- Последний пост
- 27 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 74
- 1/48двое суток
- 84
- 1/72трое суток
- 91
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
" #ነፃነት_መለሰ|#Netsanet_Melese_ende_hamile_tsehay_እንደ_ሐምሌ_ፀሐይ " እንደ ሐምሌ ፀሐይ በጭንቅ የምትወጣው፣ ምን ልሁን ብለህ ነው ባ'ሳቤ ምትመጣው? 👇👇 https://youtu.be/Zlcus9Yp1DA?si=QFjGaXsmPNKoB1w8 አነጋጋሪ ሚዲያ_Hot issue Media
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን #subscribe, #join and #follow በማድረግ ይጎብኙን፦👇👇 YouTube ➲ https://youtube.com/channel/UCOX7tTMpW1lyPzmsRaqlo1Q?si=yfQVI_q-w7vYqwDL Telegram ➲https://t.me/Zena_Keminchu Facebook ➲https://www.facebook.com/profile.php?id=100064053341970 Tiktok ➲ http://www.tiktok.com/@hotissuemedia
ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:- አጀንዳ ቁጥር 1 1. የሀገር ግንባታ 1.1 የማንነት እና የሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች 2. ታሪክ እና ማንነት 3. የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች (እሴቶችንም የሚመለከቱ ጉዳዮች) 4. ሀገር ግንባታና ብዝሀነት አስተዳደር ጉዳዮች 5. የቋንቋ ጉዳዮች 1.6 የባህል፣ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ቁጥር 2 2. የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም የፖለቲካ ስርአት፣የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት 2.1 የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ 2.1.1 የመንግስት አደረጃጀት፣አስተዳደር ስርአት አይነት 2.1.2 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት (በቅንፍ ውስጥ ሲቲዝንሺፕ ዜግነት) ህዝባዊ...አንድ 2.1.3 የብሄር ብሄረሰቦች ትርጓሜ (አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ህገ መንግስቱ) 2.1.4 የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት መሪዎች የስልጣን ዘመን 2.1.5 የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት። የስልጣን ክፍፍል፣የፌደራልና የክልል መንግስት። የፊሲካል ፌደራሊዝምና የሀብት ክፍፍል 2.1.6 የክልል አስተዳደር እና ወሰኖች፤ የአዳዲስ ክልሎች አመሰራረት። የክልል አስተዳደራዊ ወሰኖች 2.1.7 የህግ አውጪው አካል ወይም ፓርላማ አወቃቀርና ሚና 2.1.8 ህገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን 2.1.9 የህገ መንግስት ማሻሻያ ስርአት (አንቀጽ 104ና 105) 2.2 የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርአት ጉዳዮች 2.2.1 የሀገሪቱ የምርጫ ስርአት 2.2.2 የመድብለ ፓርቲ ስርአት 2.2.3 የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት 2.2.4 የመንግስትና የገዢ ፓርቲ ሚና መለያየት 2.2.5 የምርጫ ክልሎች አወቃቀር 2.2.6 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስት ሀብት አጠቃቀም አጀንዳ ቁጥር 3 3. የፌደራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) 3.1 የአዲስ አበባ ጉዳይ 3.1.1 የአዲስ አበባ ህጋዊ አቋም። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት የአዲስ አበባ ከተማ የበጀት ድርሻ ጉዳይ 3.1.2 የፌደራል ዋና ከተማ ጉዳይ 3.1.3 የአዲስ አበባ ፖሊስና ፍ/ቤት ጉዳይ 3.1.4 የአዲስ አበባ ወሰንና የቦታዎች ስያሜዎች 3.1.5 የአዲስ አበባ የስራ ቋንቋ 3.1.6 የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣አካታችነት ጉዳይ 3.2 የድሬዳዋ ጉዳይ 3.2.1 የድሬዳዋ ህጋዊ አቋም 3.2.2 የድሬዳዋ የወደፊት አስተዳደራዊ ሁኔታ፣የህዝቦቿ ውክልናና ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር ያላት ግንኙነት 3.2.3 የድሬዳዋ በፌደራል መንግስት ውክልና። ድሬዳዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ጉዳይ አጀንዳ ቁጥር 4 4. የሃይማኖት ጉዳዮች፣ታሪካዊ ቅሬታዎች እና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.1.1 በሴኪውላሪዝምና በሃይማኖት ነጻነት መካከል ጤናማ ሚዛን መጠበቅ 4.1.2 የሃይማኖት ነጻነትና ገደቦቹ 4.1.3 አናሳ የተከታይ ቁጥር ያላቸው ሃይማኖት ተቋማት ጥበቃ 4.1.4 ከባህል እና ከሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር የሚጋጩ ድርጊቶች ጉዳይ 4.2 ታሪካዊ ቅሬታዎችና እርቅን የሚመለከቱ ጉዳዮች 4.2.1 ታሪካዊ መገለል እና ልዩ ተጠቃሚነት 4.2.2 የእርቅና እውቅና የመስጠት ሂደት 4.3 በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት እና አብሮ መኖርን በተመለከተ 4.3.1 በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ውጥረቶችና መፍትሄዎቻቸው 4.3.2 በሃይማኖቶች መካከል የውይይት እና ምክክር ዘዴዎችን ማጠናከር 4.4 ሃይማኖት በህዝብ ህይወት እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ያለውን መስተጋብር በተመለከተ 4.4.1 በህዝብ ተቋማት ውስጥ የሃይማኖት ሚና 4.4.2 የሃይማኖት መድረኮች፣ሚዲያና ህዝባዊ ውይይቶች 4.4.3 የሃይማኖት ተቋማት የድምጽ አጠቃቀም እና የህብረተሰብ መብት አጀንዳ ቁጥር 5 5. የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነትና ሰብአዊ መብቶች 5.1 የሰብአዊ መብቶች 5.1.1 ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማእቀፍ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ 5.1.2 በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች መብቶች 5.1.3 አካል ጉዳት፣ተጋላጭና የተገለሉ ቡድኖች መብቶች 5.1.4 የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በግጭት እና በጸጥታ ሁኔታዎች ውስጥ 5.1.5 ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማዊ ማእቀፎች የማጠናከር ጉዳይ 5.1.6 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ (ዳያስፖራ)። የጥምር ዜግነት መብት እውቅና እና ሌሎች ጉዳዮች 5.2 የህግ የበላይነት 5.2.1 የህግ የበላይነት (ህጋዊነት) 5.2.2 በህግ ፊት እኩልነት 5.2.3 ተጠያቂነት 5.2.4 የፍትህ ተደራሽነት 5.3 የተቋማት ግንባታ 5.3.1 የዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ነጻነትና ተደራሽነት 5.3.2 የፍትህ ተቋማት ነጻነትና ተጠያቂነት 5.3.3 የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና አደረጃጀት 5.3.4 የሶስቱ የመንግስት አካላት ሚዛን፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.5 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማዊ ገለልተኝነት፣ ነጻነት እና ተጠያቂነት 5.3.6 የሲቪል ማህበራት ነጻነት፣ ሚናና ተጠያቂነት አጀንዳ ቁጥር 6 6. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች 6.1 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች 6.1.1 የሴቶች ጉዳይ እና ተያይዘው የቀረቡ ጥያቄዎች 6.1.2 የሀብት አስተዳደር እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል 6.1.3 የመሬት ይዞታና ባለቤትነት 6.1.4. የህዝብ ቆጠራ ውክልና እና አካታች አስተዳደር 6.1.5 ማህበራዊ አገልግሎቶች (ጤና፣ ትምህርትና የኑሮ ደረጃ) 6.1.6 የሰራተኛ መብቶች እና ፍትሀዊ የስራ ሁኔታ 6.1.7 ዘላቂ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ። 6.1.8 የተፈጥሮ ሀብት መብቶችና ጥቅም መጋራት 6.1.9 አካታች ኢኮኖሚ፣ኢንቨስትመንት እና ምርታማነት 6.1.10 ማህበራዊ ደህንነትና የስራ እድል 6.2. የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይ 6.2.1 የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተሳትፎና እኩልነት ተጠቃሚነትን የማሳደግ ጉዳይ 6.2.2 የግብርና ግብአቶች ወቅታዊና ፍትሀዊ ተደራሽነትን በተመለከተ። 6.2.3 የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 5ና አንቀጽ 41 ንኡስ አንቀጽ 8 ላይ የተጠቀሰውን 'ዘላን' የሚለውን ስያሜ ማስተካከል 6.2.4 ነጻ የገበያ እድልና የገበያ ትስስር መፍጠር 6.2.5 የአርሶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች የጋራ መልማትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ 6.2.6 የአርብቶ አደሮች የኑሮ ዘይቤያቸውን ያማከለ የልማት ፖሊሲ አጀንዳ ቁጥር 7 7. ሙስና እና መልካም አስተዳደር 7.1 የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች። 7.2 የጸረ-ሙስና ስርአት ግንባታ 7.3 የመልካም አስተዳደር ስርአት ግንባታ 7.4 ፍትሀዊ ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.1ፍትሀዊና አካታች ፓብሊክ ሰርቪስ 7.4.2 በብቃት ላይ የተመሰረተ የሰው ሀብት አመዳደብ እና ቅጥር አጀንዳ ቁጥር 8 8. ሰላም ግንባታ 8.1የግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች ግጭቶችንና መሳሪያ ያነሱ አካላትን በሚመለከቱ 8.3 የዘላቂ ሰላም መሰረቶች 8.4 ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች እውቅና፣ ማጠናከር እና ዘመናዊ ውህደት 8.4.1 ባህላዊ እውቅና እና ህጋዊ ማእቀፍ 8.4.2 የእርቅና ይቅርታ ጉዳይ 8.4.3 የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነቶች 8.4.4 የሽግግር ፍትህ 8.5. ሃይማኖት ተቋማት ሚና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም
без подписи
ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የቀረቡ ስምንት አጀንዳዎች በዝርዝር:-👇👇
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀበሉ #Ethiopia | የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በአሜሪካ ከሚገኘው ሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አመራር (Educational Leadership) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀቁ። ብፁዕነታቸው ይህንን የትምህርት ማዕረግ በስኬት በማግኘታቸው በበላይ ሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝዳንቱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ በይፋ ገልጿል። ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ በስፋት የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀትና በማሳተም እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመምህርነትና በአስተዳደር ኃላፊነት የላቀ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩና አሁንም በማገልገል ላይ የሚገኙ ምሁር አባት ናቸው። ከዚህም ባለፈ ባከናወኗቸው ሰፊ አካዳሚያዊ ተግባራትና ተከታታይ አገልግሎቶች ምክንያት ላለፉት ዓመታት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማግኘታቸው ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያስታውሳል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን #subscribe, #join and #follow በማድረግ ይጎብኙን፦👇👇 YouTube ➲ https://youtube.com/channel/UCOX7tTMpW1lyPzmsRaqlo1Q?si=yfQVI_q-w7vYqwDL Telegram ➲https://t.me/Zena_Keminchu Facebook ➲https://www.facebook.com/profile.php?id=100064053341970 Tiktok ➲ http://www.tiktok.com/@hotissuemedia
“በቻይና የጋብቻ ገበያ ተቋቋመ”‼️ በቻይና ሻንጋይ በሚገኝ አንድ የሕዝብ ፓርክ ውስጥ ወላጆች ለልጆቻቸው የትዳር አጋር የሚፈልጉበት ልዩ “የጋብቻ ገበያ” በየሳምንቱ መጨረሻ እየተካሄደ መሆኑን ቢቢሲ (BBC) እና ሲኤንኤን (CNN) የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ወላጆች የልጆቻቸውን ዕድሜ፣ ቁመት፣ የትምህርት ደረጃ፣ ገቢ እና የቤት ባለቤትነት ዝርዝር መረጃ በወረቀት ላይ በመጻፍ በጃንጥላዎች ወይም በገመዶች ላይ ይሰቅላሉ። ገበያውን በብዛት የሚያደምቁት በትዳር ዕድሜ ላይ ለደረሱ ነገር ግን በሥራ መብዛት ወይም በሌላ ምክንያት አጋር ላላገኙ ልጆቻቸው የሚጨነቁ ወላጆች ናቸው። በገበያው ውስጥ ከፍቅራዊ ስሜት ይልቅ የኢኮኖሚ አቅም፣ የትምህርት ደረጃና ማኅበራዊ መደብ ለትዳር መሠረት ተደርገው በሰፊው ይገመገማሉ። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን #subscribe, #join and #follow በማድረግ ይጎብኙን፦👇👇 YouTube ➲ https://youtube.com/channel/UCOX7tTMpW1lyPzmsRaqlo1Q?si=yfQVI_q-w7vYqwDL Telegram ➲https://t.me/Zena_Keminchu Facebook ➲https://www.facebook.com/profile.php?id=100064053341970 Tiktok ➲ http://www.tiktok.com/@hotissuemedia
ኢሰማኮ በፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ አይቀርብም፣ የሽግግር ፍትሕ አፈጻጸም ዘግይቷል እንዲሁም ግጭቶች እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየጨመሩ ነው ሲል አስታወቀ ማክሰኞ፣ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሰናደው ሪፖርት ላይ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ አይቀርብም፣ የሽግግር ፍትሕ አፈጻጸም ዘግይቷል እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች የሚከሰቱ ግጭቶች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት መሆናቸው እየጨመረ ነው ሲል አስታውቋል። ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት ክንውን በተመለክተ ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት እና አዲስ ማለዳ የተመለከችው ሰነደ እንደሚያስረዳው በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ፤ በትግበራ ሂደቶች ላይ የታዩ መዘግየቶችን፣ በፖሊስ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤቶች ያሉ የአቅርቦት ክፍተቶችን እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች ያስከተሏቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ናቸው ያላቸውን ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ በ492 ፖሊስ ጣቢያዎች፣ 79 ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም 11 መደበኛ ያልሆኑ ማቆያ ሥፍራዎች ጎብኝቻለሁ ያለ ሲሆን እነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ አለማቅረብ እና የማቆያ ቦታዎች ክፍተቶች እጅጉን እየተባበሳ መሄዱን አመልክቷል። ኮሚሽኑ አክሎም “በበርካታ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ አይቀርብም” በማለት የምግብ በጀቱ ቢስተካከልም ታራሚ እና ተጠርጣሪዎችን ተጠቃሚ ያደረግ አይደለም ብሏል። ኮሚሽኑ ባደረገው የክትትል ሥራ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የሕግ ማቆያ ስፍራዎች በተለይም በተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ረገድ በርካታ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች መቀጠላቸውን ተናግሯል። ኮሚሽኑ አክሎም የምግብ አቅርቦት እጥረት ክትትል ከተደረገባቸው በርካታ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ የማይቀርብ ስለመሆኑ ማረጋገጡን ጠቅሶ በማረሚያ ቤቶች ምንም እንኳን የምግብ በጀት ማስተካከያ የተደረገ ቢሆንም፣ ለታራሚዎችና ለተጠርጣሪዎች በቂ እና ጥራቱን የጠበቀ ምግብ ከማቅረብ ረገድ አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩ በሪፖርቱ ላይ ስፍሯል። ኮሚሽኑ መቆያዎችን በተመለከተ ደግሞ በብዙ ፖሊስ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤቶች በወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ወይም የተጠረጠሩ ሕፃናትን ለአካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች ጋር በአንድ ክፍል እንዲኖሩ እየትደረገ ነው ብሏል። በተጨማሪም ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች “በቂ ስፋት በሌላቸውና ንጽሕናቸው ባልተጠበቁ ክፍሎች”ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ ይገኛሉ ሲል ለምክር ቤቱ ባዘጋጀው ሪፖርት ላይ ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ፍኖተ ካርታን ተከትሎ ዋና ዋና ተቋማት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆች እና የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ሕግ መረቀቃቸው እንደ መልካም እመርታ የተጠቀሰ ቢሆንም፣ በትግበራው ላይ የታዩ መዘግየቶች አሳሳቢ ናቸው ሲል አስታውቋል ። የሽግግር ፍትሕ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ማቋቋም፣ የትግበራ ቅደም-ተከተል ጥቅል ዕቅድ ማውጣት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን፣ የሕዝብንና የባለድርሻ አካላትን ድጋፍና ባለቤትነት የሚያጠናክሩ ሥራዎች “በታቀደው ግዜ ማከናወን አለመቻላቸው አሳሳቢ ናቸው” ብሏል። ኮሚሽኑ የተዘጋጁት ረቂቅ ሕጎችና ሰነዶች እስካሁን ለሕዝብ ውይይት አለመቅረባቸው ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሏል። በሀገሪቱ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲቀጥሉ እና እንዲባባሱ ካደረጉ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል በተለያዩ ክልሎች የሚከሰቱ ግጭቶች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። በአማራ፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚከሰቱ ግጭቶች እንዲሁም የጸጥታና ደኅንነት ስጋቶች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደ ዋነኛ መንስኤ ሆነው ቀጥለዋል ብሏል። ለዚህም ጉዳይ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ተጠያቂዎች ሁነው ለግጭቱ ደግሞ ሰላማዊ መፍትሄ መፈለግ አለበት ብሏል። በነዚህ የግጭት ዐውዶች ውስጥና ውጪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተገቢውን ምርመራ አለማድረግና ተጠያቂነትን አለማረጋገጥ አሁንም ትልቅ ክፍተት ሆኖ መቀጠሉን በምክንያትነት አስቀምጧል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እነዚህን መሠረታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ክፍተቶችን ለመቅረፍ መንግሥት እርምጃዎች እንዲወስድ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ለማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ለተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች ምግብን ጨምሮ መሠረታዊ አቅርቦቶች እንዲሟሉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አጽዕኖት ሰጥቷል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን #subscribe, #join and #follow በማድረግ ይጎብኙን፦👇👇 YouTube ➲ https://youtube.com/channel/UCOX7tTMpW1lyPzmsRaqlo1Q?si=yfQVI_q-w7vYqwDL Telegram ➲https://t.me/Zena_Keminchu Facebook ➲https://www.facebook.com/profile.php?id=100064053341970 Tiktok ➲ http://www.tiktok.com/@hotissuemedia
без подписи
በአውሮፓ የተከሰተው ከባድ የሙቀት ማዕበል የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፋ መሆኑ ተሰማ በአህጉረ አውሮፓ የተከሰተው ከባድ የሙቀት ማዕበል ቢያንስ 18 ሰዎችን ለሞት መዳረጉ ተሰምቷል። ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ብሪታንያ እና ጣሊያንን ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ያጠቃው ይህ ከባድ ሙቀት፣ በብዙ ከተሞች ከዚህ ቀደም ያልተሰስተዋለ ከፍተኛ የሙቀት መጠን አስመዝግቧል። በፈረንሳይ ብቻ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኝ አካባቢ በሞቃት መኪና ውስጥ የነበሩ የ2 እና የ4 ዓመት ሕፃናት ይገኙበታል። የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ሕፃናቱን ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም ሕይወታቸውን ማትረፍ እንዳልቻሉ ሮይተርስ በዘገባው አመላክቷል። በተጨማሪም በቦርዶ ክልል ከ80 እስከ 95 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሦስት አዛውንቶች በሙቀቱ ሳቢያ በተከሰቱ የጤና ችግሮች ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። ሰዎች ከሙቀቱ ለማምለጥ ወደ ወንዞችና የመዋኛ ቦታዎች በመሄዳቸውም የ13 ሰዎች ሕይወት በሞትና በመስጠም አደጋ ማለፉም ተገልጿል። የሙቀት ማዕበሉ በበርካታ ከተሞች አዳዲስ የሙቀት ክብረ ወሰኖችን አስመዝግቧል፤ በዚህም፣ በፈረንሳይ የወይን ምርት ማዕከል በሆነችው ቦርዶ፣ የሙቀት መጠኑ 41.9 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል። በዚያው በፈረንሳይ ፖይቲየርስ፣ 41.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል። በስፔን ሰሜናዊ ከተማ ሳን ሴባስቲያን፣ የሙቀት መጠኑ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል። የብሪታንያ የአየር ትንቢያ ተቋም በዚህ ሳምንት የሰኔ ወር የሙቀት ክብረ ወሰን ሊሰበር እንደሚችል ያስጠነቀቀ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሙቀት መጠኑ እስከ 39 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል። ጣሊያን በበኩሏ ለ12 ከተሞች ከፍተኛው የአደጋ ደረጃ የሆነው የቀይ የሙቀት ማስጠንቀቂያ ታውጇል። የአየር ንብረት ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ይህ የሙቀት ማዕበል የተከሰተው ከሰሃራ በረሃ የሚነሳ ሞቃት አየር ወደ አውሮፓ በመግባቱ ነው። ባለሙያዎቹ አያይዘውም የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ እንደዚህ ያሉ ከባድ የሙቀት ማዕበሎችን ይበልጥ እያባባሰ መምጣቱን ጠቁመዋል። ======================== የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ Join 👇👇 https://t.me/Zena_Keminchu https://t.me/Zena_Keminchu
ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው‼️ ቶታል ነዳጅ ማደያ ኢትዮጵያን ለቆ ሊወጣ ነው‼️ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ75 አመታት በላይ በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ማቀዱ ተገለፀ፡፡ በመላው ኢትዮጵያ ወደ120 ያህል ማደያዎች ያሉት ይህ ተቋም ንብረቱን በሙሉ ለኦላ ኢነርጂ ወይንም ለቀድሞው ኦይልሊቢያ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ አፍሪካ ቢዝነስ ባቀረበው ዘገባ ሁለቱ ድርጅቶች በሽያጩ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፆ በምን ያህል ዋጋ ግብይቱ እንደተከናወነ ያለው ነገር የለም፡፡ ቶታል ኢነርጂስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከብራዚል፣ ፓኪስታንና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት የነዳጅ ማደያዎቹን ሸጦ የወጣ ሲሆን ይህ እርምጃውም የዚህ አካል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ 👇👇👇 Join https://t.me/Zena_Keminchu https://t.me/Zena_Keminchu
📱 Xenderን ለፋይል ማስተላለፊያ ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ እነዚህን 4 ድብቅ ጥቅሞች አምልጠውዎታል! ብዙዎቻችን Xenderን የምናውቀው ፎቶ እና ቪዲዮ ከስልክ ስልክ ለመላላክ ብቻ ነው። ነገር ግን ይህ መተግበሪያ ህይወታችንን የሚያቀሉ ሌሎች አስገራሚ ጥቅሞችን በአንድ ላይ ይዟል። መተግበሪያው ውስጥ ተደብቀው የሚገኙትን 4 ዋና ዋና ጥቅሞች እነሆ👇 1️⃣ ቪዲዮን ወደ MP3 (ኦዲዮ) መቀየር ጥቅሙ፡ የቪዲዮ ሙዚቃዎችን ወይም ንግግሮችን ወደ ኦዲዮ (Audio) ለመቀየር ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ መጫን አያስፈልግዎትም። አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ገብተው ከታች "ToMP3" የሚለውን ይጫኑ ➡️ "Select Video" የሚለውን በመንካት ቪዲዮዎን ይምረጡ። በሰከንዶች ውስጥ ወደ MP3 ይቀየርልዎታል። 2️⃣ የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎችን ማውረጃ (Downloader) ጥቅሙ፡ ከፌስቡክ፣ ከኢንስታግራም ወይም ከቲክቶክ ቪዲዮዎችን በቀላሉ ማውረድ ይችላሉ። አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ከታች "Social" የሚለውን ይጫኑ ➡️ ማውረድ የሚፈልጉትን የቪዲዮ ሊንክ (Link) ኮፒ አድርገው እዚህ ላይ ይለጥፉ (Paste ያድርጉ) ➡️ "Download" የሚለውን ይንኩ። 3️⃣ ያለ ኬብል ስልክን ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ጥቅሙ፡ ምንም አይነት የዩኤስቢ (USB) ኬብል ሳይጠቀሙ ፋይሎችን ከስልክ ወደ ላፕቶፕ/ኮምፒውተር በፍጥነት መጫን ያስችላል። አጠቃቀም፡ Xender ላይ በቀኝ በኩል ያለውን ምልክት ነክተው "Connect to PC" ይምረጡ ➡️ የስልክዎን Hotspot አብርተው ኮምፒውተርዎን ያገናኙ ➡️ ኮምፒውተርዎ ብሮውዘር (Browser) ላይ ስልኩ ያሳየዎትን የድር አድራሻ (IP Address) ይተይቡ። 4️⃣ አዲስ ስልክ ሲገዙ ዳታ ማዛወሪያ (Phone Clone) ጥቅሙ፡ አዲስ ስልክ ሲቀይሩ በድሮ ስልክዎ ላይ ያሉትን ስሞች (Contacts)፣ ፎቶዎች እና መተግበሪያዎች በአንድ ጊዜ ወደ አዲሱ ስልክ ያዛውራል። አጠቃቀም፡ በሁለቱም ስልኮች Xender ላይ "Phone Clone" የሚለውን ይምረጡ ➡️ አንዱን "Old" ሌላኛውን "New" በማድረግ ያገናኙ እና ሁሉንም መረጃዎች በቀላሉ ያዛውሩ። 👇👇👇 Join https://t.me/Zena_Keminchu https://t.me/Zena_Keminchu
ኢራን በአሜሪካ ጦር ተከበበች፤ ትራምፕ ለኢራን የ10 ቀናት ገደብ ሰጡ! https://youtu.be/e8V7QE0pyLQ?si=Qcp3D1MjlP74JHai
"ትራንፕን እናስተምረዋለን|We will teach Trump a lesson" ስትል ኢራን በአሜሪካ ላይ ዛተች!! የአለም ግዙፏ የጦር መርከብ "አብርሐም ሊንከን" ወደ ኢራን ድንበር አቅራቢያ በሆርሙዝ ባህር በኩል እየተጠጋች ነው። ነገሩ ወደለየለት ፍጥጫ እያመራ ነው። https://youtu.be/x3kNoQ7N0fM
https://www.facebook.com/share/p/1AqgDhXFaw/
без подписи
ሰበር መረጃ! ✍️ በጥንቃቄ የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ብቻ በዶላር ይከፈሉ ከዛ በቀጥታ ወደ ባንክ ሂሳብዎ በቀላሉ ይገባል!! በፍጥነት ተመዝገቡ፣ ለጓደኛ ጓብዙና እናንተም ተሸላሚ ሁኑ 👉 https://timebucks.com/?refID=227821608 👆👆👆 ከላይ ያስቀመጥኩላችሁን ድህረገጽ ይከፍላል ወይ ብዬ Google Gemini ን ጠይቄ መልሱን ተመልከቱ(100%) ከፋይ ነው ብሏል።ከታም ሰክሪንሻቱን ተመልከቱት ቶሎ ጀምሩት ቶሎ የተገኘ ምንጊዜም ከበረከቱ ተካፋይ ነው። First com first served!
без подписи
без подписи
ሰበር ዜና! ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር፡፡ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንትና ሰራተኞች ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ባልደረቦቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል በማለት መግለጫ አውጥቷል። ለነፃነት ወዳጅ ቤተሰቦች መፅናቱ እመኛለሁ።