tgindex
Save Amhara Fano 💚💛❤️

Save Amhara Fano 💚💛❤️

Статистика

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
17
Всего постов
135
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
794
0 Са 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
106
40 постов
Вовлечённость
13,4%
к подписчикам
Постов в день
2,4
всогО 135
УпОПинаниК
1
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
75
1/48двое суток
85
1/72трое суток
92

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • йоС пОдписи

  • #ኢትዮጵያዊ ነን” በሚለው ብዙኃንና “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” በሚሉ ኦነጋውያን መካከል የሚካሄደው “አገራዊ ምክክር ጉባዔ” #ቢቢሲ ሾለ ምክክር ኮሚሽን ተብዮው መሰንበቻ ዛሬ ያወጣው ዘገባ፣ መድረኩን በየዋህነት “አገራዊ ምክክር” የሚደረግበት ገለልተኛ መድረክ ነው ብለው ለሚያምኑት ሁሉ፣ በውስጡ እየተፈጸመ ያለውን ዐቢይ አሕመድ መር ኦነጋዊ ሸፍጥ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። #ዘገባው እንደሚያሳየው፣ ምክክር ተብዮው እየተደረገ ያለው “ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን፤ አዲስ አበባም የኢትዮጵያ ዋና ከተማና፣ በአስተዳደሯም ራሷን የቻለች የሁሉም ኢትዮጵያውያን የፌዴራል ከተማ ትሁን” በሚሉ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን እና “አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚል አቋም በያዙ፣ ኢትዮጵያዊ አይደለንም በሚሉ ኦነጋውያን መካከል ነው። በእነዚህ ሁለት አቋሞች መካከል ያለው ልዩነት ተራ የሐሳብ ልዩነት ሳይሆን፣ መሠረታዊ የሀገር ማንነት ጥያቄ ነው። #ከሁሉም ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ፣ “አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚል አቋም የሚያራምዱትን፣ ኢትዮጵያዊ አይደለንም የሚሉትን የኦነጋውያን ቡድን የሚመራው፣ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየመው ዐቢይ አሕመድ የሚባለው ጉድ መሆኑ ነው። #በሌላው ዓለም፣ የአንድ ሀገር መሪ ዋናው ተግባር የዚያችን ሀገር የጋራ መሠረት፣ የጋራ ዋና ከተማና የጋራ ማንነት ማጠናከር ነው። ዐቢይ አሕመድ የሚባለው ኦነጋዊ ጉድ ግን፣ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ተሰይሞ የሚገዘግዛትን አገር “አላውቅሽም” ብሎ፣ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም፤ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሳትሆን የኦሮሞ ብቻ ናት፤ ስለሆነም የኦሮሚያ አካል መሆን አለባት” የሚለውን ኦነጋዊ ቡድን ይመራል። #መስፍን አርአያ የሚባለው የዐቢይ አሕመድ ከዳም በተደጋጋሚ ኮሚሽኑ “ተመካካሪዎች የሚመካከሩበት መድረክ ነው” ሲል ይሰማል። ይህ ከሆነ ታዲያ፣ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ ከተማ መሆኗን ዕውቅና ይሰጣት” የሚለው ጉዳይ፣ ከታች ጀምሮ በተካሄደው ምክክር ተብዮው ያልተነሳ፣ ያልተወያዩበትና “ተመካካሪዎቹ” ያልጠየቁት ጉዳይ ሆኖ ሳለ፣ ድንገት “ከበላይ የመጣ ሐሳብ” ተብሎ በቃለ ጉባኤ ውስጥ እንዴት እንዲገባ ተደረገ? #በእውነቱ ይህ ብቻ የምክክር ተብዮውን ኦነጋዊ ማጭበርበሪያ መሆኑን ለማሳየት ከበቂ በላይ ነው። ከታች ያልተነሳን ጉዳይ ዐቢይ አሕመድ ከላይ ስላወረደው ብቻ፣ ተመካካሪዎቹ ተብዮዎች ያልጠየቁትን እንደጠየቁ አስመስሎ፣ ያልተወያዩበትን እንደተወያዩበት አድርጎ በቃለ ጉባኤ ማስፈር ምክክር አይደለም። ይህ አብነት የሚያሳየው ምክክር ኮሚሽን ተብዮው ምድረካ ኦነጋዊ የማይጠረቃ ፍላጎትን በሕዝብ ስም ለማስፈጸም የተዘረጋ ኦነጋዊ ማጭበርበሪያ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ የተናገርነውን የሚያረጋግጥ ብቻ ነው። #የነ ዐቢይ አሕመድ ኦነጋዊ ቲያትር በዚህ ብቻ አያበቃም። አብዛኞቹ “ተመካካሪዎች” አዲስ አበባ ራሷን የቻለች የፌዴራል ከተማ ትሁን ሲሉ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ የኦሮሚያ ትሁን ማለታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል። ይህ እውነታ “አብዛኞቹ እንዲህ አሉ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ እንዲህ አሉ” ተብሎ በቃለ ጉባኤ እንዲሰፍር ሲባል ግን፣ “አብዛኞቹ” እና “የተወሰኑ” የሚሉት ቃላት እንዲጠፉና ሁለቱም “አማራጭ አንድ፣ አማራጭ ሁለት” ተብለው እንዲመዘገቡ ተደርጓል። #ይህ ተራ የቃላት ምርጫ አይደለም። ይህ ብዙኃኑን ከቃለ ጉባኤ ላይ የማጥፋት፣ ጥቂቶችን ወደ ብዙኃን ደረጃ የማሳደግ፣ እውነተኛውን የድምፅ ሚዛን ደብቆ የጥቂቶቹን ፍላጎት ሕዝባዊ አማራጭ አስመስሎ የማቅረብ ኦነጋዊ አሻጥር ነው። #ቁጥርን አጥፍቶ፣ የብዙኃኑንና የጥቂቶቹን ልዩነት ደብቆ፣ ሁለቱንም እኩል “አማራጭ” ብሎ መመዝገብ እውነታን መዝግቦ ማስቀመጥ አይደለም፤ እውነታን ቀይሮ ለተፈለገው ፖለቲካዊ ውጤት ማመቻቸት ነው። መስፍን አርአያ “ሁሉም ነገር በቃለ ጉባኤ ተይዟል” የሚለን ሆዳም ስለኾነ እንጂ ቁጥር እየተደበቀ፣ የብዙኃኑና የጥቂቶቹ ልዩነት እየተፋቀ፣ ሁለቱ እኩል አማራጭ እየተደረጉ ከተጻፈ፣ የእውነታ መዝገብ ሳይሆን እውነታ የተጣመመበት ድሪቶ መሆኑ ጠፍቶት አይደለም። #ከዚህ በተጨማሪ፣ ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ መሠረት፣ “አጠናቃሪዎች” የተባሉት ሰዎች ራሳቸው እንደ ተመካካሪ ሆነው ኦነጋዊ ሐሳብ እንደሚሰጡ፣ “ይህ መሆን አለበት” ብለው እንደሚከራከሩ መስፍን አርአያ ልሹ አምኗል። ኦነጋዊ ፍላጎታቸውን በተመካካሪው ላይ እንዲጭኑ የተሰማሩ ኦነጋውያንን መስፍን አርአያ የሚባለው ጉድ ግን እንደ ባለሙያ ነው የሚቆጥራቸው። #የኦሮሞ ባለሥልጣናት በአካልና በስልክ ጭምር ጫና ለመፍጠርና ጣልቃ ለመግባት ሞክረዋል የሚል አቤቱታ በተሳታፊው ሁሉ ቀርቧል። ከታች ያልተነሳ አጀንዳ “ከበላይ” እየወረደ፣ አጠናቃሪዎች ከአጠናቃሪነት ወጥተው ተከራካሪ እየሆኑ፣ በባለሙያነት ስም ኦነጋዊ ፍላጎትን እየጫኑ፣ ባለሥልጣናትም ጫና ያደርጋሉ የሚል ቅሬታ እየቀረበበት ያለው የመስፍን አርአያ ኮሚሽን አሁን መጠየቅ ያለበት “ሂደቱ ችግር አለበት ወይ?” የሚል ሳይሆን፣ “ከዚህ ውስጥ ምክክር ሊባል የሚችል የቀረው ምንድን ነው?” የሚል ነው። #ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲታይ፣ ምክክር ኮሚሽን ተብዮው የሕዝብን ፍላጎት በገለልተኝነት የሚመዘግብ መድረክ ሳይሆን፣ ቀድሞ የተያዘን ኦነጋዊ አጀንዳ በ“ሕዝባዊ ምክክር” ማኅተም ለማጽደቅ የተዘጋጀ መሣሪያ መሆኑን ነው። ከታች ያልመጣን ከላይ አውርዶ፣ ያልተባለን እንደተባለ ጽፎ፣ የብዙኃኑን ድምፅ አጥፍቶ፣ የጥቂቶቹን ፍላጎት ከብዙኃኑ ጋር እኩል አማራጭ አድርጎ ማቅረብ ከሆነ፣ ይህንን “ምክክር” ማለት ለቃሉ ልሹ ስድብ ነው።

  • #ከመርማሪ ኮሚሽን እስከ ምክክር ኮሚሽን፡ ኦነጋውያን ላለፉት ኀምሳ ዓመታት ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በሕዝብ ላይ ለመጫን የተጠቀሙባቸው ተለዋዋጭ ስልቶች! 👇 https://drive.google.com/file/d/1iN-EKqd3ZsjyMl_cxcAGp8m5B9wZgmzZ/view?usp=sharing

  • ♦ ማስታወሻ ደብተራችሁን አውጡ! – እነ ጸጋዬ አራርሳ ያመለጣቸው የ16ኛው ክፍለ ዘመን የታሪክ ትምህርት 😁 1. የኦሮሞ ህዝብ መነሻና ጥንታዊ መኖሪያ ፤ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ የህዝብ እንቅስቃሴና ፍልሰት በፊት፣ የኦሮሞ ህዝብ ዋና መገኛ ግዛት በደቡባዊ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች እና በሰሜን ኬንያ አዋሳኝ ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ነበረ። የመሃል ማዕከሉ "ማዳ ወላቡ" (በአሁኑ የባሌና ቦረና አዋሳኝ) በመባል ይታወቃል። የጎሳ አደረጃጀት ፤ ቦረና (በደቡብና ደቡብ ምዕራብ) እና ባሬንቱ (በደቡብ ምስራቅ) የኑሮ ዘይቤ ፤ በዋነኝነት ከብት አርቢ የነበረና ህይወቱ ከግጦሽ መሬትና ከዝናብ ዑደት ጋር የተቆራኘ ነበረ። 2. የ16ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ መስፋፋት (Oromo Expansion / Movement) ከ1520ዎቹ ጀምሮ በክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት እና በአዳል ሱልጣኔት (በአህመድ ግራኝ) መካከል በነበረው አውዳሚ ጦርነት ሳቢያ የተፈጠረውን የኃይል ክፍተት በመጠቀም፣ የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ በሶስት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ተካሄዷል ። ሀ. ወደ መካከለኛውና ምዕራብ ኢትዮጵያ የመጫ እና የቱለማ ቅርንጫፎች ወደ ሸዋ፣ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ጂማ እና ከፋ አካባቢዎች። ለ. ወደ ምስራቅ ኢትዮጵ ፤ የባሬንቱ ወገኖች (ኢቱ እና ሀምባና) ወደ ሐረርጌ እና አርሲ። ሐ. ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ፤ የወሎ እና የጁ ኦሮሞዎች መካከለኛው ሸዋን አቋርጠው እስከ ወሎ፣ ደቡብ ትግራይ እና ጎንደር አዋሳኝ። 3.በOromo Expansion / Movement የማህበራዊና ስነ-ህዝብ ለውጦች (የጠፉና የተዋሃዱ ብሔሮች ፤ የማስፋፋት ሂደቱ በየ8 ዓመቱ በሚካሄደው የገዳ "ሉባ" ዘመቻ እንዲሁም በባህላዊ ውህደት ስርዓቶች (ሞጋሳ እና ጉዲፈቻ) አማካኝነት ተከናወነ። በዚህ ሳቢያ የሚከተሉት ጥንታዊ ህዝቦችና መንግሥታት ታሪካዊ ህልውናቸውን አጥተዋል ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ ቀልጠዋል፦ ሀ. ጋፋት ፤ በአባይ ወንዝ ዙሪያና በምስራቅ ጎጃም/ወለጋ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን፣ በሂደት ቋንቋቸውና ማንነታቸው ጠፍቷል ። ለ. የዳሞት መንግሥት ፤ ህዝቡ ወደ ሰሜን (ጎጃም) ለመሰደድ ተገዷል፤ የቀረውም በኦሮሞ ማንነት ውስጥ ቀልጧል ። ሐ. ፈጠጋር እና ጋንጅ ፤ በመካከለኛውና ምስራቅ ኢትዮጵያ (ሸዋና አርሲ) የነበሩ ህዝቦች ሲሆኑ፣ በሞጋሳ ስርዓት ተዋህደዋል። መ. የእንጅናርያ መንግሥት፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የነበረ ባለጸጋ የኦሞቲክ/ሲዳማ መንግሥት ሲሆን፣ በሊሙ ኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ፈርሷል። ሠ. ሐዲያ እና ሲዳማ ፤ ሰፊ ግዛታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝባቸው በሞጋሳ ስርዓት ተዋህዷል ። 4. ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የአዲስ አበባ (በረራ) ገጽታ ፦ አሁን አዲስ አበባ የምትባለው ስፍራ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በታሪክ ማህደሮች "በረራ" በሚል ስም የምትታወቅ የኢትዮጵያ ነገሥታት (የሰሎሞናዊው ሥርወ-መንግሥት) ዋና ከተማና የንግድ ማዕከል ነበረች። እንደ አፄ ዳዊት፣ አፄ ይስሐቅ እና አፄ ዘርአ ያዕቆብ ያሉ ነገሥታት ቤተ-መንግሥት የሰሩበት ስፍራ ነበረች። በጊዜው በአካባቢው ይኖሩ የነበሩት ነባር ህዝቦች፦ የአማራ ህዝብ ፤ የመካከለኛው ሸዋ የክርስቲያኑ መንግሥት እምብርት በመሆኑ በስፋት ይኖርበት ነበር። የጋፋት፣ የጉራጌ እና የአገው ህዝቦች በአሁኑ አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ባሉ የሸዋ ክፍሎች ከጥንት ጀምሮ ይኖሩ የነበሩ ሴማዊና ኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ነበሩ። ማጠቃለያ ! የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት፣ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን የታላቁ ህዝቦች እንቅስቃሴ በፊት አሁን አዲስ አበባ የምትባለው "በረራ" አማራ፣ ጋፋት፣ ጉራጌ እና አገው ህዝቦች ይኖሩባት የነበረች ታሪካዊ ቦታ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ነባር መኖሪያ አልነበረችም። እርግጥ ነው፣ የወቅቱ የፖለቲካ ተንታኞች ይህን የታሪክ ሂደት አይፈልጉትም ፤ አሁን ባለው ህገ-መንግስት መመራት አለብን የሚል ሙግት ያቀርባሉ፤ ሆኖም የታሪክ እውነታውን መካድ ግን ፈጽሞ አይቻልም ፤ ለዘላቂ መፍትሄ መሰረት አይሆንም። የታሪክ ድርሳናት ማጣቀሻዎች (Sources) • Prof. Richard Pankhurst – "The Ethiopian Borderlands" (1997) • Prof. Taddesse Tamrat – "Church and State in Ethiopia (1270-1527)" • Abba Bahrey – "Zenahu Galla" (1593) • Prof. Mohammed Hassen – "The Oromo of Ethiopia: A History 1570-1860" • Ulrich Braukämper – "Islamic History and Culture in Southern Ethiopia" • Prof. Getachew Haile –"የአባ ባሕርይ ድርሳናት"

  • йоС пОдписи

  • የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቴዎድሮ ሩዝቬልት(Theodore Roosevelt) አንድ ዝነኛ አባባል አላቸው ይህም "ለድርድር ወይም ለውይይት ከመቀመጥህ በፊት ከአጠገብህ ጠብደል ዱላ መኖሩን ማረጋገጥ አለብህ" የሚል ነው ብዙ ሰዎች ቀደም ብሎ ሾለ ምክክር ኮሚሽኑ ሲነገራቸው ፈጽሞ መቀበል አልፈለጉም ነበር። ማዕከላዊ ስልጣን እና ጉልበት ያልያዘ የትኛውም ኃይል በየትኛውም መንገድ ጥቅሙን ለማስከበር አይደለም በግለሰብ ደረጃ የመከበር ዕድል እንደሌለው ግልጽ ነው። ምክክር ኮሚሽኑ "የቄጠማ ምርኩዝ" ከመሆን ያለፈ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ አቋም ወስዶ አርፎ መቀመጥ የነበረበት አንድ ሰው ዛሬ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ የኦህዴድ ባለስልጣናት እኮ ክብራችን ነኩት እያለ ፀጉሩን እየነጨ ነው። ከአምስት ዓመታት በፊት አዲስአበባ እንዳትገባ ኬላ ላይ ሲመልሱህ እነ መልል ጉድና አዲስ አበባ በሮችን እንዘጋለን ሲሉህ ጃዋር መሐመድ ዱላ ይዞ ድሃ በቆጠበው ገንዘብ የተሰራ ቤት እየሰበረ በመኪና ጭኖ እያመጣ ሲያስገባ አዲስ አበባ እርባና ቢስ ከተማ እናደርጋታለን በማለት ሽመልስ አብዲሳ ሲያቅራራ አስከትሎም ሸገር ብሎ አዲስአበባን በሲባጎ ገመድ ሸምቀቆ ውስጥ ሲያስገባት ኮሪደር ልማት በሚል ውጫዊ የልማት ገፅታ ወስጠ ማኅበረሰባዊ ስሪቱ ሲበጠስ ከተማው መዋቅር 60% ሲነጠቅ ያልታየህ ወዳጄ ዛሬ አንድ የኦህዴድ ባለጊዜ ባለ ስልጣን"ቀነዓ ያደታ" ምክክር ኮሚሽኑ ላይ የተከበሩ ፕሮፌሰር አዋረደ ተሳደበ አስጠነቀቀ በሚል ለቅሶ ብታላዝን ሙሾ ብታወርድ የሚለወጥ ነገር የለም። ሩዝቬልት እንዳለው ከአጠገቤ ምን አለ ነው ብለህ መጠየቅ ያለብህ!? ይሄ ምክክር ኮሚሽን ከወጣበት ገንዘብ ከፈሰሰው ጉልበት ከወጣው የሰው ሐብት ይልቅ ያስገኘው አንድ ትልቅ ጥቅም ኦህዴድ-ብልጽግና በራሱ ድግስ ዕራቁቱን የታዬበት ጥቂትም ቢሆን በደንብ ያላወቁት እንዲያውቁት መሆኑ ነው።

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • These three evil sprited Eritreans are the ones who steered Oromo nationalism and prevented reconciliation with Ethiopia! 1) Professor Asmarom Legesse (They dubbed him *Abba Gada* because he wrote—under the guise of anthropology and the like—criticizing his own country and people.) This professor spent his time writing based on the false, anti-Ethiopian propaganda of Ciurletti—Mussolini’s chief fascist "scholar" and advisor on East Africa. 2) Tesfaye Gebreab (They trusted him and even erected a monument in his honor because he wrote falsehoods while disparaging his own people.) 3) Dr. Samuel Kifle (He is steering them toward irreconcilable hatred under the guise of "consultation.") Asmarom Legesse and his ilk did this from abroad, citing fascist anti-Ethiopian propaganda to drive a wedge between Oromo nationalism and Ethiopia. Dr. Samuel, meanwhile, has been doing so from within Addis Ababa University, operating from the halls where "consultations" and similar forums take place.

  • የኦሮሚያው ፓብሎ ኤስኮባር...! '' መከላከያና ልዩ ሀይል ወደወረዳው ሲገባ ነፍጠኛን ከዚህ አካባቢ አፅ-ዱ-ልኝ እያለ በነፍስ ወከፍ እስከ 70ሺህ ብር የሚከፍለው ፤ የአርሷደሩ ማዳበሪያ ሲመጣ በቀጥታ የሚረከበውና በውድ የሚሸጠው ፤ ባለሀብቶችን እያስፈረጀ በማሳሰር ከፍተኛ ገንዘብ የሚቀበለው ፤ ማሳገትና ማስገደል ዋና የገቢ ምንጩ የሆነለት ፣ ከኖኖ እስከ ወሊሶ ፤ ከዳርጌ እስከ ወልቂጤ እንደመንግስት የሚቆጠረው ፤ ሰማዩም ምድሩም የኔ ነው ያለ ፤ በቀጠናው ለሚፈፀመው እያንዳንዱ እልቂት እጁ ያለበት ፥ ስልጣን ሳይኖረው ባለስልጣናትን እንደፈለገ የሚያሽከረክረው ፣ ልክ እንደሲሲሊ ማፊያዎች ሁሉ አደገኛ የወንጀል ቡድኖች ያሉት ፥ አረመኔው ፣ ጨካኙ የኦሮሚያው ፓብሎ ኤስኮባር .....!'' ስለዚህ አደገኛ ሰው ማንነትና ዝርዝር መረጃዎችን አጠናቅረን እንመለሳለን! በቀንም ሆነ በጨለማ የፈፀማችሁት እልቂትና ግፍ ሁሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም! በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር!😥

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • ይህ በዘር ማጥ- ፋት ወንጀል ለፍርድ መቅረብ ያለበት ግለሰብ ፣ የአብሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆነው አቶ ካሱ ጁሀር ነው። ሰሞኑን አነጋጋሪ የሆነው የ3ቱ ወጣቶች አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበትን የእ-ል-ቂት ወረዳ እየመራ ይገኛል። ከኦሮሚያ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ ያቋቋሙት ጨ-ፍ-ጫ-ፊ ኮማንድ ፖስትም አመራር ነው። ✅ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ ከ70 በላይ ወጣቶች በማንነታቸው ብቻ እየተመረጡ እንዲ-ረ-ሸ ኑና ደብዛቸው እንዲጠፋ አድርጓል ፣ አስደርጓል። ✅በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለሀብቶች ፣ አርሷደሮች ፣ ወጣቶች ፣ ... ሀሰተኛ ክስና ምስክር እያደራጀ ለአመታት ያለፍርድ እያሰቃያቸው ይገኛል። በወልቂጤ ማረሚያ ቤት በአንድ መዝገብ ብቻ የተከሰሱ ከ140 በላይ አማራዎች ታስረው ያለፍትህ ሁለት አመታት አልፏቸዋል። ✅ በአበሽጌ ወረዳና ዳርጌ ከተማ ላይ አማራዎች ለዘመናት ጥረው ግረው ያፈሩት ሀብት እንዲወረስ ፣ እንዲዘረፍና እንዲወድም አስደርጓል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ የበርካታ አማራዎች መኖሪያ ቤት ፣ መኪናዎች ፣ መጋዘኖች በእሳት እንዲቃጠሉ ተደርጓል። ✅ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ለዘመናት ያፈሩትን ሀብት ንብረት ትተው ወደተለያዩ ከተሞች እንዲሰደዱና ጎዳና እንዲወድቁ የተደረገበትን የማፅዳት ሂደትም መሪና አስተባባሪ ነው። ይህ ሰውና በዙሪያው ያሉት ሀይሎች በዚህ ስርአት በፍርድ አደባባይ ቀርበው ፍትህ ይሰፍናል ብዬ ባላምንም ፣ መላው የአማራ ህዝብና የሚፈፀመው አሰቃቂ ማንነት ተኮር ፍጅ-ት የሚያመው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በውል ለይቶ ሊያውቃቸው ይገባል! በአካባቢው ለአመታት ረፍት አልባ የሆነ እልቂት ፣ ማሳደድና የጅምላ እስር እየተፈፀመ ቢቀጥልም ፥ ሰሞኑን የተረ-ሸ ኑት 3 ወጣቶች ጉዳይ እስኪወጣ ድረስ ድምፅ አልባውን ሰቆቃ ማንም አልተረዳውም ነበር። በዚህ አጋጣሚ የምርመራ ጋዜጠኞች ፣ ሚዲያዎች ፣ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ፣ ወደዚህ የእልቂት ወረዳ በመሄድ ከተገለፀውም በላይ የሆነውን አስከፊ ሁኔታ በሚገባ እንድታጣሩና ለመላው አለም እንድታሳውቁ ለመጠቆም እወዳለሁ! በዛህ አሰቃቂ እልቂት ላይ የተሳተፉ ፣ የመሩ ፣ ያስተባበሩ ዋናዋና የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች ፥ ባለሀብቶችና ግለሰቦች ይፋ ማድረጋችንን እንቀጥላለን!

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • ሰበር ዜና ከግልገል በለስ!!! የቤንሻንጉል ጉሙዝ ነፃ አዉጭ የሆነዉ የጉሙዝ ሀይል አንድነት ግንባር ሰራዊት እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር በጥምረት ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 3:00 ሰዓት በመተከል ዞን ዋና ከተማ በሆነችዉ ግልገል በለስ ከተማ በከባድ መሳሪያ የታገዘ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በማድረግ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ከተማዋን መቆጣጠር ተችሏል። አረመኔው አብይ አህመድ መልሽ የብልጽግና አገዛዝ በኢትዮጵያውያን ሀይሎች ጥምረት ሊወገድ ጫፍ ላይ ደርሶ በጣዕረ ሞት እየቃዠ እያቃሰተ ይገኛል። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

  • #በሦስተኛ ደረጃ፣ የአንድ ሀገር መሪ ሀገራዊ አንድነትን እና እርቅን ለመፍጠር ታሪክን እንደ ማስተሰሪያ መሳሪያ ለመጠቀም መሞከሩ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ታሪክን ከሳይንሳዊ መሠረቱ ውጭ ለፖለቲካ ፍጆታ ማስፋፋት የራሱ የሆኑ የረጅም ጊዜ አደጋዎች አሉት፡፡ በቅድመ-ሁኔታ ደረጃ፣ ታሪክ በፖለቲከኞች ፍላጎት እና ጊዜያዊ ፍላጎት ብቻ የሚፃፍ እና የሚለወጥ ከሆነ፣ የታሪክ ጥናት እና አርኪዮሎጂ ሳይንሳዊ እሴታቸውን እንዲያጡና የፖለቲካ መሳሪያ ብቻ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም፣ የሌሎችን ማኅበረሰቦች (እንደ ኢሮብ፣ ሳሆ፣ አገው፣ ኩናማ፣ ናራ ወዘተ) ታሪካዊ እና ሥነ-ልሳናዊ ቅርሶች በቀጥታ ወደ አንድ ብሔር ታሪክ ጠቅልሎ ለማስገባት መሞከር፣ በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬን፣ ቅሬታን እና አለመተማመንን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ሕዝቡ በአንድ በኩል ‹‹እኔ ብቻ ነኝ የሀገሩ ባለቤት››፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ተበዳይ እና ባሪያ ነበርኩ›› የሚል የተጋጨ ሥነ-ልቦና እንዲይዝ ያደርገዋል፤ ይህም ለዘላቂ ሀገራዊ ስማምነት እና ለጋራ ሀገር ግንባታ አይበጅም፡፡ #በአጠቃላይ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሃገረ-መንግሥት ግንባታ፣ በባሕል፣ በወታደራዊ እና በፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ያለው ሚና ግዙፍ እና በራሱ እውነተኛ ታሪክ ላይ የቆመ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ለማስረገጥ ያልተረጋገጡ የቋንቋ ምስስሎሾችን፣ ዘመናትን እና ሁነቶችን የመቀላቀል ስሕተቶችን እና የተጋጩ የ‹‹ባርነት›› ተረኮችን መጫን አያስፈልግም፡፡ የአብይ አህመድ ንግግር የፖለቲካ ተረክን ለመቀየር የተደረገ ጥረት ቢሆንም፣ ወደፊት የሚሰሩ ሀገራዊ ትርክቶች በፖለቲካዊ ፍላጎት ላይ ሳይሆን፣ አሳማኝ፣ ሳይንሳዊ እና የታሪክ ምሁራን በተቀበሉት እውነተኛ ማስረጃ ላይ መመሰረት ይኖርባቸዋል፡፡ ሀገራዊ እርቅ እና አንድነት ሊመጣ የሚችለው ታሪክን በነበረበት ታሪካዊ ዐውድ እና ሳይንሳዊ ሚዛን መቀበል ስንችል ብቻ ነው።

  • #የአብይ አህመድ የታሪክ ክለሳ እና የተቃርኖዎች ትንተና “ሀገራዊ እርቅ እና አንድነት ሊመጣ የሚችለው ታሪክን በነበረበት ታሪካዊ ዐውድ እና ሳይንሳዊ ሚዛን መቀበል ስንችል ብቻ ነው፡፡” #የአብይ አህመድ የታሪክ ክለሳ #ከሰሞኑን ዐቢይ አሕመድ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ባደረገው ሁለት ክፍል ያለው ሰፊ ቃለ-መጠይቅ፣ በርካታ ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ታሪካዊ ጉዳዮችን አንስቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል በዋናነት የብዙዎችን ትኩረት የሳበው እና ያነጋገረው አብይ የኦሮሞን ሕዝብ ታሪካዊ ሥፍራ ለማብራራት የተጠቀመበት አቀራረብ ነው፡፡ ባለፉት አምስት አሥርት ዓመታት ገዢ ሆኖ የዘለቀውን ‹‹ኦሮሞ በኢትዮጵያ ሃገረ-መንግሥት ውስጥ ገለልተኛ ወይም ተጎጂ ብቻ ነበረ›› የሚለውን የብሔረተኝነት ተረክ ለመቀየር የተደረገው ጥረት እንደ በጎ የፖለቲካ ፍላጎት ሊታይ የሚችል ቢሆንም፤ ያቀረቧቸው ታሪካዊ እና ሥነ-ልሳናዊ ማሳያዎች እንዲሁም የተጠቀሟቸው ተቃራኒ ተረኮች ግን በታሪክ እና በሥነ-አመክንዮ ሚዛን ሲመዘኑ በርካታ መሠረታዊ ጥያቄዎችን የሚያስነሱ ናቸው፡፡ #የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሃገረ-መንግሥት ግንባታ እና ጥበቃ ሂደት ውስጥ የነበረው መዋቅራዊ ሚና ያልተረጋገጡ የቃላት ድምፅ ምስስሎሽን ወይም ጥንታዊ ሥልጣኔዎችን በምኞት በመሻማት የሚገለፅ አይደለም፡፡ ይልቁንም በታሪክ ሳይንስ የታወቁና አሳማኝ የሆኑ እውነተኛ የታሪክ ክስተቶች በበቂ ሁኔታ የሚያስረዱት ነው፡፡ ለአብነት ያህል፣ በ16ኛው እና በ17ኛው ክፍለ ዘመን በሃገረ-መንግሥቱ ማዕከላዊ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መዋቅር ውስጥ የታየውን የአመራርነት፣ የጎንደር ዘመነ-መንግሥት ሲመሰረትና ሲጠናከር ደግሞ የየጁ ባላባቶች እና የመሐል ሀገር የኦሮሞ ተዋጊዎች ያበረከቱትን ወሳኝ አስተዋፅኦ፣ እንዲሁም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ወሰን ሲካለልና ሀገር ከውጭ ወረራ ሲጠበቅ እንደ ልሾ ጎበናና ሌሎችም ያሉ የኦሮሞ የጦር አበጋዞች የተጫወቱትን የፊት-አውራሪነት ሚና መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሆኖም አብይ አህመድ ከዚህ አሳማኝ እና ተጨባጭ ታሪክ ተሻግሮ የሄደበት የታሪክ ክለሳ በበርካታ መሠረታዊ ጥያቄዎች የተከበበ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ #በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብይ አህመድ የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ እና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከሺህ ዓመታት በፊት የነበረውን ሕልውና ለማስረዳት በርካታ የቦታ፣ የሰዎች እና የባሕል ስሞችን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ ሆኖም እነዚህን ስሞች በቀጥታ ከኦሮምኛ ቋንቋ መድብለ-ቃላት ጋር ብቻ ማያያዝ፣ በታሪክ ሳይንስ ‹‹የሕዝብ ሥነ-ቃላት ትርጓሜ›› (Folk Etymology) ወይም በቋንቋዎች መካከል በሚፈጠር የድምፅ እና የቃላት ምስስሎሽ (Linguistic Coincidence) ላይ የተመሰረተ የታሪክ ስሕተት ይፈጥራል፡፡ ለአብነት ያህል፣ በአንድ ወቅት የባሕረ-ነጋሽ (ኤርትራ) አስተዳዳሪ መኾናቸው ተመዝግቦ የምናገኘውን ‹‹ዶሪ›› የተባሉ መሪ ስም በመጥቀስ፣ ቃሉ [በገዳ ሥርዓት ውስጥ ካለው አንድ የአባ ገዳ ስያሜ ጋር እንደሚመሳሰል በማስታወስ] የኦሮሞን ታሪካዊ ስፍራ እንደሚያሳይ በድፍረት ተናግሯል፡፡ #ሆኖም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እና በኤርትራ ዐውድ ‹‹ዶሪ›› የሚለው ስም በሳሆ/ኢሮብ፣ በትግራይ እና በኤርትራ ማህበረሰቦች ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ያለ የወንድ ስም ሲሆን፣ በአሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በአቶ ዶሪ አስገዶም ስም ላይ እንደምናየው በኢሮብ ማህበረሰብ ዘንድ አሁንም ድረስ በስፋት የሚሰራበት እና በቋንቋው የራሱ ሼረ-መሠረት ያለው ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፣ በኤርትራ የሚገኘውን ‹‹ባረንቱ›› የተባለ ቦታ ከኦሮሞው ባረንቱ ጎሳ ጋር ማያያዝ፣ በቦታው የሚኖሩትን የማህበረሰቦች ታሪካዊ እና ሥነ-ልሳናዊ መሠረት ያላገናዘበ ነው፤ በኩናማ እና ናራ ቋንቋዎች ‹‹ባረንቱ›› ማለት ‹‹ግራር›› (የግራር ዛፍ) ማለት ሲሆን፣ ስሙም አካባቢያዊ የተፈጥሮ ስያሜን መሠረት ያደረገ እንጂ በቀጥታ ከኦሮሞ የጎሳ ክፍፍል ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አርኪዮሎጂያዊም ሆነ ታሪካዊ ማስረጃ በፍፁም የለውምም አይኖርምም፡፡ #በተመሳሳይ መልኩ፣ የዛጉዌ ሥርወ-መንግሥት መሥራችና መሪ የነበሩትን ‹‹መራ ተክለሃይማኖት›› ከኦሮምኛው ‹‹መረራ›› ጋር በማያያዝ ዛጉዌዎችን የኦሮሞ ድርሻ እንደነበራቸው ለማስረዳት መሞከር፣ የታሪክ ሂደትን እና የቋንቋዎችን ሼረ-መሰረት ያላገናዘበ ዘመን እና ሁነቶችን የመቀላቀል ስሕተት (Anachronism) ይፈጥራል፡፡ በተጨማሪም በአክሱም ሐውልት ላይ የሚታዩ የተቀረጹ ምስሎችን ከገዳ አባቶች ‹‹ከለቻ›› እና ‹‹ቦኩ›› ጋር በማመሳሰል የኦሮሞን ድርሻ ለማስረዳት መሞከር ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ነው፡፡ በአክሱም ሥልጣኔ ወቅት የነበሩት የጠረጴዛ፣ የምሰሶ እና የጌጣጌጥ ቅርጾች በሴማዊ እና በደቡብ ዐረቢያ ሥልጣኔዎች ውስጥ የራሳቸው ሃይማኖታዊ እና ኪነ-ሕንፃዊ ትርጉም የነበራቸው ሲሆን፣ ሁለት የተለያየ ዘመን እና የባሕል ዐውድ ያላቸውን ምስላዊ ቅርጾች በመልክ ተመሳሳይነት ብቻ የባሕል ወራሽነት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ በታሪክ አርኪዮሎጂ ዘንድ ተቀባይነት የለውም አይኖረውም፡፡ ይህ ዓይነቱ አቀራረብ የኦሮሞን ሕዝብ እውነተኛ እና ግዙፍ የሆነ ታሪካዊ አስተዋፅኦ ከማጎልበት ይልቅ፣ ለሳይንሳዊ ትችት እና ለተቃውሞ በር የሚከፍት ሆኖ ይገኛል፡፡ #በሁለተኛ ደረጃ፣ በአብይ አህመድ ንግግር ውስጥ ታላቁ የሥነ-አመክንዮ እና የፖለቲካ ተቃርኖ የሚታየው በሁለት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ታሪካዊ ተረኮች መካከል ወጥ የሆነ ድልድይ ለመስራት ሲሞከር ነው፡፡ በአንድ በኩል፣ የአብይ አህመድ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ሃገረ-መንግሥት ዋና አካል፣ ሰሪ፣ እና ባለቤት እንደነበረ፤ በሰሜንም ሆነ በደቡብ በሀገሪቱ ሥልጣኔ እና መንግሥት ግንባታ ውስጥ የመጀመሪያ መሾመር ተሳታፊ እንደነበረ ያስረዳል፡፡ ይህ ተረክ ኦሮሞን እንደ ሀገር ባለቤት እና መዋቅራዊ ኃይል አድርጎ የሚያቀርብ ሀሳብ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ በተመሳሳይ ንግግሩ ውስጥ ‹‹ኦሮሞ ከባርነት ነፃ ወጥቷል፤ አሁን ነፃ ወጥተናል፤ ደግሞ ተመልሰን የሌሎች ባሪያ አንሆንም›› የሚል የ‹‹ባርነት›› (Slavery) ቋንቋ ሲጠቀም ይደመጣሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ሀሳቦች በአንድ ጊዜ ሊሄዱ የማይችሉ ተቃራኒ ጽንሰ-ሀሳቦች ናቸው፡፡ #ምክንያቱም አንድ ማህበረሰብ የሀገረ-መንግሥቱ መሥራች፣ የጦር ሰራዊቱ መሪ፣ የፖለቲካው እና የባሕሉ የበላይ አካል (ባለቤት) ከሆነ፣ በተመሳሳይ ጊዜ በዚያው ሃገረ-መንግሥት ውስጥ ‹‹በባርነት›› ሼር ነበረ ሊባል አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተለያዩ ሕዝቦች የፖለቲካ ገለልተኝነት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ ወይም የባሕል ጭቆና ደርሶባቸው ሊሆን ይችላል፣ ‹‹ጭቆና›› (Oppression) እና ‹‹ባርነት›› (Slavery) በሶስዮሎጂ እና በሕግ ፍጹም የተለያየ ትርጉም አላቸው፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ ታሪካዊ ሂደት እንደ ‹‹ባርነት›› አድርጎ ማቅረብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበረውን ወሳኝ ሚና ዝቅ የሚያደርግ እና ከራስ ታሪካዊ ታላቅነት ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ ይህ ተቃርኖ የሚያሳየው፣ ንግግሩ የታሪክ ሳይንስን ተከተሎ የተዘጋጀ ሳይሆን፣ በተለያዩ የፖለቲካ ደጋፊዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የተደረገ የተቀየጠ የፖለቲካ ንግግር (Political Rhetoric) መሆኑን ነው፡፡

  • የግፍ ቁና ሞልቶ ሲፈስ..!😥 ለሞራልም ሆነ ለህግ ተገዢ ያልሆነው አገዛዝ ''ማንም ሰው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ እስካልተወሰነበት ድረስ እንደንፁህ የመቆጠር መብት አለው'' የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ጭምር በሚጥስ መልኩ ፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ (ፍርድ) ያልተሰጠባቸውን የፖለቲካ እስረኞች ፦👇 '' በአማራ ክልል ፅንፈኛው ቡድን በሚያደርገው ትግል ላይ መሳተፌ ስህተት መሆኑን በማመን መንግስትና ህዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ። በክልሉ ለጠፋው ህይወት (በአሃዝ ተጠቅሷል) እና ለወደመው ንብረት (በአሃዝ ተጠቅሷል) ሀላፊነት እወስዳለሁ። ሁለተኛ በእንዲህ ያለ ፀረ-ሰላም ተግባር እንደማልሳተፍ ቃል እየገባሁ ፣ ይህንን አድርጌ ብገኝ መንግስት ማንኛውንም እርምጃ እንዲወሰድብኝ በፈቃዴ እፈርማለሁ!'' የሚል እጅግ አስነዋሪ የይቅርታ ፎርም አዘጋጅቶ ''ፈርሙ'' ሲል እንደሰነበተ የሚታወስ ነው። በዚሁም መሰረት፦ 1. የተከበሩ አቶ ዩሀንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ሀ/ማርያም 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ 5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ 6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው 7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 10. ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ 11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 12. አቶ አለልኝ ምህረት 13. አቶ መንበር አለሙ 14. አቶ ማይክ መላክ 15. አቶ አሳምነው ታደሠ 16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 17. አቶ እሱባለው በለጠ 18. አቶ እስክንድር ሽፈራው 19. አቶ መሰለ ቸሩ 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. አቶ ጫኔ ዘየደ 22. ወ/ት ሀሊማ አህመድ 23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ታደሰ ወዳይነው 26. አቶ በላይ ሲሳይ 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ማረው ሾለሺ 29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ 30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ '' እዚሁ ግ-ደ-ሉ-ን እንጂ ይህን ለህግም ለሞራልም ተቃራኒ የሆነ የይቅርታ ፎርም አንሞላም '' ብለው እስካሁን በአቋማቸው የፀኑ 30 የአማራ የህሊና እስረኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ለ3 አመታት ያለምንም ፍትህ በማንነታቸውና በፖለቲካዊ አመለካከታቸው በግፍ ታስረው የሚገኙ የህሊና እስረኞች ፤ በአገዛዙ ይቅርታ መጠየቃቸው ለደረሰባቸው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል መካሳቸው ቢቀር ፣ ከፍርድ በፊት እንደጥፋተኛ ራሳቸውን ቆጥረው ውል እንዲገቡ ማስገደድ ከሰብአዊም ሆነ ከህገ-መንግስታዊ መብት አንፃር ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ይገልፃሉ! አንድ በህግ ጥላ ሾር የሚገኝ ሰው ቶርቸር እየተፈፀመበትና በኢ-ሰብአዊ አያያዝ ውስጥ ሆኖ የሚሰጠው የእምነት ቃል ተቀባይነት እንደሌለው ሁሉ ለ3 አመታት በግፍ ታስረው የሚገኙ የህሊና እስረኞችም እያለፉበት ባለው ከቶርቸር ያልተናነሰ ስቃይ ጫና ውስጥ በመክተት ፣ ይህን የሞት ፍርድ ውል እንዲቀበሉ መደረጉም አግባብነት የሌለው አሳዛኝ ጉዳይ ነው! አገዛዙ ለትክክለኛ ብሔራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ፣ ጥቂት እንኳ ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ ለአመታት ያለፍትህ ታስረው የሚገኙትን የህሊና እስረኞች ፣ ሙሉ በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታቸው ነበር። በመሆኑም - ይህንን የአገዛዙን ባህሪ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ግፍ ፣ መላው የአማራ ህዝብ ፣ ሚዲያዎች ፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት እንዲያውቁት ማድረግ የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃል። እያንዳንዳችን ከህሊና እስረኞቹና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ልንቆምና የመንፈስ ብርታት ልንለግሳቸውም ይገባናል! #ሟር