መጋቤ ምስጢር መ/ር ኃይለማርያም (Megabe mistir m/r Hailemaryam Girma)ስልክ 09 42 42 46 46 ይደውሉ።
Статистикаበዚህ ፔጅ ትምህርት ፣ተግሳፅ እና ምክር ይቀርብበታል ።
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 125
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 72
- 1/48двое суток
- 82
- 1/72трое суток
- 88
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
• ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰኑይ፡፡ "…ከዕለታት ባንድ ቀን ዕለቱ #ሰኑይ (ሰኞ)፥ ጊዜው ነግህ (ጠዋት) ነው። ቅዱስ #ኤፍሬም የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል። ከዚያም ላይ ሁና "ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ #ኤፍሬም" ትለዋለች፤ እሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል። "ወድሰኒ" ትለዋለች እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራዊያን። (ምድራዊያን ጻድቃን ሰማዕታት ሰማያውያን መላእክት አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት።) "በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ ተናገር አለችው።"በተረቱበት መረታት ልማድ ነውና፤ እፎ ይከውነኒ ዝንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ ብትለው መልአኩ መንፈሰ #እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ብሏት ነበርና። "…ከዚህ በኋላ ለመንፈስ ቅዱስማ ይሳነዋል ብል ክህደት ይሆንብኝ የለምን ብሎ "ባርኪኒ እግዝእትየ መዝገበ በረከት" ይላታል፤ "በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅደር በላዕሌከ ትለዋለች።" ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል። ሲያመሰግናትም ደቀ መዝሙር ቅኔ ቆጥሮ እንዲቀኝ ድርሰት አስቦ እንዲያጽፍ አይደለም። ብልህ ደቀ መዝሙር ያጠናውን ቀለም ከመምህሩ ፊት ሰተት አድርጎ እንዲደርስ እንደዚያ ነው። ስታስደርሰውም ከሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች። ስለምን ቢሉ በሰባቱ ዕለታት መመስገን ፈቃዷ ስለሆነ። “…የእመቤታችን፣ የአማላጃችን፣ የረዳታችን፣ የቅድስት ድንግል #ማርያም ምልጃዋ አይለየን። ጣዕሟን በአንደበታችን፣ ፍቅሯንም በልባችን ይሣልብን፣ ያሳድርብን።
#እግዚአብሔር ለችግራችን ሁሉ ምላሽ አለው ✝️ #ጭንቀት ➔ ጸልዩ (ፊልጵስዩስ 4፡6) ✝️ #ፈተና ➔ ሽሹ (2ጢሞቴዎስ 2፡22) ✝️ #እውቀት ማነስ ➔ ተማሩ ጥበብንም ፈልጉ (ምሳሌ 4፡7) ✝️ #ሰንፍና ➔ ትጉ ሁኑ (ምሳሌ 6፡6-11) ✝️ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ➔ አመስግኑ (2ተሰሎንቄ 5፡18) #መንፈሳዊ ብስለት የሚመጣው እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ የሚፈልገውን ነገር አስተውሎ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ነው። ለሁሉም በሽታ #መድኃኒት አለው!!
#ተወዳጆች!!እንኳን ለጾመ #ማርያም አደረሳችሁ!!
የሰንበት ቁርስ ! ▫️ሰዓቱ ደርሷል!! አንድ እናት ልጇ እድሜዉ ሲደርስ #ጡት መጥባት አቁሞ ምግብ መብላት አንዲጀምር የተቻላትን ሁላ ትሞክራለች። ይሄ ልጅ ግን ምንም እንኳን እድሜዉ ቢጨምር #ጡት መጥባቱን አላቆም ካለና ካስቸገራት ግራዋም ቢሆን ቀብታ እንዲያቆም ታስገድደዋለች። ታዲያ አንዳንዴ የለመድነዉ #ስራ ፣ የለመድነዉ ኑሮ ላይ የሚመር ነገር በተደጋጋሚ ሲያጋጥመን መልቀቅ ያለብንን ለቀን እድገት ማምጣት ያለብን #ሰዓት ደርሶ ቢሆንስ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ! መልካም ሰንበት 🙏
видео или голосовое, без подписи
▫️የሰንበት መልዕክት ! በምን ዉስጥ እያለፍክ እንደሆነ ይገባኛል ፤ ነገሮች ከቁጥጥርህ ዉጪ ሆኑብህ ? በህይወትህ ያልጠበቅካቸዉ ያላሰብካቸዉ ነገሮች ተከስተዉ ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብህ መረዳት #አቃተህ ? አንድ ነገር አስታዉስ #ዝናቡን ማስቆም አትችልም : #ዣንጥላ መያዝ ግን ትችላለህ ፤ የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም : መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ። እዚህ ጋር አንድ የ ’ማርቲን ሉተርን’ አባባል ልጨምርልህ ከቻልክ #ሩጥ ፣ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ ፣ መራመድ ካልቻልክ ዳዴም በል ብቻ ወደፊት መጓዝህን ቀጥል ! #ሰናይ ሰንበት 🙏
"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ" (፪ኛ ቆሮ. ፭፣፲፬)። #ክርስቶስ የሞተው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ጻድቃን እሴት (ዋጋ) ሽቶ አይደለም። በክፉ ሥራችን ሞተን የነበርን #እኛን ለማዳን ነው እንጂ። አንዱ እርሱ ስለሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ። ሁሉንም በመስቀል ተሰቅሎ አዳነ። እንግዲህ ምን እንላለን። እኛን ለማዳን፣ ስለእኛ ተሰቅሎ መከራ የተቀበለልንን መድኃኔ ዓለምን ዛሬም ለዘለዓለምም እናመሰግነዋለን። በመከራው መከራችንን አራቀልን። በሞቱ ሞታችንን አጠፋልን። "ሞተ #ክርስቶስ በሞተ ዚኣነ ከመ ይቅትሎ ለሞት በሞቱ" እንዲል። ሞትን በሞቱ ያጠፋልን ዘንድ ክርስቶስ የእኛን ሞት ሞተ። እርሱ #ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወታችን ሁሉ በቸርነቱ ነግሦልን እንዲኖር የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን።
አስቸጋሪ ሰዎችን #በጥበብ መታገስ! አስቸጋሪ ሰዎችን መታገስ ማለት በዝምታ በደልን መቀበል ማለት አይደለም። ትዕግስት ድክመት አይደለም፤ መታገስም ጎጂ ባህሪን እንደ መታገስ አይቆጠርም። ይልቁንም፣ በጥበብ፣ በራስ መግዛት እና በድፍረት ምላሽ የመስጠት #ችሎታ ነው። ሰባት መመያሪዎች፡- 1. ከሁኔታው በመማር #መታገስ። "የዚህ #ሰው ሁኔታ ምን እያስተማረኝ ነው?" ብለህን እንጠይቅ። እያንዳንዱ ፈተና ትዕግስትን፣ ጥበብን፣ ትህትናን፣ ማስተዋልን እና ስሜታዊ ብስለትን ሊያዳብር ይችላል። 2. #ምክር እና ድጋፍ በመፈለግ መታገስ። ተጨባጭ ምክር፣ ማበረታቻ እና ተግባራዊ እገዛ ሊሰጡን ከሚችሉ አስተዋይ፣ ታማኝ እና የበሰሉ ሰዎች ጋር መመካከር። 3. ደህንነትህ አደጋ ላይ ከሆነ፣ መውጫ መንገድ በማዘጋጀት መታገስ። ግንኙነቱ በአካል ወይም በስሜት ላይ የማይቀለበስ አደጋ የሚያስከትል ከሆነ፣ ከመቆየት ይልቅ ደህንነቱ የተጠበቀ የመውጫ #ስልት ማውጣት። 4. ጤናማ ወሰኖችን በማበጀት መታገስ። #ትዕግስት ገደቦችን የማስቀመጥ አስፈላጊነትን አያስቀርም። ምን አይነት ባህሪ ተቀባይነት እንዳለው እና ምን እንደሌለው በግልፅ ተናገር። ጤናማ ወሰኖች ክብርህን እና ግንኙነታችሁንም ይጠብቃሉ። 5. በስሜት ከመንቀሳቀስ ይልቅ #በጥበብ ምላሽ በመስጠት መታገስ። በቁጣ ወይም በብስጭት ውሳኔ ከመወሰን መቆጠብ። ቆም ማለት፣ ጸሎት ማድረግ፣ ማሰብ፣ እና ብስለትን እና ራስን መግዛትን በሚያሳይ መንገድ ምላሽ መስጠት። 6. እንደ አስቸጋሪው #ሰው ላለመሆን በመወሰን መታገስ። የሌላ ሰውን ምሬት፣ ቁጣ፣ ማጭበርበር ወይም ንቀት የራሳችንን ማንነት እንዲቀርፅ አንፍቀድ። የራሳችን እሴቶች ባህሪያችንን እንዲወስኑ እናድርግ። 7. በምትቆጣጠረው ነገር ላይ በማተኮር #መታገስ። የሌላውን ሰው #አመለካከት ወይም ምርጫ መቀየር አንችልም፤ ነገር ግን የራሳችንን ቃል፣ ተግባር፣ አመለካከት እና ምላሽ መቆጣጠር እንችላለን።
ሰውን እኩል ማስደሰት ባይቻልም እኩል ማየት ግን ይቻላል።
#Life goes on!!!!
❤️ሕይወት ❤️ይቀጥላል! እንኳን አሁን ከምታልፉበት አስቸጋሪ ሁኔታ አይደለም፤ ከሞት በኋላ እንኳን #ሕይወት አለ። አንዳንድ ጊዜ ያለንበት ሁኔታ ሁሉም ነገር ያበቃ ያስመስለናል። ነገር ግን #ሕይወት እጅግ ከዚያ የበለጠ ነው። ዛሬ የሚያስለቅሰን ነገር ነገ የምንማርበት ትምህርት ሊሆን ይችላል፤ ዛሬ የተዘጋ የሚመስለው በር ነገ ወደ ተሻለ እድል የሚመራ መንገድ ሊሆን ይችላል። 👉ከክስረት በኋላ ሕይወት አለ። የገንዘብ ኪሳራ፣ የንግድ መውደቅ ወይም የእቅድ መፈራረስ የሕይወት መጨረሻ አይደለም። ብዙ ሰዎች ከከባድ ኪሳራ በኋላ እንደገና ተነስተው ተሻለ ሕይወት ገንብተዋል። ክስረት መጨረሻ ሳይሆን አዲስ ጅማሮ ሊሆን ይችላል። 👉ከፍቅረኛ መለየት በኋላ #ሕይወት አለ። አንድ ግንኙነት ሲያበቃ ልብ በጣም ሊሰበር ይችላል። የወደድነውን ሰው ማጣት እንደ ዓለም መፍረስ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን ሕይወት አይቆምም። እንደገና መሳቅ፣ መውደድ እና ተስፋ ማግኘት ይቻላል። 👉ስራ ከማጣት በኋላ ሕይወት አለ። ስራችን የማንነታችን አንድ ክፍል ቢሆንም ሙሉ ማንነታችን አይደለም። ስራ ማጣት ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ግን አዲስ አቅጣጫ፣ አዲስ #ክህሎት እና አዲስ እድል የሚጀምርበት ጊዜም ሊሆን ይችላል። 👉ከውድቀት በኋላ #ሕይወት አለ። ማንም ሰው ሳይወድቅ አይማርም፤ ሳይሳሳትም አይበስልም። ውድቀት የሕይወት መጨረሻ ሳይሆን የሚያስተምረን እና የሚያጠናክረን ሂደት ነው። ዛሬ የወደቃችሁበት ቦታ #ነገ የምትነሱበት ቦታ ሊሆን ይችላል። ታላላቅ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከብዙ ውድቀቶች በኋላ ነው ወደ ስኬት የደረሱት። ስለዚህ ውድቀትን እንደ መጨረሻ ሳይሆን እንደ አዲስ ትምህርት እዩት። ስለዚህ አሁን የምታልፉበት ሁኔታ የመጨረሻው ምዕራፍ አይደለም። የዛሬው ሕመም የነገውን ታሪክ እየጻፈ ሊሆን ይችላል። #ሕይወት ሁልጊዜ ከመጨረሻ በኋላ አዲስ ጅማሮ አላት። ዛሬ የምታልፉበትን ሁኔታ እንደ ሕይወታችሁ መጨረሻ አትቁጠሩት
Liturgy=working for the people and for God.
የስኬት መሰረት#ብርቱ ጎንን ማግኘት!! ለራሳችን እድገትም ሆነ ለሌሎች ሰዎች መልካም አቅርቦት የምንውለው #እግዚአብሔር የሰጠንን ጥንካሬዎች በመለየት እና በማዳበር ነው። እያንዳንዱ #ሰው የተለየ ጥንካሬ አለው። አንዳንዶቹ በተፈጥሮ የሚገኙ ችሎታዎች ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ በትምህርት እና በተሞክሮ የሚዳበሩ ክህሎቶች ናቸው። ጥንካሬዎቻችን #አመራርን፣ ማስተማርን፣ ፈጠራን፣ ችግር መፍታትን፣ ርህራሄን፣ ማደራጀትን፣ መግባባትን ወይም ሌሎችን የማበረታታትን ችሎታ ሊያካትቱ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች በድክመታቸው ላይ በመጨነቅ ብዙ ጊዜ ስለሚያጠፉ፣ በምን ላይ ጥሩ እንደሆኑ አያውቁም። ደካማ ጎኖችን ማሻሻል አስፈላጊ ቢሆንም፣ ታላቁ እድገት የሚመጣው ጥንካሬዎችን በማዳበር ነው። ጥንካሬውን በቋሚነት የሚጠቀም ሰው ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ በራስ መተማመንን፣ ውጤታማነትን እና እርካታን ያገኛል። #ጥንካሬዎቻችንን ማግኘት የምንጀምረው ራስን እንዲህ ብሎ በመጠየቅ ነው፡- • ምን ዓይነት ተግባራት #ጉልበትና መነሳሳት ይሰጡኛል? • ምን ዓይነት ነገርን ነው በፍጥነት የምማረው? • #ሰዎች ብዙውን ጊዜ በምን ጉዳይ ላይ ነው የሚያመሰግኑኝ ወይም የሚያደንቁኝ? • ምን ዓይነት #ችግሮችን መፍታት በተፈጥሮ ደስ ይለኛል? #ጥንካሬዎቻችንን ለማግኘት ሌላው መንገድ በደንብ የሚያውቁዎትን ሰዎች ቅን አስተያየት መጠየቅ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሌሎች በእኛ ውስጥ ያለውን ችሎታ እኛ ራሳችን ከማወቃችን በፊት ያዩታል። ጥንካሬዎቻችን ለግላችን #ስኬት ብቻ የተሰጡ እንዳልሆኑ እናስታውስ። ችሎታ ያለው አስተማሪ ሰዎች እንዲማሩ ይረዳል። #ርህሩህ ሰው ለሌሎች መጽናናትን ያመጣል። #ክህሎት ያለው መሪ ቡድንን ያነሳሳል። ጥንካሬዎችዎ በሌሎች አገልግሎት ላይ ሲውሉ የበለጠ ዋጋ ይኖራቸዋል። ጥንካሬዎቻችንን በፍጹም ከሌላ ሰው ጋር #ማወዳደር የለብንም፡፡ ዛፍ፣ አበባ እና ወይን ተክል እያንዳንዳቸው የተለያየ መልክና ዓላማ አላቸው፣ ሁሉም የራሳቸው ውበት አላቸው፣ ሁሉም የራሳቸውን መዋጮ ያደርጋሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፣ የእኛ ልዩ የችሎታ የራሱ የሆነ ውበትና ዓላማ አለው፡፡ ጥንካሬዎቻችን እንደ #ዘር ናቸው፤ ምንም እንኳን ጥቂት ሆነው ቢጀምሩም፣ ሙሉ አቅማቸው ላይ የሚደርሱት በልምምድ፣ በዲሲፕሊን እና ቀጣይነት ባለው ትምህርት ስንንከባከባቸው ብቻ ነው። #ዳይ ወደ ትግበራ እንግባ!!
መጀመር! መቀጠል! መጨረስ! ➡️ ምንም አይነት አስገራሚ #ሃሳብ ብናፈልቅ፣ የማንጀምረው ከሆነ ምንም አይጠቅመንም፡፡ ➡️ ምንም ያህል የመነቃቃት አቅም ኖሮን አንድን ነገር ብንጀምርም፣ #ዲሲፕሊን ከሌለን የጀመርነውን መቀጠል አንችልም፡፡ ➡️ ምንም ያህል የጀመርነውን የመቀጠል ዲሲፕሊን ቢኖረን፣ ለመድረስ እና ለማጠናቀቅ በፈለግነው ነገር ላይ ግልጽ የሆነ #ግብ ከሌለን መጨረስ አንችልም፡፡ ይህ ሁላችንንም የሚነካ እና የሚያታግል ችግር ካልተቀረፈ በሕይወታችን የምንፈልገውን እድገት ማግኘት አንችልም፡፡
#ስሜትን መቆጣጠር!! #ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው፡- #ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ በተለይም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስሜታቸውን በሚገባ መግራት ይችላሉ። #ቁጣ፣ #ብስጭት ወይም ቅያሜ ሊሰማቸው ይችላል፤ ነገር ግን ምላሻቸውን በጥንቃቄ ይመርጣሉ። ራስን የመግዛት ችሎታ የሌላቸው ሰዎች፦ ብዙውን ጊዜ በስሜቶቻቸው ይመራሉ። መዘዙን ሳያጤኑ በቁጣ ወይም በብስጭት ምላሽ ስለሚሰጡ ሁል ጊዜ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ያገኙታል።
ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • #ሰዎች በእኔ ላይ ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ የታገልኩትን ያህል #ራሴን ለማወቅ ብሰራ ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በፍጹም የማይፈልጉኝን #ሰዎች ስለማመጥና ስከታተል ያሳለፍኩትን ጊዜ ለእኔ ዋጋ ላላቸው ሰዎች ሰጥቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በማያገባኝ የሰዎች ስራና #ሃሳብ ላይ በማውራትና በመቃወም ያባከንኩትን ጊዜ የሚደገፍ ሰው ፍልጌ ደግፌ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በየጊዜው #ካለእቅድ የማወጣቸውን የገንዘብ መጠኖች በጥንቃቄ ብቆጥባቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ምንም ያህል ብጨነቅ መለወጥ በማልችላቸው #ነገሮች ላይ መጨነቄን ትቼ ለመለወጥ አቅም ያለኝ ነገሮች ላይ አተኩሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የሚወዱኝ #ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ሲመክሩኝ የመስማትና ጥሩውን ምክር የመቀበል ልማድ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለመጀመር ያሰብኳቸውን እነዛን #ወሳኝ ነገሮች ጀምሬያቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የማይሆኑ የማሕበራዊ #ጎጾች ሳስስ ያመሸሁባቸውን ምሽቶች የቀኑን ውሎየን ለመገምገምና ለነገ በማቀድ ባሳልፋቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለየእለት #ገጠመኞች ምላሽ እየሰጡ ከመሯሯጥ ይልቅ በራእይና በዓላማ ኖሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! ያም ሆነ ይህ ያለፈው አልፏል! ከጥቂት አመታት በኋላ እንደገና “ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!” የሚል የግምገማ #ስሜት እንደሚመለስብኝ ስለማውቅ አሁኑኑ ለውጥን አመጣለሁ፡፡ ዳይ ወደለውጥ ጎዳና እንጎዝ!!!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ጊዜ ነጻ ነው፣ ግን ውድ ነው!! “#ጊዜ በነፃ የሚገኝ ቢሆንም፣ ዋጋው ግን በገንዘብ አይተመንም” ጊዜ “#በነፃ የሚገኝ” ነው የሚባለው፣ የማኅበራዊ ደረጃ፣ ሀብት ወይም መልክና ቁመና ሳይለይ ለሁሉም ሰው እኩል የሚሰጥ በመሆኑ ነው። እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ እኩል 24 ሰዓታትን ያገኛል። ጊዜን ማከማቸት ወይም መውረስ አይቻልም። ሆኖም ግን “ዋጋው በገንዘብ የማይተመን” ነው፤ ምክንያቱም አንዴ ካለፈ በኋላ መልሶ ማግኘት፣ መተካት ወይም ለጥቂት #ጊዜ ማቆም አይቻልም። እንደ ገንዘብ ወይም ንብረት ሳይሆን፣ ጊዜ ያለፈውን ነገር እንደገና ለመመለስ ሁለተኛ ዕድል አይሰጥም። ይህም #ጊዜን በሕይወት ውስጥ ካሉ እጅግ ውድ ሀብቶች አንዱ ያደርገዋል። እያንዳንዱ ቅጽበት የራሱ የሆነ አቅም (ዕድል) አለው—ይህም ለማደግ፣ ለወዳጅነት፣ ለመማር እና ለግል ብስለት የሚሆን ዕድል ነው። #ጊዜ በከንቱ ሲባክን፣ ከእሱ ጋር የተያያዘው ዕድልም ለዘላለም አብሮ ይጠፋል። በመወላወል፣ በጭንቀት፣ በሰዎች በመገደድና እንዲሁ ቁጭ ብሎ በማሳለፍ ጊዜያችሁ አይባክን፡፡ 👉ዛሬ ነቃ በሉና #ለነገ እቅድ አውጡ! ነገ ደግሞ ተነሱና ያቀዳችሁትን ተግብሩ!
"ሁሉም #ሰው ገነት መግባት ይፈልጋል ፣ ማንም ግን ለመሞት ዝግጁ አይደለም" እንደሚባለው ሁሉ ሁሉም #ሰው የተቀናጣ ህይወት መኖር ይፈልጋል ፤ ነገር ግን ለዛ የሚከፈለውን #ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ አይደለም።፣ እናንተስ ዝግጁ ናችሁ ? 👉ንስር አሞራ ራሱን ለማደስ የሚከፍለው ዋጋ አለ!