- Последний пост
- 6 нояб.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የደመወዝ ጭማሪጉዳይ💴💰 ==================== በክልሎች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት ያጋጠመው ኮሚሽኑ በፈጠረው የቀመር ሥሌት አረዳድ ችግር እንደሆነ ተነገረ። ከ2016 ሰኔ ወር በኋላ ለተቀጠሩ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት አይመድብም ተብሏል። ከአንድ ወር በኋላ የመንግሥት ሠራተኞች ቆጠራ እንደሚደረግ ተሰምቷል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ያጋጠመው የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሠራው የቀመር ሥሌት ላይ በተፈጠረ የአረዳድ ችግር ምክንያት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መምርያ ኃላፊ አቶ ፍሬው ኃይሌ፣ አምስቱ ክልሎች የበጀት ጉድለት እንዳጋጠማቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡
"በአፋር ክልል በተከሰተው ግጭት ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል" =================== #Ethiopia በአፋር ክልል “የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረዋቸዋል” ከተባሉ እና ከአጎራባች አካባቢዎች ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ተናገሩ። ከቀያቸው የተፈናቀሉት ነዋሪዎች፤ በአፋር ክልል፣ ዞን ሁለት፣ መጋሌ ወረዳ በሚገኘው በፋሮ ቀበሌ እና በአቅራቢያው በሚገኙ ቦታዎች መጠለላቸውንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በስልክ አነጋገርኳቸው ብሎ በእማኝነት ያቀረባቸው ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች ይህንኑ የክልሉን መረጃ አረጋግጠዋል። በአሁኑ ወቅት በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ያሉ ቦታዎች ሚልኪ፣ ዋረዓ፣ ሚላ፣ ከረፈቱ፣ ካኦሶበራ እና ከረሙአጋ የተባሉ አካባቢዎች መሆናቸውን እነዚሁ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ©️ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ኢትዮጵያ በሶስት ወራት 300 ድሮኖች አመረተች ድሮኖቹ በስካይዊን እና ኤሮአባይ ፋብሪካዎች የጋራ ጥረት መገንባታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ፤ ለፓርላማ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሩቡን ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም ኩባንያዎች በቅርብ ጊዜ የተመረቱት ድሮኖች በዋናነት ለመዝናኛና ገቢ ማስገኛነት የሚውሉ እና የሀገር ውስጥና የቀጣናዊ ገበያዎችን ዒላማ ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ድሮኖች በመመረት ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት ም/ዳይሬክተሩ፤ የምርት አቅምን ለማሳደግ የጥሬ ዕቃ ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል። በሀገር ውስጥ የተሠሩ ድሮኖች ከዚህ ቀደም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ እና በኢሬቻ በዓል ወቅት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ በዘገባው አስታወሷል፡፡ ©️ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፤ የትግራይ ኃይሎች በወረዳው ቶንሳ ቀበሌ ላይ "በከፈቱት ጥቃት"፤ "ወደ 15 ኪሎ ሜትር ዘልቀው" መግባታቸውን እና "ስድስት መንደሮችን" መቆጣጠራቸውን በመግለጽ ከሰሱ። የትግራይ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በበኩሉ "የከፈትነው ጥቃትም ሆነ የተቆጣጠርነው መሬት የለም" ሲል ወንጀላውን አጣጥሏል። የመጋሌ ወረዳ አስተዳዳሪ "ሙሉ ቀን ያንን ቦታ ይዘው፣ እስከ 12 ሰዓት ሕዝቡ እየሸሸ፣ [ታጣቂው ቡድን] ቦታ እየያዘ ሄዷል። ከዚያ ሁሉንም ቦታ ከተቆጣጠረ በኋላ ከባድ መሳሪያ ወደ ሕዝቡ መወርወር የጀመረው [ምሽት] 12 ሰዓት አካባቢ ነው" ሲሉ በክልሉ መንግሥት የቀረበውን ውንጀላ አጠናክረዋል። የአፋር ክልል መንግሥት "ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ"፤ "በሞርታር እና በዙ-23" ከባድ መሳሪያዎች ተኩስ መከፈቱን በመጥቀስ በመግለጫው ወንጅሏል። የአካባቢው ነዋሪ በተኩሱ ድምጽ "ተደናግጦ፣ መሸሹን" የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው አቶ አብዱ፤ ወደ ክልሉ እንቅስቃሴ ያደረገው "በጣም ብዙ ኃይል" መሆኑን አንስተዋል። የትግራይ ጦርነትን ያስቆመው "የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል" ሲልም ወቅሷል። "አሁን ይሄ ነው ሊባል የሚችል አይደለም" ሲሉ የታጣቂዎችን ብዛት በቁጥር መጥቀስ እንደማይችሉ አክለዋል። መጋሌ ወረዳ ከትግራይ ክልል ጋር "በአራት ወረዳ" እንደሚዋሰን የሚናገሩት አቶ አብዱ፤ "በዚያ ግንባር ሁሉ ኃይሉ ገብቷል" ብለዋል። በአፋር ክልል መንግሥት የቀረበውን ክስ በተመለከተ የትግራይ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ተክላይ ኪዳነ "አፋር ገብተን የተቆጣጠርነው አንድም ቦታ የለም" ሲሉ በትግራይ ኃይሎች ላይ የቀረበውን ክስ አስተባብለዋል። ©️ ቢቢሲ አማርኛ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥምት ወር ምርጥ ተጫዋቾች ይፋ ሆነዋል
የባህር በርን የተመለከተ አዋጅ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 16/1980 👉 የትግራይ፣ 👉 የአሰብ፣ 👉 የድሬዳዋ እና 👉 የኦጋዴን ራስ ገዝ አካባቢዎች አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ነው። የኤርትራ የሚባል መጠሪያ ያለው ስፍራ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግስት ሥር በፌድሬሽን ይተዳደር በማለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አ 15 December 1950 ባካሄደው 326ኛ መደበኛ ጉባኤው ያጸደቀው ውሳኔ ቁጥር 390 (V)A የኢትዮጵያ መንግስት በወደቦች ላይ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤት መሆኑን ያትታል።ትውልዱ ሰነድ ያጣው አሰብን ማን ለኤርትራ እንደሰጠ የሚገልፅ ብቻ ነው። ©️ ዋሱመሐመድ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ትናንት ምሽት የአፋር ክልላዊ መንግሥት የህወሃት ቡድን ወደ ክልሉ ወሰን ውስጥ በመግባት ስድስት መንደሮች በጉልበት ተቆጣጥሯል በማለት ከሷል። የአፋር ክልል ኮምዩንኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫው አክሎም ቡድኑ «ንጹሐንን በሞርታርና በዙ 23 መደብደቡን» ወንጅሏል። መግለጫው አያይዞም በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች የህወሃት ቡድን ወሰን ተሻግሮ መግባቱን፤ ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መክፈቱን በማመልከትም «የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል» ሲልም ከሷል። ተኩስ በተከፈተበት ወቅት የአፋር ሽማግሌዎች የቡድኑን ታጣቂዎች እንዲመለሱ መማጸናቸውን ሆኖም ግን ሳይቀበሏቸው በመቅረታቸው ግጭት መከተሉንም መግለጫው ዘርዝሯል። ህወሓት እስካሁን በአፋር ክልል ኮምዩንኬሽን ቢሮ በኩል ስለቀረበው ክስ ምላሽ አልሰጠም። ሰሜን ኢትዮጵያ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ያደረሰውን ጦርነት ያስቆመው በፌደራል መንግሥትና በህወሃት መካከል ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ላይ የተደረሰው ስምምነት ሦስት ዓመት የደፈነው ባሳለፍነው እሑድ ነው። ©️ DW Amharic
без подписи
без подписи
የፖሊስና ኅብረተሰብ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛዋ ኢንስፔክተር ኪያ ንጉሴ ቱሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፖሊስና ኅብረተሰብ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢበት፣ በፕሮግራም መሪነት እና በመድረክ አስተዋዋቂነት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ለበርካታ ዓመታት ስታገለግል የነበረችው ኢንስፔክተር ኪያ ንጉሴ ቱሉ ባጋጠማት ህመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በ40 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተነገረ፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል ተብሏል፡፡
без подписи
без подписи
ልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሊሰማራ ነው የልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያሠማራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ፌደራል ፖሊስ በቅርቡ የሚያስመርቀውን የልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያሠማራ ነው ያስታወቀው፡፡ ኮማንዶው ለበርካታ ወራት ልዩ ሥልጠና እንደወሰደና የትኛውንም ዓይነት ግዳጅ መፈፀም የሚችል ስለመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልፀዋል፡፡ “የፖሊስን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግና ተልዕኮውን የሚያሳልጥ ዘመናዊ የትጥቅ አቅም በልዩ ሁኔታ ተሟልቷል፤ ይህንን መጠቀም የሚችል የልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ኃይል አሠልጥነን ለማስመረቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል” ብለዋል፡፡ ©️ - ኢ.ፌ.ፖ.ሚ
без подписи
Update በክብር በተሸኙት አቶ ደመቀ መኮንን ቦታ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።