WOLAITA SODO UNIVERSITY
СтатистикаAcademic Institution Information Sharing Channel
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 47
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 619
- 1/48двое суток
- 709
- 1/72трое суток
- 765
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ማስታወቂያ ለድህረምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!!
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከነሀሴ 13 እስከ 15/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን የፈተናው መርሃ-ግብርና ሌሎች መረጃዎች በቴሌግራም ቻናል(https://t.me/M0H_EThiopia) ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማስታወቂያ ለPGDT ትምህርት ፈላጊዎቾ በሙሉ!
የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያ!! #የመመዝገቢያ_ሊንክ፡- 👇👇 https://ngat.ethernet.edu.et
በተመሳሳይ የፈተናው ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፌደራልና ከክልል የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በቅንጅት በመስራት የደህንነትና የዲሲፕሊን ስራዎችን በንቃት ላከናወኑ የጸጥታ አካላት ልዩ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። ይህ ቁርጠኝነት ተማሪዎች ያለምንም የደህንነት ስጋት በትኩረት ፈተናቸውን እንዲፈተኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ጠቁመዋል። እንደተቋም የፈተናውን አጠቃላይ ሂደት በማሳለጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን በተሳካ ሁኔታ ለመራው የዩኒቨርሲቲው የፈተና አስፈፃሚ ግብረኃይል (Task Force) አባላት ፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ግብረኃይሉ ከተማሪዎች መግቢያ እስከ መኖሪያ፣ ምግብ፣ ጤና እና ሌሎች ድጋፎች ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን በቅርበት በመከታተል የተቀናጀ አመራር መስጠት መቻሉን በመጠቆም አድንቀዋል። በዩኒቨርሲቲው ለወላድ ሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች የተደረጉ ሰዋዊ ድጋፎች የሚደኑቁ በመሆናቸው በቀጣም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መጥተው የተፈተኑ ተማሪዎችም የፈተናውን ህግና ደንብ በማክበርና የተቋሙን ዲሲፕሊን በመጠበቅ ረገድ ላሳዩት ትጋት አድናቆታቸውን ችረዋል ። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፣ ዩኒቨርሲቲው መሰል ሀገራዊ ኃላፊነት በስኬት ለመወጣት የሚያስችል ጠንካራ መሠረተ ልማት እየገነባ የቆየ በመሆኑ ውስብስብና መሰል ሰፊ ስራዎችን በቅንጅት የመምራት አቅሙን እያሳደገ ስለመምጣቱ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)፣ የፈተናው በሰላም መጠናቀቅ የሁላችንም የጋራ ጥረትና ትብብር ውጤት በመሆኑ በዚህ ሥራ አሻራቸውን ያሳረፉትን ሁሉ አመስግነው በ2019 በጀት ዓመት በየዘርፋችን የሚሰጡንን ተግባራት በተመሳሳይ ቁርጠኝነትና ኃላፊነት በመሥራት ውጤታማ እንድንሆን ጥሪ አቅርበዋል።
በዪኒቨርሲቲው ሲሰጥ የቆየው ሀገርአቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ተጠናቋል። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ከሰኔ 23 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም፣ መጠናቀቁን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) የምስጋና መልዕክት አስተላልፏል። ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የምስጋና መልዕክት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኩረጃን ባስቀረ ሁኔታ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ የተቀናጀ የትብብር ሥራ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርስቲው እንዲፈተኑ የመደባቸውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በተከታታይ አምስት ዙር በወረቀትና በበይነመረብ በአጠቃላይ 9,943 ተማሪዎች በተሳካ ሁኔታ አስፈትኖ ማጠናቀቁ ተጠቁሟል። በዘንድሮ ፈተና ከዝግጅት ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሌት ተቀን በትጋት የሰሩ የፈተና ማዕከል ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የፈተና ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ የፈተናውን ሂደት በብቃት በመምራታቸው የተገኘው ስኬት የእነርሱ ትጋት ፍሬ መሆኑን በመግለፅ ምስጋና አቅርበዋል።
ለነባር የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ!!
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው ፡፡ ወ.ሶ.ዩ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በ2018 ዓ.ም ሀገርአቀፍ የ2ኛ ደረጃ የመልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡትን ተማሪዎች እየተቀበለ ይገኛል፡፡ ከተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች በ2ኛ ዙር ሀገርአቀፍ የ2ኛ ደረጃ የመልቀቂያ ፈተና ለመፈተን የተመደቡ ተማሪዎች ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ መግባት የጀመሩ ሲሆን በቅበላ ኮሚቴ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ፈተናው ከሰኔ 23 ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች የእስካሁን ሂደት ሰላማዊና የተሳካ እንደሆነ የፈተና ግብረ-ኃይሉ ሪፖርት ያሳያል፡፡ በዩኒቨርሲቲያችን በ2ኛ ዙር ከ800 በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ስለፈተና አጠቃላይ ሂደት በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ ገለጻ የሚሰጣቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ እንደወትሮ ሁሉ ለዚህ ዙር ተፈታኞችም የተሳካ የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡፡