tgindex
Ethio Ananas/ኢትዮ አናናስ🍍

Ethio Ananas/ኢትዮ አናናስ🍍

Статистика

ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸው የግል እይታዎች፣መጣጥፎች፣ግጥሞች፣ፎቶወች፣ስእሎች እና መሰል ስራዎች።

Последний пост
24 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
156
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
294
20 постов
Вовлечённость
188,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 4.  አሁን ካለንበት እንነሳ ሁኔታዎች እንዳልነበሩ ሲሆኑ በፊት የነበርንበት እያሰብን ያንንው የሕይወት ዘይቤ ለማምጣት ከመታገል መቆጠብ አስፈለጊ ነው፡፡ በወቅቱ ለውጥ ምክንያት አሁን ካለንበት ደረጃ ለመነሳት በፍጹም አንፍራ፣ አንፈርም፡፡ አሁን ካለንበት በመነሳት የምንችለውን ብቻ ስናደርግ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡ 5.  ከብዙ ሰው ሃሳብን ከመስማት እንቆጠብ ነገሮች ሳናስበው ሲለዋወጡና ስሜታችን ሲናወጥ የሰዎችን ሃሳብ መስማትና ወገን ማግኘት ያምረናል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ለተለያዩ ሰዎች አሳብ አጋልጦ ሊሰጠን ይችላል፡፡ ስለሆነም፣ ስሜታችን እስሚረጋጋ ድረስ የምናማክረውን ሰው ለይተን እንወቅ፣ የምንቀበላቸውንም ሃሳቦች አመዛዝነን እንውሰድ፡፡ በ Dr Eyob ካነበብኩት ተጋበዙልኝ መልካም እረፍት ። አንዋር ይመር (አናናስ)

  • ከዜሮ መጀመር የግድ ሲሆን! አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ የገነባነው ነገር ይፈራርሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የወደፊት ሕይወታችንን አብረን ለማሳለፍ ያቀድነው ሰው በድንገት ይለየናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ያቀድነው ዓላማ እንደማይሰራ እየገባን ይመጣል፡፡ እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ሲገጥሙን “ከዜሮ” የመጀመርን አቅምና ጥበብ ማዳበር የግድ ነው፣ ይቻላልም! ጥቂት መመሪያዎች! 1.  የሆነብንን ሁኔታ ሳንክድ እውነታውን እንቀበል እውነታውን መቀበል ማለት ሁኔታው እንደተከሰተ ወዲያውኑ ከመፍጨርጨርና እንዳልተከሰተ ለማሰብ ከመታገል ይልቅ የሆነውን አምኖ መቀበል ማለት ነው፡፡ የሆነው ሆኗል! ያለፈው አልፏል ያጣነውን አጥተነዋል! ይህንን እውነታ ስንቀበል አእምሯችን ጥርት ባለ መልኩ ማሰብ ይጀምራል፡፡ በክህደት መኖር ግን ግራ ያጋባናል፡፡   2.  በሁኔታው ማዘን የሂደቱ አካል እንደሆነ እንቀበል ከዜሮ የሚያስጀምር ሁኔታ ሲገጥመን ማዘን የጤናማ “ሰውነት” ምልክት ነው፡፡ ተስፋ ያደረግነው ከእኛ ሲወሰድ በሃዘን ስሜት ውስጥ መግባት የትክክለኛ ሂደት ምልክት ነው፡፡ ሆኖም፣ በዚያ ድባብ ውስጥ ላለመክረም የምችለውን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የሃዘን ስሜት ጊዜያዊ ሁኔታ እንጂ ቋሚ ልምምድ መሆን የለበትም፡፡ 3.  ሙሉ ሃላፊነትን እንውሰድ የሆነብን ነገር የሆነው በራሳችን ጥፋት ከሆነ ራሳችንን ከመውቀስ ይልቅ ከሁኔታው በመማር ሃላፊነትን እንውሰድ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዎች ካደረጉብን ወይም ማድረግ ሲገባቸው ካላደረጉልን ነገር የተከሰተ ከሆነ የምንሰጠው ምላሽ ሙሉ ሃላፊነቱ እኛ ጋር እንደሆነ አምነን በመቀበል ትክክለኛ ምላሽ እንስጥ፡፡

  • ሳነብ ካገኘሁት ➸➸➸➸➸ የወንድ (የሰዎችን) ሕይወት በቀስታ የሚያፈርሱ 20 ነገሮች 20 THINGS THAT QUIETLY RUIN A MAN’S LIFE:/: ➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸ 1.Laziness ➸ ስንፍና 2.Gambling ➸ ቁማር 3.Bad friends ➸መጥፎ ጓደኞች 4.Ignoring health ➸ጤናን መተው 5.Procrastination ➸ስራን ማዘግየት 6.Fear of failure ➸ውድቀትን መፍራት 7.Victim mindset ➸የተጎጂ አስተሳሰብ 8.Porn addiction ➸ የፖርኖ (ወሲብ)ሱስ 9.No clear goals ➸ ግልፅ ግብ አለመኖር 10.Lack of self respect ➸ራስን አለማክበር 11.Constant complaining ➸ሁልጊዜ መንገራገር 12.Jealousy of others ➸ሌሎችን መቀነስ (ቅንዓት) 13.Refusing responsibility ➸ኃላፊነትን አለመቀበል 14.Alcohol abuse ➸ አልኮልን ከመጠን በላይ መጠቀም 15.Wasting time online ➸ጊዜን በመስመር ላይ መጣል 16.Poor sleep routine ➸ የእንቅልፍ ልማድ መጥፎ መሆን 17.Chasing temporary pleasure ➸ጊዜያዊ ደስታን መከታተል 18.Weak discipline ➸ደካማ ዲሲፕሊን (ራስን መቆጣጠር እጥረት) 19.Living for validation ➸ ለሌሎች ማረጋገጫ (approval) መኖር 20.Overspending money ➸ገንዘብ ከመጠን በላይ ማውጣት (ማባከን) በ አንዋር ይመር (አናናስ)

  • አቡበክር እንድሪስ በአንድ ወቅት በወሎ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ  የነበረ አንድ ፀሀፊ ልጅ  ይነጋል (ከጨለማ ወዴ ብርሃን/softly - bright 2012 ዓ.ም) በሚል ርዕስ በፃፈው መፃሀፋ ላይ የሚከተሉትን ቃላቶች በዚህ መንገድ ተርጎሟቸዋል። እናተስ ምን ያህል ተስማማችሁ ? እነሆ ላጋራችሁ። ➸ዋዛ ፈዘዛ : አቅም የሌላቸው ዱላ ነው ➸ሐሜት : ያለመሳሪያ ሰው መግደል ነው ➸ብስጭት : ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው ➸ማጉረምረም : ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው ➸ቁጣ : ከስድብ የማያንስ የክፋ አድራጎት መሰረት ነው ➸ችኮላ : የትእግስት ጠላት የፀፀት አባል !! ልጁም ወኔ ነው ➸ውሸት : እውነተኛ ሰው በስውሩ የሚጎዳበት ረቂቅ ጠር ነው ➸መንፈግ : የተቸገረውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፈለግ ነው ➸ተስፋ :ከማጣት ወደ ማገኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነው ➸ማሽማጠጥ : ሰውን የሚደበድቡበት የእነ እዩኝ አላዩኝ ባይ ዱላ ነው ➸በሀሰት መማል : ሰው ለማዘናጋት ሆን ብለው የያዙት የትኩረት መሳቢያ ነው ➸ምኞት : የቁም ህመም ነው ህመሙ በሀሳብ ተፀንሶ በቅዥት የሚወለድ ነው ➸መሳደብ :ህሊናን የሚያቆስል ቶሎ የማይድን በስልት የሚያገኙት የስራፈቶች በገና ነው በ አንዋር ይመር (አናናስ)

  • 🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍 "የተበላሸውን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል የሚናገሩትን ሰዎች አዳምጡ እንጂ ሰዎችን በችግሮች ላይ ቂም እንዲይዙ የሚያደርጉትን አይደለም። ሌሎችን ብቻ የሚወቅሱትንሳይሆን ነገሮችን እንዴት መስተካከል እንዳለበት ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ያዳምጡ።" ~ ሞሊ ኢቪንስ 🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍

  • 🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍 ብዙ በአላህ እገዛ የታለፉ ከባድ ቀናት ወደፊት ለምታጣጥመዉጥዑም ጊዜ የተከፈሉ ቀብዶች ናቸዉ ። ቀብድ የከፈልክበት ሰላምህ እስኪመጣ ዝም ብለህ ፈገግ በል ! 🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍

  • ወይ እንዳልታገል ከእልፍ ተጣብቄ ከመጣ ከሄደው እንዳላልፍ ስቄ ወይ አልሰበሰብ አልተው እንደ ዋዛ ወይ ምኞቴ አይበርድ ወይ ልቤ አይገዛ ወይ እንዳልዘረጋ አልያ እንዳላጥፍ የእጣ ፋንታን ነገር እጅ መጥፎ እንዳይጥፍ ወይ እንዳልቀመጥ ወይ እንዳልረመድ ሆና አስቸገረችኝ ህይወት መንታ መንገድ ። ቢሆንም ግን ! አልሃምዱሊላህ 🟡🟢🔴🍍አንዋር ይመር (አናናስ)🟡🟢🔴

  • አንዬ ሆይ ! አንተ ራሴ የምወድህ እስኪ ዛሬም ላስቸግርህ ሰው እንደሆን : ዝም ያልክ እንደሁ ሞኝ ይልሃል ዝቅ ስትል ይረግጠሀል ቢሆንም ግን አንየ ሆይ! እንደ መሬት ሁሉን ቻለው አንዳንደዬ መሸነፍም ማሸነፍ ነው ። "አንዳንድ ሰው ቤት እየሰራህለት ሚስማር ይነፍግሃል ።"  አይገርምም ! 🟢🟡🔴✒️ አንዋር ይመር (አናናስ)🟢🟡🔴

  • без подписи

  • 👆👆👆ከምስሉ በመነሳት አዝመራው ሲደርስ እሸቱ ሲያአፈራ ምድሩ ሰላም ሲሆን መስከረም ሲበራ ከብርቱካን ፍሬ ከጣዝማ ወላላ ናፍቆቴን ላስታግስ በብዙ ልበላ ከሙላቱ ወራት ከፀደይ ደርሼ ሙሉአለም ሆናልኝ ተስፋዬን ለብሼ ሲሳይ ሲሰበሰብ በረከት ሲሰፋ ምነው በነፃነት ብላ እሚል ሰው ጠፋ ? just for enjoyment በሚለው። 💚💛❤✒️ አንዋር ይመር (አናናስ)💚💛❤

  • አልሃምዱሊላህ ! ያረብ ዛሬን እንድኖር የፈቀድክልኝ ጌታ ሶብር :ተቅዋ : ኢስቲቃማን አንተ ወፍቀኝ።  ያኢላሂ ቀኔን አንተን የማስታውስበት ከወንጀል አንተን ፈርቼ የምሸሽበት ወደ አንተ በኸይር ነገር የምቃረብበት ቀን ታደርግልኝ ዘንድ እጠይቀዋለሁ። ያ ጀባር የተሰበረውን ልቤን ትጠግንልኝ ዘንድ : አይቶ ማለፍን ሰምቶ መቻልን አንተ ወፍቀኝ ውብ በሆኑ ስሞችህ እጠይቅሃለሁ ያ ከሪሙ : ያ ሀኪሙ ያሰብኩትን ሳይሆን ያሰብክልኝን የፈለኩትን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ትሰጠኝ ዘንድ ያንተው ባሪያ እለምንሃለሁ። አላህዬ በቃ በለኝ ከመከራ ከጭንቀት አውጣኝ  ያ ቅዱሱ ሀገሬን ሰላም አርገህ ወገኔን ደስታውን ትመልስለት ዘንድ በታላቁ ሸህ ራመዳን ተማፀንኩህ 😭😭😭😭 💚💛❤አንዋር ይመር (አናናስ) 💚💛❤

  • " ህዝብ መገዛት : ገዥዎችም መግዛት ሲያቅታቸው ያኔ አብዮት ይመጣል::" ሌኒን

  • እስኪ ሃሳቤን አንድ አጥር ባለች የይስማዕከ ወርቁ ግጥም ልጀምር : "የኔማ ጓደኛ ይሄው እስከ ዛሬ ፌቴ ተጓልቶ አትችልም ይለኛል የሱን አለመቻል እኔ ውስጥ ከቶ" ትላለለች። የእናንተን ባላውቅም እኔ መስታወት ፊት ስቆም በአእምሮዬ የሚመጡት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው። እንደት ካለችሁኝ: በግማሽ የተሰበረ (ከቆሸሽ) መስታወት ፊት ስቆም ያ! አትችልም:ትችላለህ ፣አቅም አለህ ፣ አቅም የለህም ታምራለህ : አታምርም እያለ ባልጠራ እይታ ተወዛግቦ የሚወዛግብ ግማሽ  እኔቴን የሚነግረኝ ጓደኛዬ ትዝ ይለኛል። ሌላው የተጋነነ የመስታወት እይታ ፊት ስቆም የሌለ ማንነቴን እየነገ አብሮ ለመዝለቅ ብቻ ጉም የሚስጨብጠኛ ወዳጄ ይታወሰኛል። ሶስተኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ትክክለኛው መስተዋት ሲሆን ከዚህ መስታወት ፊት ስሆን ደግሞ ጉድፌን እያሳዬ አቅሜን እየለካ ማንነትቴን የሚገልጽልኝን ትክክለኛ ጓደኛዬን አስባለሁ። ማውራት የፈለኩት ስለመስተዋቱ አይደለም። እውን ሁላችንም የያዝናቸው ጓደኟች ለኛ ያላቸው አመለካከት ወይም እይታ እውነታ እና ሚዛናዊ ነውን? አንዋር ይመር (አናናስ)

  • без подписи

  • አስተያየት ካለወት 👉 @Anu0932

  • без подписи

  • አልሞት ባይ ተጋዳይ! ፈረሱን አግርታ ሜዳውም ያው ብላኝ አልጨክንም ብሎ ልቤ ነው ያስበላኝ . . . በቃ በዚህ ይብቃ ደግሞ የምን ግጥም በገዛ ብእሬ ሽንፈቴን አልገልጥም። 🟢🟡🔴ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር🟢🟡🔴 አንዋር ይመር (አናናስ)

  • ወይ ዘንድሮ🙆‍♀ የ9 እና 10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ልጆቹን በፒንሳ እየቆነጠጠ አስገድዶ የደፈረው ወላጅ አባት በ20 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ !! 🟢🟡🔴የብላቴናዋ እርግማን🟢🟡🔴 "ያልተኖረ ልጅነቴ ድንቡሽ ገላ ሰውነቴ ጽጌረዳ ተቀጠፍኩኝ በአባቴ እንቡጥ ጨቅላ ንፁህ ደሜ ህልሜ ጠፋ ደፈረሰ በወንድሜ የነገዬን ተስፋ ለጋረዳችሁ ብርሃኔን በፅልመት የቀየራችሁ አሚን በሉ እርግማን ቢጤ ልመርቃችሁ አሚን…

  • без подписи

  • ስሙማ.......... እውነት ጠፍታኝ ስፈልጋት በእሷ ድርሻ ውሸት ስጋት ያልጋረዳት የሀዘን ማቅ የት ደረሰች የእውነቷ ሳቅ ? ቢያጋጥምም መንገድ መሳት ይቅር የት ነው በአንዴ መርሳት ? ሳቁ! ናፍቆኝ ፍቅር! ጠፍቶኝ ህብረት! አምሮኝ ደስታ! አምልጦኝ ይሄ ሁሉ ተሰውጦኝ ስፈልገው............. ስፈልገው ............ ስፈልገው ............ እልል! በሉ የጠፋችሁ ዝቅ በሉ ላሳያችሁ ። ዝቅ ዝቅ አሁንም ዝቅ . . . ከላይ ባጣው ዝቅ ብዬ ባስተውለው ከልጅ ጋር ነው ሁሉም ያለው። 🟢🟡🔴ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!🟢🟡🔴 አንዋር ይመር (አናናስ)