- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 682
- 1/48двое суток
- 781
- 1/72трое суток
- 842
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በተያዘው በጀት አመት ከ250 ኪ.ሜ በላይ ከፍተኛና መለስተኛ የውሃ መስመር ለመዘርጋት ታቅዷል! ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም (AAWSA) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት የከተማዋን የውሃ መስመር መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የተለያዩ የውሃ መስመር ዝርጋታ ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ ይዟል። በዕቅዱ መሠረት 16.25 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ውሃ መስመር እና የውሃ መስመር ማዛወሪያ ሥራ ይከናወናል። የከፍተኛ ቧንቧ ዝርጋታ ስራው የውሃ ምርትና ስርጭት ተግባራትን ለማቀላጠፍ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሳይቶች ፣ በተለያዩ የመንገድ ግንባታ አካባቢዎች እንዲሁም ለመስመር ማዛወሪያ አገልግሎት የሚውል ነው ። በተጨማሪም 235.4 ኪሎ ሜትር የመለስተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል ለማከናወን ታቅዷል። የ2019 ዓ.ም. የውሃ መስመር ዝርጋታ ዕቅድ የውሃ ምርትና ስርጭትን ለማሻሻል፣ የውሃ መስመር አውታሩን ለማስፋፋት እና ተጨማሪ አካባቢዎችን ከውሃ አገልግሎት ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው።
ባለስልጣኑ በ2019 በጀት አመት 130 ሺኅ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችል ውሃ እያለማ ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ስርጭት ሲገቡ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (AAWSA) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በከተማዋ የሚታየውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማሟላት የውሃ ማምረት አቅሙን በቀን በ130 ሺህ ሜትር ኩብ የሚያሳድጉ ሁለት ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በበጀት ዓመቱ ማብቂያ ድረስ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት አቅዷል ። ይህም የከተማውን የውሃ ፈረቃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋከል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በበጀት ዓመቱ ቀደም ብሎ መልማት የጀመረው የጭቋላ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኩብ ንጹህ መጠጥ ውሃ በማምረት ወደ ስርጭት ሲስተም የሚያስገባና ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ የከተማዋን ህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ በተጨማሪም በቀን እስከ 30 ሺህ ሜትር ኩብ ውሃ በተለያዩ ቦታዎች በማልማት ከ300 ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዷል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ባለስልጣኑ ወደ ስርጭት ከሚያስገባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ባለስልጣኑ እነዚህን ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት አስፈላጊውን የክትትልና ድጋፍ ስራ እያከናወነ ይገኛል። ----------------------------------- መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኪን ይጫኑ https://linktr.ee/AAWSA_Social_media
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ባከናወናቸው የብክነት ቅነሳ ስራዎች ከ108 ሺህ ሜትር ኩብ በላይ ንጹህ ውሃ ከብክነት አደነ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (AAWSA) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በከተማዋ የሚታየውን የውሃ እጥረት ለመቀነስ እና ያልተቆጠበ ውሃ ብክነትን ለመግታት ባከናወናቸው የተለያዩ የቴክኒክና የኦፕሬሽን ስራዎች ከፍተኛ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አስታወቀ። ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከተከናወኑት አበይት ስራዎች መካከል 24.43 ኪሎሜትር ያረጁና በብልሽት የሚያፈሱ መስመሮችን በመቀየር ብቻ 38,311 ሜትር ኩብ ንጹህ ውሃ ከብክነት ማዳን ተችሏል። በተጨማሪም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ 3,366 ቆጣሪዎችን በመቀየር 70,338 ሜትር ኩብ ውሃ ማዳን ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ ባለስልጣኑ መስመሮችን በመቀየር እና ያረጁ ቆጣሪዎችን በስፋት በመተካት ከ108,600 ሜትር ኩብ በላይ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ከብክነት ማዳን የቻለ ሲሆን፣ ይህም በርካታ ደንበኞችን ተጨማሪ የውሃ አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ አስችሏል። በመጨረሻም ባለስልጣኑ በቀጣይም የዲጂታል አሰራሮችን እና የቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚታዩ የውሃ ብልሽቶችንና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በነጻ የጥሪ ማዕከል 906 በመጠቆም የተቋሙ አጋርነቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል። ----------------------------------- መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኪን ይጫኑ https://linktr.ee/AAWSA_Social_media
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ210 ኪሎ ሜትር በላይ የከፍተኛና መለስተኛ የውሃ መስመር ዝርጋታ አከናውኗል (ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም - AAWSA) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የመዲናዋን ንጹህ ውሃ አቅርቦትና ስርጭት ለማሻሻል በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን የከፍተኛና የመካከለኛ (መለስተኛ) ውሃ መስመሮች ዝርጋታ እንዲሁም የጥገና ስራዎች በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል። ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ 12.00 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ መስመር ለመዘርጋት ታቅዶ 11.98 ኪሎ ሜትር (100%) ያከናወነ ሲሆን መለስተኛ የውሃ መስመር ደግሞ 201.02 ኪሎ ሜትር ለመዘርጋት ታቅዶ 198.44 ኪሎ ሜትር የእቅዱን 99% አከናውኗል፡፡ የመስመር ዝርጋታ ስራው ሙሉ ለሙሉ በራስ ሀይል የተሰራ ሲሆን፡- ለውሃ ምርትና ስርጭት ማሻሻያ ፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ፣ ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የተከናወነ የመስመር ቅየራ ስራ ያጠቃልላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የውሃ ብክነትን ለመቀነስና አቅርቦቱን ለማስተካከል በተደረገው ጥረት 895 ኪ.ሜ የመካከለኛ መጋቢ መስመሮችን ለመጠገን ታቅዶ 872 ኪ.ሜ የእቅዱን 97 በመቶ መጠገን ተችሏል፡፡ በተጨማሪም 1,093 የስብራት አደጋዎች በከፍተኛ መስመሮች ላይ ያጋጠሙ ሲሆን በፍጥነት ጥገና ተደርጎላቸዋል። ይህ የውሃ መስመር ዝርጋታና የጥገና ስራ ተቋሙ የህብረተሰቡን የንጹህ ውሃ ጥያቄ ለመመለስና የውሃ ብክነትን ለመቀነስ የሚያደርገውን አጠቃላይ ጥረት የሚያፋጥን ነው፡፡ ----------------------------------- መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኪን ይጫኑ https://linktr.ee/AAWSA_Social_media
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በተጠናቀቀው በጀት አመት ባለስልጣኑ ከ91 ኪሎ ሜትር በላይ የፍሳሽ መስመር በተለያዩ አካባቢዎች ተዘርግቷል፡፡ ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም (AAWSA) በበጀት አመቱ የፍሳሽ መስመር ኔትወርክን በማስፋት የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋንን ለማሳደግ ከፍተኛ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለይም የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ጥናትና ዲዛይን ሥራ በራስ ኃይል 230.94 ኪ.ሜ በመከናወኑ የዕቅዱ 116.4 በመቶ አከናውኗል ። ይህ አፈጻጸም ተቋሙ የውስጥ አቅሙን በተሻለ መልኩ በመጠቀም የፍሳሽ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከግንዛቤ እስከ አፈጻጸም ለማስኬድ እየሠራ መሆኑን ያሳያል። ለዚህ ውጤት ከፍ ማለት ከወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር በተያያዙ ሥራዎች ላይ በራስ ኃይል ሰፊ የጥናትና ዲዛይን ሥራ መከናወኑ ይጠቀሳል። የጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን በውስጥ አቅም ማከናወን የፕሮጀክት ዝግጅትን ለማፋጠን፣ የሥራ ቅንጅትን ለማሻሻልና በቀጣይ የሚከናወኑ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታዎች የተሻለ መሠረት እንዲኖራቸው ያግዛል። በመስመር ዝርጋታ ሥራም በራስ ኃይልና የሦስተኛ ወገን 93.05 ኪ.ሜ ለማከናወን ታቅዶ 91.52 ኪ.ሜ በመፈጸሙ የዕቅዱ 98 በመቶ ተሳክቷል። ይህም የተቋሙን የራስ አቅም ከውጭ ባለሙያና ተቋማት አቅም ጋር በማጣመር ሥራዎችን በስፋት ለማከናወን የተከተለውን የተቀናጀ አሠራር ያሳያል። በአጠቃላይ፣ የጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን በራስ ኃይል ከዕቅድ በላይ ማከናወንና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉ የፍሳሽ መሠረተ ልማትን ለማስፋት የሚደረገው ጥረት በተግባር እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ የተቋሙን የውስጥ አቅም በማጠናከርና ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመቀናጀት የሚከናወኑ ሥራዎችም የከተማዋን የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን ለማሳደግና ዘላቂ የፍሳሽ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጠንካራ መሠረት ይጥላሉ።
без подписи
без подписи
без подписи