🌼ሀላል ዘውጅ🌼
Статистикаለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) #ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም #ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች #ተዓምራቶች አልሉ፡፡ (አል ሩም) 21 Direct message @Xwalletg ሀላል #ዘውጅ
- Последний пост
- 17 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጀነት ሱቅ! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ في الجَنَّةِ لَسُوقًا، يَأْتُونَها كُلَّ جُمُعَةٍ، فَتَهُبُّ رِيحُ الشَّمالِ فَتَحْثُو في وُجُوهِهِمْ وثِيابِهِمْ، فَيَزْدادُونَ حُسْنًا وجَمالًا، فَيَرْجِعُونَ إلى أهْلِيهِمْ وقَدِ ازْدادُوا حُسْنًا وجَمالًا، فيَقولُ لهمْ أهْلُوهُمْ: واللَّهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنا حُسْنًا وجَمالًا، فيَقولونَ: وأَنْتُمْ، واللَّهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنا حُسْنًا وجَمالًا﴾ “በጀነት ውስጥ በየሳምንቱ ጁምዓ (አርብ) ሰዎች የሚመጡበት (የሚሰበሰቡበት) ሱቅ (ገበያ) አለ። በዚህ ጊዜ የሰሜን ነፋስ ይነፍስና ፊቶቻቸውና ልብሶቻቸው ላይ (የጀነትን እጣንና ውበት) ይረጭባቸዋል። በዚህም ውበትና ግርማቸው ይበልጥ ይጨምራል። ውበታቸው ጨምሮ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ፣ ቤተሰቦቻቸው፦ ‘በአላህ ይሁንብን! ከእኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ግርማችሁ ይበልጥ ጨምሯል’ ይሏቸዋል። እነሱም መልሰው፦ ‘እናንተም በአላህ ይሁንብን! ከእኛ በኋላ ውበትና ግርማችሁ ይበልጥ ጨምሯል’ ይሏቸዋል።” ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2833 http://t.me/Halal_Zewje
ከሰለፎች አንደበት! ኢማሙ ኢብኑልቀዪም እንዲህ ይላሉ፦ ﴿وغض البصر عن النساء يورث في قلبك القوة والشجاعة والفراسة ويورثك انشراح في الصدر﴾ “እይታን ከተከለከሉ ሴቶች መስበር በልብህ ውስጥ ጥንካሬን፣ ጀግንነትን እና ጥልቅ ማስተዋልን (የልብ ብልህነትን) ያሳድጋል። በደረትህም (በውስጣዊ ማንነትህ) ውስጥ የልብ ሰላምንና እፎይታን ያወርሳል።” ረውደቱል ሙሒቢን፡ 101 http://t.me/Halal_Zewje
የአሹራ ቀን ፆም! መልካም ስራ እናስታውስ! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾ “የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1134 በሌላ ሀዲሳቸው ﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾ “የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 http://t.me/Halal_Zewje
በቂያማ እለት አላህ ሶስት ሰዎችን አያናግራቸውም ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ثَلَاثَةٌ لَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ: شَيْخٌ زَانٍ، وَمَلِكٌ كَذَّابٌ، وَعَائِلٌ مُسْتَكْبِرٌ﴾ “ሶስት አይነት ሰዎች በቂያማ እለት አላህ አያናግራቸውም፣ ከወንጀላቸው አያፀዳቸውም፣ ወደነሱም አይመለከትም፣ አሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። እነሱም፦ የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ የመሪ ውሸታምና የድሃ ኩራተኛ ናቸው።” ሙስሊም ዘግበውታል፡ 107 http://t.me/Halal_Zewje
🥀 የኢድ ተክቢራ 🥀 https://t.me/Halal_Zewje
ሐዲሰል ቁድሲ! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ قالَ اللهُ تعالى:‐ ﴿يا ابنَ آدمَ إنّكَ ما دعَوتَني ورجَوتَني غفَرتُ لَكَ على ما كانَ فيكَ ولا أُبالي، يا ابنَ آدمَ لو بلغَت ذنوبُكَ عَنانَ السَّماءِ ثمَّ استغفرتَني غفرتُ لَكَ ولا أبالي، يا ابنَ آدمَ إنّكَ لو أتيتَني بقِرابِ الأرضِ خطايا ثمَّ لقيتَني لا تشرِكُ بي شيئًا لأتيتُكَ بقرابِها مغفرةً﴾ የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የአደም ልጅ ሆይ! እስከጠራኸኝና ከእኔ ዘንድ እስከጠየቅክ ድረስ፤ ለሠራኸው ኃጢያት ይቅር እልሃለሁ ምንም ግድ አይሰጠኝም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ኃጢአቶችህ ከሰማይ ቢደርሱ እንኳ እኔን ይቅር በለኝ ካልክ ይቅርታ አደርግልሃለሁ ምንም ግድ አይሰጠኝም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን የሚሞላ ኃጢአቶች ይዘህ ወደኔ ብትመጣና ከዚያም ከእኔ ጋር አንድንም አካል ሳታጋራ ፊቴ ከቀረብክ ከወንጀልህ የሚልቅ ማህርታን ይዤ እመጣሃለው።” ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 127 http://t.me/Halal_Zewje
ፊትን ከመምታት ተጠንቀቁ!! ረሱል እንዲህ ﷺ ብለዋል፦ ﴿إذا ضرَب أحَدُكم فليتَّقِ الوَجْهَ.﴾ “አንዳችሁ በተማታችሁ ግዜ ፊትን ከመምታት ይጠንቀቅ።” አልባኒ በሱነን አቢ ዳውድ ውስጥ ሶሂህ ብለውታል: 4493 http://t.me/Halal_Zewje
🌼ሀላል ዘውጅ🌼 pinned «የፈረሰ ጣሪያ የዘገየ ፀፀት (ሲንግል ማዘርነትን እንደ "ጀብዱ" ላዩ እህቶች የተላከ መራራ እውነት!) || እህቴ ሆይ… አንዴ ቆም ብለሽ ስሚኝ! ይህንን ጽሑፍ ስታነቢ ሊከፋሽ ይችላል፤ ግን ጥላቻ አይደለም። ፈውስ የሚገኘው መራራውን መድሀኒት በመዋጥ ነውና እውነቱን እንጋፈጠው። በአሁኑ ዘመን "ሲንግል ማዘርነት" (በራስ ምርጫ ትዳርን አፍርሶ ልጅን ይዞ መውጣት) እንደ ጀብዱ፣ እንደ ነፃነትና እንደ…»
ጊዜን መሳደብ የተከለከለ ነው! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿قال اللهُ: يَسُبُّ بَنو آدَمَ الدَّهرَ، وأنا الدَّهرُ، بيَدي اللَّيلُ والنَّهارُ﴾ “አላህ እንዲህ ብሏል፦ ‘የሰው ልጅ ዘመንን (ጊዜን) ይሳደባል። ዘመን ማለት እኔ ነኝ። ቀንም ሆነ ሌሊት በእኔ እጅ’ ናቸው።” ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6181 http://t.me/Halal_Zewje
የፈረሰ ጣሪያ የዘገየ ፀፀት (ሲንግል ማዘርነትን እንደ "ጀብዱ" ላዩ እህቶች የተላከ መራራ እውነት!) || እህቴ ሆይ… አንዴ ቆም ብለሽ ስሚኝ! ይህንን ጽሑፍ ስታነቢ ሊከፋሽ ይችላል፤ ግን ጥላቻ አይደለም። ፈውስ የሚገኘው መራራውን መድሀኒት በመዋጥ ነውና እውነቱን እንጋፈጠው። በአሁኑ ዘመን "ሲንግል ማዘርነት" (በራስ ምርጫ ትዳርን አፍርሶ ልጅን ይዞ መውጣት) እንደ ጀብዱ፣ እንደ ነፃነትና እንደ ስልጣኔ (Upgrade) እየታየ መጥቷል። ብዙ እህቶች በማህበራዊ ሚዲያ የ"ፌሚኒዝም" እና የ"ኢንዲፔንደንት ሴትነት" (Independent) ስብከት ተታለው የሞቀ ቤታቸውን በገዛ እጃቸው እያፈረሱ ነው። አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ሀላል "ፍቺ" መሆኑን ረስተው፣ ትዳርን እንደ እስር ቤት ማየት ጀምረዋል። … ግን የዚህ ጀብዱ መጨረሻ ምንድን ነው? በ"ነፃነት" ስም የተሸፈነ፣ በብቸኝነት የተጠቀለለ ጥልቅ ፀጸት! ትዳራቸውን በገዛ እጃቸው አፍርሰው ከወጡ በኋላ፣ የዘገየ ፀፀት ሆኖባቸው የሚማሯቸው 10 መራራ እውነቶች እነሆ፡- 1.ማንም ወንድ እንደ ባልሽ አይታገስሽም! የተውሽው ባልሽ… ትዕግስተኛ ነበር። ባህሪሽን ቻለ፣ ስድብሽን ዋጠ፣ ሲከፋሽ አጽናናሽ፣ አኮርፈሽ ስትተኚ አባበለሽ። ከትዳር ውጭ ባለው ዓለም ግን? ማንም ወንድ ያንቺን ትዕቢት፣ ጭቅጭቅ እና ስሜታዊ ቀውስ ለመታገስ ጊዜም ፍላጎትም የለውም። ያጣሽው ባልሽን ብቻ አይደለም፤ አንቺን የሚሸከም ትልቅ ትዕግስትን ጭምር ነው! 2.የማህበራዊ ሚዲያ ጭብጨባ...የቤት ኪራይ አይከፍልም! ትዳርሽን ስታፈርሺ ሶሻል ሚዲያ ላይ "ጀግና፣ ነብር፣ ለማንም አትንበርከኪ" ብለው አጨበጨቡልሽ። ግን ወሩ አልቆ ኪራይ ሲደርስ? መብራት ሲጠፋ? የልጅሽን ህመም ብቻሽን ስታስታምሚ? ብቸኝነት ሲጫጫንሽ? ያጨበጨቡልሽ ሁሉ የሉም። የፌስቡክና የቲክቶክ "ላይክ" ብርድ ልብስ አይሆንም፤ መፈክር እንጀራ አይጋግርም! 3.አዲሱ የህይወት ምዕራፍሽና የምርጫ ገበያው! አሁን 23 አመትሽ አይደለም። ታሪክ አለብሽ፣ ስሜታዊ ስብራት አለብሽ፣ ልጅ አቅፈሻል፣ የራስሽ የሆነ መስፈርት አለሽ። "አልሞላ ያለኝን የሚሞላልኝ ሌላ ምርጥ ወንድ አገኛለሁ" ብለሽ ይሆናል። ነገር ግን ምርጫና አቅም ያላቸው የተረጋጉ ወንዶች የሚፈልጉት፣ ታሪክ የሌላትን፣ ያልተወሳሰበችና የተረጋጋች ሴት ነው። ገበያው አንቺ እንዳሰብሽው አይደለም፤ ጊዜ ደግሞ ለማንም አይራራም። 4."#ነፃነት" ያልሽው...አስፈሪ ብቸኝነት ነው! "አሰልቺ ትዳር" ብለሽ ወጣሽ። አሁን ግን… ብቻሽን ትበያለሽ። ብቻሽን ትተኛለሽ። ያንቺን ሀሳብ የሚጋራ፣ የልጅሽን ኮቴ ሰምቶ አብሮሽ የሚደሰት አባት የለም። ስልክሽን ስትጎረጉሪ ታድሪያለሽ። ኦንላይን ላይ ፈገግታና የ"እኔ እችላለሁ" ፎቶ… ቤት ውስጥ ግን ልብ መሰበር። ነፃነት ያለ ቤተሰብ መዋቅር… ባዶነት ነው! 5.የውሳኔሽ ትልቁ ገፈት ቀማሽ... ልጆችሽ ናቸው! አንቺ የተውሽው ባልሽን ብቻ አይደለም። ያፈረስሽው የልጆችሽን የህይወት መሰረት ነው። ያለ አባት ያደጉ ልጆች፣ የአባትነትን ባዶነትና ቁስል ተሸክመው ነው የሚያድጉት። ባልሽን ለመቅጣት ብለሽ ልጆችሽን በአባት አልባነት ቀጣሻቸው። ይህ የማይሽር ጠባሳ ነው! 6."ሲንግል ማዘር" መሆን የሚኮሩበት ሜዳሊያ አይደለም! ከባድ ነው። ብቸኝነት ነው። ድካም ነው። አላማና ራዕይ ያለው ወንድ፣ አዲስ ህይወት መገንባት እንጂ፣ የሌላውን የተበላሸ ታሪክ የመጠገን ስራ (Rescue Mission) ውስጥ መግባት አይፈልግም። እውነት ለስሜታዊ መፈክር ቦታ የላትም። 7.የህልምሽ ወንድ...ሌላ ህልም አለው! "የበለጠ ሀብታም፣ የበለጠ የተማረ፣ የበለጠ ቆንጆ አገባለሁ" ብለሽ ታስቢያለሽ። ግን ያሰብሽው ወንድ… እንደ አዲስ አብራው የምታድግ ሴት እንጂ፣ የሌላ ሰው ጥላ ያረፈባትን አይሻም። ያሰብሽውና የሚያጋጥምሽ ፍፁም ይለያያል። 8.የወንዶች ትኩረት (Attention) ማለት ክብር አይደለም! ላይክ ርካሽ ነው። ኢንቦክስ (DM) መግባት ነፃ ነው። ቲክቶክ ላይ አምረሽ ስትወጪ ያገኘሽው የወንዶች ትኩረት፣ "ለመዝናናት" የሚመኙሽን እንጂ፣ አክብረው ለትዳርና ለሀላል የሚፈልጉሽን አያሳይም። ውስጥሽ እውነቱን ጠንቅቆ ያውቀዋል! 9.የናቅሽው የትዳር ሰላም...የነገ ቅንጦትሽ ነው! ባልሽ መቶ በመቶ ፍጹም አልነበረም (ፍፁም ሰው የለምና)። ግን መረጋጋትን፣ ዋስትናን እና ስርዓት ያለው ህይወትን ሰጥቶሽ ነበር። አሁን ያለው የውጪ ዓለም ግን… ድራማ፣ ጭንቀት፣ ፉክክር እና ግራ መጋባት ነው። ውጪው ጩኸቱ ይበዛል እንጂ፣ የልብን ባዶነት አይሞላም። 10.ኢንተርኔት ቢያፋታሽም ሀዘንሽ ላይ ግን አይገኝም የቲክቶክ "አማካሪዎችን" ምክር ሰማሽ። የትዳርን ጣዕም የማያውቁ ሰዎችን አመንሽ። አሁን ግን ብቻሽን ታለቅሻለሽ። እነሱ ቪዲዮ ሰርተው ቪው (View) አገኙ፣ ኑሯቸውን ኖሩ፤ አንቺ ግን የፈረሰ ቤተሰብን ታቀፍሽ። ማጠቃለያ ይህ ሁሉ የሚሆነው… መከባበርን በአመጽ ስትቀይሪ ነው። አላህ የሰጠሽን ቤተሰብ በቲክቶክ ምናብ (Fantasy) ስትለውጪ ነው። ትዳር እኮ እስር ቤት አይደለም፤ መጠለያ ጋሻ ነው! ሰው የራሱን መጠለያ በገዛ እጁ አፍርሶ… ፀሀይና ብርድ ሲመታው ማልቀሱ አይቀርም። ብዙዎች የትዳርን እና የባልን ዋጋ የሚያውቁት… ቤቱ ፈርሶ፣ ጣራው ተነቅሎ፣ የውጪው ብርድ ሲገባባቸው ብቻ ነው። ያኔ ግን… ጊዜው ሄዷል! ምርጫውም ጠቧል! ወዳጄ… ይህ ጽሁፍ ባል ሞቶባቸው፣ ወይም ባል ኃላፊነት የማይሰማው ሱሰኛና ደብዳቢ ጨካኝ ሆኖባቸው አምልጠው ብቻቸውን ልጆቻቸውን ለሚያሳድጉ ጀግና እናቶች አይደለም! ለእነሱ ክብርና አድናቆት አለኝ! ይህ መልእክት… በቲክቶክ የ"ነፃነት" ስብከት ተታልለው፣ ትዕግስት አጥተው፣ ያለበቂ የሸሪዓ ምክንያት፣ "ይበቃኛል አዲስ ህይወት አምሮኛል" ብለው የሞቀ ትዳራቸውን በገዛ እጃቸው ላፈረሱትና ለማፍረስ አፋፍ ላይ ላሉት ነው። ልዩነቱ ይግባችሁ። ጀግናዋ መከራ ገፍቷት ብቻዋን ትቀራለች፤ ሞኟ ግን መከራን "ነፃነት" ብላ በገዛ እጇ ገዝታዋለች። ትዳር ክቡር ነው! የአላህ ፀጋ ነው! በከንቱ የሶሻል ሚዲያ ጀብዱ አታፍርሱት! (ይህ መራራ እውነት ቢያንስ የአንዲትን እህት ቤተሰብ ከፈረሳ ይታደግ ዘንድ ሼር አድርጉት!) t.me/Halal_Zewje
☘ከመንገድ ላይ አስቸጋሪን ነገር ማሰወገድ ከሙዐዝ ቢን ጀበል (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن رَفَعَ حَجَرًا عنِ الطَّرِيقِ، كُتِبَ له حَسَنةٌ، ومَن كانَتْ له حَسنَةٌ، دخل الجنةَ﴾ “ከመንገድ ላይ የሚያስቸግር የሆነ ድንጋይን ያነሳ (ያሰወገደ) ለሱ መልካም ስራ ተደርጎ ይመዘገብለታል። ለሱ መልካም ስራ ያለው ደግሞ ጀነት ያስገበዋል።” ሶሂህ አልጃሚ፡ 6265 https://t.me/Halal_Zewje
ሪዝቅ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لو أنَّ ابنَ آدمَ هرب من رزقِه كما يهرُبُ من الموتِ، لأدركه رزقُه كما يُدرِكُه الموتُ﴾ “የአደም ልጅ ከሞት እንደሚሸሸው ሁሉ ከሪዝቁ (ከሲሳዩ) ቢሸሽ ኖሮ ሞት እንደሚያገኘው ሲሳዩም ያገኘው ነበር።” ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 952 https://t.me/Halal_Zewje
አንተ መከራ ያገኝህ ሰው ሆይ አብሽር! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿يودُّ أَهلُ العافيةِ يومَ القيامةِ حينَ يعطى أَهلُ البلاءِ الثَّوابَ لو أنَّ جلودَهم كانت قُرِضَت في الدُّنيا بالمقاريضِ﴾ “በቂያማ እለት ዱኒያ ላይ እያሉ ጤናማ (ከመከራ) ነፃ የነበሩ ሰዎች፤ የመከራ ባልተቤቶች የነበሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ምንዳ ሲያዩ፤ እንደነሱ ቢሆኑ ይመኛሉ። እዚህ ዱኒያ ላይ እያሉ ቆዳቸው በመቀስ (በስለት) የተቆረጠ በነበር ቢሆን ይመኛሉ።” ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል፡ 2402 https://t.me/Halal_Zewje
🌼🍃🌸🍃🌺🍃🌸🍃🌺 🍃🌺🍃🌸🍃🌺 🌺🍃🌸 🌸 . 人 . (____) . ┃口 ┃ . ┃口 ┃ . ┃口 ┃ውድ የሀላል ዘውጅ ተከታዮች . ┃口 ┃ --------------------------- . ┃口 ┃ እንኳን ለ1447ኛው . ┃口 ┃ ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ #ኢድ ሙባረክ تقبل اللہ منا ومنکم صاله الاعمال 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 @Eid_Mubarek 🌹 @Eid_Mubarek 🌹 @Eid_Mubarek 🌹 🌸 🌺🍃🌸 🍃🌺🍃🌸🍃🌺 🌼🍃🌸🍃🌺🍃🌸🍃🌺 https://t.me/Halal_Zewje
#BREAKING የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ (ጁምዓ) ይውላል። ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል። ዒድ ሙባረክ ! #Haramain https://t.me/Halal_Zewje
ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ فِي أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ﴾ “የሐሰት ንግግርን በሐሰት መስራትን እንዲሁም መሀይምነትን (የመሐይማንን ተግባር) ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም።” ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1903 https://t.me/Halal_Zewje
ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إذا كانَت أوَّلُ ليلةٍ من رمَضانَ صُفِّدتِ الشَّياطينُ ومَردةُ الجِنِّ وغلِّقت أبَوابُ النّارِ فلم يُفتَحْ منها بابٌ وفُتِحت أبوابُ الجنَّةِ فلم يُغلَقْ منها بابٌ ونادى منادٍ يا باغيَ الخيرِ أقبِلْ ويا باغيَ الشَّرِّ أقصِر وللَّهِ عتقاءُ منَ النّارِ وذلِك في كلِّ ليلةٍ﴾ “የመጀመሪያው የረመዳን ሌሊት በሆነ ግዜ ጂኒና ሸይጣናት ይታሰራሉ። የጀሀነም በሮች ላይከፈቱ ይዘጋሉ። የጀነት በሮች ላይዘጉ ይከፈታሉ። ተጣሪው ይጣራል፡- መልካም ፈላጊ ሆይ ና፤ ተሰብሰብ ጠጋ በል። ሸር ፈላጊ ሆይ ተመለስ (ሸርህን አቁም) ይላል፡፡ ረመዳን እስኪያልቅ ድረስ በየቀኑ አላህ ከእሳት ነፃ የሚያወጣቸው ባሮች አሉት፡፡” ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 1339 https://t.me/Halal_Zewje
ረመዿን ነገ ነው‼ ✍ የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ረቡዕ የካቲት 11, 2018 E.C. የረመዿን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን! ረመዿን ሙባረክ! https://t.me/Halal_Zewje
#የባልሽን ልብ #ለመያዝ✍️ የትዳር ህይወትን በኢማን ያበበ ጣፋጭ ለማድረግ የትዳር ክህሎቶችን ማወቅ ያስፈልጋል። ወደ አዲስ የትዳር ህይወት እግሯን ያስገባች ወጣት ሴት የትዳር ክህሎቶችን በተለይም የትዳር አጋሯን ልብ መቆጣጠር የምትችልባቸውን ባህሪያት ጠንቅቃ ማወቅ አለባት። በርግጥ የትዳር ህይወት ክህሎቶችን ማወቅ አዲስ ትዳር ውስጥ የገቡ ወጣት ሴቶችን ብቻ ሳይሆን በትዳር ውስጥ ያሉትን ሁሉ ይመለከታል። #ጓደኛው ሁኚ! ባልሽ ሚስቱ ብቻ ሳይሆን ጓደኛውም እንድትሆኚ ይፈልጋል። ልቡን በእጅሽ ለማስገባት ከማንም በላይ የሚቀርበው ጓደኛ ሁኚለት ሁሉንም ጉዳዩቹን ተካፈይው። ችግሮቹን አድምጪው። ለርሱ ችግር መጨነቅሽንና በችግሩ ፊት አብረሺው እንደምትቆሚ አስረጂው ጓደኝነታችሁ የጠለቀ እንዲሆን በምድር ላይ የሚያስፈልግሽ ብቸኛው ሠው እርሱ እንደሆነ እንዲሠማው አድርጊው ጓደኛሞች የሚያደርጉትን ሁሉ አብራችሁ አድርጉ። #እናቱን ሁኚለት፣ እንደ እናቱ ተንከባከቢ ሁኚለት፤ እንደ አባት አሳቢ ይሆንልሻል፤ ልቡን አሳልፎ ይሰጥሻል። ህፃን መሆን ሲያምረው እቀፊው። እናት ለልጇ የምትሠጠውን እንክብካቤ ስጪው። አርፍዶ ሲገባ መጨነቅሽን አሳይው። ዓለሙን ሁሉ ሁኚለት በሚወዳቸው ትናንሽ ነገሮች ላይ ሳይቀር ትኩረት አድርጊ። እንክብካቤሽና የምታሳይው አሳቢነት ልቡን ይቆጣጠረዋል። ከአንቺ መለየት ከእናቱ እንደመለየት ይከብደዋል። #ከግትርነት ራቂ ወንድ ልጅ ግትራና ጨቅጫቃ ሴትን አይወድም። በንዝንዝ ህይወቱን ወደ እስር ቤት የምትለውጥበትን ሴትን አይወድም ግትርነት እና ጭቅጭቅ የትዳር ሠላምን ያናጋል። በምትነጋገሩበት ወቅት ስህተቱን ብትነግሪው ችግር የለውም። በፍጹም ግን ከብሩንና ወንድነቱን አትፈታተኞው። የምትፈልጊውን የሟሟላት ብቃት አንደሌለው እንዲሰመው አታድርጊ። ከዚህ በኋላ ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርሽም። የወንድ ልጅ ክብር የሚቆስለው በፍጥነት ነው። ከዚያ በኋላ ለማከም ያስቸግራል። #ንፁህ ልብ #ይኑርሽ ባል ንፁህ ልብ ያላት ሚስቱን እስከ እድሜው መጨረሻ ከመውደድ አይቆጠብም። ረሡል አላህ ሠላምና ሠላት በርሳቸው ላይ ይሁን) የመጀመሪያ የህይወት አጋራቸውን ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድን ምን ያህል ይወዷትና ከህልፈቷ በኋላም ምን ያህል ያስታውሷት እንደነበረ አስታውሺ ለኸዲጃ ካላቸው በጣም ብዙ የውዴታ ምክንያቶች አንዱ ኸዲጃ ንፁህ ልብ ያላት ምርጥ ሴት መሆኗ ነው። በተንኮል ልቧን ለሞላች ሚስት ልቡን አሳልፎ የሚሠጥ ባል የለም። ሚስቱን መጀመሪያ ላይ የሚወድ ቢሆን እንኳ ተንኮለኛ ልብ ካላት በሂደት እየጠላትና ልቡን ከእርሷ እያራቀ ይሄዳል። ቀስበቀስም አንዲትም ደቂቃን ቢሆን ከእርሷ ጋር ለማሳለፍ ይጠላል። የባልሽ https://t.me/Halal_Zewje
ሪዝቁ የዘገየበት (የጠበበበት) የሚያደርገው ዱዓእ! ከአብደላህ ቢን መስዑድ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦ ﴿اللهم إني أسألُك من فضلِك ورحمتِك؛ فإنَّه لا يملُكها إلا أنت﴾ “አላህ ሆይ! ትሩፋትህንና እዝነትህን እለምንሃለው። እነኚህ ፀጋዎች ከአንተ ውጪ በሌላ እጅ የማይገኙ ናቸውና።” ሶሂህ አልጃሚ፡ 1278 http://t.me/Halal_Zewje