C R R S A - የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
СтатистикаCRRSA is a government organization established by law to deliver Civil Registration & Residency services in Addis Ababa. The agency is responsible for registration of vital events & issuance of residency identification within the domain of the city.
- Последний пост
- 14:26
- Последнее чтение
- 20:14
- Постов за неделю
- 81
- Всего постов
- 137
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 812
- 1/48двое суток
- 930
- 1/72трое суток
- 1 003
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሀሰተኛ መረጃን በመከላከል ግልጽ፣ ተደራሽና ተዓማኒ አገልግሎትን ማረጋገጥ CRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋሙ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የብልሹ አሰራር ምክንያቶችንና የአደጋ ምንጮችን በመለየት፣ተገቢ የመከላከያ ሥርዓቶችን በመዘርጋት እና የሥራ አፈጻጸምን በቋሚነት በመከታተል ብልሹ አሰራርን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችል አቅጣጫ በማስቀመጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ሠራተኞች በሕግና በሥነ-ምግባር መርሆች መሠረት በታማኝነት፣ በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በፍትሐዊነት እንዲሠሩ ማበረታታት፣ የተገልጋዮችን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና ለብልሹ አሰራር የማይመች የሥራ አካባቢ በመፍጠር ለከተማዋ ነዋሪዎች ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዲጂታል ዘመን መረጃ በፍጥነትና በስፋት የሚሰራጭ በመሆኑ፣ ትክክለኛ መረጃን ከሀሰተኛና ከተዛባ መረጃ መለየት እየተፈታተነ መጥቷል። ሀሰተኛ መረጃ በተለይም ከመንግሥታዊ ተቋማት፣ ከሕዝብ አገልግሎቶችና ከማኅበረሰብ ከሚመለከቱ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሲሰራጭ የሕዝብን ግንዛቤ ሊያዛባ፣ አላስፈላጊ ጥርጣሬን ሊፈጥር እና በተቋማት ላይ ያለውን እምነት ሊያሳንስ ይችላል። በመሆኑም ሀሰተኛ መረጃ በሚሰራጭበት ጊዜ በተረጋገጠ ማስረጃ ላይ በመመስረት በፍጥነት፣ በግልጽነትና በሙያዊ አግባብ ማስተባበል አስፈላጊ ነው። ይህም ሕዝብ ትክክለኛውን መረጃ ከተዛባ መረጃ እንዲለይ ከማገዝ ባሻገር የተቋሙን ተዓማኒነትና የሕዝብ እምነት ለማጠናከር ያስችላል። የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሚሰጠው አገልግሎት ዙሪያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ፣ የተዛቡ ወይም ከእውነታው የራቁ መረጃዎችን በመለየት፣ በተረጋገጠ መረጃ በመደገፍ እና ተገቢውን የማስተባበያ መልዕክት በወቅቱ ለሕዝብ በማድረስ የተሳሳተ ግንዛቤን ለመቅረፍ የሚያስችል አቅጣጫ ለመዘርጋት አስፈላጊ ነው። የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ለማረጋገጥ ግልጽነት፣ተጠያቂነትና ተዓማኒነት በማጠናከር ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው ፈጣን፣ተደራሽ እና ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ እነዚህንም በዝርዝር ስንመለከታቸው 1ኛ.የነዋሪዎችን መረጃ ማደራጀት (DMS):-የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎችን መረጃ ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋ በመከላከል እንዲሁም ከሰው ንክኪ የፀዳ ለማድረግ የነዋሪዎችን መረጃ ወደ ሶፍት ኮፒ የመቀየር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ይህ አገልግሎት መረጃዎችን ከአዳጋ ከመጠበቁም ባሻገር ነዋሪዎች በየትኛውም ቦታ በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል፤በተጨማሪም ያለባለቤት ፈቃድ ማንኛውም ሰው ወይም ባለሙያ ያለባለቤቱ ፈቃድ ተጨማሪ መረጃ መስጠት እንዳይቻል በማድረግ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለመከላል ያስችላል፡፡ 2ኛ.የኦንላይን አገልግሎት መጀመር፡-ይህ አገልግሎት ነዋሪዎች በየትኛውም ቦታ ሆነው እጃቸው ላይ በሚገኝ የቴክኖሎጂ አማራጭን በሞባይል ስልክ ወይም ኮምፒውተር በመጠቀም አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበት የዲጂታል አሰራር ስርዓት ሲሆን የፊት ለፊት አገልግሎትን በማስቀረት ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ያለው የአገልግሎት አማራጭ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ 3ኛ.የኦዲት ስርዓት መዘርጋቱ፡-የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ በኤጀንሲው የሚሰራጩ የህትመት ውጤቶችን ትክክለኛ አገልግሎት መስጠታቸውን እና ለታለመለት ዓላማ ስለመዋላቸው በየጊዜው የኦዲት ስርዓት በመዘርጋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ 4ኛ.የተጠያቂነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱ፡ ኤጀንሲው ብልሹ አሰራርን እና ሌብነትን በቁርጠኝነት እየተከላከለ ሲሆን ተፈፅሞ ሲገኝም አስቸኳይ እርምጃ ወስዷል፣እየወሰደም ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በበጀት ዓመቱ ከማዕከል እስከ ወረዳ በሚገኙ ተጠያቂ የተደረጉ ባለሙያዎች፣አመራሮች እና ተገልጋይ ደንበኞች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ማሳያ ይሆናሉ፡፡ 5ኛ.የብልሹ አሰራር የጥቆማ ስርዓት የዘረጋ መሆኑ፡-ኤጀንሲው ብልሹ አሰራርን በመከላከል ፈጣን ተደራሽ እና የህብረተሰቡን እርካታ ያረጋገጥ አገልግሎት ለመስጠት የነፃ ጥሪ መቀበያ መስመር በ7533 ጥቆማዎችን እና ቅሬታዎችን በመቀበል እና በመከታተል አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በእውነታና በሚታመኑ ምንጮች ላይ የተመሠረተ መረጃን ከሚያሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን በመከታተል፣ ሕዝብን ከሚያሳስቱ እና ትክክለኛ ካልሆኑ የመረጃ ምንጮች ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምንም አይነት የሚዲያ ፈቃድ በሌላቸው እና ህብረተሰቡን ለማሳሳት ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ አካላት ራሱን እንዲጠብ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ከኤጀንሲው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመከታተል፣በነፃ የስልክ መስመር 7533 ላይ በመደወል እንዲሁም ከትክክለኛ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች መረጃ እንዲወስድ ኤጀንሲው ጥሪ ያቀርባል፡፡ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpres ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office ኢንስታግራም (Instagram)
без подписи
ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ስለማሳወቅ CRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ም ዋዜማ ሬዲዮ ሃገር ዉስጥ ምንም የዘገባ ፍቃድ ሳይኖረዉ በቀን 12/12/2018 ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር የሰራዉ ዘገባ ሚዛኑን ያልጠበቀና አግባብነት የሌለዉ አሉባልታ መሆኑን እያሳወቅን፤ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጉዳዮች ተጠያቂ የሆነ ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ተቋሙ ምን እየሰራ እንዳለ ሳያረጋግጥ የተሳሳተ ዘገባ በመስራት ተቋሙ እየሰራ ያለዉን ሪፎርም ለማጠልሸት የተሰራ ዜና መሆኑን በማወቅ ኤጀንሲዉ አሁን ላይ በዉስጡ ያሉ ህገ ወጥ አሰራሮችን በአግባቡ እየታገለና ተጠቂነትን እያሰፈነ ሪፎርም ያደረገ ሲሆን ተገልጋዩ ከቤቱ ሳይወጣና ባለሙያ ጋር መገናኘት ሳያስፈልገዉ የኦንላይን አገልግሎት ጭምር በመስጠት ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለዉ ደረጃ ላይ እየደረሰ ያለ ሲሆን፤ችግሮች ካሉም ኤጀንሲዉ በዘረጋዉ ነፃ የስልክ መስመር 7533 በመቀበል ተጠያቂነትን እያሰፋነ መሆኑን እያሳወቅን፤ የተሰራዉ ዘገባ አገር ውስጥ በሌለው ሪፖርተር በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ ሄዶ ይህን ዘገባ ሊሰራ ቻለ? በኤጀንሲው በአካል ተገኝቶ ለምን መረጃ መውሰድ አቃተው? አዲስ አበባ ውስጥ ሳይገኙ ስለኤጀንሲው ትክክለኛ መረጃ በምን የዜና መስፈርትና የሙያ ስነምግባር ማሰራጨት ቻለ? ስለሆነም የሰራውን ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ ፈጥኖ በማስተካከል ሚዛናዊ አድርጎ እንዲያቀርብና ከገፁ ላይ አንስቶ ይቅርታ እንዲጠይቅ እያሳሰብን በህግ አግባብ ጉዳዩን የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/ ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935
без подписи
без подписи
без подписи
ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ስለማሳወቅ CRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ም ዋዜማ ሬዲዮ ሃገር ዉስጥ ምንም የዘገባ ፍቃድ ሳይኖረዉ በቀን 12/11/2018 ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር የሰራዉ ዘገባ ሚዛኑን ያልጠበቀና አግባብነት የሌለዉ አሉባልታ መሆኑን እያሳወቅን፤ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጉዳዮች ተጠያቂ የሆነ ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ተቋሙ ምን እየሰራ እንዳለ ሳያረጋግጥ የተሳሳተ ዘገባ በመስራት ተቋሙ እየሰራ ያለዉን ሪፎርም ለማጠልሸት የተሰራ ዜና መሆኑን በማወቅ ኤጀንሲዉ አሁን ላይ በዉስጡ ያሉ ህገ ወጥ አሰራሮችን በአግባቡ እየታገለና ተጠቂነትን እያሰፈነ ሪፎርም ያደረገ ሲሆን ተገልጋዩ ከቤቱ ሳይወጣና ባለሙያ ጋር መገናኘት ሳያስፈልገዉ የኦንላይን አገልግሎት ጭምር በመስጠት ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለዉ ደረጃ ላይ እየደረሰ ያለ ሲሆን፤ችግሮች ካሉም ኤጀንሲዉ በዘረጋዉ ነፃ የስልክ መስመር 7533 በመቀበል ተጠያቂነትን እያሰፋነ መሆኑን እያሳወቅን፤ የተሰራዉ ዘገባ ፈጥኖ በማስተካከል ሚዛናዊ አድርጎ እንዲያቀርብና ከገፁ ላይ አንስቶ ይቅርታ እንዲጠይቅ እያሳሰብን በህግ አግባብ ጉዳዩን የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935 ቲክቶክ (TikTok): ww
https://web.facebook.com/reel/922768250869669
“ኤጀንሲው አገልግሎቱን ወደ ልህቀት ደረጃ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ ነው” አቶ ጥጋቡ ሹመይ CRRSA:ነሐሴ10/2018ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎቱን ወደ ልህቀት ደረጃ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ልህቀትን መገንባት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ አመራሮች እና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡ የኩነት እና የነዋሪነት አገልግሎቶችን ታሪካዊ አመጣጥ መነሻ በማድረግ አሁን የደረሰበትን ነባራዊ ሁኔታ ያስረዱት አቶ ጥጋቡ በጋራ ጠንክሮ በመስራት እና የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት የነበሩ ውስንነቶችን በማረም የተጀመሩ ሪፎርሞችን በማጠናቀቅ ተቋሙን ወደ ልህቀት ማሸጋር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከተቋማት ጋር በቅንጅት የምንሰራው የኩነት ምዝገባን ለማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ ጥጋቡ የአሰራር ስርዓትን ዕውን ለማድረግ፣ የምዝገባ ጥራትን ለማረጋገጥ፣ከምዝገባ የተገኘ መረጃን ለታለመለት ዓላማ ለማዋል እንዲሁም የኩነት መዝገባ ሽፋንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልፀው ኩነት በሚከሰትባቸው ተቋማት ሙሉ አገለግሎት በመስጠት ሽፋንን ከማሳደግ ወደ ተሟላ ምዝገባ መሸጋገር እንደሚገባ ምክትል ዋና ዳይሬከተሩ አስገንዝገበዋል፡፡ ወደ ስራ የገባው አዲሱ ሲስተም፣ዌብ2 ሪፎርም፣ISO 9001:2015 QSME አሰራር፣የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መሻሻል ፣በወረዳዎች የነዋሪነት ዲጅታል መታወቂያ ህትመት መጀመሩ ልህቀት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታች መሆናቸውን አቶ ጥጋቡ አስረድተዋል፡፡ በዕለቱ የቫይታል ስትራቴጅ ምዝገባ ምንነት እና አስፈላጊነት የቀረበ ሲሆን በመድረኩ የተሳተፉ የክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት አመራሮች እና ቡድን መሪዎች፣የኤጀንሲው የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት የተወያዩ ሲሆን የተጀመረውን ሪፎርም ከግብ በማድረስ የተቋሙን ልህቀት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/@CRRSA1935 ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/@aacrrsa_head_office ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/ ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи