tgindex
Mado-Media

ሩቁን እናቀርባለን!

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
16
Всего постов
35
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
305
−1 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,33%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
36
35 постов
Вовлечённость
11,8%
к подписчикам
Постов в день
2,3
всего 35
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
28
1/48двое суток
32
1/72трое суток
34

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • የአሜሪካ ሴኔት የአጎዋ ነፃ የንግድ ፕሮግራም ማራዘሚያ ረቂቅ ሕግን አጸደቀ።   ከአፍሪቃ ሀገራት ጋር የሚደረገውን የነፃ ንግድ ትስስር የሚያጠናክረውን የአጎዋ ፕሮግራም ማራዘሚያ ረቂቅ ሕግ አስመልክቶ የተወያየው የአሜሪካ ሴኔት በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ሕጉን ማጽደቁን አስታውቋል።   ​በውሳኔው መሠረት፣ ከሰሐራ በታች የሚገኙ 32 መስፈርቱን የሚያሟሉ የአፍሪቃ ሀገራት የጨርቃጨርቅ፣ የመኪና እና ሌሎች ከ1,800 በላይ ምርቶቻቸውን ያለ ምንም ቀረጥ ወደ አሜሪካ ገበያ የሚያስገቡበት ፍቃድ እስከ 2028 ድረስ እንዲራዘም መደረጉን አፍሪቃን ኒውስ አስነብቧል።   ላለፉት 25 ዓመታት የአሜሪካ እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት መሠረት ሆኖ የቆየው አጎዋ ስምምነት የሚያበቃበት ጊዜ ከመድረሱ በፊት መራዘሙ በአሜሪካ ገበያ ላይ ለሚተማመኑ በርካታ የአፍሪቃ አምራቾች እና ላኪዎች መረጋጋትን የሚፈጥር መሆኑን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።   ​የሕጉን መጽደቅ ከደገፉት የአሜሪካ ሴናተሮች መካከል አንዱ የኾኑት ሴናተር ራፋኤል ዋርኖክ፥ የስምምነቱ መራዘም የዕለት ተዕለት የሸቀጦች ዋጋን ከመቀነሱም በላይ የዓለም-አቀፍ አጋር ሀገራትን ኢኮኖሚ በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል ብለዋል።   ምክር ቤቱ ከአጎዋ አዋጅ ጎን ለጎን ለሀይቲ የተዘጋጁ ተመሳሳይ የንግድ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ማራዘሙ በአፍሪቃ ኒውስ ዘገባ ላይ ተመላክቷል።

  • የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) 5ኛውን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ቻሌንጅ ፕሮግራም አስጀምሯል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በሃገር በቀል ቴክኖሎጂዎች የሃገርን መሰረተ ልማቶች የሚጠብቅ "ዲጂታል ሰራዊት" ለመገንባት ያለመውን 5ኛውን ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ (Cyber Talent Summer Camp Challenge) ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስጀምሯል። አስተዳደሩ ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ሲያካሂደው የቆየው ይህ ፕሮግራም፣ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንዲሁም  በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት በዘርፉ ብቁ የሆኑ "የዲጂታል ሰራዊት" ወጣቶችን ለማፍራት ያለመ መሆኑ ገልጿል። ስልጠናው ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በባህር ዳር ፣ ደብረ ብርሃን ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ሐረማያ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በኢመደአ ታለንት ማዕከል ይሰጣል ። በአጠቃላይ በሰባት የስልጠና ማዕከላት የሚሰጠው ይህ ፕሮግራም 1ሺ 249 ተማሪዎች ለአንድ ወር ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚቆዩ ይሆናል። ስልጠናው :- • ሳይበር ደህንነት (Cyber Security) • ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት(Software Developmet) • ኤምቤድድ ሲስተም (Embedded System) • ኤሮስፔስ (Aerospace) • ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ (Emerging Technology) ዘርፎችን ያካተተ ነው። በቆይታቸው የአካል ብቃት ፣ የስነልቦና ድጋፎችን እና ቼዝን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ተከታታይ የሆኑ ስልጠናዎችን የሚሰጣቸው ሲሆን በማብቂያው ላይም ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ይሆናል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • በኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በታሪክ የከፋው ሊኾን ይችላል - የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ በኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከቀደሙት ወረርሽኞች የከፋ ወደ መኾን እያመራ መኾኑን አሳሰበ። በወረርሽኙ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ ሲያልፍ ፤ በመዛመት መጠኑ ፈጣኑ ኾኖ ተመዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ወረርሽኙ ዓለምን አስደንግጧል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በዚህ ፍጥነቱ ከቀጠለም እ.ኤ.አ. ከ2014 - 2016 በምዕራብ አፍሪካ ከተከሰተው ወረርሽኝ የከፋ ሊኾን እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። ለአኹኑ የወረርሽኙ ምክንያት የኾነው ቡንዱቡግዮ ቫይረስ የተረጋገጠ ክትባት አለመኖሩ ለመባባሱ አንዱ ምክንያት ሆኗል ሲል አሶሸትድ ፕረስ ዘግቧል።

  • በኮሎምቢያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 132 ሰዎች ሲሞቱ 480 ተጎዱ። በበርካታ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሰዎች ተቀብረዋል የሚል ስጋት በመኖሩ የሟቾች ብዛት ከ132 ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በኮሎምቢያ ከባድ መሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ ይህም በሬክተር ስኬል 7.4 ሆኖ ተመዝግቧል። በቾኮ ግዛት የተከሰተው አደጋው ከመሬት በ103 ኪሎሜትር በታች የተከሰተ እንደሆነ የአገሪቱ…

  • በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ቡርሃካባን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። በቤይ ክልል የምትገኘው ቡርሃካባ በአልሸባብ ሀይሎች መከበቧን ተከትሎ ነው ኢትዮጵያ ጦሯን ያስወጣችው ተብሏል። በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የአረጋጊ ተልዕኮ (AUSSOM) ስር የተሰማራው የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ለሶማሊያ ጦር አስረክቦ መውጣቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በዚህ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላለፉት 12 አመታት መቆየቱ ተመላክቷል። ቡርሃካባ በሰሜን ምዕራብ ከሞቃዲሾ 187 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ናት። #somaliguardian

  • በኮሎምቢያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 132 ሰዎች ሲሞቱ 480 ተጎዱ። በበርካታ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሰዎች ተቀብረዋል የሚል ስጋት በመኖሩ የሟቾች ብዛት ከ132 ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በኮሎምቢያ ከባድ መሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ ይህም በሬክተር ስኬል 7.4 ሆኖ ተመዝግቧል። በቾኮ ግዛት የተከሰተው አደጋው ከመሬት በ103 ኪሎሜትር በታች የተከሰተ እንደሆነ የአገሪቱ የጂኦሎጂካል አገልግሎት አሳውቋል። በመሬት መንቀጥቀጥ ከ480 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ከመሬት መንቀጥቀጥ መነሻ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፒሬራ ከተማ የከፋው ጉዳት ተመዝግቧል። ቢቢሲ ትክክለኛነቱን አረጋገጥኩት ያለው አንድ ቪዲዮ፣ 'ፕላዛ ቦሊቫር' በተባለው የከተማው ዋና አደባባይ የሚገኝ አንድ ሕንፃ ሲደርመስ አሳይቷል። በርካታ ሰዎች ተሰብስበውበት የነበረ ስፍራ በፍርስራሽ እና አቧራ ሲሞላም ይታያል። በከተማው 40 ሰዎች መሞታቸውን እና 65 ሕንፃዎች መፍረሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በ15ቱ ሕንፃዎች ፍርስራሽ ስር ሰዎች ተቀብረው ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል። ከመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ካሊ ከተማ ውስጥ ደግሞ 32 ሕንፃዎች ፈርሰዋል። በቾኮ እና ቫሌ ዴል ካውካ ግዛቶች በሚገኙት ማኒዛሌስ፣ ኪብዶ እና ሜዴሊን ከተሞችም የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል። ንዝረቱ በጎረቤት አገራት ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ፓናማም ደርሶባቸዋል። የአሁኑ አደጋ የተከሰተበት ኮሎምቢያ አጎራባች በሆነችው ቬንዙዌላ ከ6 ሺሕ በላይ ሰዎች በተመሳሳይ አደጋ መሞታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። #Bbc

  • የሶሪያ ፍርድቤት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ላይ የሞት ፍርድ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ አል አል አሳድን ሰብዓዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ነው የሞት ፍርድ ያስተላለፈባቸው። በፕሬዝዳንቱ የወንጀል ዝርዝር ግድያ፣ ስቃይ እና ድብደባ ተካተዋል። አላሳድ "ወንጀሉን የፈጸሙት" በ2011 በነበረው የአረብ አብዮት ወቅት መሆኑን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል። ደማስቆ የሚገኘው አራተኛው የወንጀል ችሎት በቀድሞው የደህንነት ባለስልጣን አቴፍ ናጂብ፣ በአልአሳድ እና በወንድማቸው ማሄር አልአሳድና በሌሎች ሶሪያውያን ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች ውሳኔ ሰጥቷል። #iranintl

  • ታይላንድ ለአንድ አመት ለዜጎቿ የጦር መሳሪያ ፈቃድ መስጠት አቆመች። የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርኒቫኩል የጦር መሳሪያ ፈቃድ ለአንድ አመት እንዲራዘም መወሰናቸውን ገልፀዋል። ይህ ውሳኔ የመጣው ሀገሪቱ በቅርቡ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ካስተናገደች በኋላ ነው። ቻርኒቫኩል የህዝብ መረጋጋት ለመፍጠርና አደጋዎችን ለመቀነስ ተመሳሳይ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የታይላንድ ሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል። ታይላንድ በሳምንት ውስጥ በትምህርት ቤት እና አደባባይ ላይ በተከሰቱ ጥቃቶች 37 ሰዎች ተገድለዋል። #anadoluagency

  • ሴኔጋል በተመሳሳይ ፆታ ወንጀል የጠረጠረቻቸውን 71 ሰዎች አሰረች። ሁሉም ወንጀለኞች ወንዶች መሆናቸው በክስ መዝገቡ ላይ ተገልጿል። የሴኔጋል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዚህ ወንጀል ታዋቂ ግለሰቦች መካተታቸውን አስታውቋል። ቢሮው አክሎም ከተያዙት ውስጥ የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ገልጿል። ሀገሪቱ በተመሳሳይ ፆታ የተጠረጠሩ ሰዎች የ10 አመት እስር እንዲፈረድባቸው የሚፈቅደውን አዋጅ ያፀደቀችው ባሳለፍነው መጋቢት ነው። ህጉ የኤች አይ ቪ ኤድስ እንዲስፋፋ የሚያደርግ ወንጀል ነው ብሎ ፈርጆታል።  #thesunmalaysia

  • #Ethiopia "የፌደራል መንግስት እና የክልል መሪዎች ከጦርነት ድርድርን እንዲመርጡ አሳስባለሁ" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር (WHO) ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል። "ለሦስት አመታት በአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት ሊገለጽ የማይችል ህይወት ቀጥፏል፣ ኦሮሚያ እየደማች ነው፣ ትግራይ ወደ ጦርነት እየተመለሰ ነው" ብለዋል። "አፋር ወደ ጦርነት እየገባ ነው፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልም በአመጽ የተሞላ ነው" ሲሉም ገልጸዋል። "በቃ የፌደራል መንግስት እና የክልል መሪዎች ከጦርነት ድርድርን እንዲመርጡ አሳስባለሁ" ነው ያሉት። "ትክክለኛ የፖለቲካ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ "ኢትዮጵያ የምትፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም ነው" ብለዋል። "ጦርነት ሁሌም ቢሆን ሞትን፣ ጥፋት፣ መፈናቀልና ውድመትን ነው የሚያስከትለው" ሲሉ አውግዘው፣ "ኢትዮጵያ የተሻለ ይገባታል" ብለዋል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • #Hormuz ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ "አይከፈትም" አለች። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አሜሪካ የኢራንን ወደቦች ካልከፈተች ሰርጡ እንደተዘጋ ይቆያል ብለዋል። ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን በበኩላቸው በኦማን እየተደረገ ያለው ድርድር ሰርጡ እንዲከፈት ስምምነቱ ከጫፍ መድረሱን ጠቁመዋል። ይህ ለአራግቼ ትክክል አይደለም። ኢራን ሆርሙዝን ለመክፈት ተስማምታለች የሚለው መረጃ "በፍጹም የተሳሳተ ሲሉ" አስተባብለዋል። አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ምሽት ኢራን ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ምክንያት የሁለቱ ሀገራት ስምምነት ፈርሷል። ሀገራቱ በፓኪስታን አደራዳሪነት ለ60 ቀናት የሚዘልቅ ስምምነት በዲጂታል አማካኝነት የፊርማ ስነስርዓት አካሂደው ነበር። #telegraph

  • видео или голосовое, без подписи

  • በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት 20,000 ሰዎችን አፈናቀለ። በምዕራብ ካናዳ የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት ከባድ አደጋ ተጋርጦባታል። በሀገሪቱ ያለው ከባድ ሙቀት ለአደጋው ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። የግዛቲቱ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አውጇል። 50 ባለሙያዎችና 18 የእሳት አደጋ መከላከያ ሄሊኮፕተሮች መሰማራታቸውን የሀገሪቱ ደን ጥበቃ ሚኒስትር ራቪ ፓርመር ተናግረዋል። #itv

  • በዳርፉር በድሮን ጥቃት 35 ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን መብት ተሟጋች ተቋም አስታወቀ። በሰሜን ሱዳን ዳርፉር ግዛት ባህላዊ የፍርድ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ባለበት የሱዳን ጦር በፈጸመው የድሮን ጥቃት 35 ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን መብት ተሟጋች ተቋም አስታውቋል። ትናንት ከሰዓት በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውንም ገልጿል። ንጹኃን ላይ የሚፈጸም ጥቃትን የሚከታተለው 'ዘ ኢመርጀንሲ ሎየርስ ግሩፕ' እንዳለው የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ጋህራ አል-ዛዊያ በተባለ መንደር ነው። መንደሩ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ነው። ስለተፈጸመው የድሮን ጥቃት የሱዳን ጦር አስተያየት አልሰጠም። ለሦስት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ በሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል። ኤኤፍፒ ያነጋገራቸው የዓይን እማኝ "የእሑዱ የፍርድ ሥነ ሥርዓት የማኅበረሰብ መሪዎች በተገኙበት ዛፍ ሥር እየተከናወነ ነበር' ብለዋል። አራት የጎሳ መሪዎች እና ሁለት የአርኤስኤፍ ኮማንደሮች በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል እንደሚገኙበት የዓይን እማኙ ገልጸዋል። የግል ሚዲያ የሆነው ዳርፉር 24፣ ሁለት ድሮኖች በአካባቢው በርረው ከአራት ሚሳዔል በላይ መተኮሱን ዘግቧል። የመብት ተሟጋች ቡድኑ የድሮን ጥቃቱን አውግዞ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል። ንጹኃን ዜጎችን እና መሰረተ ልማትን ዒላማ ማድረግ "ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጋር የሚጻረር" መሆኑን ገልጿል። #Bbc

  • видео или голосовое, без подписи

  • #Update "የሰላም ለኪ ዋሻ የመደርመስ አደጋ ደርሶበታል" ተባለ። በጻድቃኔ ማርያም ገዳም "የሰላም ለኪ ዋሻ የመደርመስ አደጋ ደርሶበታል" ሲል የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ሚዲያ ዘግቧል። በዋሻ መደርመስ ዛሬ በከፍተኛ ሀዘን ላይ እንገኛለን፣ ገዳሙ ከእድሜው ብዛት የተነሳ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በመረዳት እና ለዕድሳት በመዘጋጀት ላይ በነበረበት ወቅት፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ/ም በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኘው የሰላም ለኪ ዋሻ የመደርመስ አደጋ ደርሶበታል ብሏል። በ100 ለሚቆጠሩ አመታት ሲያገለግል የነበረው የምህላ ማድረሻ ዋሻ በድንገት በተከሰተ መሸርሸር ከ10 በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ምዕመናን ሕይወታቸው ሊያርፍ ችሏል። በበርካታ ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት ደርሷል። ድንገተኛ አደጋው ለሕዝበ ክርስቲያኑ፣ ለአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ለገዳሙ አባቶች፣ ለተወዳጅ ምእመናን ቤተሰቦች እጅግ ልብ ሰባሪና ታላቅ የሀዘን ጊዜ በመሆኑን፣ ገዳሙ ሕይወታቸውን ያጡትን ወገኖች ነፍስ ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያኖራቸው ዘንድ ዘወትር በጸሎት እንደሚያስብ ተገልጿል።

  • видео или голосовое, без подписи

Mado-Media — tgindex