጻፈው ከኢማም አሕመድ "ሙስነድ" መጽሐፍ ጋር ሲነጻጸር፣ አንድም ቃል ሳይቀነስና ሳይለወጥ ልክ በ60 ዓ.ሂ እንደተጻፈው ሆኖ ተገኝቷል። ይህ የሚያሳየው ሐዲስ በቃላት ደረጃ ሳይለወጥ በጽሑፍ ይተላለፍ እንደነበር ነው። ​ከዚህም ባሻገር ኸሊፋ ዑመር ኢብኑ ዐብደልዐዚዝ በ99 ዓ.ሂ በነገሠ ጊዜ፣ የሐዲስ ሊቃውንት በየሀገሩ ያሉትን ሐዲሦች በይፋ ሰብስበው በአንድ መጽሐፍ እንዲያደራጁ የመጀመሪያውን የመንግሥት ትዕዛዝ አስተላለፈ። በዚህም መሠረት ታላቁ ኢማም ኢብን ሺሃብ አል-ዙህሪ ሐዲሦችን በይፋ ሰብስቦ መጻሕፍትን ማዘጋጀት ጀመረ። ከዚያም በመቀጠል እንደ ኢማም ማሊክ (ሙወጣእ) ያሉ ሊቃውንት በ150 ዓ.ሂ አካባቢ መጻሕፍትን አሳተሙ። ​ስለሆነም "ሐዲስ የተጻፈው ከ200 ዓመት በኋላ ነው" የሚለው ክስ፣ አንድ ሰው መጥቶ "የኢትዮጵያ ታሪክ የተጻፈው በ21ኛው ክፍለ ዘመን የታሪክ መጻሕፍት ሲታተሙ ነው" ብሎ እንደ መከራከር ያህል ስሁትና የታሪክ መረጃዎችን መካድ ነው። ሐዲስ ከመጽሐፍ ቅንብር በፊት በሰነዶች የተመዘገበ፣ በሊቃውንት ትውስታ (ሒፍዝ) የተጠበቀና በሳይንሳዊ ሰንሰለት (ኢስናድ) የተደገፈ እውነተኛ መለኮታዊ ቅርስ ነው። ሐዲስ ከመጽሐፍ ቅንብር በፊት በሰነዶች የተመዘገበ፣ በሊቃውንት ትውስታ የተጠበቀና በሳይንሳዊ ሰንሰለት (ኢስናድ) የተደገፈ እውነተኛ መለኮታዊ ቅርስ ነው። አላህ ያጽናን! © Nesru Khedir/ነስሩ ኸድር

  • ባለፈው ሁልጊዜ ማስበውን ነገር አንድ ሰው የሆነ ቪዲዮ ላይ ሲናገር እያደምጥኩት ነበር ። የቤተሰብ ጨዋታን ማን ይምራው በሚለው ዙሪያ ‹ነገ ለሚተካህ ስራህ በጣም አትሰቃይ› Just Relax ብሎ ነው ልጁ ንግግሩን የሚጀምረው ። አያይዞም ለስራ ብላቹ ኑሮኣቹም ቤተሰባቹም ጤናችሁን እና ሁሉ ነገራቹን አሳልፋቹ የሰጣቹ ሰዎች እናንተ ባለፋቹ ማግስት ትተካላችሁና ሁሉም በልኩ ይሁን አይነት መልዕክት ያስተላልፋል ። ይሄ ነገር ከድሮ ጀምሮ ማምንበትና የኔም የህይወት ፕሪንሲፕሌ ነው ። እሰራለው ለመለዉጥ እጥራለው ። ግን በፍፁም ለስራ ብዬ ከቤተሰብ ጊዜ ላይ አልቀንስም ፣ ከመድረሳ ጊዜ ላይ አልቀንስም ፣ ከሰላት ሰዐቴ ላይ አልቀንስም ፣ ከጓደኞቼ ጊዜ አልቀንስም ። እንደውም የቤተሰብ ፕሮግራም ከስራ ጋ ከተጋጨብኝ የቤተሰብ ፕሮግራምን አስቀድማለው ። ቤት ከገባው ገባው ነው ፣ ስለ ስራ ማሰብም ሆነ የስራ ስልክ ማውራት አልፈልግም ። መድረሳም ከገባው እንዲሁ ። ልጁ እንዳለው ህይወት ስራ ብቻ አደለም ። ለራስህም ጊዜ ያስፈልግሀል ሰላምህ ሊጠበቅ አዕምሮህም ሊያርፍ ግድ ይለዋል ፣ ለቤተሰብም እንዲሁ ጊዜ መስጠት አለብህ ፣ ትዳርና ልጅ ካለም እንዲሁ ከነሱ ጋ ረዘም ያለ እለታዊና ሳምንታዊ ጊዜ ያስፈልጋል ። ሀዲሱም ' ነፍስህ ባንተ ላይ ሀቅ አላት ፣ ቤተሰቦችህም ባንተ ላይ ሀቅ አላቸው ፣ ጌታህም ባንተ ላይ ሀቅ አለው ' ብሎናል ።