A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
Статистика- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 47
- Всего постов
- 94
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 5 162
- 1/48двое суток
- 6 606
- 1/72трое суток
- 7 124
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ሂደቱ በይበልጥ እየተጠናከረ መሆኑ ተገለጸ። የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት መመሪያ መነሻ በማድረግ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ፅ/ቤቱ በመገኘት ውላቸውን በማደስ ላይ ይገኛሉ። በስፍራው ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ አገልግሎቱ ቅልጥፍና ባለው መልኩና ረጅም ሰልፎችን በሚቀንስ አሰራር ለማስተናገድ የተደረገው ዝግጅት የሚደነቅ ሲሆን ፣ ነዋሪዎችም ህጋዊ አሰራሩን ተከትለው ውላቸውን ለማደስ የሚያሳዩት ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ለመታዘብ ተችሏል። የውል እድሳት ሂደቱ በዋናነት የአከራይና ተከራይን መብትና ግዴታ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት ያልተገቡ የኪራይ ጭማሪዎችንና ያለአግባብ ተከራይን ከቤት የማስወጣት ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ነው። በዕለቱ ያነጋገርናቸው የጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊ አቶ ታመነ አበበ እንደገለጹት፣ ህብረተሰቡ ስለ መመሪያው ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የምዝገባ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየሄደ ይገኛል ብለዋል። ሆኖም አሁንም የተወሰኑ አከራዮች አስፈላጊውን ሰነድ አሟልቶ በመቅረብ በኩል የሚያሳይዋቸው መዘግየቶች በመኖራቸው፣ ሂደቱን የበለጠ ለማፋጠን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አገልግሎቱን ለማግኘት የመጡ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የውል እድሳቱ መደረጉ በሁለቱም ወገኖች መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በህጋዊ መንገድ ለመፍታት ትልቅ ዋስትና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል። በተለይም የአሰራሩ ግልጽነትና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚሰጡት ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ነሀሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aahdab
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈፀም የተከለከለ ነው ‼️
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ምክትል ስራአስኪያጅ እና የቀድሞ የልደታ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ። ለመላው ቤተሰቦቻቸው ፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የስራ ባልደረቦቻቸዉ መፅናናትን እመኛለሁ። ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ውል በዲጂታል አሠራር በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና የልማድ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታት እርምጃ በመውሰድ የ2019 ዓ.ም የመኖርያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ዋጋ 11.5 በመቶ እንዲሆን ወስኗል፡፡ በወቅታዊ ጥናት ላይ ተመርኩዞ የተላለፈው ውሳኔ አከራዮች የወቅቱን የኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፤ ተከራዮች ደግሞ ከሚያገኙት ገቢ ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና እንግልት ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያስችላል። ይህን ውሳኔ ተከትሎ አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት የአከራይ ተከራይ ውል አዲስና እድሳት አገልግሎትን በሁሉም ምቹና ዘመናዊ ማዕከላቱ በተቀላጠፈ ዲጂታል አሠራር እየሰጠ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱን የወሰዱ የከተማችን ነዋሪዎች በአሠራሩ ቅልጥፍና እና ምቾት የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን፤ ማዕከላችን አገልግሎቱን ፈልገው የሚመጡ ዜጎች የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች አሟልተው እንዲመጡ ጥሪ ያቀርባል፡፡ በውል እድሳት ወቅት መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (ማስታወሻ፡- የሁሉም ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ መያዝ ግዴታ ነው) o የቤት ሰነዶችና የክፍያ ማስረጃ: -የቤት ካርታ -ቀደም ሲል የነበራቸውን የውል ስምምነት ሰነድ -ኪራይ ሲከፍሉበት የነበረ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ሠነድ o ከአከራይ የሚጠበቁ: -የዲጂታል መታወቂያ፣ የነዋሪነት መታወቂያ/የታደሰ/ ፣ ቢጫ ካርድ /የታደሰ/ o ከተከራይ የሚጠበቁ: - የዲጂታል መታወቂያ፣ የነዋሪነት መታወቂያ/የታደሰ/፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ/የታደሰ/፣ መንጃ ፍቃድ/የታደሰ/፣ ፓስፖርት/የታደሰ/፣ የጠበቃ ፍቃድ/የታደሰ/፣ የሰራተኞች ጡረታ መታወቂያ፣ የዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ተማሪ የሙያ ስራ ፍቃድ/የታደሰ/ o በወኪል የሚከናወን ከሆነ : -ህጋዊ የውክልና ሰነድ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи