Pharo School - Assosa
СтатистикаDear all, Welcome to Pharo School - Assosa Telegram channel. We will be able to reach you through this telegram channel, and share messages and update you with important information. Thank you! The school.
- Последний пост
- 17 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 091
- 1/48двое суток
- 1 250
- 1/72трое суток
- 1 348
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰኞ ነሐሴ 11 2818 ዓ.ም ውድ የፋሮ አሶሳ ቀጥር 2 ት/ቤት ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ!!! 🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵 ት/ቤታችን በ2018 ዓ.ም የት/ት ዘመን በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%)ወደቀጣዪ የክፍል ደረጃ ማሳለፍ ችሏል። ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መመዝገብ ትልቁን ሚና ለተወጡ መ/ራን፣ የት/ቤት አመራር፣ወላጆችና ከምንም በላይ ለተማሪዎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ነባር ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ነሐሴ 13-14(ሮብ እና ሐሙስ) ይሆናል። ለምዝገባ ሲመጡ መመዝገቢያ ወርሀዊ ክፍያ ድምር 7ኛ...300 1750 2050 9ኛ...300 1875 2175 ከላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ይዘው አዲሱ ት/ቤት በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታካሂዱ በማለት እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ ሮብ እና ሐሙስ ጠዋት ከ3:00-6:00 ከሰዓት ከ8:00-10:00 መሆኑን እየገለፅን ከዚህ ሰዓት ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። በተጠቀሰው ዕለት ያልተመዘገበ ተማሪ ት/ቤቱ አንዳቋረጠ በመውሰድ በቦታው አዲስ ተማሪ የሚተካ ይሆናል። ት/ቤቱ
አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ውድ የፋሮ አሶሳ ቁ.1 ት/ቤት ወላጆች! እንኳን ደስ አላችሁ!! 🎉🎉🎉🎉🎉🎉 🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖 ት/ቤታችን በ2018 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ወደ 7ኛ ክፍል ማሳለፍ ከመቻሉም በላይ ከ93% በላይ ተማሪዎቻችን የት/ቤቱ መለያ የሆነውን 70% እና በላይ ውጤት የማስመዝገብ ግብ አሳክተዋል፡፡ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መመዝገብ ትልቁን ሚና ለተወጡ መምህራን፣ የት/ቤቱ አመራር አካላት፣ ተማሪዎቻችንና ወላጆች እንዲሁም መላው የት/ቤታችን ማህበረሰብ ላቅ ያለ ምስጋናና አድናቆታችንን እያቀረብን ት/ቤታችንን ወደ መለስተኛ ደረጃ በማሳደግ እነዚህኑ ተማሪዎች በ2019 የትም/ዘመን የ7ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለማስቀጠል አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቅን በመሆኑ ሰኞ ነሃሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ምዝገባ ስለሚካሄድ በወቅቱ ተገኝታችሁ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡ 🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆🎖🏆 በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!! እያልን ለተማሪዎቻችን መልካም የዕረፍት ና የዝግጅት ጊዜ እንመኛለን!! ት/ቤቱ
ውድ የትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን። እንኳን ለ2019 ዓ.ም የት/ት ዘመን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐 💥🔥💥⭐️💫💥🌟💥💫💥✨💥✨ ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች ከ 1ኛ - 4ኛ ክፍል * 8 ባለ ሀምሳ ገፅ ደብተር * 2 ባለ 32 ገፅ ደብተር * 1 የስዕል ደብተር * 1 የእጅ ፅሑፍ ደብተር ባለ አራት መስመር * 2 እርሳስ * አንድ ፓኬት ባለቀለም እርሳስ * 2 ላጲስ * 2 መቅረጫ * 1 እስኪርብቶ * 1 ኮምፓስ ከ 5-6 ክፍል * 9 ባለ ሀምሳ ገፅ ደብተር * 1 ባለ 100 ገፅ square ደብተር * 1 የስዕል ደብተር * 2 እርሳስ * አንድ ፓኬት ባለቀለም እርሳስ * 2 ላጲስ * 2 መቅረጫ * 1 እስኪርብቶ * 1 ኮምፓስ ከ 7 -8 * 4 ባለ መቶ ገፅ ደብተር * 5 ባለ ሀምሳ ገፅ ደብተር * 1 ባለ 100 ገፅ square ደብተር * እስኪርብቶ * ኮምፓስ ከ 9 -10 * 11ባለ መቶ ገፅ ደብተር * 1 ባለ 100 ገፅ square ደብተር * እስኪርብቶ * ኮምፓስ ከ 11 -12 * 6 ባለ መቶ ገፅ ደብተር * 1 ባለ 100 ገፅ square ደብተር * እስኪርብቶ * ኮምፓስ የምትገዙት ደብተር Radical ወይም Sinarline መሆን አለበት።
ለፋሮ ቁ2 ት/ቤት ተማሪ ወላጆች የአዲስ ተማሪዎች ለመግቢያ ፈተና ምዝገባ የሚከናወነው ነገ 06/11/2018 ዓ.ም 2:30-6:30 ጠዋት 8:00-10:00 ከሰዓት እና ማክሰኞ 07/11/2018 ዓ.ም ጠዋት ከ2:30-6:30 ብቻ መሆኑ አውቃችሁ በተባለው ጊዜና ሰዓት በአዲሱ ጊቢ በአካል በመገኘት ልጆን እንዲያስመዘግቡ እያልን ፨ ይህ ምዝገባ ተማሪወችን ለፈተና ለማስቀመጥ ብቻ ነው። ፨ የተመዝጋቢው ተማሪ ውጤት አማካኝ 60 መሆን አለበት። ፨ የመግቢያ ፈተናው የእንግሊዘኛ እና የሒሳብ ትምህርቶች ናቸው። የፈተናው ይዘትም በ2018 ዓ.ም የት/ት ዘመን የነበሩበትን የክፍል ደረጃ ይሆናል። ፨ ፈተና የሚካሄደው ሮብ 08/11/2018 ዓ.ም ከ3:00_5:00 ይሆናል። ፨ ውጤት ሮብ ከሰዓት ይገለፃል። ፨ ምዝገባ ሀሙስ ከ2:30-6:30 ጠዋትና 8:00-10:00 ከሰዓት ብቻ ይደረጋል። ማሳሰቢያ ማንኛውም ወላጅ ፈተና አልፎ ለምዝገባ ብቁ የሆነውን ልጁን በተጠቀሰው ቀን ተከታትሎ ማስመዝገብ ይኖርበታል። በምንም አይነት ጉዳይ ምዝገባ ያልፈፀመን የተማሪ ወላጅ የማናስተናግድ መሆኑንና በቦታውም ተጠባባቂ ተማሪ የምንተካ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን። የኬጂ 1 እና 2 ተማሪዎች ምዝገባ የመግቢያ ፈተና የለውም። ስለሆነም ቀድሞ የመጣን ተማሪ ብቻ የምናስተናግድ የሆናል። ት/ቤቱ
ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም ለፋሮ ቁ2 ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች! ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለጽነው መሰረት የ2019 ዓ/ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሀምሌ 3 2018 ዓ.ም የሚጠናቀቅ በመሆኑ አስቀድማችሁ ላስመዘገባችሁ ወላጆች ላቅ ያለ አክብሮትና ምስጋናችንን እያቀረብን እስካሁን ያልተመዘገቡ ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን ከዝርዝሩ ላይ ስላገኘን ዛሬ ሀሙስ ሀምሌ 02 2018 2:30-10:00 እና ዓርብ ሀምሌ 03 2018 እለት እስከ 6:30 ሰአት ብቻ እንድትመዘገቡ የመጨረሻ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ማሳሰቢያ ፤ በወቅቱ ባለመመዝገብ ምክንያት አዲስ ተማሪ ከተተካ በኋላ ለሚከተለው ችግር ሃላፊነቱን ት/ቤቱ አይወስድም!!
Pharo School - Assosa pinned a photo
ሃምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ለፋሮ ቁ1 ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች! ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለጽነው መሰረት የ2019 ዓ/ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ በመሆኑ አስቀድማችሁ ላስመዘገባችሁ ወላጆች ላቅ ያለ አክብሮትና ምስጋናችንን እያቀረብን እስካሁን ያልተመዘገቡ ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን ከዝርዝሩ ላይ ስላገኘን በዛሬው እለት እስከ 10፡00 ሰአት ብቻ እንድትመዘገቡ የመጨረሻ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ማሳሰቢያ ፤ በወቅቱ ባለመመዝገብ ምክንያት አዲስ ተማሪ ከተተካ በኋላ ለሚከተለው ችግር ሃላፊነቱን ት/ቤቱ አይወስድም!!
World's Best School Prizes 2026 https://share.google/AXLwD6e2pRNCovoVs Click the link - Search Entries - Pharo - Vote Now - Fill the form - Vote
ውድ የፋሮ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች የፋሮ ት/ቤቶች አካል የሆነዉ የፋሮ ሆሞሻ የሴቶች አዳሪ ት/ቤት በዓለም አቀፍ የት/ቤቶች ዉድድር "አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ ስኬታማ በሆኑ ት/ቤቶች" ዘርፍ ከአስር የዓለማችን ምርጥ ት/ቤቶች አንዱ ሆኖ በመመረጡ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ዉድድሩን በ1ኛነት እንዲያጠናቅቅ የርስዎ ድምፅ አስፈላጊ በመሆኑ ከታች ያለዉን ሊንክ/ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ በመግባት Pharo School - Homosha የሚለው ላይ Vote የሚለውን በመጫን የወደፊት የክልላችን ሴት ልጆች ተስፋ ለሆነው ትም/ቤት ድምፅዎን እንዲሰጡ እንጠይቃለን።
ውድ የካምፖስ 2 ተማሪ ወላጆች ወርሀዊ መመዝገቢያ ድ. 1. ኬጂ -6ኛ 1500 300 1800 2. 7እና8 1750 300 2050 3. 9-12 1875 300 2175 ልጆን ለማስመዝገብ ሲመጡ ከላይ የተመለከተውን ክፍያ መሠረት በማድረግ እና ዝርዝር ብር በመያዝ ተዘጋጅተው እንዲመጡ እናሳውቃለን። ምዝገባው የነባር ተማሪዎች ሲሆ ከዛሬ ሰኞ እስከ ዓርብ ከ3:00-6:30 ጠዋት 8:00-10:00 ከሰዓት መሆኑን እየገለፅን ከተጠቀሰው ሰዓት ዉጭ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ቀጣይ ሰኞ ና ማክሰኞ ለመግቢያ ፈተና ዝግጅት ምዝገባ የሚደረግበት ሲሆን ሮብ ፈተና ይቀመጣሉ።ያለፉ ተማሪዎች ምዘገባ ሀሙስና ዓርብ ይካሄዳል። ት/ቤቱ
Pharo School - Assosa pinned Deleted message
https://youtu.be/RBkpGgbIccM?si=2nxgO3szGip3Y8J3
ውድ የካምፓስ 1 ተማሪ ወላጅች በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን ነገ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሚከበረው የመዝጊያ በአል ላይ የገበያ ቀን (Market Day) ስለሚኖር እንግሊዝኛ ተናግረው የሰበሰቡትን ኩፖን ይዘው እንዲመጡ እንጠይቃለን። ት/ቤቱ
ውድ የካምፓስ 1 ተማሪ ወላጅች በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የፋሮ ት/ቤት ካምፓስ 1 በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር መሰረት እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 2፡30 – 6:00 የት/ቤት መዝጊያ በዓል ላይ እንዲገኙልን እናሳዉቃለን። ት/ቤቱ
ውድ የካምፓስ 2 ተማሪ ወላጅች በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የፋሮ ት/ቤት ካምፓስ 2 በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር መሰረት እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 2፡30 – 6:00 የት/ቤት መዝጊያ በዓል ላይ እንዲገኙልን እናሳዉቃለን። ት/ቤቱ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 የአራተኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ፈተና ከ1ኛ-5ኛ ክፍል ከሰኔ 15-17፣ 2018; ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በቀረበው የፈተና መርሀግብር መሠረት ለልጅዎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያድርጉ። ት/ቤቱ