tgindex
Rafidim Youth Academy Public Relation Channel

Rafidim Youth Academy Public Relation Channel

Статистика

"ተማሪዎች ላይ መስራት አገር ላይ መስራት ነው!"

Последний пост
16 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 087
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 567
20 постов
Вовлечённость
144,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ለፈረንሣይ ቅርንጫፍ የአንደኛ ደረጃ እና ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን እንዲሁም ለቂርቆስ ቅርንጫፍ ቅድመ መደበኛ ወይም ኬጂ ትምህርት ቤታችን ቤተሰቦች በሙሉ 👇 በሁለቱም ቅርንጫፍ የቅድመ መደበኛ እና የፈረንሳይ ቅርንጫፍ ደግሞ የአንደኛ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ በይፋ መጀመሩን ለማብሰር እንወዳለን ። በመሆኑም እንደሁልጊዜው ቀድመን የምንመዘግበው ነባር ተማሪዎቻችንን በመሆኑ ነባር ተማሪዎች ቀድማችሁ መመዝገብ አለባችሁ ። ማሳሰቢያ ፦ ለነባር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀነ ገደቡም ከነገ 10 /11/ 2018 ዓ.ም እስከ 15 / 11 / 2018 ዓ.ም ድረስ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ብቻ መጥታችሁ መመዝገብ አለባችሁ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በኋላ ላይ ለሚፈጠረው መጨናነቅም ሆነ የቦታ እጥረት ክፍተት ትምህርት ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ። መልካም ምሽት

  • 4 июл.1 6491

    ዛሬ የትምህርት ቤታችን የራፊዲም ታላቅ ድግስ ተደርጓል ።  👏👏👏👏👏👏👏 ቤተሰቦቻችን ይህንን ደስ የሚል እና የሚያኮራ ጉዞ ከእናንተ ጋር እያደረግን ስለሆነ እጅግ ደስተኞች ነን ። ሃገርን የሚሰራ ትውልድ የመቅረፅ ትልቅ ሃላፊነትን እየተወጣን እንዳለን እናምናለን ። ለዚህም ደግሞ ዛሬ ያስመረቅናቸው ህፃናቶቻችን እና በዬደረጃው ጀግና ተማሪዎች ሆነው አንደኛ የሚወጡት አዳጊ ልጆቻችን ፤  ከውጤትም በላይ የሆነው ደግሞ የተማሪዎቻችን ግብረ ገብነት ስኬቶቻችንን የምንለካባቸው ግልፅ ማሳያዎች ናቸው ። ዛሬ በአምባሳደር ቲያትር ቤት ከ500 በላይ ቤተሰቦቻችን የታደማችሁበት ፤ ኢትዮጵያን በትንሽ መድረክ ተወክላ ያዬንበት ቀን ነው ። በውዝዋዜ ፣ በድራማ በመዝሙሮች ቀናችን አምሮ ውሏል ። የታሪካዊ አርበኞች ታሪክ በልጆቻችን ጣፋጭ አንደበት ሲወሳ ነበር ። ዛሬ በሁለቱም ቅርንጫፍ 137 የኬጂ ተማሪዎችን መርቀን ወደ አንደኛ ክፍል ያሸጋገርንበት ዕለትም ነው ። ወደፊታችን ብሩህ መሆኑንም የትምህርት ቤታችን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ግርማ የደረስንበትን ከፍታ ገልፀውልናል ። በዚህ መርሃግብር በዓመቱ በነበረው የክፍል ለክፍል ወድድር ከዬክፍላቸው አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቁትን የምስክር ወረቀት የሰጠን ሲሆን ከሁለቱም ቅርንጫፍ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡትን ተማሪዎች ሽልማት ሸልመናል ። በቀጣዩ  ዓመት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለመሆን ዛሬ ያስመረቅናቸው የኬጂ ተማሪዎቻችንም በቀጣይ ዓመት እንግዳ ነገር እንዳይሆንባቸው እና በደንብ እንዲላመዱት ብለን በማሰብ በዚህ ዓመት የክፍል ለክፍል ውድድር ማድረጋችን ይታወሳል ። በዚህም በዬቅርንጫፉ አንደኛ የወጡት ተማሪዎች ተሸልመዋል ። በዓመቱ ትምህርት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በመሆን በዬክፍሉ ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የወርቅ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ ሸልመናል ። ከአጠቃላይ ክፍሎችም አንደኛ በመሆን በሁለቱም ቅርንጫፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎቻችንን ደግሞ የዋንጫ ሽልማት ሸልመናል ። በዚህ አጋጣሚ እነዚህ በሁለቱም ቅርንጫፍ አንደኛ የሆኑት ተማሪዎቻችን ሴቶች ናቸው ። ወደፊት ለሃገራቸው ብዙ እንደሚያበረክቱ እናምንባቸዋለን ። እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን ! ራፊዲም ትምህርት ቤት የእውቀት ቤት !

  • 3 июл.1 5502

    ነገ በዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን የዓመቱ ስኬታማ የመማር እና የማስተማር ሥራችንን እና የድካማችንን ፍሬ የምናይበት ዕለት ነው ። በእርግጥ የራፊዲም ጥረት ፤ ትጋት እና ሂደት የዓመት ሳይሆን የዓመታት መሆኑ እርግጥ ነው ። ነገእንደ አምና እንደ ታች አምናው የቅድመ መደበኛ ተማሪዎቻችንን ልናስመርቅ ፣ የደረጃ ተማሪዎቻችንን ልንሸልም ፣ መምህራኖቻችንን ልናመሰግን ብሎም ዳግም ለሌላ አዲስ ዓመት እና አዲስ ቀን ልንዘጋጅ የዓመቱን ሥራችንን ልንዘጋ ነው ። ነገ ታላቁ ድግሳችን እንደ አምናው ሁሉ በተመሳሳይ በአምባሳደር ቲያትር ቤት ይደረጋል ። ታዲያ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ጠዋት 1 : 30 በስፍራው በመገኘት ያለንን ሰዓት በአግባቡ እንድንጠቀም እናሳስባለን ። እንኳን ለዚች ቀን አደረሰን 👏

  • 2 июл.1 5462

    በፈረንሳይ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤታችን የክልል አቀፍ ፈተና ካስፈተንናቸው የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች 97 % ማሳፋችንን እንገልፃለን ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ደግሞ እንደተለቀቀ የምናሳውቃችሁ ይሆናል ።

  • 29 июн.1 7077

    👉 እንደሚታወቀው የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል የክልል አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ተለቋል ። ታዲያ እኛም በቂርቆስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤታችን 100 % ተማሪዎቻችንን አሳልፈናል ። ከስድስተኛ ክፍል 51 ተማሪዎችን ከስምንተኛ ክፍል ደግሞ 42 ተማሪዎችን አሳልፈን እጅግ ደስ ብሎናል ። እንደ ትምህርት ቤትም ታላቅ ኩራት ይሰማናል ። 👉 ታዲያ በዚሁ አያይዘን የምናስታውሳችሁ የፊታችን ቅዳሜ በ27 / 10 / 2018 ዓ.ም የትምህርት ቤታችን የዓመቱ ትምህርት የመዝጊያ መርሃግብር በደማቅ ሁኔታ በአምባሳደር ቲያትር ቤት ይደረጋል ። የደረጃ ተማሪዎች እና የጥያቄ እና መልስ ውድድርን ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ሁናችሁ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በዕለቱ ከጠዋቱ አንድ ተኩል ላይ እንድትገኙ እያሳስባለን ። መልካም ምሸት 👏

  • በዓመቱ በተደረገው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ከ1 እስከ 9 የወጡ ተማሪዎቻችን ናቸው ።

  • без подписи

  • የተማሪዎች ሙዝ የመብላት ውድድር እጅግ አዝናኝ ነበር ።

  • без подписи

  • без подписи

  • 👉 እንደሚታወቀው በሁለቱም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቻችን የሁለተኛውን መንፈቅ ዓመት የአጋማሽ ፈተና ሰጥተን ጨርሰናል ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት በሁለቱም ቅርንጫፍ ለተማሪዎቻችን የፈተና ወረቀቶቻቸውን መልሰናል ። 👉 ዛሬ ደግሞ በፈረንሳይ ቅርንጫፍ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሸጋገሩትን የኬጂ 3 ተመራቂ ተማሪዎችን ምክንያት በማድረግ የመዝጊያ እና የሽኝት ፕሮግራም አድርገናል ። እጅግ ደስ የሚል ቀን አብረናቸው አሳልፈናል ። ተመልከቷቸው 👇

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 👉 ዛሬ በቂርቆስ ቅርንጫፍ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን  የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ እና የደረጃ 2 ተመራቂ ተማሪዎች የቅድመ አንደኛ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን በማስመልከት እጅግ ደማቅ ዝግጅት አድርገን ከልጆቻችን ጋር ቆንጆ ቀን አሳልፈናል ። በተለይም ተመራቂ ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን አመስግነዋል ። ይህን ማዬት ደግሞ ለእኛ እጅግ የሚያኮራን ነገር ነው ። 👉 በመጨረሻም የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና የፊታችን ሰኞ በ15 / 10 / 18 ዓ.ም  የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን ወላጆች በተሰጣችሁ ፕሮግራም መሰረት ልጆቻችሁን በማገዝ ለፈተና ብቁ ሆነው እንዲቀርቡ እንድታደርጉ መልክታችንን እናስተላልፋለን ። ፎቶዎች አሉን መልካም ምሽት

  • በነገው ዕለት በሁለቱም ቅርንጫፍ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤታችን የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የክልል አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እንደሚወስዱ ይታወቃል ። በመሆኑም ተማሪዎች ነገ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ ዩኒፎርማችሁን ለብሳችሁ እንዲሁም ምሳ እቃችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን ። ከዚሁ ጋር ተያዬዞ ለፈተና የሚያስፈልጓችሁን እርሳስ ላጲስ ፣ መቅረጫ እንዲሁም የትምህርት ቤት መታወቂያ እና የመፈተኛ አይዲያችሁን እንዳትረሱ እናሳስባለን ። መልካም ምሽት

  • 16 июн.1 4921

    без подписи

  • 16 июн.1 4402

    ዛሬ በቂርቆስ ቅርንጫፍ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤታችን የዓመቱ የመጨረሻ የጥያቄና መልስ  የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ተከናውኗል ። ታዲያ ይህን / ይችን አሸናፊያችንን ለይተን ያወቅን ሲሆን ማን እንደሆነ ግን በዓመቱ የመማር ማስተማር ሥራችንን መዝጊያ በምናደርግበት ደማቅ መርሃግብር ላይ የምንገልፅላችሁ ይሆናል ። የተወዳዳሪዎችን ፎቶ ግን ከታች እንደሚከተለው እናጋራችኋለን 👇 መልካም ምሽት