tgindex
SNE Ethiopia (ልዩ ፍላጎት)

SNE Ethiopia (ልዩ ፍላጎት)

Статистика
@snie_ethioанглийский

This channel focuses on raising public awareness, increasing education and sharing tips about childrens with and without disabilities. For more info @Snie_bot

Последний пост
29 мар.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
504
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
803
20 постов
Вовлечённость
159,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • በኦቲዝም ውስጥ የሚታይ የክህሎት መቀነስን (Regression) መረዳት የክህሎት መቀነስ (Regression) ምንድን ነው? Regression ወደ አማርኛችን ስንመልሰው ማሽቆልቆል/መመለስ/ወደኋላ መመለስ ማለት ሲሆን ይህም አንድ ልጅ ቀድሞ የተማራቸውንና ያዳበራቸውን ክህሎቶች መልሶ ሲያጣ ማለት ነው። ይህም የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦ - የንግግር መቀነስ ወይም ቃላትን መርሳት - የአይን ንክኪ ወይም ማህበራዊ ግንኙነት መቀነስ - የጨዋታ ወይም የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን (እንደ ራስን መመገብ፣ መልበስ) ማጣት - የባህሪ መለዋወጥ (ቶሎ መቆጣት) ወይም ራስን ማግለል * ይህ ሁኔታ በድንገት ወይም በሂደት ሊከሰት ይችላል። የክህሎት መቀነስ (Regression) ለምን ይከሰታል? ለዚህ አንድ ወጥ የሆነ ምክንያት ባይኖርም፣ የተለመዱት መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦ - የአንጎል እድገት ለውጦች፦ የልጆች እድገት ፍጥነት የተለያየ ነው። አንዳንድ ጊዜ አንጎላቸው ራሱን መልሶ በሚያደራጅበት ወቅት በክህሎቶቻቸው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። - ውጥረት ወይም ትልልቅ ለውጦች፦ አዳዲስ ነገሮች ለልጁ ከአቅም በላይ ሊሆኑባቸው ይችላሉ። ለምሳሌ፦ አዲስ ትምህርት ቤት፣ የመኖሪያ ቤት መቀየር፣ አዲስ ጨቅላ ህጻን ወደ ቤት ሲመጣ ወይም የለመዱት የዕለት ተዕለት ተግባር ሲቀየር። - የመግባባት ችግር መፈጠር፦ አንድ ልጅ ፍላጎቱን መግለጽ ካልቻለ፣ ንግግርን መሞከር ሊያቆም ወይም በምትኩ በለቅሶና በንዴት ስሜቱን ሊገልጽ ይችላል። - የጤና ወይም የስሜት ህዋሳት ችግር፦ እንደ ህመም፣ የእንቅልፍ እጦት ወይም ለከፍተኛ ድምጽና ብርሃን መጋለጥ ለክህሎት መቀነስ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። - ልምምድ ማነስ፦ አንድ ክህሎት በየቀኑ ካልተተገበረ ሊረሳ ይችላል። ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? - በመረጋጋት ሁኔታውን መከታተል፦ የትኞቹ ክህሎቶች ተቀየሩ? መቼ ጀመረ? በወቅቱ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? የሚሉትን በማስተዋል መንስኤውን ማወቅ ይቻላል። - ከመሰረታዊ ነገሮች መጀመር፦ ልጁ ያጣቸውን ክህሎቶች በድጋሚ በቀላል ደረጃ እናስተምረው። "ከዜሮ እየጀመርን ሳይሆን፣ የነበረውን መልሰን እየገነባን ነው" ብለን እናስብ። - የተለመዱ ተግባራትን አለማዛባት፦ በየቀኑ ተመሳሳይ የጊዜ ሰሌዳ ይኑረን። ለውጦች ከመደረጋቸው በፊት አስቀድመን ማሳወቅ፤ ምስሎችን በመጠቀምም ነገሮችን ማስረዳት አለብን። - የመግባቢያ መንገዶችን ማበረታታት፦ ልጁ በእጅ ምልክትም ይሁን በምስል ለመግባባት የሚያደርገውን ሙከራ ሁሉ መቀበል አለብን። ምርጫዎችን እንስጠው (ለምሳሌ፦ "ውሃ ወይስ ወተት?")። - ጥረቱን ማድነቅ፦ ውጤቱን ብቻ ሳይሆን ሙከራውንም እናበረታታ። ለትናንሽ ስኬቶች ሽልማት እንስጥ። - ውጥረትን መቀነስ፦ ጸጥ ያሉ ቦታዎችን እናዘጋጅለት። ለልጁ የሚረብሹትን ድምጾች ወይም ብርሃናት እናስወግድ። - ከባለሙያዎች ጋር መሥራት፦ ከህክምና ባለሙያዎችና ከመምህራን ጋር በቅንጅት መስራት ፈጣን መሻሻል ለማምጣት ይረዳል። ተጨማሪ እርዳታስ መቼ ያስፈልጋል? የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ባለሙያ እናማክር፦ - የክህሎት መቀነሱ እየቀጠለ ከሄደ - ልጁ ሙሉ በሙሉ መግባባት ካቆመ - ድንገተኛና ከፍተኛ የባህሪ ለውጦች ከታዩ ለወላጆች ማሳሰቢያ - የክህሎት መቀነስ የሚያስደነግጥ ቢሆንም ተስፋ አስቆራጭ ግን አይደለም። - ብዙ ልጆች ተገቢው ድጋፍ ከተደረገላቸው ክህሎቶቻቸውን መልሰው ያገኛሉ። - ለዚህ ሁኔታ መከሰት ተጠያቂዎቹ እኛ አይደለንም። - የእኛ ትዕግሥትና ድጋፍ ለልጁ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

  • Channel photo updated

  • Channel name was changed to «ልዩ ፍላጎት (SNE Ethiopia)»

  • видео или голосовое, без подписи

  • ስለ ኦቲዝም (Autism) ማወቅ የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች ኦቲዝም ምንድን ነው? ኦቲዝም ወይም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ASD) የልጆችን ማህበራዊ ግንኙነት፣ ተግባቦት (ንግግር) እንዲሁም ባህሪ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የነርቭ እድገት ሁኔታ ነው። «ስፔክትረም» የተባለበት ምክንያት ምልክቶቹ የአንዱ ልጅ ሁኔታ ከሌላው ልጅ በጥንካሬያቸውና በዓይነታቸው ስለሚለያዩ ነው። የኦቲዝም ቁጥር መጨመር ምክንያቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በወላጆች፣ በመምህራንና በዶክተሮች ዘንድ ያለው ግንዛቤ እየጨመረ በመምጣቱ ምልክቶቹን ቀድሞ መለየት ተችሏል። ቀደም ሲል መጠነኛ ምልክት ያላቸው ልጆች ትኩረት ሳይሰጣቸው ይታለፉ ነበር፤ አሁን ግን በዘመናዊ የምርመራ ዘዴዎች ገና በለጋነታቸው መለየት ተችሏል። መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው? ሳይንሳዊ ምርምሮች እንደሚያሳዩት ለኦቲዝም ዋነኛው መንስኤ የዘር ውርስ (Genetic factors) ነው። ከዚህ በተጨማሪ፦ - ያልተሟላ የእርግዝና ጊዜ (ከቀኑ ቀድሞ መወለድ) - በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ የጤና እክሎች - አንዳንድ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ለችግሩ የመጋለጥ እድልን ሊጨምሩ ይችላሉ። የተሳሳቱ አመለካከቶች - ኦቲዝም በወላጆች የአስተዳደግ ጉድለት የሚመጣ አይደለም። - በክትባትና በኦቲዝም መካከል ምንም አይነት ሳይንሳዊ ግንኙነት የለም። 🚨 ወላጆች ሊያስተውሏቸው የሚገቡ የጥንቃቄ ምልክቶች ልጅዎ የሚከተሉትን ምልክቶች ካሳየ ወደ ባለሙያ በመውሰድ ማማከር ያስፈልጋል፦ ~ ስሙ ሲጠራ ምላሽ ካልሰጠ። ~ የአይን ለአይን ግንኙነት (Eye contact) ካላደረገ ወይም ግንኙነቱ ካነሰ። ~ ንግግር ላይ ከዘገየ። ~ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወት ወይም መቀላቀል ካልፈለገ። ~ አንድን ድርጊት ወይም እንቅስቃሴ ደጋግሞ የሚያደርግ ከሆነ። 🛠️ ቀድሞ መድረስ (Early Intervention) ያለውን ጥቅም ኦቲዝምን ገና በልጅነት መለየትና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት በልጁ እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። የሚከተሉት የድጋፍ ዓይነቶች ልጁ የዕለት ተዕለት ኑሮውን በብቃት እንዲመራ ይረዱታል፦ - የንግግር ህክምና (Speech Therapy) - የባህሪ ህክምና (Behavior Therapy) - የሙያ ህክምና (Occupational Therapy) - ልዩ የትምህርት ድጋፍ ለሌሎቹ ያጋሩ። #autismawareness #autismacceptance #autismsupport #awereness #autismparenting #Ethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • ስለ ዲስሌክሲያ (Dyslexia) ወይም የማንበብ ችግር ምን ያህል ያውቃሉ? 📚🧠 እንደ ሀገራችን ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ ብዙ ጊዜ ልጆች ማንበብና መፃፍ ካልቻሉ «ሰነፍ ናቸው» ተብለው ይታወቃሉ። ሰዎች «ውይ! የእከሌ ልጅ እኮ ሰነፍ ነው፤ የሰው ስም እንኳን በአግባቡ ማንበብ አይችልም» በማለት ከብልህነቱ ጋር ያያይዙታል። ነገር ግን ምክንያቱ ዲክሌክሲያ (Dyslexia) ሊሆን ይችላል። ዲክሌክሲያ ከልጁ ብልህነት ወይም የማሰብ ችሎታ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ነገር ግን አእምሮ ቃላትንና ድምጾችን የሚረዳበት መንገድ ልዩ በመሆኑ ምክንያት የሚከሰት የተፈጥሮ ሁኔታ ነው። «ሰነፍ» የሚለው ቃል ራሱን የቻለ ትንታኔ ቢፈልግም በተለምዶ አጠራር «ሰነፍ» ልጆች አብዛኛውን ጊዜ በሁሉም ነገር (በንግግር፣ በጨዋታ፣ በንባብ…) ፍላጎት ሊያጡ ይችላሉ። ዲስሌክሲያ ያለባቸው ልጆች ግን በፈጠራ፣ በሥዕል፣ በንግግር ጎበዝ ሊሆኑ ይችላሉ። ድንገት ግን ንባብና ፅሁፍ ላይ ሲደርሱ መንገዱ ይጠፋባቸዋል። ይህ የስንፍና ሳይሆን የአዕምሮ መረጃ የማቀናበር ችግር ነው። 🔍 ዲስሌክሲያ ዋና ዋና ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? የንባብ መዘግየት፡ ቃላትን ለማንበብ መቸገር ወይም ደግሞ በጣም በዝግታ ማንበብ። የፊደላት ድምጽ ግራ መጋባት፡ የፊደላትን ቅርጽ ከድምጻቸው ጋር አዛምዶ ለመጥራት መቸገር። የአጻጻፍ (Spelling) ችግር፡ ቃላትን በትክክል ለመጻፍ መቸገር። የቃላት አጠቃቀም፡ የታወቁ ቃላትን እንኳ በንባብ ጊዜ ለማስታወስ መቸገር። 💡 ከዲክሌክሲያ ጋር አብረው ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች (Comorbidities): ዲክሌክሲያ ያለባቸው ልጆች የሚከተሉት ተደራራቢ ችግሮች ሊታዩባቸው ይችላሉ፦ ADHD፡ ትኩረትን ሰብሰብ አድርጎ የመቆየት ችግር። ዲስካልኩሊያ (Dyscalculia)፦ የሒሳብ ስሌቶችን ለመስራት መቸገር። ልዩ ተሰጥኦ (Giftedness)፦ ብዙ ጊዜ እነዚህ ልጆች በሥዕል፣ በፈጠራ ስራ ወይም በቴክኒክ ሙያ ረገድ በጣም ጎበዝ ናቸው። ⏰ ዲስሌክሲያ መቼ ነው የሚታወቀው? ብዙውን ጊዜ ልጆቹ 2ኛ ወይም 3ኛ ክፍል አካባቢ ሲደርሱ በግልጽ ይታያል። ነገር ግን ከዚያ በፊትም ምልክቶች ከታዩ ቀድሞ ድጋፍ ማድረግ ለልጁ ውጤታማነት ወሳኝ ነው። 🛠️ መፍትሄው ምንድን ነው? ዲክሌክሲያ «መድኃኒት» የለውም፣ ነገር ግን ልጁ በተገቢው መንገድ የትምህርት ድጋፍና ልምምድ ካገኘ ስኬታማ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የተሳሳተ አሠራር አለ። ይኸውም የሙዚቃ ቴራፒ ወይም ምሥሎችን ብቻ የማየት ልምምዶች እንደ ብቸኛ መፍትሔ አድርጎ ማየት ነው። እነዚህ ልምምዶች ለልጁ የንባብ ችግር ቀጥተኛ መፍትሄ ላይሆኑ ስለሚችሉ፣ ከእነዚህ በተጨማሪም ሌሎች በሳይንሳዊ መንገድ የተረጋገጡ የንባብ ድጋፎችን (Phonics-based) መጠቀም ይመከራል። ልጆቻችን «ሰነፍ» ከመባላቸው በፊት ችግራቸውን እንረዳላቸው! ❤️ ፅሁፋችንን በማጋራት ሁሉም ጋር እንዲደርስ ይተባበሩን። በፌስቡክ ይከታተሉን፦ https://www.facebook.com/snieet #dyslexia #readingproblems #specialneeds #AwarenessMatters #inclusion #Ethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • በሕፃናት ላይ የሚታዩ ሥነልቦናዊ ችግሮች መንስኤ በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ ሥነልቦናዊ (የአዕምሮ ጤና ችግሮች) አብዛኛዎቹ በድንገት የሚከሰቱ አይደሉም። ይልቁንም ሥነሕይወታዊ፣ ሥነልቦናዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች ተደማምረው ቀስ በቀስ የሚያመጡት ነው። እያንዳንዱ ሕፃን የተለያየ ባህሪ እንዳለው ሁሉ የችግሮቹም መንስኤ ሊለያይ ይችላል። ታዲያ ዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ሥነሕይወታዊ (Biological)ና የዘር ውርስ፦ በቤተሰብ ውስጥ የድብርት፣ የጭንቀት፣ የአትኩሮት ማጣትና የመቅበጥበጥ ባህሪ (ADHD)፣ ኦቲዝም ወይም ሌሎች የነርቭ ሕመሞች ታሪክ ካለ ለሥነልቦናዊ ችግር የመጋለጥ ዕድሉ ሰፊ ሊሆን ይችላል። የወላጆች አያያዝና የቤት ውስጥ ሁኔታ፦ በቤተሰብ መካከል የሚፈጠር ግጭት፣ የልጁን ፍላጎት ችላ ማለት፣ ጠንካራ ወይም ጨካኝ የቅጣት እርምጃዎች እንዲሁም ለልጆች በቂ የሆነ ስሜታዊ ድጋፍ አለመስጠት ወዘተ የችግሩ መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ። አሰቃቂ ገጠመኞች (Trauma)ና ውጥረት፦ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት፣ በትምህርት ቤት የሚደርስ ትንኮሳ (Bullying)፣ የቅርብ ሰውን በሞት ማጣት ወይም ድንገተኛ አደጋዎች ወዘተ እንደዚሁ ተጠቃሽ መንስዔዎች ናቸው። የትምህርት ጫና፦ በተለይም ባለንበት ዘመን ወላጆች ከልጁ አቅም በላይ የሆነ ውጤት የመጠበቅ ፍላጎት አለ። ይሄ አካሄድ ደግሞ አደገኛ ነው። በተጨማሪም ልጆች ራሳቸው በውድድር ውስጥ የመሸነፍ ፍርሃት ወይም የመማር ችግር (Learning difficulties) ውስጥ ይወድቁና ለሥነልቦናዊ እክሎች ይጋለጣሉ። የማህበራዊ ሚዲያና የቴክኖሎጂ ተጽዕኖ፦ ከልክ በላይ ስክሪንን መመልከት (ስልክ፣ ቲቪ፣ ታብሌት) ወይም ሕፃናት ለማይገቡ ምስሎችና መረጃዎች መጋለጥ ሥነልቦናዊ እክልን ያመጣል። አካላዊ ጤናና የአኗኗር ዘይቤ፦ ሥር የሰደደ ሕመም፣ የአስፈላጊ ንጥረ ነገር እጥረት (የምግብ እጥረት) ወይም በቂ እንቅልፍ አለማግኘት እንደዚሁ ተጋላጭ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ በልጆቻትን ላይ የሚከተሉት ምልክቶች ለረጅም ጊዜ ዘልቀው ከታዩ የባለሙያ ምክር ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው። እነሱም፡- የባህሪ ለውጥ፦ ተከታታይ የሆነ የሐዘን ስሜት፣ ከፍተኛ ቁጣ ወይም ራስን ከሰዎች የማግለል ባህሪ በተከታታይ ካሳየ፤ የአካል ለውጥ፦ የእንቅልፍ መዛባት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር ካለ፤ የትምህርት ሁኔታ፦ በትምህርት ቤት የሚታይ የውጤት ማሽቆልቆል ወይም የመማር ፍላጎት መቀነስ ካለ በትኩረት መከታተልና ባለሙያን ማማከር ያስፈልጋል። #parenting #parentingtips #ParentingSupport #psychology #parenthood #parents #children #Psychological #Ethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • የABA ቴራፒ (Applied Behavior Analysis) ABA (ተግባራዊ የባህሪ ትንተና) የኦቲዝም ችግር ላለባቸው ልጆችና የተለያዩ የዕድገት ውስንነት ለሚታይባቸው ልጆች የሚሰጥ ሳይንሳዊ የድጋፍ ዘዴ ነው። ይህ የሕክምና ዘዴ ልጆች ጠቃሚ የሆኑ የሕይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እንዲሁም አስቸጋሪ የሆኑ የባህሪ ችግሮችን በአዎንታዊ ማበረታቻ (Positive Reinforcement) እንዲቀንሱ ይረዳል። የABA ቴራፒ ዋና ዋና ጥቅሞች የተግባቦት ክህሎትን ይጨምራል፦ ንግግርን፣ በምልክት መረዳዳትንና ፍላጎትን በግልጽ መግለጽን ለማሳደግ ይጠቅማል። ማህበራዊ ግንኙነትን ያጠናክራል፦ ከእኩዮች ጋር አብሮ መጫወትን፣ ሰላምታ መለዋወጥንና ግለሰባዊ ድንበሮችን ማወቅን ማለማመድ ያስተምራል። የዕለት ተዕለት የሕይወት ክህሎትን ያሻሽላል፦ ራስን መመገብ፣ የግል ንጽህና መጠበቅንና መመሪያዎችን ተከታትሎ መተግበርን ያካትታል። ባህሪንና ስሜትን ለመቆጣጠር፦ የንዴት፣ ግልፍተኝነትና የስሜት መረበሽን (Sensory triggers) በአግባቡ ለመቆጣጠር ይረዳል። ራስን መቻልን ያለማምዳል፦ ልጁ በራሱ እንዲተማመንና ሌሎችን ሳይጠብቅ ራሱን ማገዝ እንዲችል ያደርጋል። እያንዳንዱ የABA መርሃ-ግብር እንደ ልጁ የግል ፍላጎትና ጥንካሬ የሚቀረጽ ሲሆን፤ አገልግሎቱም በቤት፣ በትምህርት ቤት ወይም በልዩ ማዕከላት ሊሰጥ ይችላል። የABA ቴራፒ ውጤታማ የሚሆነው የልጁን ስብዕናና ስሜት ባከበረ መልኩ ሲተገበር ብቻ ነው። ዘመናዊው አቀራረብ ልጁን ከማስገደድ ይልቅ ፍላጎቱን ተከትሎ ማስተማር ላይ ያተኩራል። በመሆኑም በቂ ስልጠናና ርህራሄ ያለው ባለሙያ መምረጥ ለለውጡ መሰረት ነው። ወላጆች ቴራፒ ከመጀመራቸው በፊት ሊጠይቋቸው የሚገቡ ጥያቄዎች የአሰልጣኙ አቀራረብ የልጁን ፍላጎትና ዝንባሌ (Child-led) ያከበረ ነው? አስቸጋሪ ባህሪያት የሚታረሙት በምን ዓይነት ዘዴ ነው? ተቋሙ በቂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አለው? የልጁ ለውጥ ወይም እድገት የሚለካው በምን መስፈርት ነው? በአጠቃላይ ABA ሕፃናት የተሻለ የሕይወት ክህሎት እንዲኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ቢኖረውም፣ የእያንዳንዱ ልጅ እድገትና ፍላጎት ግን የተለያየ ነው። ትክክለኛው ባለሙያ፣ የቤተሰብ ንቁ ተሳትፎና የቴራፒው አቀራረብ ለስኬቱ ወሳኝ ናቸው።

  • видео или голосовое, без подписи

  • እንዴት በአዎንታዊ መንገድ የልጆችን ፀባይ መቀየር ይቻላል? የልጆችን ፀባይ መቀየር ትዕግስትን፣ ያላሰለሰ ክትትልንና ፍቅርን ይጠይቃል። ቤት ውስጥም ሆነ ትምህርት ቤት፣ እነዚህ ቀላል ስልቶች ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ውጤታማ የሆኑ ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ፤ 1. ከፀባዩ ጀርባ ያለውን ምክንያት መረዳት/Understand the Behavior ልጁን ከመቅጣታችን በፊት ያለበትን ሁኔታ ማስተዋል ያስፈልጋል። «ልጁ ደክሞታል? ርቦታል? ወይንስ ትኩረት ይፈልጋል?» ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ብዙ ጊዜ ልጆች መጥፎ ፀባይ የሚያሳዩት የተቸገሩበትን ነገር መግለጥ ሲፈልጉ ነው። 2. ግልጽና ቀላል ደንቦችን ማስቀመጥ/ Set Clear and Simple Expectations አጫጭርና የማይቀያየሩ ደንቦችን መጠቀም አለብን። እነዚህንም ደንቦች ለልጆች በአወንታዊ መልኩ ማስተማር አለብን። ለምሣሌ፦ «ቤት ውስጥ ጥሩ/ አወንታዊ ቃላትን እንጠቀም።» «እጃችን የተፈጠረው ሰው ለመርዳት እንጂ ለመምታት አይደለም።» የሚሉ ህጎችን ማውጣት። 3. ጥሩ ሲያደርጉ ማበረታታት/Reinforce Postive Behavior ልጆችን ጥፋት ሲያጠፉ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ነገር ሲያደርጉም መመልከትና እውቅና መስጠት አለብን። ለምሣሌ፦ «መጫወቻህን ለእህትህ ስለሰጠሃት በጣም ደስ ብሎኛል!» በማለት ማወደስ አለብን። 4. ምክንያታዊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ/ Use Fair Consequences የምንወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያታዊና እርጋታ ያለባቸው መሆን አለበት። አንዳንዴ በተፈጠረው ችግር ውስጥ ተውጠን ምክንያቱን ሳናጣራ አላስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ልጆች ላይ መጮህ ወይም እነሱን መምታት ፍርሃትን እንጂ ትምህርት አይሰጥም። 5. ወጥ የሆነ አቋም/ Be Consistent ለልጆች የምንሰጠው ደንብ ዛሬም ነገም ሁሌም ተመሳሳይ መሆን አለበት። በመሆኑም ወላጆች፣ መምህራንና የልጆች ተንከባካቢዎች አንድ ዓይነት ደንብ መተግበር አለባቸው። 6. ስሜታቸውን እንዲያውቁ ማስተማር/ Teach Emotional Skills ልጆች የሚሰማቸውን ስሜት በስም እንዲጠሩት እንርዳቸው። «ተናደሻል አይደል? ይገባኛል» የሚሉ ቃላትን እንጠቀም። ከዚያም ስሜትን የማረጋጋት ብልሃቶችን ማለማመድ - በጥልቀት እንዲተነፍሱ ማድረግ - እስከ 10 እንዲቆጥሩ… ማድረግ አለብን። 7. ምርጫ መስጠት/Offer Choices ልጆች እልኸኛ እንዳይሆኑ ቀላል ምርጫዎችን ብንሰጣቸው የተሻለ ነው። «የቱን መልበስ ትፈልጋለህ? ቀዩን ሸሚዝ ወይስ ሰማያዊውን?» ማለት። እንደዚህ ያሉ ምርጫዎች ልጆችን በራሳቸው እንዲተማመኑ ይረዳል። 8. ሥዕላዊ መግለጫዎችን መጠቀም (በተለይ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ልጆች) ኦቲዝም፣ የአትኩሮት ማጣትና የመቅበጥበጥ ችግር (ADHD) ወይም የመማር ችግር ላለባቸው ልጆች የቀን ውሏቸውን በሥዕል መልኩ ማሳየት፥ በዕለቱ ምን እንደሚጠበቅባቸው እንዲረዱት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። 9. መወገድ ያለባቸው የተለመዱ ስህተቶች - ልጆች ጥፋት ሲያጠፉ ብቻ ትኩረት መስጠት፦ ልጆች ጥሩ ነገር ሲያደርጉ ትኩረት ካልሰጠናቸው፣ የእኛን ትኩረት ለማግኘት ሲሉ መጥፎ ፀባይ ሊያዳብሩ ይችላሉ። ስለዚህ በጥሩ ፀባያቸው ላይ ትኩረት እናድርግ። - መነሻ ምክንያቶችን ችላ ማለት፦ ድካም፣ ረሃብ ወይም በአካባቢያቸው ያለው ግርግር የልጆችን ፀባይ ሊቀይሩ ይችላሉ። ከመቆጣታችን በፊት ልጁ የተራበ ወይም የደከመ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። - አቋም አልባ መሆን/Inconsistency፦ ዛሬ የከለከልነውን ነገር ነገ ከፈቀድን ልጁ ግራ ይጋባል። ደንቦች ሁልጊዜም ተመሳሳይ መሆን አለባቸው። በፌስቡክ ይከታተሉን https://www.facebook.com/snieet

  • 🌟 «ለእያንዳንዱ አካል ጉዳተኝነት፤ ተግዳሮቶቻችሁን ለማሸነፍ የሚያስችል ከበቂ በላይ በሆኑ ችሎታዎች ተባርከችኋል።» - ኒክ ቩጂቺች 💪 የተሰጠህ ጉልበት ከማንኛውም እንቅፋት ይበልጣል። ቀጥልበት፤ አንተን ምንም ነገር ከማድረግ አያስቆምህም! ✨

  • ልጆች ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ይዘው እንዲወለዱ የሚያደርገው አዲስ ፈጠራ አል-ዐይን መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው አዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለማሰብ የሚከብዱ ፈጠራዎችን ለአገልግሎት አብቅቻለሁ ብሏል፡፡ ሄሊዮስፔክት ጄኖሚክስ የተሰኘው ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ልጆች ከመወለዳቸው በፊት ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ወይም አይኪው እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ ኩባንያው ላለፉት ዓመታት በተለይም በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ወይም በህክምና እገዛ በሚወለዱ ህጻናት ላይ በርካታ ሙከራዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ቴክኖሎጂው ወላጆች ልጃቸው በሚፈልጉት ጾታ፣ ቁመት፣ የማሰላሰል አቅም መጠን እና ሌሎችም እንዲወለድ የሚያደርግ ነው፡፡ ወላጆች ይህን አገልግሎት ለማግኘት እስከ 50 ሺህ ዶላር መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አገልግሎቱን እያገኙ ያሉ ወላጆች እንዳሉም ተገልጿል፡፡ እስካሁን ለ12 ልጆችን በተፈጥሮ መንገድ መውለድ ላልቻሉ ነገር ግን በህክምና እገዛ ለወለዱ ወላጆች አገልግሎቱ ተሰጥቷቸዋል የተባለ ሲሆን ህጻናቱ በዚህ ቴክኖሎጂ የማሰላሰል አቅማቸው በተፈጥሯቸው ሊያገኙ ከሚችሉት ስድስት እጥፍ የተሻለ ነውም ተብሏል፡፡ ቴክኖሎጂው የማሰላሰል አቅም ወይም አይኪውን ከመጨመር በተጨማሪ ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ የአዕምሮ ህመም፣ ከመጠን በላይ ውፍረት እና ሌሎች ስጋቶች ህጻናቱን እንዳያጠቁ የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ለአገልግሎት መብቃቱን ተከትሎ አድናቆት እና ትችቶችን ያስተናገደ ሲሆን ቴክኖሎጂው የማህበረሰብ ልዩነት እንዲፈጠር የሚያደርግ እና ተፈጥሮን የሚጋፋ ነው የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡ ቴክኖሎጂውን ያበቃው ኩባንያ በበኩሉ አገልግሎቱ ገና በጅምር ላይ መሆኑን እና በቀጣይ ለሁሉም ማህበረሰብ እንዲቀርብ ሊደረግ እንደሚችል አስታውቋል፡፡

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

SNE Ethiopia (ልዩ ፍላጎት) — tgindex