tgindex
Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ)

Статистика

የዩትዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ !!! ይህን ሊንክ በመጫን 👉👇 https://www.youtube.com/c/QesesTube ሰብስክራይብ ያድርጉ ⛔ በቻናሉ ሚለቀቁ ትምህርቶች - ሀዲሶች ፣ ፈትዋዎች ፣ ኢስላማዊ ታሪኮች ፣ ኒካህን እና ትዳርን የሚመለከቱ ትምህርቶች ...........ወዘተ በተለያዩ ኡስታዞች ይቀርብላችኋል !!!

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 250
+3 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
779
21 постов
Вовлечённость
24,0%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
339
1/48двое суток
388
1/72трое суток
419

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/U22DHT5t9QY

  • https://youtu.be/DIqI_fy_Ejc

  • 8 авг.46912из ahmedadem

    ልብህን ለማን እንደምትሰጥ እወቅ! የዱኑያ ምሽት ላይ እንደመሆናችንና የመሲሐድ'ደጃል መምጫም እንደመቃረቡ ዲኑ ላይ የሚጫወቱና እራሳቸው ተደናብረው ኡማውን የሚያደናብሩ ሰዎች በዝተዋል። ማህበራዊ ሚዲያውም የራሱ ጥሩ ጎን እንዳለው ሁሉ ሰዎችን ማሳሳትና ግራ ማጋባት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል። መችና ከማን የሸሪዓህ እውቀት እንደተማሩ የማይታወቅ ሰዎች በካሜራ (በስልክና ኮምፒዩተር) መስኮት…

  • 8 авг.44972из ahmedadem

    ልብህን ለማን እንደምትሰጥ እወቅ! የዱኑያ ምሽት ላይ እንደመሆናችንና የመሲሐድ'ደጃል መምጫም እንደመቃረቡ ዲኑ ላይ የሚጫወቱና እራሳቸው ተደናብረው ኡማውን የሚያደናብሩ ሰዎች በዝተዋል። ማህበራዊ ሚዲያውም የራሱ ጥሩ ጎን እንዳለው ሁሉ ሰዎችን ማሳሳትና ግራ ማጋባት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል። መችና ከማን የሸሪዓህ እውቀት እንደተማሩ የማይታወቅ ሰዎች በካሜራ (በስልክና ኮምፒዩተር) መስኮት ብቅ እያሉ የፈለጉትን ሐላል፣ የፈለጉትን ሐራም ብለው ያለ በቂ እውቀት በስሜትና በግምት በመናገር ብዙ አላዋቂዎችን ያሳስታሉ። ከዚህም አልፎ ገና አዲስ ወደ ኢስላም የገቡ ወንድምና እህቶች እራሳቸው እንኳ ዲኑን በትክክልና በጥልቀት ሳይረዱ መደበኛ አስተማሪ ሆነው ቀርበው ኢስላምና ሙስሊሞችን ወክለው ሲናገሩና ሲከራከሩም ይታያል !! ይህ በጣም ይገርማል፤ ያሳዝናልም! ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንደ ትልቅ አዋቂ ቆጥረው የሚከተሏቸውና ልባቸውን የሚሰጧቸው ሰዎች ሁኔታ ነው!! ኢስላማዊ እውቀት የዲኑ/የእምነቱ አንድ አካል ነው፤ ከኔ ይሻላል ከሚሉት ሁሉ (ከየትም፣ ከማንም) እውቀትን ዝም ብሎ መቀበል እምነትን ሊያበላሽ፣ ማንነትና አስተሳሰብን ሊቀይር ይችላልና ምላስና ድፍረት ስላለው ብቻ ራሱን በራሱ ጊዜ አስተማሪ አድርጎ የቀረበን ሁሉ ከመስማትና ከመከተል እንጠንቀቅ!! ለአካላዊ ጤናችን ሃኪም ከምንመርጠው በላይ ለልብና ለእምነታችን መሪና መካሪ እንምረጥ። ትልቁ መሲሐድ'ደጃል ከመምጣቱ በፊት ለሱ መንገድ የሚያመቻቹ ብዙ ትናንሽ ደጃሎች እንዳሉ ተነግሯል። ቂያማ ሲቃረብ ሸይጣን በሰው ተመስሎ አስተማሪ ሆኖ እንደሚቀርብም ተገልጿልና ልብህን ለማን እንዳምትሰጥ/ጪ፣ የሸሪዓህ እውቀትን ከማን እንደምትቀስም/ሚ ጠንቅቀህ/ሽ እወቅ/ቂ። የሸሪዓህ እውቀትን ከምንጩ ያልወሰደና በዑለሞች ያልተመሰከረለት የዩቱበር፣ የቲክቶከርና ፌስቡከር ... መጫወቻ እንዳትሆን/ኚ!! ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ዛዱል-መዓድ https://telegram.me/ahmedadem

  • https://youtu.be/3yAybxgxYhY

  • 7 авг.543103

    https://youtu.be/DWDcMjW0UUg?si=YHNJNChD6NR6Oywh

  • 7 авг.46591из Qesestube

    ረሱል ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ በማብዛት የሚገኙ ጥቂት ትሩፋቶች። 😻 https://t.me/Qesestube 🔍share ሼር

  • https://t.me/IbnuMunewor?livestream

  • https://youtu.be/nAQpqn_fyQQ

  • 4 авг.604245из MuradTadesse

    በእስልምና የቦክስ እና የድብድብ ስፖርቶች (MMA) ብይን‼ ============================== ✍️ በዘመናችን በወጣቶች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እየሆኑ ከመጡ ስፖርቶች መካከል ቦክስ (Boxing)፣ የቅይጥ ማርሻል አርት (MMA/UFC)፣ ሙአይ ታይ (Muay Thai) እና መሰል የድብድብ ውድድሮች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። እስልምና የሰውነት ብቃትን፣ ራስን መከላከልን እና ጤናን የሚጠብቁ ስፖርቶችን (እንደ ዋና፣ ሩጫ፣ ቀስት ውርወራ፣ የፈረስ ግልቢያ የመሳሰሉትን) አጥብቆ ያበረታታል። ነገር ግን ማንኛውም ስፖርት ከሸሪዓህ (ከኢስላማዊ ህግጋት) ማዕቀፍ መውጣት የለበትም። ታላላቆቹ የዘመናችን ሊቃውንት እነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ አል-አልባኒ እና ሼኽ ኢብኑ ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና)፣ እንዲሁም የዓለም አቀፉ የኢስላማዊ ፊቅህ አካዳሚ (በፈታዋ ቁጥር 50 [3/10]) እነዚህ የድብድብ ስፖርቶች በእስልምና ክልክል (ሐራም) መሆናቸውን በሙሉ ስምምነት አፅድቀዋል። 🤩 ምክንያቶቹም ስሜታዊ ሳይሆኑ፣ ጥልቅ ሸሪዓዊ እና ሎጂካዊ ማስረጃዎች ላይ የተመረኮዙ ናቸው፦ 1⃣ አላህ ያከበረውን ፊት መምታት (Violating the Sanctity of the Face): በእነዚህ ስፖርቶች ውስጥ ከፍተኛው ነጥብ (Point) የሚሰጠው የተቃዋሚን ፊት በኃይል በመምታት ነው። በእስልምና ግን የሰውን ልጅ ፊት መምታት (ሙስሊምም ይሁን ኢ-ሙስሊም) ፍፁም ክልክል ነው።   🌷 ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ∴አንዳችሁ ወንድሙን በሚመታ (በሚጣላ) ጊዜ ፊትን ከመምታት ይቆጠብ (ይራቅ)።»     (ቡኻሪና ሙስሊም)   🌷 ኢማም አል-ነወዊ ይህን ሲያብራሩ፦ "ፊትን መምታት የተከለከለበት ምክንያት ፊት ልስላሴ ያለው፣ የሰው ልጅ ውበትና አብዛኛዎቹ የስሜት ህዋሳት የሚገኙበት ቦታ ስለሆነ ነው። በፊቱ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት አደገኛና ገፅታን የሚያበላሽ ነው" ብለዋል። 2⃣ ራስንና ሌላውን ለአደጋ ማጋለጥ (Harm to Self and Others): የቦክስ እና MMA ዋነኛ ግብ ተቃዋሚን ክፉኛ መጉዳት፣ ደም ማፋሰስ እና ራሱን ስቶ እስኪወድቅ (Knock-out) ድረስ መደብደብ ነው።   🌷 አላህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፦ "በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡" (አል-በቀራህ 195)   ✅ እንዲሁም "ነፍሶቻችሁንም አትግደሉ፤ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና።" (አል-ኒሳእ 29)   ✅ ነብዩ ﷺ "ጉዳት ማድረስም ሆነ በጉዳት መበቀል የለም!" ብለዋል። ✅ የህክምናው ዓለም ምስክርነት፡- የምዕራቡ ዓለም የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀሩ ይህ ስፖርት ሊታገድ ይገባል ይላሉ። የብሪቲሽ ሜዲካል ካውንስል ቃል አቀባይ የሆኑት ዶ/ር ሮጀር ዊርቲ ሲናገሩ፤ "ቦክስ ስፖርት ሊባል የማይገባው እጅግ አደገኛ ድርጊት ነው። ከ1945 እስከ 1983 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 350 ቦክሰኞች በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው አልፏል። በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ የአዕምሮ መናወጥ (Brain damage) እና የዘላቂ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል።" ይህ አይነቱን እልቂት እስልምና "ስፖርት" ብሎ አይቀበለውም። 3⃣ የዓቂዳህ ጥሰት፡ ለፍጡር ማጎንበስ (Bowing to the Opponent): በብዙ የማርሻል አርት እና የድብድብ ውድድሮች ላይ ከመጀመራቸው በፊትም ሆነ ሲያበቁ ለተቃዋሚ (ወይም ለዳኛው) ማጎንበስ የተለመደ ህግ ነው። የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ይህንን አስመልክቶ፡- "ለሙስሊምም ሆነ ለካፊር በአክብሮት (ሰላምታ) መልክ በሰውነት የላይኛው ክፍል መጎንበስ (Bowing) አይፈቀድም። ምክንያቱም በአክብሮት መልክ የሚደረግ መጎንበስ ዒባዳ (አምልኮ) ነው፤ አምልኮ ደግሞ ለአላህ ብቻ እንጂ ለማንም አይገባም" በማለት ከልክሏል። 4⃣ ጊዜን፣ ገንዘብን ማባከን እና ሌሎች ጥሰቶች: እነዚህ ውድድሮች የሚካሄዱት ብዙ ጊዜ ዓውራን (ከእምብርት እስከ ጉልበት ያለውን የሰውነት ክፍል) በሚገልጡ አጫጭር ትጥቆች፣ በሙዚቃ ታጅበው፣ ሴቶችና ወንዶች በተቀላቀሉበት (ኢኽቲላጥ) እና ቁማር (Betting) በነገሰበት መድረክ ላይ ነው። ⬇️ ጥያቄ 1፡ "በስፖርቱ የእስልምናን ስም አስጠራለሁ (ዲንን አገለግላለሁ)" የሚሉ ወጣቶችስ? አንዳንድ ሙስሊም ወጣቶች "እኔ የምወዳደረው ዲኔን ላስጠራ ነው፣ ሳሸንፍ ስለ እስልምና እናገራለሁ፣ ገንዘቡንም ሰደቃ አደርጋለሁ" ይላሉ። 🤍ምላሽ፡- የዓላማ ማማር (ጥሩ ኒያ) አንድን ሐራም የሆነ ድርጊት ሐላል አያደርገውም። ነብዩ ﷺ "መልካም የሆነ፣ ከራስ ላብ የመነጨ ስራ (ገቢ) እንጂ አላህ አይቀበልም" ብለዋል። ወጣትነትንና ጉልበትን እርስ በርስ በመደባደብ ከማሳለፍ ይልቅ፣ ጠቃሚ በሆኑ ሐላል መንገዶች እስልምናን ማገልገል ይገባል። 🌷 ጥያቄ 2፡ መወዳደሩ ክልክል ከሆነ "መመልከቱስ" ይፈቀዳል? በዚህ ጉዳይ ላይ (አል-ፊቅህ አል-ኢስላሚ ወ-አዲለቱሁ) እንዲሁም ሌሎች የፊቅህ መጽሐፍት ላይ የተቀመጠ አንድ ወርቃማ የፊቅህ ህግ አለ፦ "መሥራቱ (መተግበሩ) ሐራም የሆነን ነገር፣ መመልከትም ሐራም ነው (What is forbidden to do is forbidden to watch)።" ሰዎች ሲደባደቡ፣ ደም ሲፋሰሱ፣ አላህ ያከበረውን ፊት ሲመታቱ እየተመለከቱ መደሰትና ማጨብጨብ ለዚያ ሐራም ድርጊት "ይሁንታን" (Consent/Approval) መስጠት እና ማበረታታት ስለሆነ፣ መመልከቱም የተከለከለ ሐራም ነው። ▶️ እውነተኛ የሙስሊም ጥንካሬ የሚለካው ሌላውን በመማረክ፣ በመዘረር እና ደም በማፋሰስ ሳይሆን ነብዩ ﷺ እንዳሉት "ትክክለኛ ጠንካራ (ጀግና) ማለት በንዴት ጊዜ ራሱን መቆጣጠር የሚችል ነው" በሚለው የነብዩ ሚዛን ነው። ወጣቶች ሆይ! የድብድብ ውድድሮችን እንደ ኃይማኖታዊ የፉክክር መድረክ አድርጋችሁ አትውሰዱ። ሐቢብ ወይም ሌላ ሙስሊም ስላሸነፈ እስልምና ከፍ አይልም፤ ሲሸነፍም እስልምና ዝቅ አይልም። ህይወታችን፣ ስራችንና ስፖርታችን በአላህ ሸሪዓህ የተቃኘ ሊሆን ይገባል! አላህ ትክክለኛውን መንገድ ይምራን! || t.me/MuradTadesse

  • 2 авг.942244

    ⚠️ያስዝናል! በነብዩ ﷺ የሞት ገርገራ ህመምና ጭንቀት ታሪክ ድቤ እየደበደበ የሚጨፍር አሳዛኝ ትውልድ እያየን ነው❗️ ✅https://t.me/Qesestube

  • 2 авг.9102110

    መውሊድን ወደ ቁርኣን የማስጠጋት ውሸትና የስሜት ተፍሲር! ቁርኣን ማንም እየተነሳ በመሰለውና በስሜቱ ሊፈስረው አይገባም። 🛬https://t.me/Qesestube

  • 1 авг.874112из IbnuMunewor

    አሳሳቢ የክረምት መልእክቶች ~ 1. ልጆች የተሻለ ሰፊ ጊዜ የሚያገኙበት ጊዜ እንደመሆኑ ቁርኣን እንዲቀሩ፣ ኪታቦችን እንዲማሩ መስራት ይገባል። 2. በቅጡ የሚለበስ የሌላቸው ወገኖችን በዚህ በብርድ ወቅት ካለን ብናካፍል ትልቅ ሶደቃ ነው። 3. በየጎዳናውና ጉሊቱ ትናንሽ ነገሮችን ለመሸጥ ኩርምት ብለው የተቀመጡ እናቶችን የያዙትን በመግዛት፣ ከተቻለ ከዚያም አለፍ ብሎ ማገዝ ብዙ ሰዎች የሚዘጉት ሶደቃ ነው። 4. ለቀጣይ የትምህርት ዓመት አቅመ ደካማ ተማሪዎችን በማሰብ ያለፉ ተማሪዎችን የደምብ ልብሶች (ዩኒፎርም) መሰብሰብ እና አስተባብሮ ደብተር በመግዛት ላይ በየአካባቢው ብንረባረብ ትልቅ ስራ ነው። አገሩን የሚወድ አገር ተረካቢ ትውልድ ላይ ይሰራል። 5. ብዙ የሀገራችን አካባቢዎች በዚህ ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ ህዝብ ጭንቅ ላይ ነው። አጥብቀን ዱዓእ እናድርግ። 6. ዝናብ ባለበት አካባቢ ያላችሁ ኢማሞችና ኸጢቦች በሶላታችሁም፣ በኹጥባችሁም ታዳሚውን እያሰባችሁ፣ ወቅቱን እያገናዘባችሁ ፈጽሙ። በናንተ ያፈፃፀም ችግር ሰው ዝናብ እንዳይመታው ተጠንቀቁ። ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች እና መሰል ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ለማህበረሰብ ግንዛቤ ስጡ። ኹጥባ ማለት ማህበረሰብን መቀየሪያ ሁነኛ መድረክ ነውና እየተጠቀማችሁበት መሆናችሁን ገምግሙ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 30 июл.1 0614

    https://youtu.be/oZZ2iLhxNrk

  • 28 июл.1 050243из IbnuMunewor

    ህክምና በጣም ምርጥ ሙያ ነው። በዚህ ትልቅ ሙያ ላይ የተሰማራ ሰው ከገንዘብ ያለፈ ኒያ ሊኖረው ይገባል። ቅንነት፣ ተቆርቋሪነት፣ ሐቀኝነት፣ ሰው አክባሪነት ሲኖረው ስሙም፣ ዋጋውም፣ ቦታውም ይለያል። የተጎዳን፣ የተጨነቀን ሰው መፈረጅ ዋጋው በምን ይገለፃል? ክፋት፣ ማታለል፣ ግዴለሽነት ከሌለበት እና አላህን ካሰቡበት ሁሌም ዒባዳ ላይ ፣ ሁሌም አጅር የሚያስገኝ ዘርፍ ላይ ነው የተሰማሩት። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 26 июл.1 2857

    https://youtu.be/6nyy4Xuov84

  • 26 июл.1 15662

    https://t.me/ahmedadem?livestream

  • 26 июл.9171из ahmedadem

    በአላህ ፈቃድ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የተፍሲር ደርስ በቀጥታ ይተላለፋል።

  • 26 июл.1 14985

    https://youtu.be/QsYmzpe6crY

  • 24 июл.955195из Qesestube

    የዱንያ አካውንትህ ባዳ ከመሆን የበለጠ ሚያሳስበው የአኼራህ የመልካም ስራ አካውንትህ ባዶ መሆኑ ነው። 📱 https://t.me/Qesestube

Qeses Tube (ቀሰስ ቲዩብ) — tgindex