መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጅንሲ ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት
Статистика- Последний пост
- 7 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የአረንጋዴ አሻራ የችግን ተከላ ተደረገ። "ተስፋን እንትከል" "ውብ፣ አረንጓዴና ለንሮ ምቹ ከተማን ለቀጣዮ ትዉልድ እናሳርፍ" በሚል መሪ ቃል ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት ይዛታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በስሩ ካሉ ክ/ከተማዋች ጋር በመሆን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አይሲቲ ፓርክ የችግሮች ተክላ አከናወነ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን ተቋማቸው በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ከዚ ቀደም ከፍተኛ ስራዎች ሲከውን መቆየቱን አስታውሰው የአቃቂ ክ/ከተማን በምሳሌነት አንስተዋል፤በቀጣይም ተቋማቸው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ችግኖቹን የመንከባከብና እድገታቸውን የመቆጣጠር ስራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ላይ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አመራር፣ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ቀጣዩ ትውልድ ንፁ የአየር ንብረት እና ለንሮ ምቹ የሆነ ከተማ እንዲኖረው ማድረግ የሁሉም ማህበረሰብ የጋራ ድርሻ ነው በማለት ሃላፊነት መወጣት ግዴታ ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ዘገባው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
Live stream started
ውድ ተገልጋዮቻችን :- ቅዳሜ አገልግሎት እንሰጣለን በመደበኛ የስራ ቀናት የምሳ ሰዓትን ጨምሮ ሁል ጊዜ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ሙሉ አገልግሎት እየሰጠን እንደሆና በአክብሮት ለማስታወስ እንወዳለን።
без подписи
ውድ ተገልጋዮቻችን በመደበኛ የስራ ቀናት የምሳ ሰዓትን ጨምሮ ሁል ጊዜ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ሙሉ አገልግሎት እየሰጠን እንደሆና በአክብሮት ለማስታወስ እንወዳለን።
የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያዘምኑ SSRMS እና የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በይፋ አስመረቀ !! የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽነትና ቀልጣፋነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ የአገልግሎት ስታንዳርድ የሬጂስትሬሽንና ሞኒተሪንግ ሲስተም (SSRMS) እንዲሁም ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል (Call Center) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል። 1. SSRMS ኤጀንሲው ለዜጎች የገባውን የስታንዳርድ ቃል ኪዳን በተግባር ለማሳየት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የተገለፀለት ይህ ሲስተም በተቋሙ የአይቲ ባለሙያዎች የለማ (In house developed System) ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መመዝገቢያ እና መቆጣጠርያ ለሲስተሙ መነሻ ከሆነው ቂርቆስ ክ/ከተማ በይፋ ተመርቋል። #ሲስተሙ እያንዳንዱ አገልግሎት በምን ያህል ጊዜ እንደተጠናቀቀ፣ በስታንዳርድ የሚለካና የስራ ሂደቱን ደረጃ በደረጃ ለመከታተል የሚያስችል ሲሆን ከተቀመጠው ስታንዳርድ በታች ስራዎች ሲፈፀሙ ጭምር መከታተል የሚያስችል መሆኑም ታውቋል። 2. የጥሪ ማዕከል (Call Center) 🫴6577 ደንበኞች ቢሮ ድረስ መምጣት ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ሆነው የመረጃና የቅሬታ ጥቆማ ማቅረቢያ #6577 ላይ በመደወል በይፋ ስራ ጀምሯል። #እነዚህ፤ ሁለቱ ሲስተሞች የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮችና የክፍለከተማው #ሰራተኞች በተገኙበት ምርቃቱ የተከናወነ ሲሆን #የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን እንደገለጹት፣ ሲስተሞቹ ተግባራዊ መደረጋቸው አገልግሎትን ለማፋጠን፣ ተገልጋዩን ማህበረሰብ በአገልግሎት አሰጣጥ በማርካት፣ በተለይም የመሬት መረጃን ለውሳኔ ሰጪዎችና ለባለጉዳዮች በታማኝነትና በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ሲሉ የገለፁ ሲሆን አያይዘውም ሲስተሙን በሁሉም ክ/ከተማ ተግባራዊ በማድረግ፣ በሌሎች ክ/ከተሞች እየለሙ የሚገኙ ተመሳሳይ ሲስተሞች ወደ አንድ በማድረግ የተቋሙ ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል። #በተያያዘም የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ቶላ በበኩላቸው አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አንስተው፣ በሲስተሙ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን አካላት አመስግነው፣ ኤጀንሲው በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ መሆኑን አፅኖት ሰተዋል። ለዚህ ዝግጅት መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉት የቂርቆስ ቅ/ፅ/ቤት ሁሉም ስታፍ ሲሆን፣ በመዝጊያው ላይ የፅ/ቤቱ ዋና ሃላፊ አቶ እንዳልካቸው ፍሰሃ የሰርተፊኬት ስጦታም አበርክተዋል። #በእለቱም ከቅ/ፅ/ቤት ሃላፊዎችና ከታዳሚው የተሰጡ ገንቢ አስተያየቶችን በማካተት በሁሉም ቅ/ፅ/ቤቶች ተግባራዊ የማድረግ ስራ እንደሚጀመር ተጠቁሞ የእለቱ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። #Digital Staff #Digital Agency🫴 #Digital Ethiopia !
የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አገልግሎቶችን አዲስ በተሻሻለው ሲስተም መሰጠት ጀመረ --------------------------------------------- የካቲት 10/2018 ዓ.ም (የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አገልግሎቶችን በማሻሻል በተተገበሩት አዲስ ሲስተም በአዲስ መሶብ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። አገልግሎቱን የአዲስ መሶብ እና የተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ማስጀመር ተችሏል። የሚሰጡ አገልግሎቶች ዝርዝር: * የቋሚ ንብረት እዳ መያዣ /ዋስትና ምዝገባ አገልግሎት ፤ * የቋሚ ንብረት እዳ ስረዛ ምዝገባ አገልግሎት ፤ * የቁራሽ መሬት ይዞታ የፍትህ ተቋማት/ፍርድ ቤት ዕግድ ምዝገባ አገልግሎት፤ * የቁራሽ መሬት ይዞታ የፍትህ ተቋማት/ፍርድ ቤት ዕግድ ስረዛ አገልግሎት፤ * የቋሚ ንብረት እዳ ምዝገባ ዕድሳት ምዝገባ አገልግሎት፤ * የሪል እስቴት፣ የማህበራት የጋራ ሕንጻ እና የግል አልሚ፤ የጋራ ሕንጻ የተናጠል ሰርተፍኬት /ካርታ አገልግሎት እና * የሪል እስቴት ፣ የማህበራት የጋራ ሕንጻ እና የግል አልሚ የጋራ ሕንጻ የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ናቸው። ውድ ተገልጋዮች አገልግሎቱን በዋና መስርያ ቤት ቀርበው ይገልገሉ:: በቅርብ ግዜ በቦሌ ቅርንጫፍም አገልግሎቱ የሚጀመር መሆኑን እንገልፃለን! Addis MESOB ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት: Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ Website: addis.mesobcenter.et
без подписи
ውድ ተገልጋዮቻችን ማንኛውንም የአገልግሎት ክፍያ ስትፈፅሙ ከይዞታው ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካይ የንግድ ባንክ አካውንት ወደተቋሙ አከውንት ማስገባት አለባችሁ በተጨማሪም ገንዘቡን በማዘዣ ወይም ከአካውንት ስታስተላልፉ ናሬሽኑ ቦታ ላይ የባለይዞታው ስም ተፅፎ የባንክ ስሊፑ ወይም ደረሰኙን አምጥታችሁ በኛ ፋይናንስ ማወራረስ አለባችሁ።
без подписи
без подписи
መሬት ነክ ንብረት ምን ማለት ነው? *** መሬት ነክ ንብረት ማለት በመሬት ይዞታ ላይ ከላይ እና ከታች ለንግድ፣ ለመኖሪያነት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለማህበራዊ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ለሽያጭ፣ ለኪራይ ወይም ለኪራይ አገልግሎት እንዲውል የተገነባ ህንፃ እና በመሬት ላይ የሚገኙ ቋሚ ተክሎችን የሚያካትት ነው፡፡ የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መሰረቱ *** 1/ ከመሬት በላይ እና በታች ያለውን መሬት ነክ ንብረት መረጃን ከይዞታው ጋር አስተሳስሮ በወረቀት እና በዲጅታል ፎርም ይዘጋጃል፤ 2/ የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ የሚገልፅ መረጃ በወረቀት ወይም በወረቀት እና በዲጅታል ፎርም ከኦርቶ ፎቶ ጋር ተቀናጅቶ ይዘጋጅለታል፤ 3/ የቁራሽ መሬቱ ልዩ መለያ ኮድ ለመሬት ነክ ንብረትም እንደመለያ ኮድ ሆኖ ያገለግላል፤ 4/ የተደራጀው መረጃ የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ በመዝጋቢ ተቋም ውስጥ ተደራጅቶ የሚቀመጥ ሲሆን ለንብረት ዋጋ ግምት ዋና ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል፡፡ የመሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ዓላማዎች *** 1/ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ያለን መብት፣ ክልከላና ሃላፊነትን በምዝገባ በማረጋገጥ፣ የባለይዞታውን የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት እና በይዞታው ላይ ላረፈ የመሬት ነክ ንብረት የባለቤትነት መብት ዋስትና በመስጠት ዜጎች ሃብታቸውን ልማት ላይ እንዲያውሉ በማበረታታት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ልማትን በማፋጠን የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ 2/ ለነጻ ገበያ ኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና ለሚጫወተው የንብረት ገበያና ለባለይዞታዎችም ጭምር አስፈላጊ የሆኑትን በከተማ መሬት ይዞታ ላይ የተጠቃሚነት መብትን ዋስትና የሚያረጋግጡ እና በይዞታው ላይ ላረፈው መሬት ነክ ንብረት ባለቤትነት እውቅና የሚሰጡ መረጃዎችን በተሳለጠ ሁኔታ ለመስጠት፤ 3/ መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ፍትሃዊ ግብር አሰባሰብ እና ወቅታዊ የንብረት ዋጋ ግምት መነሻ የሚሆን መረጃን በማደራጀት የከተሞችን ገቢ ለማሳደግ እና ለንብረት ካሳ ግምት ለመወሰን የመረጃ መንጭ ለመሆን፤ የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አተገባበር *** 1/ በመሬት ይዞታ ላይ ወይም በታች ያረፈ መሬት ነክ ንብረት ዝርዝር መረጃዎችን በማረጋገጥ የሚመዘገብ ይሆናል፤ 2/ በተመዘገበ መሬት ነክ ንብረት ላይ የሚከሰቱ ለውጦች እና መገለጫዎች ይመዘገባሉ፤ ለመሬት ተጠቃሚነት መብት እና መሬት ነክ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ *** ተቃራኒ ሁኔታ መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 36 ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የተሰጠው ማንኛውም ሰው በመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ላይ ለተጠቀሰው መሬት ባለይዞታ እና በመሬት ይዞታው ላይ ላረፈው መሬት ነክ ንብረት ባለቤት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ ምንጭ፡- የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1381/2017 ኅዳር 19/2018 ዓ.ም AA-LHRIA
የቀጠለ… ስለ ማስረጃ አቀራረብ (ክፍል ሁለት) --------------------------------------- 5/ በሪል ስቴት በጋራ የተያዘ ይዞታ ሲሆን ተያያዞ ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፡- ሀ/ በሪል ስቴት አላሚው ለአጠቃላይ የጋራ መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ የሊዝ ክፍያ የከፈለበት ሲሆን፤ በጋራ መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ የሚቀርብ የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ሲቀርብ፡- 👉 ህጋዊ ማህበር የተመሰረተበት መተዳደሪያ ደንብ፣ 👉 የህንጻ ዲክለሬሽን ወይም የጋራ እና የግል የሆነውን መብት ለይቶ የሚደነግግ ማስረጃ፣ 👉 የጋራ ይዞታው የተገኘበት ሰነድ፣ 👉 ለሪል እስቴቱ ተሰጥቶ የነበረ ካርታ 👉 ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ 👉 ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ 👉 ለሪል እስቴት ተሰጥቶ የነበረ የሊዝ ውል፣ 👉 ለባለይዞታዎች ማህበር ከመብት ሰጪው ተቋም የተሰጠ የይዞታ ማስረጃ፣ ለ/ የሪል እስቴት አልሚው ለአጠቃላይ የጋራ መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ የሊዝ ክፍያ የከፈለበት ሲሆን፣ የግለሰብ ይዞታዎች ላይ የሚቀርብ የተናጠል የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ሲቀርብ፡- 👉 አጠቃላይ የይዞታው በማህበር ስም የተረጋገጠበት ሰነድ፣ 👉 የግለሰቦቹ ይዞታ የተገኘበት ደጋፊ ሰነድ፣ 👉 ከመብት ሰጪው የተሰጠ የይዞታ ማስረጃ፣ 👉 ከባንክ ጋር የደተደረገ ውል (ካለ)፣ 👉 ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ 👉 ሌሎች ከመብት ሰጪው ተቋም የተሰጠ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መጠየቅ አለበት፣ ሐ/ የሪል እስቴት አልሚው በጋራ መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ የሊዝ ክፍያ ያልከፈለ ሲሆን፣ በጋራ መጠቀሚያዎቹ ላይ ለጋራ የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ሲቀርብ፡- 👉 የጋራ መጠቀሚያዎቹ የህዝብ በመሆናቸው ምክንያት በማረጋገጥና ምዝገባ ደንብ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 44 መሰረት የከተማን መሬት ለማልማት ስልጣን በተሰጠው መንግስታዊ ተቋም ስም የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ሲርብ የሚስተናገድ ይሆናል፣ 👉 ስለሆነም በዚሁ ንዑስ አንቀጽ (ሐ) (1) መሰረት የቀረበ የይረጋገጥልኝ ጥያቄ በመብት ሰጪው ተቋም መሬቱን ለሚያስተዳድረው ተቋም መብት ከፈጠረለት ሰነድ ጋር በተጨማሪ በማረጋገጥ እና ምዝገባ ደንብ አንቀጽ 44 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የይዞታውን ስፋት እና አድራሻ፣ የከተማ ጣቢያ እና የቁራሽ መሬቱን ልዩ መለያ ኮድ፣ የይዞታወን አገልግሎት እና ደረጃ የሚገልጽ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፣ መ/ የሪል እስቴት አልሚው በጋራ መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ የሊዝ ክፍያ ያልከፈለ ሲሆን ፤ የግለሰብ ይዞታዎች ላይ የሚቀርብ የተናጠል የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ሰነዶች፤ 👉 በመብት ሰጪው ተቋም የተሰጠ ማስረጃ፣ 👉 የመሬት ይዞታው የተገኘበት ከሪል እስቴት የተሰጠ የማስተላለፊያ ውል ማስረጃ፣ 👉 ለሪል እስቴት ተሰጥቶ የነበረ ካርታ፣ 👉 ለሪል እስቴት ተሰጥቶ የነበረ የሊዝ ውል፣ 👉 የመብት መደራረብና ግጭት አለመኖሩን በመብት ሰጪ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ፣ 👉 ይዞታው ሊዝ ከሆነ ወቅታዊ የሊዝ ወይም የመሬት ኪራይ የተፈጸመበት ደረሰኝ፣ 👉 የጋራ ግቢ ያላቸው አካላት ይዞታ / ተነጻጻሪ ይዞታ ሲሆን የይረጋገጥልኝ ጥያቄ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ሰነዶች፡- ሀ/ የጋራ ግቢ ባለቤትነት ላይ የሚገኝ ተነጻጻሪ መብትን ለማረጋገጥ የቀረበ ሲሆን ፡- ➺ የግለሰብ ድርሻ የሚያሳይ ካርታ፣ ➺ የጋራ ወሰኑን የሚያመላክት ካርታ፣ ➺ የጋራና የግላቸው መብት እንዴት እንደሚተዳር ወስነው ያስመዘገቡበት የሰነድ ማስረጃ ፣ ➺ የዘመኑ የመሬት ይዞታ ግብር ክፍያ ደረሰኝ፣ ➺ ከባክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ ➺ ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ) ፣ ➺ ቦታው የተገኘበት አግባብ በሰነድ ማስረጃ የተደገፈ ከሆነ ይሄው ሰነድ መቅረብ አለበት፣ ለ/ በይዞታው ስሪት ልዩነት ላይ የሚገኝ ተነጻጻሪ መብትን ለማረጋገጥ የቀረበ ሲሆን፡- ➺ የመሬት ይዞታ ምጣኔ የሚያሳይ ካርታ፣ ➺ በአንዱ የመሬት ይዞታ ስሪት ተጠቃሎ እንዲረጋገጥ የተወሰነበት ሰነድ ሲቀርብ፣ ➺ ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ ➺ ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ ➺ የዘመኑ የመሬት ይዞታ ግብር ክፍያ ደረሰኝ፣ ➺ ቦታው የተገኘበት አግባብ በሰነድ ማስረጃ የተደገፈ ከሆነ ይሄው ሰነድ መቅረብ አለበት፣ 7/ በማህበር የተያዘ የጋራና የተናጠል ይዞታ ሲሆን ተያያዘው ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፡- ሀ)በማህበሩ ስም የማረጋገጥ ጥያቄ ሲቀርብ፡- 👉 ለማህበሩ የተሰጠ የጋራ ካርታ፣ 👉 የመብት መደራረብና ግጭት አለመኖሩን የተረጋገጠበት ማስረጃ፣ 👉 ቦታው የተገኘበት አግባብ በሰነድ ማስረጃ የተደፈገ ከሆነ ይሔው ሰነድ መቅረብ አለበት፣ 👉 ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ 👉 ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ 👉 ማህበሩ የኮንዶሚኒየም ቤት ለመገንባት እና ለማስተዳደር የተደራጀ ሲሆን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 (ሀ) ላይ በተደነገገው መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል፣ ለ) የማህበሩ አባላት በሆኑ ግለሰቦች ባለይዞታዎች የተናጠል የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ሲቀርብ፡- 👉 ለማህበሩ የተሰጠ ካርታ፣ 👉 ለየግላቸው የተሰጠ ካርታ፣ 👉 ከባንክ ጋር የተደረገ ውል ካለ፣ 👉 ከባክክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ 👉 የመብት መደራረብና ግጭት አለመኖሩን በመብት ሰጪው ተቋም የተረጋገጠበት ማስረጃ፣ 👉 የማህበሩ አባላት በሆኑ የኮንዶሚኒየም ቤት ባለይዞታዎች የተናጠል የይረጋገጥልኝ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 (ለ) ላይ በተደነገገው መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል፣ ህዳር 3/2018 ዓ.ም AA-LHRIA የተሻሻለው የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 61/2010 መሰረት
ስለ ማስረጃ አቀራረብ (ክፍል አንድ) ----------------------------- ማንኛውም በመሬት ይዞታ ላይ መብቴ ይረጋገጥልኝ ብሎ ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው አሟልቶ መቅረብ የሚጠበቅበት ማስረጃ:- 👇 ይዞታው በሊዝ አግባብ የተገኘ ከሆነ ከማመልከቻው ጋር ተያይዘው ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፡- ✍️ የሊዝ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ወይም ካርታ፣ ✍️ የሊዝ ውል፣ ✍️ በእዳ የተያዘ ከሆነ ህጋዊ የመያዣ ውል ወይም የፍርድ ትዕዛዝ ሰነድ መያዣውን ከሰጠው ተቋም እንዲቀርብ ይደረጋል፣ ✍️ ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎች፣ 👇 የነባር ይዞታ ከሆነ ከማመልከቻው ጋር ተያያዘው ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፣ ✍️ የነባር ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ወይም ካርታ፣ ✍️ በእዳ የተያዘ ከሆነ ህጋዊ የመያዣ ውል ወይም የፍርድ ትእዛዝ ሰነድ መያዣውን ከሰጠው ተቋም እንዲቀርብ ይደረጋል ✍️ ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎች ፣ 👇 የአርሶ አደር ይዞታ ከሆነ ከማመልከቻው ጋር ተያይዘው ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፡- ✍️ በመሬቱ የመጠቀም መብት የተገኘበት ደብዳቤ፣ ✍️ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ሠርተፊኬት ፣ ✍️ የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር፣ ✍️ ሌሎች ከገጠር መሬት አስተዳደር የቀረበ ማስረጃ ፣ 👇 ከኮንዶሚኒየም እና የጋራ ህንጻ ቤቶች ይረጋገጥልኝ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ተያይዘው ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰነዶች፡- 👉 በኮንዶሚኒየምና በጋራ ህንጻ ቤቶች ማህበር ስም የይረጋገጥልኝ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፡- ✍️ በይዞታው ላይ ተደረገ የርክክብ ውል እና የህንጻው ፕላን ጋር፣ ✍️ ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ ✍️ ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ ✍️ የህንጻ ዲክረሬሽን (ካለ)፣ ✍️ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ፣ ✍️ የይዞታ ባለመብትነት ካርታ ፣ ✍️ ሌሎች ከመብት ሲጪ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መጠየቅ አለበት፣ 👉 በኮንዶሚኒየምና በጋራ ህንጻ ቤቶች ባለይዞታ ግለሰብ ስም የይረጋገጥልኝ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፡- ✍️ ለኮንዶሚኒየም ማህበር የተረጋገጠበት እና የተመዘገበበት ማስረጃ፣ ✍️ ከመብት ሰጪው ተቋም ለግለሰብ የተሰጠ የዩኒት ወይም የፍላት ወይም የሴክሽን ባለቤትነት ማስረጃ፣ ✍️ ከባንክ ጋር የተደረገ ውል (ካለ)፣ ✍️ ከባንክ ዕዳ ጋር የተያያዘ ማስረጃ (ካለ)፣ ✍️ ሌሎች ከመብት ሰጪው ተቋም የተሰጠ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መጠየቅ አለበት፣ ✍️ ሌሎች ከመብት ሰጪው ተቋም የጠሰጠ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መጠየቅ አለበት ህዳር 2/2018 ዓ.ም AA-LHRIA ከመመሪያ ቁጥር 61/2010 የተወሰደ ማስታወሻ፡ ሌሎች ስለ ማስረጃ አቀራረብ የይረጋገጥልኝ ጥያቄ አቀራረብ መስፈርቶችን በሚቀጥለው ፅሁፍ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ውድ ተገልጋዮቻችን ቅዳሜ ቅዳሜ አገልግሎት መስጠት እንዳላቆምን እያስታወስናችሁ መታችሁ የትኛውንም አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ እናሳውቃለን።