KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /
СтатистикаKotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /
- Последний пост
- 14:00
- Последнее чтение
- 14:43
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 119
- 1/48двое суток
- 2 428
- 1/72трое суток
- 2 619
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች የአተገባበር ማንዋል ይፋ አድርጓል። 👉 በመተግበሪያ ማንዋሉ መሰረት አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የሙያ ዓይነት ብቻ መርጦ የሚማር ሲሆን፣ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም 11 ዓይነት ሙያዎች በአንድ ጊዜ እንዲተገብሩ አይገደዱም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና ተማሪዎችን ለሥራው ዓለም ለማዘጋጀት ያለመ አዲስ የአተገባበር ማንዋል አዘጋጅቷል። በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ማንዋል፣ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች ትግበራ የሚውል ሲሆን፤ የትምህርቱን አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ የአመራረጥ ሂደት እና የተግባርና ኃላፊነት ክፍፍልን በዝርዝር አካቷል። ቢሮው በመመሪያው መግቢያ ላይ እንደገለጸው፣ ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ሚና ቢኖረውም፣ በተካሄደው የፍኖተ ካርታ ጥናት መሰረት የአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ ከሥራና ተግባር ጋር ያልተሳሰረና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎትን ያላካተተ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ችግር ተማሪዎችን በመሠረታዊ እውቀት ብቻ ያቆምና በሥራ ዓለም ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የማያስችል ነው ይላል። ችግሩን ለመፍታትም በ2017 እና 2018 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ ተማሪዎች በስምንት የሙያ መስኮች ማለትም ፦ - በግብርና ፣ - መረጃ ቴክኖሎጂና ኮምፒውተር ሳይንስ ፣ - ጤና ሳይንስ፣ - ኮንስትራክሽን፣ - ማኑፋክቸሪንግ ፣ - ኮሙኒኬሽንና የማህበራዊ ሳይንስ ፣ - ቢዝነስ ሳይንስ እና ስነጥበባት ውስጥ ከሚገኙት የሥራ አይነቶች አንዱን መርጠው እንዲማሩ መደረጉን አስታውሷል። ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮም ከዕድሜ ጋር የተመጣጠነ የሥራና ተግባር ትምህርት እንደተሰጠ የአተገባበር መመሪያው ያስረዳል። አሁን ደግሞ በ2019 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚቀርቡ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤቱ እና በተማሪው ምርጫ ተግባራዊ ለማድረግ የመተግበሪያ መመሪያ (Manual) መዘጋጀቱ አመልክቷል። በዚህ አዲስ የአተገባበር ሥርዓት ውስጥ የተካተቱት 11 የሙያ ዓይነቶች በስድስት ዋና ዋና የሙያ ዘርፎች (Career Clusters) የተከፋፈሉ ናቸው። ° በግንባታ ዘርፍ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የቧንቧ ስራ፤ ° በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ እና አልባሳት ቴክኖሎጂ ፤ ° በቢዝነስ ሳይንስ ዘርፍ የሆቴል አገልግሎት፣ የፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም የምግብ ዝግጅት ተካተዋል። በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሶፍትዌር ማበልጸግ፣ በግብርና ሳይንስ የሰብል አመራረት እና በጤና ሳይንስ የጤና ክብካቤ አገልግሎት የሙያ ዓይነቶች ለተማሪዎች እንዲቀርቡ ተለይተዋል። የሙያ ዓይነቶቹ የሚመረጡበት ሂደት ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን በመመሪያው ታዟል። ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን ከመምረጣቸው በፊት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ያሉትን የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ግብዓቶች፣ እንዲሁም የተማሪዎችን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአተገባበር በመመሪያው መሠረት አንድ ትምህርት ቤት ሁሉንም 11 የሙያ ዓይነቶች ማቅረብ አይጠበቅበትም፤ ይልቁንም እንደ አቅሙና እንደ አካባቢው ሁኔታ የተወሰኑትን መርጦ ተግባራዊ ያደርጋል። ተማሪዎችም ከቀረቡት አማራጮች መካከል የአንዱ የሙያ ዓይነት ባለቤት እንዲሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ምርጫቸውም ከፍላጎታቸውና ከችሎታቸው ጋር የተገናኘ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል። ለመመሪያው መሳካት የተለያዩ አካላት የየራሳቸው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የመሪ ዕቅድ የማዘጋጀትና ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሲኖርበት፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ደግሞ ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን እንዲለዩ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ሙያውን የሚከታተሉ ባለሙያዎችንም ይመድባሉ። ትምህርት ቤቶች በበኩላቸው ካሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር የሙያ ዓይነቶችን የመምረጥ፣ ለተማሪዎች ግንዛቤ የመፍጠርና ትግበራውን የመምራት ቀጥተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ይህ የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከግል ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው መተግበሪያ መመሪያው ያሳስባል። ይህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲሆኑና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ቢሮው ለትግበራው ምቾት ይረዳ ዘንድ ለትምህርት ቤቶችና ለተማሪዎች ምርጫ የሚሆኑ ቅጾችንም ከመመሪያው ጋር አያይዞ አቅርቧል። ሙሉ የአተገባበር ማንዋሉን በዚህ ያገኛሉ : አዲስ አበባ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም
видео или голосовое, без подписи
ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል። በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተናበበ የሥልጠና ማዕቀፍ፣ ፕሮግራሙን ለመምራት የሚያስችሉ የትግበራ ሰነዶችን እና የሰልጣኝ መምህራንን ምልመላ፣ መረጣ እና ምደባ መከናወኑን አመልክቷል። ባለፉት አመታት በስልጠናው አሰጣጥ ጥራት ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመምህራን የክረምት የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በዚህ ክረምት ለማስጀመር 8 ዩኒቨርሲቲዎች ተለይተዋል። እነዚህም፦ - ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - መቐለ ዩኒቨርሲቲ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ - ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲሆኑ፣ በ2018 ዓ.ም. ክረምት 8,273 መምህራንን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል። የመግቢያ ምዘና ወስደው ያለፉና በየዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ሰልጣኝ መምህራን፣ ምዝገባው ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም. የሚካሄድ መሆን ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዩኒቨርሲቲው በለውጥ ላይ ነው! … - የካውንስል አባላት የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኝተዋል *** *** ***** (ኮትዩ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም) - የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላትና መምህራን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተገነቡ አዳዲስ እና እድሳት የተደረገላቸው ነባር ሕንጻዎችን ጎብኝተዋል፡፡ የግንባታ ፕሮጅክቶቹ ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተዘጋጀውን የአካላዊ ምልከታ መርሐግብር በንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዩኒቨርሲቲውን ወደ ተሟላ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለመቀየር የተካሄዱት የሪፎርም ስራዎች ሂደታቸውን ጠብቀው ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተከናወኑ በመሆናቸው ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በተጨባጭ ለውጥ ላይ ነው ብለዋል፡፡ ከተከናወኑት የለውጥ ስራዎች መካከልም ከዩኒቨርሲቲው የአመራር ቦርድ እስከ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ድረስ የአመራር ለውጥ ማድረግ፣ አዲስ ካውንስል ማቋቋም፣ የሕግ ማዕቀፎች ይልቁንም የዩኒቨርሲቲውን የወደፊት አቅጣጫ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ፣ የሌጅስሌሽን፣ የአካዳሚክ ፕርግራሞች ማሻሻያ፣ ኢንተርናላይዜሽን፣ ስፔሻላይዜሽን እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ እነዚህም ተግባራት ዩኒቨርሲቲው ስርነቀል ለውጥ በማካሄድ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በቀጣይም ልዩ ልዩ ፖሊሲዎችን ከማዘጋጀት እና መዋቅራዊ ለውጦችን በወረቀት ላይ ከማስፈር አንፃር ብዙ ይቀረናል ያሉት ፕሬዘዳንቱ ዶ/ር ተሾመ፣ ከሽግግር ወደ ተረጋጋ አሰራር ለመድረስም ከፊታችን ብርቱ ስራዎች ስለሚጠብቁን የካውንስል አባላትና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ስራዎቻቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ በበኩላቸው፣ የጉብኝት መርሐግብሩ የተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎችን በቅርበት እንዲያውቁና የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልፀው፣ በእጃችን ላይ ከሚገኙት 10 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች መካከል 98 በመቶ ያህል የተጠናቀቁት የተማሪዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብሎክ ኤ እና ቢ ህንፃ፣ የተማሪዎች ክሊኒክ፣ ተጠናቆ አገልግሎት የጀመረው የአይሲቲ መሠረተ ልማት፣ የዩኒቨርሲቲው አጥርና የመግቢያ በሮች፣ የተማሪዎች መመገቢያና ኪችን ህንፃ፣ እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት የሆኑ የሦስት ነባር ህንፃዎች እድሳት፣ የምድረ ግቢ ውበት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ከአንድ ወር በኋላ የሚጀመሩ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ፣ ለተማሪዎች መኝታ የሚሆኑ ሁለት መንታ ሕንጻዎች፣ የቋንቋዎች ትምህርት ኮሌጅ ግንባታ የዲዛይን ሥራ፣ የውኃ መሠረተ ልማት ግንባታ ዝርጋታ፣ የአስተዳደር ሕንፃ ግንባታ እና ሌሎች ተመሳሳይ የእድሳት ስራዎች የ2019 ዓ.ም ፕሮጀክቶች ከመሆናቸውም በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲውን ገፅታዎች በተሻለ ሁኔታ እንደሚቀይሩም አብራርተዋል፡፡ ሕንፃዎቹም በዋናነት ለመማር ማስተማር፣ ለቢሮ፣ ለመዝናኛ ክበብ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት፣ ለመኪና ማቆሚያ እና ለገቢ ማመንጫ አገልግሎት እንደሚውሉ ተናግረዋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላትና መምህራን የቀረበውን ገለፀ ተከትሎ፣ ምድብ አንድ በአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንቱ በዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ፣ ምድብ ሁለት በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ኬሚሶ እና በምርምር እና በማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ መሪነት የአካል ምልከታ ጉብኝቱ ተከናውኗል፡፡ በጉብኝት መርሐግብሩ ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላትና መምህራን በሰጡት አስተያየት፣ በተመለከቱት ደረጃቸውን የጠበቁ ግንባታዎች በእጅጉ የተደሰቱ መሆናቸውን ተናግረው፥ የተጠናቀቁት እንዳሉ ሆነው በጅምር ላይ ያሉት ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ግንባታዎቹም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ታሳቢ እንዲያደርጉ ሃሳብ የሰጡ ሲሆን፣ የማኔጅመንት አባላቱም ለተሰጡት አስተያየቶች ትኩረት እንደሚሰጡ በማስረዳት የጉብኝት መርሐግብሩ ተጠናቋል፡፡ - የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት #Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ: Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.etቻ Website: https://www.kue.edu.et/ YouTube: https://youtube.com/@kueducation Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et) Log in or sign up to view See posts, photos and more on Facebook.
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና አሰላ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ያሰለጠናቸውን 2,349 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራንን አስመረቀ። (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የምርቃት መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣የሁለቱ ኮሌጆች ዲኖችና መምህራን እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የመርሀግብሩ የክብር እንግዳ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምቹና ተመራጭ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ በተማሪዎቹ ሁለንተናዊ እድገት ላይ መስራት መሆኑን አመላክተዋል። ኃላፊው አያይዘውም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ህጻናቱ ለቀጣዩ የትምህርት ደረጃዎች መሰረት የሚጥሉበት የትምህርት እርከን እንደመሆኑ በዛሬው እለት የተመረቁ መምህራን በኮሌጆቹ በነበራቸው ቆይታ ባገኙት ዕውቀትና ክህሎት መሰረት በጫወታ የማስተማር ስነዘዴን በአግባቡ በመተግበር ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው በመግለጽ ሁለቱን ኮሌጆች ጨምሮ ለመርሀግብሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ የቅድመ አንደኛ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለተቋማቱን ግብአት ከማቅረብ ጀምሮ ለመምህራን ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በደብረ ብርሀን አሰላ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ተምረው በዛሬው እለት የተመረቁ መምህራንም የዚሁ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጽ ለተመራቂዎች መልካም እድል ተመኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን የማህበሩ ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ገልጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሁለቱ ኮሌጆች ጋር በጋራ በመሆን መምህራኑን አሰልጥኖ በማስመረቁ በማህበራቸውና በተመራቂ መምህራን ስም ምስጋና አቅርበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
видео или голосовое, без подписи
የሙአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ልጅ ተመርቋል! #maleda :የእውቀትና የጥበብ ፍሬዎች ሲጎመሩ ማየት ለወላጅም ለሀገርም ትልቅ ደስታ ነው። ዛሬ በሀገራችን የኪነ-ጥበብና የማኅበራዊ ሕይወት ዘርፍ ጉልህ አሻራ ያኖሩት የሙአዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ልዩ የወላጅነት ኩራት ያጣጣሙበት ታሪካዊ ቀን ሆኗል። የዲ/ን ዳንኤል ክብረት ልጅ አቤሜሌክ ዳንኤል ረጅም የታማኝነትና የጥናት ዓመታትን በስኬት አጠናቆ፣ ዛሬ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል። የአባት አደራ እና የራስ ጥረት ሲገናኙ ውጤቱ ሁልጊዜም ማማር ነው!" ይህ የምረቃ ቀን የወጣቱ አቤሜሌክ የልፋት ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ልጆቻቸውን በዕውቀትና በስነ-ምግባር ቀርጸው ለዚህ ማዕረግ ያበቁት የወላጆቹ የድካም ፍሬ መገለጫ ጭምር ነው። ለአቤሜሌክ ዳንኤል የወደፊት የሕይወትና የሥራ ዘመን ብሩህ እንዲሆንልህ እንመኛለን። ይህ የትምህርት መድረክ የትልቅ ጉዞ መጀመሪያ ይሁንህ! ከዩኒቨርሲቲው የቀሰምከው ዕውቀት ለራስህ የሚጠቅም፣ ለቤተሰብህ ኩራት የሚሆንና ለሀገርህም የሚተርፍ ፍሬ እንዲያፈራ ከልብ እንመኛለን። ለአቤሜሌክ፣ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት እና ለመላው ቤተሰብ፦ እንኳን ደስ አላችሁ::
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ስነስርዓት እየተካሄደ ነው *** ** *** (ኮትዩ፣ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ፣ በቅድመ ምረቃ፣ በድህረ ምረቃ ማለትም በማስትሬት እና በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2882 ተማሪዎች በአደዋ ድል መታሰቢያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በደማቅ ስነ-ስርዓት እያስመረቀ ነው፡፡ የምረቃ ስነስርዓቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የተማሪ ወላጆች በተገኙበት እየተከናወነ ሲሆን የ2018 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ! - የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት #Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ: Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et Website: https://www.kue.edu.et/ YouTube: https://youtube.com/@kueducation Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et) Log in or sign up to view See posts, photos and more on Facebook.