tgindex
Lemi kura Communication

Lemi kura Communication

Статистика
Последний пост
7 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 405
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
842
21 постов
Вовлечённость
35,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የአረንጓዴ አሻራ ከተሞች ንጹህና ውብ ገጽታ የተላበሱ እንዲሆኑ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበበ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮችና፣ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ። በዕለቱም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለትና ከመሸርሸር በመጠበቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበበ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብም እንዲጸድቁ በማድረግ በትጋት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ሀገር በቀልና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን ጨምሮ የተለያዩ አይነት ችግኞቸን በመትከል ከተሞች ንጹህና ውብ ገጽታ የተላበሱ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 2 июл.1 1601

    "የሚደረግልን ድጋፍ ከተረጅነት ወደ ምርታማነትና ውጤታማነት እያሸጋገረን ነው" የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የሚደረግላቸው የግብዓት፣የስልጠናና የፋይናንስ ድጋፍ ከተረጅነት አልፎ ራስና ቤተሰብን በአግባቡ ወደ መምራትና ለሌሎችም የስራ እድል የመፍጠር ብሎም ወደ ተሻለ ውጤት እያሸጋገራቸው መሆኑን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ተናገሩ። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከክ/ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም GIZ ከተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተስማሚና ኃይል ቆጣቢ መሳሪያዎችን ድጋፍ ያደረገላቸው 166 የሚሆኑ በምግብ ዝግጅት የተደራጁ የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የተደረገላቸው ድጋፍ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እያሸጋገራቸው መሆኑን ገልጸዋል። "ሀይልን እንቆጥብ፣አካባቢያችንን ከብክለት እንጠብቅ፣ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ሃሳብ ድጋፋ የተደረገላቸው ተጠቃሚዎች አሁን ላይ ሴፍትኔት ድሮ ከነበረው የዘላቂ ተረጅነት ባህሪ ወጥቶ ሰዎች አምራችና ታታሪ የሚሆኑበትን አዲስ የአሰራር ማዕቀፍ ይዞ መምጣቱ ሰርቶ መለወጥ ለሚፈልግ ሁሉ ሰፊ አማራጭችን ይዞ መምጣቱን ገልጸው አስተዳደሩ ለሚያደርግላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያላቸውን ምስጋናም ገልጸዋል። የክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ ሰርቶ መለወጥ፣ጥረት ማድረግና የድህነት ታሪኩን ለመቀየር ለሚታትር ሰው ሰፋፊ እድሎችና አማራጮች እንዳሉና የሚደረጉ ድጋፎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድሎችን በመፍጠር ወጣቱን፣ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን እና ዛሬ የሚደረገው የተስማሚና ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂም ለመለወጥ ዝግጁ ለሆኑ ዜጎች የተሻለ አቅም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል። via ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን ሰኔ 25/2018

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ተስፋን እንትከል! ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የ2018 የክረምት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ንቅናቄ ምክኒያት በማድረግ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በሁሉም ወረዳዎች የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ተግባር ተከናውኗል። በችግኝ ተከላ ንቅናቄው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት፣ የመስሪያ ቦታዎች አስተዳደር ጽ/ቤት፣የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት፣ፍትህ ጽ/ቤትን ጨምሮ በርካታ ተቋማት በህብረት የችግኝ ቦታዎችን የቆፈሩ ሲሆን ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህይራድ ዳምጤ እንደ ክ/ከተማ አስተዳደሩ 1.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙን ገልጸው የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካት የተለያዩ ተቋማትን፣አደረጃጀቶችንና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ያየህይራድ የሚቆፈሩት ጉድጓዶች መጠነ ጥልቀታቸውንና ተገቢውን ርቀት የተጠበቁ እንዲሆኑ ሰፊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የወደፊት እስትንፋሳችን ምንጭ የሆኑትትን እጽዋት በስፋት ተክለን የተሻለች የጋራ ነጋችንን ለመኖር ሁላችንም የሚጠበቅብንን ሚና መወጣት ይኖርብናልም ብለዋል። ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን ሰኔ 25/2018

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ባለፈ ለከተማችን ውበትና ለነዋሪዎቻችን ጤና እጅግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከሴፍቲኔት አባላትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የጉድጓድ ቁፋሮ መርሃ ግብር የክ/ከተማው ሥራና ክህሎት ጽ/ ቤት አመራሮች የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የሴፍቲኔት መዋቅሮች፣ የተለያዩ ማኅበራትና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት አካሂዷል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ ባስተላለፉት መልእክት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ባለፈ ለከተማችን ውበትና ለነዋሪዎቻችን ጤና እጅግ ወሳኝ ነው። ዛሬ የምንቆፍረው እያንዳንዱ ጉድጓድ ነገ ለምናያት ለምለም ኢትዮጵያ የምንጥለው የመሰረት ድንጋይ ነው። ህብረተሰቡ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግን ባህል ሊያደርገው ይገባል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ እንደተናገሩት ይህንን ታላቅ አገራዊ ጥሪ ስኬታማ ለማድረግ የሴፍቲኔት አባላትና የተለያዩ ማህበራት እያሳዩ ያሉት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። የስራ ዕድል ፈጠራን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በማጣመር የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል።

Lemi kura Communication — tgindex