RN.05 - Channel
Статистикаከኢትዮጵያና አዉሮፓ የሚተላለፍ የራድዮ ፕሮግራም አዲሱን ዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ: https://www.youtube.com/c/RN05Channel ፌስቡክ ገፃችንን like ያድርጉ: https://www.facebook.com/RNZeroFive/ https://twitter.com/RNZeroFive Support Us: http://bit.ly/3c09jfJ https://RNZeroFive.com
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 321
- 1/48двое суток
- 367
- 1/72трое суток
- 396
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስለ #አዲስ_አበባ በጨዋ ደምብ እንወያይ! ~~~~~ 1.ለመሆኑ የአዲስ አበቤ ስነ ልቦና ምን አይነት ነው? 2. አዲስ አባባን በአንድ ብሄር ወይንም በአንድ እምነት አልያም በአንድ ባህል መመደብና መፈረጅ ይቻላልን?! 3.ካልሆነስ አስተዳደራዊ መፍትሄው ምን ይመስሎታል? . ሀሳብዎን ያካፍሉን! . #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05
የሰው ልጆች ሕሊና የሚመረመርበት አሳዛኝ ምዕራፍ፡ አንዋር መስጂድ እና ሊቀለበስ የማይገባው የሞራል ኃላፊነት ~~~~ #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05 . በዚህ ወንድማችን ላይ የተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ እና አጸያፊ ድርጊት የሰብአዊነትን ወሰን የተሻገረ፣ ሕሊናን የሚወቅስ ከባድ ወንጀል ነው። ከጅማ ወደ አዲስ አበባ የመጣ ፣ ሀገር የማያውቅ፣ ለሐይማኖታዊ ትምህርት በማለዳ ወደ ሐረር ለመጓዝ በመዘጋጀት ላይ የነበረ እና መሄጃ ቦታ በማጣቱ ብቻ በግቢው ውስጥ ሌሊቱን እንዲያሳልፍ አጥብቆ የለመነ ደረሳ፣ ጠለላ ሊሰጠው ሲገባ በወከባ ከምፕስጅዱ ግቢ በመባረሩ የጭካኔ ሰለባ ሆኗል። ለሊቱን ሜዳ ላይ እንዳያሳልፍ አዋክበው ወደ ውጭ የጣሉት የመስጅዱ የጥበቃ አካላት፣ እንዲሁም ይህንን ተከላካይ የሌለውን ወንድም አራት ሆነው በመክበብ አስገድደው የደፈሩት የሰው አውሬዎች የፈጸሙት ድርጊት ከባድ የሞራል እና የሕግ ተጠያቂነትን የሚያነሳ ነው። በመሠረቱ የሐይማኖት ተቋማት እና መስጂዶች መሠረታዊ መገለጫቸው ለተቸገረ መጠለያ፣ ለተፈናቀለ መታደጊያ እና ለአደጋ ተጋላጭ ወገኖች ሁልጊዜም ክፍት መሆን መሆኑ ይታወቃል። ግቢው ውስጥ ወርቅ፣ አልማዝ ወይም ሌላ ቁሳዊ ሀብት እንደሌለበት የሚታውወቅ ነው ፤በመሆኑም "አደጋ ላይ ነኝ፣ አትርፈኝ" ለሚሉ እንግዶች የአንድ ሌሊት መጠለያ መሆን ካልቻለ፣ የተቋሙ ስዋዊ አገልግሎቱ ትርጉሙን ይስታል። በመሆኑም በዚህ አሳዛኝ ድርጊት በወቅቱ የነበሩት የአንዋር መስጂድ አስተዳደር እና ኃላፊዎች የሞራል እና የተቋማዊ ተጠያቂነት ባለቤት መሆናቸውን አበክሮ መናገር ያስፈልጋል። * ለተጎጂው ወንድማችን፡ ጉዳዩ ከዓመታት በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፣ የደረሰብህን ዘግናኝ ግፍና በደል ብሎም ያንን ተከትሎ ለአመታት ያሳለፍከእን መከራ ባለን ተቋም (መስጂድ) አማካኝነት ማስቀረት ባለመቻላችን እንደ ማህበረሰብ ጥልቅ ጸጸት ይሰማናል። አላህ ጽናቱንና ብርታቱን ይስጥህ! በዚህ አጋጣሚ "ከሰማነው ይልቅ ያልሰማነው እንደሚበልጥ በመገመት" ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በምን ዓይነት ኢ-ሞራላዊና እጅግ አደገኛ ሁናቴ ውስጥ እንደምትገኝ በጥልቀት መገንዘብ ይገባል። እንዲህ ያሉ ዘግናኝ ግፎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመታገል እና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ጠንካራ፣ ፍትሃዊ እና ውጤታማ የሕግ ዝግጅት ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አበክረን ልናስብበት ይገባል። . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
видео или голосовое, без подписи
በወ/ሮ ሙፈሪሃት ከማል የሚመራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia መ/ቤት ምን እየሆነ ነው? - ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አሠራር ጋር ተያይዞ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እጅግ አስደንጋጭ ናቸው! ይህንን ገጽ ከፍተው መረጃዎቹን ይመልከቱ https://www.facebook.com/search/top/?q=seid%20ibrahim
የመከላከያ ሚስጥሩ አፈተለከ፦ ትራምፕ መረጃ አቀባዮችን 'እያደንን ነው' አሉ ~~~~~~~~~ #RN05 . አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ግጭት ምክንያት የመከላከያ እና የጦር መሳሪያ (በተለይም የሚሳኤል) ክምችቷ አልቋል ወይም ቀንሷል የሚሉ ዘገባዎች በCNN እና Washington Post የመገናኛ ብዙሃን ተሰራጭተዋል። . የዶናልድ ትራምፕ ምላሽ፦ የUSA ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እነዚህን ዘገባዎች በጥብቅ አስተባብለዋል። አሜሪካ በቂ የመሳሪያ ክምችት እንዳላትና የጦር መሳሪያ አምራች ፋብሪካዎችም በከፍተኛ ፍጥነት ምርት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። . የእስራት ዛቻ፦ ትራምፕ እነዚህን ምስጢራዊ የመከላከያ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሃን አሳልፈው የሰጡ አካላትን "እያደንን ነው" ብለዋል። መረጃውን አሳልፈው የሰጡ አካላት "ከባድ የሀገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል!" ሲሉ የረጅም ጊዜ የእስራት ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቅቀዋል። . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
ያም ሆኖ ጽንፈኛ አካላት ሙስሊሙ ላይ የሚያካሂዱት የማጠልሸት ዘመቻ፣ ሙስሊሙን የማጀት አድርጎ ለመያዝና ችግሮቹን አደባባይ እንዳያወጣ ለመሸፈን ከሚደረግ ጥረትም በላይ መድረኩን በመጠቀም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምናልባትም አንድ ጥያቄዉ ምላሽ እንዳያገኝ ከመስጋት የመነጨ ዘመቻ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። . ማጠቃለያ፦ ~~~~~ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ የምክክር አስፈላጊነትን ማጣጣል አይደለም። በተለይም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ካሉበት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች መካከል ጥቂቶቹንም ቢሆን በአደባባይ በማንሳት ድምፁ እንዲሰማ ማድረጉ ትልቅ ፋይዳ አለው። ሙስሊሙን የወከሉ አካላት የተደቀኑትን መሰናክሎች አልፈው መሠረታዊ ከሆኑት ዉስጥ ቢያንስ የእኩል ውክልና ጥያቄዎቹን በማቅረብ በጎ ውጤት ማምጣት ቢችሉ ቀላል ነገር ሆኖ አይደለም። ምንም እንኳን የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ችግሮች በመድረኩ እንዳይነሱና እንዳይፈቱ የታገዱ ቢሆንም መድረኩን በመጠቀም ሃገሪቱ ካሉባት ዘርፈ ብዙ ታሪካዊ ችግሮች መሃል አንዱን እንኳን መቅረፍ ከተቻለ ይህም ጥቅም መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ . ይሁን እንጂ፣ «አገራዊ ምክክር» በሚል መጠሪያ የሚካሄደው ይህ ሂደት፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ባለው ግጭትና የፖለቲካ ውጥረት እንዲሁም ከትግራይ ጋር ባለው አዲስ የጦርነት ስጋት ምክንያት "ችግሮችን በውይይት የመፍታት" አቅሙንና ቅቡልነቱን አጥቷል። ውጤቱ አስቀድሞ የተቃኘ የሚመስለው ይህ መድረክ፣ የሚወሰኑት ዋና ዋና ውሳኔዎች ከመንግሥት ፍላጎትና ቀይ መስመሮች የማይወጡ በመሆናቸው፣ አወቃቀሩ ለገዢው ፓርቲ የሥልጣን ማጽኛ ከመሆን የዘለለ መዋቅራዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም። በመሆኑም በብዙዎች ዘንድ ኢትዮጵያ ዛሬ «ከእውነተኛ ምክክር» ይልቅ «የዕድል መክሸፍ» የሚታይበት አሳዛኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች የተባለው ለዚሁ ነው። . ይህም በመሆኑ ሂደቱ የሚያስከትለው መዘዝ ለሀገሪቱ ተስፋ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ነው። በመሆኑም፣ አገር ወዳድ ዜጎች በሙሉ አሁን ያለው መድረክ በቀጣይ እውነተኛ፣ ሁሉን አካታች እና ነፃ ሌላ የሽግግርና የእርቅ መድረክ ይኖር ዘንድ እንደ መሸጋገርያ ለመጠቀም በጋራና በግልጽ ተፅዕኖ ማሳደር ይኖርባቸዋል እላለሁ። . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
🚩 ምክክር ወይንስ መምከን ?፦ የብልፅግና «አገራዊ ምክክር» ፈተናዎች እና የመዋቅራዊ ለውጥ አስፈላጊነት ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ጡፌል ዘሃበሻ (ከመናገሻ) . መግቢያ ------- ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑ መድረክ ላይ የተስተዋሉ አያሌ ጥያቄዎችን የሚያስነሱ ሂደቶች እና ድራማዊ ክስተቶች ናቸው። 1. ሰሞኑን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፦ "እዚህ አዳራሽ ዉስጥ የክልል ባለሥልጣናት፣ የከተማ ከንቲባዎች እና ሚንስትሮች አብረውን ሙሉ ቀን ይገኛሉ፤ ነገር ግን መገኘታቸው እንደ ማንኛውም ተመካካሪ በስነ-ስርዓት ቁጭ ብለው እንዲመካከሩ እንጂ ሥልጣናቸውን ወይንም ጉልበታቸዉን ሊያሳዩን አይደለም!..." ሲሉ ያደመጥናቸው ንግግር፣ የመድረኩን ነፃነት እና የባለሥልጣናቱን የፖለቲካ ተፅዕኖ በተመለከተ ከፍተኛ ሥጋት እንዲፈጠር አድርጓል። . 2. አጀንዳ በተያዘበት የሙስሊሙ መብት ጉዳይ ላይ በሙስሊም ስም የተሳተፉ የብልፅግና አፈ-ቀላጤ የሰጡትን ተጻራሪ አስተያየት ስንመለከትም፦ "ለመሆኑ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ይህንን መድረክ እውነተኛ የውይይት መድረክ አድርጎ ቆጥሮታልን? የተሳተፉትስ አንዳንድ ተወካዮች የጠቅላላውን ማኅበረሰብ እውነተኛ ድምፅ ያንፀባርቃሉ ወይስ የመንግሥት ምርጫዎች ናቸው?" የሚሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን እንድንሰነዝር ያደርገናል። . 3. በሌላ በኩል ደግሞ፣ መድረኩ ላይ ከተሳተፉት ሌሎች ማህበረሰቦች አንጻር ጥቂት የሚባሉ የተወሰኑ ሙስሊሞች ጥያቄዎቻቸዉን ይዘው በመድረኩ በመገኘታቸው ብቻ በሂደቱ ላይ ገንቢ ጥያቄ ከማንሳት ይልቅ፣ አጋጣሚውን ማኅበረሰቡን ለማጠልሸትና የጥላቻ ንግግሮችን ለማስፋፋት የተጠቀሙበትን በተለይ ጽንፈኛ "ጸረ ሙስሊም" ወገኖችን ዘመቻ ስንመለከት፣ የችግሩን መሠረታዊ ጉድለት በግልጽ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። . እውነተኛ የምክክር አስፈላጊነት፦ -------- ለዘመናት የተከማቹ መዋቅራዊ ስብራቶችን ለማቃናት፣ የታሪክ በደሎችን በሽግግር ፍትሕ ለመፈወስ እና የአገሪቱን የወደፊት ፖለቲካዊ ዕጣ-ፈንታ ለመወሰን እውነተኛ የብሔራዊ ምክክር መድረክ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አምናለሁ። የታሪክ ቁስል የሚድነው፣ የፍትሕ መጓደል የሚታረመው እና የዜጎች የባለቤትነት ጥያቄ እውነተኛ ምላሽ የሚያገኘው መላው የሀገሪቱ ሕዝቦችና ባለድርሻ አካላት በጋራ የዉይይት ማዕድ ዙሪያ ሲሰበሰቡና በአንድነት እና በልዩነታቸው ዙሪያ በግልጽና በነፃነት ሲወያዩ ብቻ ነው። . ሆኖም ግን አሁን እየተካሄደ ያለው ሂደት የምክክር ኮምሽነሩ እንዳሉት በባለሥልጣናት ጣልቃ-ገብነት እና በካድሬዎች አማካኝነት ይፋዊውን መስመሩን በመከላከል አዝማሚያ የተሞላ በመሆኑ፣ ከፍትሐዊና አካታች መድረክነት ይልቅ ቅቡልነትን ለማግኘትና ፖለቲካዊ አላማን ለማሳካት የሚደረግ ጥረት አስመስሎታል። ይህም፦ "ኢትዮጵያ እውነት እየመከረች ነው ወይስ በሂደቱ ምክንያት አገራዊ እድሏ እየመከነ ነው?" የሚል ጥልቅ ሥጋት እንድናነሳ ያስገድደናል። . ለዚህ ሥጋት ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ------------ 1. የኮሚሽነሮቹ አሰያየም እና የገለልተኝነት ጥያቄ፦ የኮሚሽኑ የመጀመሪያውና መሠረታዊው ጉድለት የአወቃቀሩ ሁኔታ ነው። ኮሚሽነሮቹ የተመረጡበት ሂደት በገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ሥር እንደዋለ የሚነሱት ቅሬታዎች ከፍተኛ ናቸው። ጎልተው የወጡ ዋና ዋና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች፣ የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች እና ነፃ ምሁራን በበቂ ሁኔታ ከሂደቱ መገለላቸው፣ የመድረኩን ገለልተኝነትና ነፃነት ገና ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል፤ ገለልተኝነት በጎደለበት ሁኔታ የሚደረግ «ብሔራዊ ምክክር» ደግሞ የሚጠበቀውን ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይችላል ተብሎ አይጠበቅም። . 2. የታሪክ ቁርሾዎችን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል፦ ለሕግ የበላይነትና ለፍትሕ በቂ ትኩረት በማይሰጥ ሥርዓት ውስጥ አገራዊ ችግሮችን በቅንነት ለመፍታት ያለው ቁርጠኝነት አጠራጣሪ ነው። ይልቁንም፣ ታሪካዊ ቁርሾዎችን አሁናዊ የፖለቲካ ጥንካሬ ማጠናከሪያ በማድረግ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የማጋጨቱ አካሄድ አሁንም ድረስ የብዙ ዜጎችን ሕይወት ለህልፈት እየዳረገ ይገኛል። ልዩነቶችን ከመሠረቱ በቅንነት ከመፍታት ይልቅ ለጊዜያዊ ሥልጣን ማጽኛ የመጠቀም አዝማሚያ ባለበት ሁኔታ፣ ከዚህ ሂደት ዘላቂ አገራዊ መፍትሔ መጠበቅ እጅግ አስቸጋሪ ነው። . ይህንን እውነታ ይበልጥ የሚያጠናክረው ራሳቸው ጠ/ሚንስትሩ በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እና የፖለቲካ ኃይሎችን ያገለለ፣ አልፎም ማስፈራራት የተሞላበት ንግግር ማድረጋቸው ነው። ይህም የመድረኩን ጅማሮ እንኳን ቢያንስ በንግግራቸው ገለልተኛ እና ሁሉንም የሚያቅፍ ማድረግ እንዳልተቻለ የሚያሳይ ነው። ለዚህም ነው ሂደቱ የሕዝብ ውይይት ከመሆን ይልቅ የመንግሥትን ፍላጎትንና ፖለቲካዊ እቅድን ብቻ የሚያንፀባርቅ «የአንድ ወገን ትርኢት» ነው የሚሉ ትችቶች የበረቱበት። . 3. የዋና ዋና ክልሎች እና ባለድርሻ አካላት አሳታፊነት ማነስ፦ ሌላው ጎልቶ የሚታየው መዋቅራዊ ጉድለት የአገሪቱን ፖለቲካዊ ዕድል በጋራ የሚቀርጹ የሚሰኙት የኦሮሚያ፣ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች እውነተኛ እና ትርጉም ያለው ውክልና አለመኖሩ ነው። በነዚህ አካባቢዎች ሰፊ ግጭት እና ጥብቅ ፖለቲካዊ ውጥረት ባለበት ሁኔታ፣ መሬት ላይ ያለዉን እውነታ የሚያንፀባርቁ አካላት ሳይወከሉ በመንግሥት በተመረጡ ወገኖች ብቻ «ምክክር» ማካሄድ ሂደቱን ውጫዊና ተፅዕኖ የሌለው ያደርገዋል። . 4. የጽንፈኛ አካላት ምላሽ እና የውክልና ክፍተቶች፦ በሌላ በኩል ደግሞ፣ የተወሰኑ የሙስሊም ተወካዮች በመድረኩ በመገኘታቸው ብቻ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም የሙስሊሙን ማኅበረሰቡን ለማጠልሸት የሚደረጉ የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎች እጅግ አሳሳቢ ሆነው ታይተዋል። እነዚህ እኩልነትን የማይሹ ጸረ ሙስሊም የሆኑ ጽንፈኛ ወገኖች አጠቃላይ ሂደቱን የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ፍላጎት ማስፈጸምያ አስመስለው ለማቅረብ እና የማህበረሰቡን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለማጣጣል ይሞክራሉ። ነገር ግን ሙስሊሙን ወክለዋል ተብለው የተሳተፉት አካላት ቁጥራቸው ከሌሎች አንጻር ሲታይ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ስፋት አንጻር እጅግ አነስተኛ ነው። ይህም ህዝበ ሙስሊሙ ለዘመናት ሲያነሳው የቆየውን ቁመቱን ያማከለ ተመጣጣኝና ፍትሐዊ የውክልና ጥያቄ ክፍተት የሚያሳይ እንጂ የማኅበረሰቡን እውነተኛ ፍላጎት የሚያስፈጽም በቂ ውክልና አይደለም።
видео или голосовое, без подписи
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ "ባንዳ "ይመስል፣ "ባዳ"ን በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ በማድረጋቸው "ተጸጸቱ" ፣ ሌሎችም ስህተቱን እንዳይደግሙ አሳሰቡ! ~~~~~~~~~~~~ #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05 . ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ቲቪ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከኤርትራ ኃይሎች ጋር ያደረጉትን ተጋግዞ ትግራይን የመዉጋት ዘመቻን «ትብብር መሳይ የጥፋት መንገድ» ሲሉ የጠሩት ሲሆን፣ ይህንንም እርምጃ በመዉሰዳቸው «ኢትዮጵያ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥለን አልፈናል» በማለት "ተጽጽተውበታል"። አያይዘውም አሁን ደግሞ ሌሎች አካላት (ሕወኃት እና ፋኖ) "ከኤርትራ ጋር በማበርና እሳቸዉን በመግጠም" ተመሳሳይ የጥፋት መንገድ እንዳይከተሉ፣ ያ ካልሆነ ግን ዳግም ሌላ ጥፋት እንደሚያመጣ ተናግረዋል። . ጥያቄው «እርሶስ?» የሚለው ነው። . ልክ አሁን ሕወኃት እና ፋኖ አጀንዳቸው ምንም ይሁን ምን በሀገራቸው ጉዳይ ለሚያደርጉት ትግል ወይም ጦርነት ኤርትራን አጋር አድርገው ለማምጣት ያላቸው ፍላጎት ትክክል እንዳልሆነው ሁሉ፤ ያኔም ብልፅግና ከትግራይ ጋር ለነበረበት ጦርነት ኤርትራን አሰልፎ የገዛ ዜጎቹን በውጭ ሀገር ወታደሮች ማስደብደቡ ትክክል እንዳልነበረና ወደፊትም በሀገራችን ላይ ይዞት የሚመጣው ጣጣ ሰፊ መሆኑን ያለመሰልቸትና ማቅዋረጥ ስንናገር ነበር። . ለ17 ዓመታት ያህል አብሮት ሲታገል ለነበረው እና በስተመጨረሻም የኤርትራን ነፃነት ከነሙሉ የባሕር በር ጥርግ አድርጎ እንዲወስድ እገዛ ላደረገለት ሕወኃት እንኳን ያልተመለሰ፣ እንዲሁም መከታ ለሆነው የትግራይ ሕዝብ ያልራራው ሻዕቢያ፤ አንድ ቀን- ቀን የተገለበጠ እና ፖለቲካ መልኩን የቀየረ ዕለት ለሌላው ኢትዮጵያዊ የሚያዝንና ገደብ የሚያውቅ እንደማይሆን ስንሞግት -በምላሹ ብዙዎች የተለያዩ ስሞችን ስትሰጡን ነበር። ከእናንተ በላይ ለሀገር ተቆርቋሪ እንደሌለ አድርጋችሁ በመቁጠር እኛን ግን «በባንዳነት» እና በሌሎችም ስሞች ስትከሰሱ የነበራችሁ የ«ስካር ፖለቲካ» ተንታኞችና የስሜት ተገዢ ደጋፊዎች፤ አሁን ደግሞ ምንም ሳታፍሩ ወይም ስህተት መሥራታችሁን ሳታምኑ ከኢሳይያስ አፍቃሪነት ያለምንም ማጠንቀቂያ ወደ ጸረ ኢሳይያስነት የተቀየራችሁ ወገኖቻችን ከዚህ ከአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገራችን ጉዳይ ላይ ኤርትራን እስከጥግ በማስገባታቸው የተጸጸቱና ለተገዳዳሪውዎቻቸዉም "ባዳን በሃገራችን ጉዳይ በማስገባት የእኔን ስህተት አትድገሙ! " ያሉበት ከሚመስለው ቃለ-መጠይቅ ምን ተማራችሁ? ለማለት ነው! . ሀገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ እንጂ ጠ/ሚንስትሩ ያኔ የወሰዱት የጥፋት መንገድ ሃገሪቱ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ማለፉን በገሃድ ካመኑ ቀጣዩ እርምጃ ምን መሆን እንደነበረበት ሌላው አለም በሚገባ ያውቀዋል፡፡ የሆነው ሆኖ ኤርትራ ራሷን የቻለች ሀገር እንደመሆንዋ በብልጽግናም በኩል ሆነ በህወሃት ወይንም በፋኖ በኩል ሆና በሃገራችን ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ በፍጹም ተቀባይነት የለዉም! ይሄው ነው፡፡ . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
видео или голосовое, без подписи
ስፔንን የመበቀል ከበባ እና የጂኦፖለቲካ ምስጢራዊ ዳራ፡ የስፔን ቀውስ! ~~~~~~ #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05 . 1. አጭር መግብያ . የሞሮኮ እና የስፔን ባለሥልጣናት ሕገ-ወጥ ስደተኞች ድንበር ጥሰው ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ አጥብቆ የሚቆጣጠር ጠንካራ ስምምነት ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በቅርቡ በተሰራጨ ሐሰተኛ መረጃ (Fake News) ድንበሩ ክፍት መሆኑ በመነገሩ ብቻ በአንድ ጊዜ ከ 60,000 በላይ ስደተኞች በድንበር በኩል ወደ ስፔን ግዛት ለመግባት ከፍተኛ ሙከራ አድርገዋል። . ይህ ድንገተኛ እና ግዙፍ የተደራጀ እንቅስቃሴ ከተለመደው የስደተኞች ፍሰት ፍጹም የተለየ በመሆኑ፣ ጉዳዩን ከቀዝቃዛው ፖለቲካዊ ጦርነት እና ከዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጋር አያይዞ መገምገም ግድ ይላል። . 2. የጂኦፖለቲካ ትንተና፡ ከስደተኞች ማዕበል ጀርባ ያለው እውነት . ይህንን ክስተት ከላይ ከተጠቀሰው አተያይ እና ከወቅታዊው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር ስናስተያየው፣ ጉዳዩ ተራ የስደተኞች እሩጫ ሳይሆን በስፔን መንግሥት ላይ ያነጣጠረ ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ የፖለቲካ ሴራ መሆኑ ግልጽ ይሆናል። . የስፔን ገለልተኛና ደፋር አቋም:- ስፔን እስራኤል በጋዛ ሕዝብ ላይ እየፈጸመችው ያለው ጂኖሳይድ (ጭፍጨፋ) አጥብቃ በመቃወም ከአውሮፓ አገራት ለየት ያለ እና ገለልተኛ ከዛ ካለፈም ጋዛን የሚደግፍ ፖለቲካዊ አቋም ይዛለች። የፍልስጤምን ግዛት ሕጋዊነት በመቀበልም ከአሜሪካ እና ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ መስመሮች ፈቀቅ ማለት ችላለች። . የአሜሪካ እና እስራኤል ምላሽ:- ይህ የስፔን ፖለቲካዊ እርምጃ የዋሽንግተንን እና የቴል አቪቭን ባለሥልጣናት ያስቆጣ ሲሆን፣ ስፔንን "ሌላዉን ማስተማርያ -ለአርአያነት የሚሆን ቅጣት" ለመቅጣት እና መንግሥቱን ከህዝቡ ጋር ለማጋጨት የተለያዩ ጫናዎችን መፍጠር መጀመራቸው ግልጽ ነው። . የቀውስ ማቀጣጠያ ስልት:-የእስራኤል እና የአሜሪካ የልብ ወዳጅ መንግስት በሚያስተዳድራት በሞሮኮ በኩል የስደተኞች ማእበልን በድንገት በመልቀቅ የስፔን መንግሥት ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ድንገተኛ ጫና ውስጥ እንዲገባ ማድረግ፤ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ዋስትና እና ፀጥታ መንቀጥቀጥ ዐበይት ዓላማዎች ናቸው። ይህ ደግሞ በስፔን ዜጎች ዘንድ በመንግሥት ላይ እምነት ማጣት እንዲፈጠር በማድረግ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲነግሥ ያደርጋል። 3. ስንጠቀልለው . በሞሮኮ ድንበር ላይ የተከሰተው ይህ ድንገተኛ እና በውሸት መረጃ የተጠነሰሰ ሰፊ የስደተኞች ሙከራ፣ ከእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ጋር ተያይዞ ስፔን የያዘችውን ጽኑ አቋም ለመበቀል የተወሰደ የመሠሪ ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት አካል ነው። ዓለም አቀፍ ኃይሎች መንግሥታትን ለማሸበር እና የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም መረጃን እንደ ጦር መሣሪያ በመጠቀም ሕዝብንና መንግሥትን የማጋጨት ስልታቸውን የቀጠሉበት ሌላው ማሳያ ነው። . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
видео или голосовое, без подписи
ፈተና በመጣ ቁጥር 'ሂጃብ እና ኒቃብ ለብሳችሁ ተምራችኋል፤ አሁን ግን ሳታወልቁ አትፈተኑም!' በማለት ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት ደጃፍ የሚያስቀሩ፣ በተማሪዎች እድሜ እና እድል፣ በዜጎች መብትና በሀገር እድገት የሚቆምሩ አካላት እስከዛሬ የፈጸሟቸው ድርጊቶች ወንጀል መሆናቸው በግልጽ ሊታወቅ ይገባል። የሃገራችን የትምህርት ስርዓት ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ዜጎችን ለይቶ ማጥቅያና መበደያ መሆኑን ግምት ዉስጥ በመክተት፣ ይህንን ያረጀ እና ያፈጀ #የአፓርታይድ አካሄድ በትምህርት ስርዓቱ ዉስጥ ለማስቀጠል የሚተጉ መሰሪዎችን ከቢሮክራሲው ቆርጦ የሚጥል ጽኑ ህግና ስርዓት እስካልተዘረጋ እና በይፋ እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ፤ የምክክር ጉባኤው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ 'እንደ ስኬታማ ጉባኤ' ተቀባይነት ሊኖረው ፈጽሞ አይችልም። #RN05
"የትግራይ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ" ምንም ይሁን ምን፤ #የአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው አፓርታይዳዊ አያያዝ በሁሉም ዘንድ ሊወገዝ የሚገባው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑ። ከተማዋም በዘመናችን ያለ #ታሪካዊ_የጭቆና_ሙዚየም መሆኗን የማያረጋግጥ የምክክር ጉባኤ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው ፈጽሞ አይችልም።" ##RN05
ስለምክክሩ! የአምናውን ችግር ፈተን የዛሬውን ችላ ካልን፣ ነገያችን ዛሬ መሆኑ አይቀሬ ነው! ~~~~~~~~~~ . ጥንት የተበላሹ ነገሮች ዛሬያችንን ስላበላሹ ተቀምጠን መመካከርና ማስተካከል ግድ ሆኖብናል በሚል ሃገራዊ ምክክር ተይዟል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ አሁን በሀገራችን ውስጥ የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች ችላ የተባሉ ይመስላሉ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለነገ የምንተወው ትልቅ እዳ ነው። ስለዚህም ምንም እንኳ የረፈደ ቢመልም የምክክሩ መድረክ በታሪካዊና በቆዩ ችግሮች ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም። . አሁን ሀገሪቱ የገባችባቸውን አጥፊ ጦርነቶችና ሁለገብ ቀውሶች አብሮ መቃኘት ይገባል። ያለፉትን ችግሮች ብቻ መፍታት ለጊዜው እፎይታ ሊሰጥ ቢችልም፣ የዛሬዎቹን ሳንፈታቸው ስንቀር ግን ለነገው ትውልድ ሌላ ከባድ ጫና እና ማነቆ እንተዋለን። . በአጭሩ፤ ነገያችን የዛሬ ድግግሞሽ እንዳይሆን ማሰቡና መፍትሔ መፈለጉ ዛሬ ሊዘነጋ የሚገባው ቁምነገር አይደለም! ይህም የሚሆነው በዋናነት በግልጽነትና በሙሉ አካታችነት ነው! #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05 . ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
ተወያይቶ መቀየር ያለበት ነገር ካለ ተስማምቶ መቀየር፣ ማስተካከል ያለ ነው፡፡ ነገር ግን ተወያይህ ለአቅመ ጡረታ የደረሰ ሁሉንም ያየ ሰው ነው ብለህ ስታበቃ ባንዲራን በሚያክል ጉዳይ ምክንያታዊ ሆኖ መነጋገር እንደሚቻል ተስፋ ሰንቀህ ፣ለመግብያ የሚሆን ታሪካዊ ዳራ ለማንሳት እየተዘግጋጀህ ሳለ ሰዉየው በድንገት "ይህ ባንዲራችን መሃል ያለው እኮ አምባሻ ነው!" ብሎ ሲያፈነዳው ፣ የዉይይት አፒታይትህ ጠፍቶ ዉስጥህ ሲያጥወለዉልህ፣ አካባቢዉን ለቆ ከመዉጣት ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለህ ስታምን የሚሰማህ ስሜት እጅግ መራር ነው፡፡ . ጎበዝ ሲጠሉም ሆነ ሲወዱ በልክና በምክኛት ቢሆን ለማለት ነው፡፡ . እርሶስ ለዉይይት ብቁ ነው ብለው ካሉት ሰው ጋር ተቀማምጠው ሲያበቁ የዚህ አይነት መራር አጋጣሚ ገጥምዎታልን? ምን አደረጉ? አሁንስ ቢገጥምዎ ምን ያደርጋሉ? ይጻፉልን! #የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለRN05 ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFive
የውክልና ጉዳይ!! ~ #የቢላል_ትዝብት . ዛሬ ፌስቡክ ውስጥ ላይ ታች ስል አንድ በፎቶ የታጀበ ጽሁፍ ተመለከትኩ። ጽሁፍ አንዲህ ይላል፤ ህወሃት ህዝብ ስታነሳሳ በፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ትግራይ ውክልና አላገኘችም እያለች ወቀሳ ታሰማለች፣ ነገር ግን ትግራይ ውስጥ መንግሥት ስትመሰርት ከሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ የክልሉ ተወላጅ ሙስሊሞችን ሙሉ በሙሉ ያገለለ ካቢኔ ታቋቁማለች።ሲል የህወሃትን ግብዝነትና ፋሽስታዊ ተክለሰውነት ለማሳየት ይሞክራል። አስገራሚው ነገር ታድያ ከጽሁፉ ሥር የሠፈሩት ኮሜንቶች ናቸው። በሚገርም መልኩ ሙስሊም ያልሆኑ (ከሥማቸው ተነስቼ ነው) አስተያየት ሰጪዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የሰጧቸው አስተያየቶች አሉታዊያን ናቸው። ካቢኔ ነው እንጂ መጅሊስ መሰለህ እንዴ የሚያቋቁሙት፣ መመዘኛው ችሎታ ነው እንጂ ሃይማኖት ነው እንዴ፣ አገር የሚመራው በእውቀት ነው እንጂ በሸሪዓ አይደለም እና የመሳሰሉ ይዘቶች ያሉዋቸው ናቸው። በአጠቃላይ ምንም እንኳን የጽሁፉ ዋና ጉዳይ የሚያተኩረው በውክልና ላይ ቢሆንም አስተያየት ሰጮዎቹ ግን የውክልና ጥያቄን ወደ ችሎታ እንዳወረዱት ነው የሚታየው። ለነገሩ ይህ አቀራረባቸው ሁሌም ቢሆን ቢያንስ አቋም ነው ብለን ልንይዝላቸው እንችል ነበር፣ ነገር ግን በተደጋጋሚ እንዳየነው ይህ አመለካከታቸው የሚንጸባረቀው የእነሱን ኢ-ፍትሃዊ ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው። . የብልጽግና መንግሥት ሥልጣን ላይ ከመጣ ጊዜ አንስቶ በርካታ የኦርቶዶክስ አክቲቪስቶች ብልጽግና ኦርቶዶክሱን ከሥልጣን ያገለለ መንግሥት ነው በሚል በተደጋጋሚ ሲወቅሱት ተመልክተናል። ከእነሱ ውጪ ማንም ሌላ አካል ሥልጣን ላይ የመጣ አንደሆን የሚይዙ የሚጨብጡትን ያጣሉ። ከአሥር ባለሥልጣናት መካከል 3 ሙስሊም የተገኘ እንደሆነ ይሄማ የሙስሊም ካቢኔ ነው ሲሉ ይፈርጁታል።ይህ ሃቅ በየቦታው በተደጋጋሚ የታዘብነው ነው። በመንግሥት ይሁን በግል መስሪያቤቶች አንድ ሁለት ሶስት ሂጃብ የለበሱ ሴቶችን ያዩ እንደሆን “ቢሮ ሳይሆን መስጊድ የገባሁ ነው የመሰለኝ” ማለት ይጀምራሉ። የትም ቦታ ላይ ይሁን እነሱ የመሰለ ካልሆነ በስተቀር ማየት አይፈልጉም። በምሳሌ ላስረዳ። አንድ ወዳጄ የሆነ ሙስሊም የአንድ ድርጅት አስተዳዳሪ የሚመራው ድርጅት ውስጥ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ቀጠረ። ወዲያው ሰራተኛው ማጉረምረም ጀመረ። መስሪያቤቱን በእስላም ሞለው እያሉ ማሾካሾክ ጀመሩ። ሹክሹክታው እየበዛ ሲሄድ ይሄ ወዳጄ ቁጥራቸው 30 የሆኑትን የመስሪያቤቱ ሠራተኞች በሙሉ ሰበሰበና “በሉ ሙስሊሞች የሆናችሁ እጃችሁን አውጡ” አለ። ወዳጄን ጨምሮ አምስት ሰራተኞች እጃቸውን አወጡ።ይሄ ነው እንግዲህ የበዛባቸው! . ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊሙና ከኮሎኒያል (ቅኝ ገዢ) አስተሳሰብ መፋታት የተሳነው ክርስቲያን እንዴት የአንድ አገር ዜጋ ሆኖ መቀጠል እንደሚችል ማሰብ ይከብዳል። እርስ በርስ አንዋደድም፣ አንከባበርም። የጋራ አጀንዳም የለንም። በብዙ ብሄራዊና አለም አቀፋዊ ክስተቶች ዙርያ የኢትይዮጵያን ጥቅም ያማከለም ሆነ በጋራ እሴት ላይ የተመሰረተ አቋም አንይዝም። ሁለታችን በጋራ የምንደግፈውም ሆነ የምንቃወመው ነገር ኢምንት ነው። ለምሳሌ እንደ አህመደል ነጃሺ፣ ቢላል ኢብኑረባህ፣ ኡሙ አይመንን የመሳሰሉ ጉምቱ ስብእናዎች አጉልቶ ማውጣት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም እንደሚያስገኝ ግልጽ ነው፣ ነገር ግን ይህ እንዲሆን ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ አይፈልግም። አለም አቀፋዊ ክስተቶች የወሰድን እንደሆነ እስራኤል በፍልስጤም ህዝቦች ላይ እያደረሰች ያለውን የዘር ፍጅት ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ከማውገዝ ይልቅ ከእስራኤል ጎን መቆማቸውን በይፋ ሲያውጁ ነው የተመለከትነው። . ቀደም ብዬ እንዳልኩት በዚህ ሁኔታ እንዴት አብረን መዝለቅ እንደምንችል አላህ ነው የሚያውቀው። እስከ አሁን ባለው የቆየነው በመካከላችን ያለው የሃይል ሚዛን እጅግ በጣም ያጋደለና በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል ያለው መስተጋብር በጣም የላላ ስለነበር ነው። አሁን ግን ያ ነገር ተቀይሯል። የሃይል ሚዛኑም ሆነ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል ያለው መስተጋብር እየተቀራርረበ መጥቷል። ከእንግዲህ እስከ አሁን በነበረው ሊቀጥል አይችልም።ወይ ተከባብረንና በፍትሃዊ መንገድ ተከፋፍለን እንቀጥላለን አለበለዚያ ማለቂ ወደማይኖረው ግጭት ውስጥ እንገባለን። ምርጫው የእናንተ ነው ክርስቲያኖች፤ ምክንያቱም ለሃገሪቱ መፍረስም ሆነ መጠገን በዋነኝነት ሃላፊነቱ የምትወስዱት እናንተ ናችሁና ! . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFi
видео или голосовое, без подписи
🚩የኦርቶ-አማራ ኤሊት ችግር! ~~~~~~~~~~ #የቢላል_ትዝብት . የኦርቶ-አማራ ኤሊት ችግሩ ኢትዮጵያን አስመልክቶ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመቀበልና በመሬት ላይ ባለው እውነታ ውስጥ ቁመናውን የሚመጥን ቦታ አለመፈለጉ ነው። አሁንም ኢትዮጵያን የሚያያት በብቸኛ ባለቤትነት አይን ነው። እርሱ የፈቀደለት ካልሆነ በስተቀር ሌላው ኢትዮጵያን አስመልክቶ በሚደረግ ማንኛውም ሁኔታ ላይ የመሳተፍ መብት የለውም። የኦርቶ-አማራ ኤሊት ያዘጋጀውና የሚመራው ስብስብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያ የሚፈይድ እንቅስቃሴ የለም። የኦርቶ-አማራው ኤሊት ያላዘጋጀውና የማይመራው ስብስብ ”የሙስሊም አሸባሪዎች” ስብስብ ነው፣ ምንም እንኳን አብዛኛው ተስብሳቢ ሙስሊም ባይሆንም። . ሀገሪቱ ”ሀገራዊ ምክክር እያደረግሁ ነው!” ማለቷ ይታወቃል። በዚህ ሀገራዊ ምክክር ላይ ከሀገር ውስጥም ከውጪ ሃገርም የተወከሉ በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገኙ ነው የሚነገረው። የአብዛኛው ተሰብሳቢ ሃይማኖት ቢመረመር አብዛኛው ተሰብሳቢ ሙስሊም እንዳልሆነ ለመገመት ጠቢብ ወይንም ነብይ መሆንን አይጠይቅም። ነገር ግን ምክክሩን በማጠልሸት ሂደት ውስጥ የኦርቶ-አማራው ኤሊት በሶሻል ሚዲያ ላይ ስማቸውን ደጋግሞ የሚያነሳው ሙስሊሞች የሆኑ ተሰብሳቢዎችን ነው። ይህ ያለምክንያት የሆነ አይደለም። በኦርቶ-አማራው ሥነ ልቦና ውስጥ የተከተበው የሙስሊሙን የሃገር ባለቤትነት እውቅና የነፈገው ህሊና በቀላሉ ይገዛዋል በሚል እምነት ነው። . ኢትዮጵያ ግማሹ ህዝቧ ሙስሊም ቢሆንም፣ በሃገሪቱ አብዛኛው የቆዳ ስፋት ላይ የሠፈሩት ሙስሊሞች ቢሆኑም የኦርቶ-አማራው ኤሊት ሃገሪቱን የክርስቲያን ሃገር አድርጎ ለማቆየት በሚያደርገው ያልተቋረጠ ትግል ሳቢያ ሀገሪቱ ሠላም ርቋት ትገኛለች። ኢትዮጵያ እንደ ህዝብ የጋራ የሆኑ እሴቶቹን ነቅሶ አውጥቶ በእነዚህ የጋራ እሴቶች ዙርያ ሃገራዊ አንድነት እንዳይፈጥር ትልቁ እንቅፋት ይህ የኦርቶ-አማራ ኤሊት ነው። ይሄ ኤሊት የያዘው “ ኢትዮጵያ የብቻዬ” አካሄድ የትም እንደማያደርሰው በማያዳግም ሁኔታ እስከሚረጋገጥለት ድረስ ከዚህ ከያዘው አፍራሽ አካሄድ የሚመለስ አይደለም። . አህመዲን ጀበል እና አብዱል ጀሊል ሸህ አሊ ካሳና ጨምሮ በርካታ የሙስሊም ምሁራን የሙስሊሙን የአገር ባለቤትነት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለማስረዳት ብዙ ታግለዋል። ትግላቸውም ተራውን ህዝብ በማስተማርና በማንቃት ረገድ መልካምና ፍሬያማም ውጤትን ያመጣ ነው። ነገር ግን የእነርሱ አካሄድ አጀንዳ ይዞ የሚንቀሳቀሰውን የኦርቶ-አማራ ኤሊት እኩይ ትርክት የሚያመክን አይደለም። የኦርቶ-አማራው ኤሊት ትርክት መሰረቱ ሳይንስ ስላልሆነ በሳይንስ አይሸነፍም። ኦርቶ-አማራው ይህንን የበሬ ወለደ ትርክት የተፈጠረውም፣ የፋፋውም በሃገሪቱ ፖለቲካና በሀገር አስተዳደር የነበረውን አቅም ተጠቅሞ ነው። እንዲህ አይነቱ ትርክት ቀጣይነት ሊኖረው የሚችለው ደግሞ የሃይል አለመመጣጠኑ ባለበት እስከቀጠለ ድረስ ብቻ ነው። ለዚህ ነው ይህ ኤሊት የሙስሊሙን አገራዊ ፖለቲካዊ ተሳትፎ በጥርሶቹም፣ በጥፍሮቹም ጭምር እየተዋጋው ያለው። . ይህንን ከምክንያታዊነት የተፋታ ኤሊት ለመዋጋት ታዲያ ሳይንስና ታሪክን መታጠቅ ብቻ በቂ አይሆንም። ሙስሊሞች በሃገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ በማጎልበት ተመጣጣኝ አቅም መፍጠር ይኖርባቸዋል። ተመጣጣኝ አቅም ለመፍጠር በበቂ ሁኔታ መደራጀትና የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ያስፈልጋል። የሙስሊሙ ግብ መሆን ያለበት ሙስሊሙ በሃገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚኖረው ቦታ በግለሠቦችና በመሪዎች በጎ ችሮታ የሚለገስ ሳይሆን ህጋዊ መሠረት ያለው እንዲሆን መሆን ይኖርበታል። . የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ? የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን! ============= . ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ https://t.me/RNZeroFi
видео или голосовое, без подписи