tgindex
#KALTUBE
@KALTUBEВидеоанглийский

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ። ዩሐ1÷ 14 " Daily Spiritual Feeding" በዚህ ያገኙናል👉 @Kaltube_bot የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇 https://youtube.com/c/KALTUBEOfficial ቃልኛ ዲጂታል መፅሔታችንን ያንብቡ👇 https://telegra.ph/KALIGNA-11-15

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
00:19
Постов за неделю
3
Всего постов
41
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
12 255
−19 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 892
40 постов
Вовлечённость
23,6%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 41
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
675
1/48двое суток
773
1/72трое суток
834

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/Y7vHQl1-aRs?si=hDDukQHzxeGcLdW7

  • ንስሐ ከገባሁ በኃላ ጸጸት ለምን አይለቀኝም? || አገልጋይ ሰይፉ ዘሪሁን https://youtu.be/UFvWXX9ap_U?si=NJoBZeZAj74MA5OC

  • https://youtu.be/JM-ZCeDsQNE?si=QzbEpAXIqkVcPf7y

  • 5 авг.1 33023

    በሕይወቴ ለምን ፈተና በዛ? | አገልጋይ ሰይፉ ዘሪሁን https://youtu.be/XPpdUTyCBS4?si=oVcJ0tsaGNHqDMVb

  • 4 авг.1 27112

    https://youtu.be/tCHaSnjyXfU?si=DD7vPNUCJOn89prz

  • 31 июл.14,7 тыс28

    ደጋግሞ የሚጥለንን ኃጢአት እንዴት እናሸንፍ? || አገልጋይ ሰይፉ ዘሪሁን https://youtu.be/ScLZAP5Uq18?si=TIaAbwxt8m5mYV02

  • 29 июл.1 3462

    https://youtu.be/K-y8M0rYYj4?si=Q65d3JcHz1SK0MU8

  • 27 июл.1 60581

    7 days left 💢ለ100 ሰው ብቻ የሚሆን የ12ኛ ክፍል ተመራቂዎች ስልጠና🎉 በዚህም :- ✅የስነ-ልቦና እረፍት ✅መንፈሳዊ ጥንካሬ ✅ተግባራዊ የሕይወት ክህሎቶችን በመስጠት ከፊታቸው ያለውን አለመረጋጋትና ውጥረት በልበ-ሙሉነት እንዲጋፈጡ እንዲረዳ ታስቦ ተዘጋጅቷል ❕ስለሆነም 300 ብር ብቻ በመክፈል የኘሮግራሙ ተካፍይ እንድትሆኑ እንጋብዛለን! ቀኑ:- ሐምሌ 25 ሰዓት :-ሙሉ ቀን ምሳንም አካቶ ቦታው:- አዋሬ ሙሉ ወንጌል 🥁በተጨማሪም የተሳታፊነት Certificate አዘጋጅናል። ለጓደኞቻችሁ share በማድረግ አገልግሎቱ አድረሱ😃 🎯ምዝገባው እንዳይሞላ ቶሎ ተመዝገቡ 🏃🏃‍♀️ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc4YSROPGI4e2t1nlotOFzbeNFvYYpuZYPLY9_lSihHcQL3zg/viewform?usp=publish-editor

  • 27 июл.8 83914

    ጸሎቴ ለምን አልተመለሰም ? አገልጋይ ሰይፉ ዘሪሁን https://youtu.be/XEhHf0k7C2M

  • 17 июл.1 99523

    https://youtu.be/nQRWy8drzrw?si=IC4g2F5GfAKxjFrT

  • 6 июн.2 90563

    የክርስቶስ ወታደር የተሰኘውን ይሄንን ትምህርት እንድትሰሙ እና ለሌሎች እንድታካፈሉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን። https://youtu.be/xBVAg47zA1g?si=2ut1LJuvg6bcAhol

  • 3 июн.2 5992510из Tzamamovment

    አልወድህም ውሸቴን ነው አልወድህም ምርጡን ጊዜ አልሰጥህም ብሰጥህም................. የድካሜን ጥፍጣፊ የሃሳቤን ትርፍራፊ ውሸቴን ነው አልወድህም ሙሉ ልቤን አልሰጥህም ብሰጥህም................ የሰው ምርኩዜን ስቀማ ባመንኩትኝ ሰው ስደማ ምጠይቅህ ያ ጩኸቴ የማልዋሽህ አንድ እውነቴ የእውነት መኖር ስለማልችል ይሙትልኝ እኔነቴ ትግሌን ልስቀል ....ብቻህን ኑር በህይወቴ! https://t.me/Tzamamovment

  • 25 мая2 670910

    በክርስቶስ IN CHRIST ክፍል 97 በመልካምነት የሚገለጡ ስጦታዎች ፣ የአመራር ስጦታ እና የምክር ስጦታ ◆ በመልካምነት የሚገለጡ ስጦታዎች 1)ምህረት የማድረግ ስጦታ (ሮሜ.12፡8) 2) የመስጠት /መለገስ ስጦታ (ሮሜ.12፡8) 3) የመርዳት ስጦታ (1ቆሮ.12፡28 1 ምህረት ማድረግ ስጦታ (ሮሜ.12፡8 የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። የማቴዎስ ወንጌል 5 : 7 ምህረት የማድረግ ስጦታ ለተጨቆኑ ሰዎች፣ለተቸገሩና በመከራ ውስጥ ላሉ ሰዎች የምናሳየው ልባዊ መሻት ነው። ምህረት የማድረግ ስጦታ ሰዎችን አካላዊ በስሜታዊ ጉዳዮች ፣በገንዘብ፣እና በመሳሰሉት ጥያቄዎቻቸው የመርዳት ፀጋ ነው። 2) የመርዳት ስጦታ (1ቆሮ.12፡28 ይህ የመርዳት ስጦታ አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሲሆን ይህ ስጦታ በዚህ ክፍል ብቻ የተጠቀሰ ነው። (1ቆሮ.12፡28) የመርዳት ስጦታ ሰዎችን ለመርዳት (Support)ለማገዝ የሚሰጥ የመርዳ ት ልብ(Passionated heart)ነው። ይህ ስጦታ (ልብ)የተቀበሉ አማኞች መንገድ ላይ የወደቁ ሰዎችን ሲያዩ ወላጅ አልባ ህፃናት እና በልዩ ልዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ሰዎችን የመርዳት እጅግ ጥልቅ ስሜትና መሻት አላቸው። ይህ ስጦታ የተቀበሉ አማኞች ከየትኛውም ሰው በላይ ሰውን ለመርዳት ፍላጎት አላቸው።እንዲሁም ባላቸው ጥቂት ነገር እንኳን ሰዎችን በትጋትና በፍቅር ይረዳሉ።  (ሮሜ.12፡8) _   ◆  የአመራር ስጦታ ➛የመግዛት /የማስተዳደር ስጦታ (ሮሜ.12፡8) ይህ ስጦታ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚመሩ እረኞችና በተለያየ የአመራር ደረጃ ላይ ላሉ አገልጋዮች የሚሰጥ የአመራር ስጦታ (ብቃት) ነው።    ◆  የምክር ስጦታ ➛የመምከር ስጦታ(ሮሜ.12፡8) ይህ ስጦታ ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች የሚገለጥ የምክር ስጦታ ነው። ይህን ስጦታ የተቀበለ አማኝ ስለ መንፈሳዊ ጉዳዮች፣ስለ ገንዘብ አጠቃቀም፣ስለ ጋብቻ፣ስለ ስራ እና ሌሎችም ምክር በሚያስፈልጋቸው የሰው ህይወት የተለያየ ምክር ይሰጣሉ። የፀጋ ስጦታ እንዴት መቀበል እንችላለን ? ሀ) የፀጋ ስጦታዎችን በብርቱ በመፈለግ መቀበል እንችላለን።ቃሉ እንዲህ ይላል   ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 : 1 የተቀበልነውን  የፀጋ ስጦታ እንዴት ማወቅ እንችላለን ? ➛ የተቀበልነውን  ፀጋ የምናውቅበት የተለያየ መንገድ ይኖራል። ሀ) በፀሎት እግዚአብሔርን መጠየቅ። ለ) በልባችን ውስጥ በተደጋጋሚ ለማገልገል ሸክም የሆነብንን ስጦታ ማስተዋል። ሐ) የቤተክርስቲያን መጋቢ እና ሌሎችም አማኞች ስላንተ/ስላንቺ የሚመሰክሩትን ምስክርነት ማወቅ።ፀጋው የሚታይ እና የሚገለጥ ስለሆነ ተደጋጋሚ ማረጋገጫዎች የበለጠ ፀጋህን አውቀህ እንድታ ገለግል ይረዳሀል። መ) የውስጥ (የመንፈስ ምስክርነት ) ማዳመጥ ሠ) በአነስተኛ ቡድኖች ውስጥ እራስህን ዝቅ አድርገህ መንፈሳዊ ተሳትፎ አድርግ። ያኔ በቀላሉ የተቀበልከው ስጦታ በቀላሉ መረዳት ትጀምራለህ። ረ) ውስጥህ የሚነሳሳው በምን ለማገልገል ነው? የውስጥህን ጥያቄ እወቀው? ክፍል 98 ✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ) 💐share 💐share 💐share @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE

  • 23 мая2 232129

    በክርስቶስ   IN CHRIST ከፍል 96 ትንቢት፣ልሳን መናገር እና ልሳን መተርጎም 1) ትንቢት መናገር 1ቆሮ 12:10 2) በልዩ ልዩ አይነት ልሳን መናገር 1ቆሮ 12:10 3) በልሳን የተነገረውን መተርጎም 1ቆሮ12:10 1-ትንቢት  የመናገር ስጦታ 1ቆሮ 12:10 ትንቢት መናገር ማለት ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚሄድ የእግዚአብ ሔርን ሉአላዊ ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ማወጅ/ መናገር ነው። ትንቢት መናገር እግዚአብሔር እንድናደርገው በቃሉ ያዘዘውን ነገሮች ለሰዎች ማወጅ/ መናገር ነው። ➛ ትንቢት የመናገር ስጦታ ያለው ሰው ሰውን ለማነጽና፣ ለመም ከር፣ ለማጽናናት ነው የሚናገረው። ''ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል። በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።''1ቆሮ14 :3 ➛ትንቢት ከመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ያነሰ ነው።  ሁላችንም ከመጽሐፍ ቅዱስ በታች ነን፣መጽሐፍ ቅዱስ ይገዛናል እንጂ አንገዛውም፣ይመራናል እንጂ አንመራውም፣ የምንናገረው ትንቢት በመጽሐፍ ቅዱስ ይመረመራል፣የማይመረመር ትንቢት የለም፣ 2) ልሳን መናገር 1ቆሮ 12:10 በልሳን መናገር ሲባል አንድ አማኝ በማያውቀው ቋንቋ ሲናገር ማለት ነው። በልሳን መናገር መንፈሳዊ ስጦታ እንጂ በልምምድና በጥናት፣በሂደት የሚመጣ ቋንቋ አይደለም። ➛ይህ ልሳን(ቋንቋ)ምናልባት ምድራዊ ቋንቋ አሊያም ከእግዚአብሔር ጋር በምስጢር የምንነጋገርበት ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ሦስት አይነት ልሳን አለ:-- ሀ) መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በወንጌል እንድንደርስ ሲፈልግ የሰዎቹን ቋንቋ ይሰጠናል። አንድ አማርኛ ተናጋሪ ለፈረንሳይኛ ተናጋሪ ወንጌል መመስ ከር ያለበት በሚሰማው ቋንቋ ስለሆነ ጌታ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ሊሰጠው ይችላል። በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ የተከሰተው ይህ ነው።እነ ጴጥሮስ በማያቁት ቋንቋ ተናግረው  3000ነፍሳትን ወደ ጌታ እንዲመጡ አድርገዋል። ለ)  ከእግ ዚአብሔር ጋር ምስጢር የምናወራበት፣የምንታነፅበት አይነት ልሳን ነው።ይህ ልሳን በአሁን ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት እየተነገረ ያለ ነው።ይህ ልሳን የምድራዊ ቋንቋ አይደለም።መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። ይህ ስጦታ ለሌሎች ወንጌል ለመመስከር የሚሰጥ ሳይሆን ራስን ለማነፅ እና ለእግዚአ ብሔር ምስጢር ለመናገር የሚሰጥ ነው። በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 : 2 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል። (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡4). ሐ) የመላእክት ልሳን በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። 1ቆሮ 13:1 ➛የመላእክት ልሳን የመላእክት ቋንቋ ነው። ሐዋርያ ጳውሎስ የመላእክት ልሳን በአማኞች ሊነገር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል። ሆኖም ግን የተብራራ ነገር ስለሌለ መጽሐፉ እስከተናገረው ድረስ ተናግረን ዝም ማለቱ መልካም ነው። 3) ልሳንን መተርጎም 1ቆሮ12:10 ➛እንደ ቃሉ መሰረት የማይተረጎም ልሳን ለሰሚው ግልፅ አይሆንም።ስለዚህ የግድ ሰዎች መረዳት በሚችሉት ቋንቋ መተርጎም አለበት። አንድ ሰው በጉባኤ ውስጥ በልሳን ሲፀልይ ሌላው አማኝ ስለማይረዳ ልሳን የመተርጎም ፀጋ ያለው አማኝ ምን እንዳለ ሊገልጥ ይችላል። ➛ልሳን መተርጎም ያለበት ጉባኤውን ከማነፅ አንፃር ነው።አንድ አማኝ ልሳኑ ለሌሎች በረከት የሚሆነው የሚሰማው ሰው ሲረዳው ብቻ ነው። ➛ጳውሎስ በማይተረጎም ልሳን ጉባኤ ውስጥ ከመፀለይ ይልቅ ሰዎች በሚግባ ቡበት የአይምሮ ቋንቋ እንዲፀልዩ ይመክራል።ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።1ኛ ቆሮ14 : 19 ➛ልሳን የመናገር ስጦታ ያለው ክርስቲያን በተጨማሪም የሚናገረውን በምድራዊ ቋንቋ ለሰው እንዲተረጉም ሊፀልይ ይገባል። ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።1ቆሮ14 : 13 ክፍል 97 ይቀጥላል ✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ) 💐share 💐share 💐share @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE

  • 12 мая2 4122

    በመንግሥተ ሰማይ ቤተክርስቲያን የነበረን ድንቅ የአምልኮ ጊዜ። https://youtu.be/fYqmCp-wiQ0

  • 11 мая2 5882014

    #ፍናና 10 ወለደች ማለት የተሳካላት ሴት ሆነች ማለት አደለምና በስኬት ሁሉ #አትቅና። ሃጥዕ ስንዝር ቆፍሮ ውሃ ቢፈልቅለት ከእንስሳቱ በወደቀው እዳሪ ውስጥ ያለው እህል ሳይኮተኩተውና ውሃ ሳይጠጣው የሚያሳድግለት መሬት ቢኖረው ኪዳን የለውምና ነፍሱ አትረካም። #ልምላሜ ከነዓንን አጽድቆ በቃዴስ በረሃ ያለውን የኪዳኑን ህዝብ አይኮንነውም ስኬት አማሌቅን ቅዱስ አድርጎ ይሹሩንን አያረክሰውም።የባለኪዳኑ ህዝብ ድሉ ከአምላኩ ፈገግታ ጋር ነውና። ጸልየህ በተሳካልህም በተበላሸብህም ነገር ኩራ በሃጥዕ ስኬት ከቀናህ መንገዱንም ትደፍረዋለህና የልብህን ምኞት ጠብቅ። ለጥቂት ግዜ ብቻ ብለህ በሃጥያት መንገድ አትሂድ የእባብ ትንሽ የለውምና። Telegram

  • 4 мая2 665135из slmethiopia

    ፍለጋ || Blog 1 ዜና 16 ¹⁰ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። ¹¹ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። ቁጥር 10 በእግዚአብሔር ስም ተደሰቱ፣ ስሙን አወድሱ፣ በማንነቱ ተደነቁ የሚል ሀሳብ ሲኖረው ጥልቅ የሆነን የውስጥ ሀሴት እግዚአብሔርን በመፈለግ፣ ፊቱንና ህልውናውን በመሻት እንዲለማመዱ ህዝበ እስራኤልን ያበረታታል። ለካስ በፍለጋ ውስጥም ደስታ አለ። ቀጥሎ ባለው ቁጥር ደግሞ እግዚአብሔርን የመፈለግ ውጤት ሲያብራራ ለመፅናት እንደሆነ ይገልፃል። የእኛ የምንለው ፅድቅ የሌለን ደካማ ሰዎች ቀርቶ የቆምንባት ምድር በማታስተማምንበት በዚህ ጊዜ ከዛሬ ነገ ምን ይፈጠር ይሆን ብሎ በስጋት ተቀፍድዶ ከመባዘን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ለመኖርና ለማረፍ አስፈላጊው ነገር እግዚአብሔርን መፈለግ የመሆኑን መልዕክት ክፍሉ ያስተላልፋል። መቼ መቼ እንፈልገው ስንልም 'ሁልጊዜ' ይለናል። በደስታም ሆነ በመከራ፣ በሀዘን ሆነ በፌሽታ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈለጋል ........ ሙሉ ለማንበብ ይጫኑ ➢ Read More ...... 💙Follow GC SLM  on: 🌐Facebook|🌐Telegram|Ask on

  • 4 мая2 42122

    ልዩ ትንቢታዊ የፀሎት፣የቃልና የአምልኮ ምሸት ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ◆ ዘወትር ረቡዕ  ◆ ከቀኑ10:00--2:00 ድረስ!! ◆ በቦሌ ሞርኒንግ ስታር ህንፃ ! ከዚህ ፀሎት በኋላ እንደ ቀድሞ መሆን አይቻልም!! ጋባዥ:- መሳይ አለማየሁ(ነቢይ) አድራሻ:- ቦሌ ሞርኒንግ ስታር 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፀሎት ቤት https://t.me/KALTUBE https://t.me/KALTUBE https://t.me/KALTUBE

  • 1 мая2 35434

    በክርስቶስ IN CHRIST ክፍል 95 ተአምራትን የማድረግ ስጦታ (1ቆሮ.12፡9 2፡9) ➛በመጽሐፍ ቅዱስ (በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን) መጽሐፍት ውስጥ በጥቂቱ ከ250-265 ተአምራት ተጠቅሰዋል። ◆በብሉይ ኪዳን ከተጠቀሱት ዋና ዋና ተአምራቶች መካከል፡- ዘፍጥረት(ፍጥረታት) ፣ የጥፋት ውሃ ፣ የግብጽ መቅሰፍታዊ ተአምራት ጨምሮ ከ100 በላይ ልዩ ተአምራትን ይዟል። ◆አዲስ ኪዳን፡- ከ80 በላይ ተአምራትን ይዟል፣ ብዙዎቹ በጌታችን በኢየሱስ ታላላቅ  አገልግሎቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። ከዚህ ውስጥ የኢየሱስ ተአምራት በወንጌላት ውስጥ  ከ37–50 ያህል ተአምራት ተጠቅሰዋል። ይህ ሲባል ግን ኢየሱስ የሰራቸው ተአምራት እነዚህ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል። ዮሐ 21:25 ➛ተአምር ማለት እግዚአብሔር የሚሰራው ከሰው አቅምና ከሰው ሃሳብ በላይ የሆነ ስራ ማለት ነው።ተአምራት  እግዚአብሔር የሚሰራቸው  ስሙን የሚያስከብሩ ስራዎች ናቸው።መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተአምራት መካከል በጥቂቱ  ባህር መክፈል፣የተዘጋ ማህፀን መክፈት፣የሞተን ማስነሳት፣ ከባዶ ነገር አንዳች ነገር ማድረግ፣ የሌለን ማምጣት፣የተጎመደ እጅ መቀጠል፣የማያዩ አይኖችን መክፈት፣መስማት የማይችል ጆሮ መክፈት፣ሁለቱን አሳና አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ ህዝብ ማብላት እና ሌሎችም እልፍ ተአምራት  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። ➛ተአምራት የራሳቸው ባህሪና አካሄድ አላቸው።ተአምራት ለሰዋዊ ማንነታችን እንግዳ ሁልጊዜ እንግዳ ናቸው። ለአዕምራችን የማይገባንና በሳይንስ የማይረጋ ገጥ የመለየኮታዊ ጣልቃ ገብነት ውጤት ነው። ➛ተአምራት እንዴት?በሚል ጥያቄ የማይ መለሱ ነገር በእምነት የምናስተውላቸው አስደናቂ የጌታ ስራዎች ናቸው። ➛መንፈስ ቅዱስ ይህን ስጦታ የሰጠው ሁሉን ቻይነቱን ሊያሳይ ነው፤ በሁሉን ቻይነቱ በእርሱ የሚያምኑትን ለማነፅ እና ወንጌል ሲሰበክ ቃሉን ሊያፀና ነው።ሃሌሉያ!! ➛ተአምራት የመስራት ስጦታ ያለው አማኝ በእግዚአብሔር ምሪት፣ ለእግዚአብሔር ክብር፣ለብዙዎች መታነፅ ሊያውለው ይገባል። ➛ይህ ስጦታ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ የነበረ ስጦታ ሲሆን ይህን ስጦታ የተቀበሉ ቅዱሳን ሰዎች ብዙ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፣ዛሬም ይደርስባቸዋል። ➛ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ የሚሰራቸውን ተአምራቶቹን የሚያናንቁ  ፈሪሳዊያን፣ ሰዱቃውያን፣ፀሐፍት እና ብዙ ሰዎች ነበሩ።ተአምራት ከተፈጥሮ አቅም በላይ የሆኑ የሰው ልጅ ችግሮችን የሚፈታ የጌታ መፍተሔ በመሆኑ በቀላሉ መረዳት ስለማይቻል። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ተአምራትንና አስማትን ነጥሎ ባለማወቅ እውነተኛ የሆነውን ተአምራት ወደ መካድና ወደ መገሰጽ የሚሄዱ ጥቂቶች አይደሉም። ➛በዚህም ዘመን ያለን ክርስቲያኖች የሃገር መሪዎች የማይችሉት፣ሳይንቲስቶች የማይፈቱት፣የምህንድስና ጥበብ የማይፈታው፣ሳይኮሎጂስቶች የማይፈቱት፣ ቴክኖሎጂ የማይፈታው ብዙ ችግር ባለበት አለም ላይ ነው ያለነው። ➛የአለም ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ፣ ሁኔታዎች ተለወጡ ሲባል ከድጥ ወደ ማጡ የሆነበት ጊዜ ላይ ነች።በዚህ ጊዜ እጃችንን ወደ ሰማይ ዘርግተን የእግዚአብሔርን ተአምራት ልንጠብቅ ያስፈልጋል።ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ዛሬ እስከ ለዘላለም ያው ነው።ትናንት የሰራውን ተአምራት ዛሬም ይሰራናል።የኛ ድርሻ ለእኛ  የማይቻል ለእግዚአብሔር እንደሚቻል ማመን ብቻ ነው። ➛ተአምራት የመስራት ስጦታ ያለው ክርስቲያን በአሁን ዘመን በቤተክ ርስቲያን ውስጥ እምብዛም ትኩረት እየተሰጠው አይደለም።ይህ ስጦታ በሃገራችን በኢትዮጵያ ላለፉት 50አመታት እውን ሆኖ ቆይቷል የሞተ ያስነሱ አባቶችና የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ፣መንገድ ላይ እየሄዱ የመኪና ነዳጅ አልቆባ ቸው ውሃ ላይ ፀልየው ወደ ነዳጅ ቀይረው ጉዟቸውን የቀጠሉ አገልጋዮች አሉ፣ ከቤት እንስሳት ላይ አጋንንት ያስወጡ፣ አይነስውራን፣ መስማት የማይችሉ  ላይ እጅ ጭነው ተአምር ያደረጉ አሁንም እያደረጉ ያሉ አገልጋዮች አሉ። ➛ቤተክርስቲያን ለተአምራት ስጦታዎች በሰጠችው ዋጋና ትኩረት ልክ ተአምራት ታያለች። ትኩረት የማትሰጥ ቤተክርስቲያን ተአምራት የሚለው የጥንት ክስተት እና የሰው ስም ብቻ ይሆንባታል። ➛በሚያሳዝን ሁኔታ በትምህርታቸው እና በአስተምህሯዋቸው ተአምራት የለም እያሉ የሚናገሩ ደፋር ሰዎችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ማየት የተለመደ ሆኗል። የነዚህ ሰዎች ትልቁ ችግራቸው ተአምራት አቁሟል ሲሉ እግዚአብሔር ስራ አቁሟል እያሉ እንደሆነ አለማወቃቸው ነው። ➛ተአምራት የእግዚአብሔር የሁልጊዜ የህይወት ዘይቤው ነው።ጌታ ትናንሽ ነገር ሰርቶ አያቅም ሁሌ ተአምር ማድረግ ይወዳል። ኢየሱስ ዛሬም ያው ነው። በማንነቱ፣በስራው፣ በአላማው አልተቀየረም። ዛሬም ኢየሱስ በስራ ላይ ነው። ተአምራትን በተመለከተ ልንረዳ የሚገቡ እውነታዎች ◆ተአምራት ከእግዚአብሔር ስለመሆናቸው በቃሉና በመንፈስ መፈተን አለብን። ◆ እውነተኛውን ተአምራት በፍሬው መመዘን። (አማኞችን ያንፃል?፣ ያላመኑትን ወደ ወንጌል እውነት ይጠራልን ብሎ መመዘን ይቻላል) ◆ተአምራት ሲሆን አላማውን መረዳት። ሰማያዊ የሆነ አላማና ዒላማ የሌለው ተአምራት አስማት ነው። ◆ ተአምራት ቃሉን ለማፅናት የሚውል እንጂ ለታይታ እና ለስጋዊ ጥቅም የሚውል ስጦታ አይደለም። ◆ስለ ተአምራት ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህርያትን ማንበብና መረዳት የእያንዳንዱ አማኝ ድርሻ ነው። ◆ተአምራት እውነተኛ፣ትክክለኛ እና የሚረጋገጡ ናቸው። አየር ላይ ያለ የማይጨበጥ ፣የማይጠቅም፣ሰላቢና ውጤት አልባ ተአምራት መተት እንጂ ተአምራት አይደለም። ክፍል 96 ይቀጥላል ✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ) 💐share 💐share 💐share @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE

  • 1 мая1 8861

    https://youtu.be/LeMtVgim0Uw?si=HbfPCV0hO69LcFXH