Ethiopian Lottery Service - የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
СтатистикаThe Official Telegram Channel of Ethiopia Lottery Service! ይህ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ብቸኛ የቴሌግራም ቻናል ነው።
- Последний пост
- 13:18
- Последнее чтение
- 18:32
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 97 667
- 1/48двое суток
- 111 926
- 1/72трое суток
- 120 716
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ትኬት ቆርጠዋል? ከወዲሁ ትኬቱን በአቅራቢያዎ ካሉ የሎተሪ አዟሪዎች በመቁረጥ ዕድልዎን ይሞክሩ ፡፡ ዕጣው ጳጉሜ 5ቀን 2018 ዓ.ም ይወጣል ። በ1️⃣ኛ ዕጣ 2️⃣0️⃣ሚሊየን ብር በ2️⃣ኛ ዕጣ 1️⃣0️⃣ ሚሊየን ብር በ3️⃣ኛ ዕጣ 5️⃣ ሚሊየን ብር በ4️⃣ኛ ዕጣ 2️⃣ሚሊየን ብር በ5️⃣ኛ ዕጣ 1️⃣ ሚሊየን ብር እና ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች ይዟል ፡፡ መልካም ዕድል ! የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
በሱሉልታ ሸገር ነዋሪ የሆነው ወጣት ሀብታሙ ገላና በቆረጠው ሚሊየን ሎተሪ በ7ኛ ዕጣ የ3 ሚሊየን ብር እድለኛ ሆኗል፡፡ ወጣት ሀብታሙ በጉልበት ስራ የተሰማራ ሲሆን በደረሰው ገንዘብ የከብት እርባታ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጾልናል፡፡
ከቶ እንዳያመነቱ! ይቁረጡ ------ ከቶ እንዳያመነቱ በጊዜ ይሞክሩ ------ ሳይረፍድ ሰዓቱ ኢንቨስተር ይሁኑ ----- ሀገር ሚገነባ ፈጥነው እንዲከብሩ ---- ከሎተሪ አምባ
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ኪዳኔ ገበየ በቆረጠው 49 ዙር አድማስ ዲጅታል ሎተሪ በ4ኛ ዕጣ 7 መቶ ሺህ ብር እድለኛ ሆኗል፡፡ ወጣት ኪዳኔ በራይድ ሾፌርነት የሚተዳደር ሲሆን የደረሰውን ገንዘብ ወደ ፊት እቅድ በማውጣት እንደሚጠቀምበት በቢሮአችን በነበረው ቆይታ ገልጾልናል፡፡
መደበኛ ሎተሪ 1770ኛ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል::
በአዊ ዞን የኮሰበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ሽፈራው በቆረጡት 49ኛ ዙር አድማስ ዲጅታል በ1ኛው ዕጣ የ4 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል፡፡ አቶ ጌታቸው በንግድ ስራ የተሰማሩ ሲሆን የደረሳቸውን ገንዘብ ንግዳቸውን ለማጠናከር እንደሚያውሉት በቢሮአችን በነበራቸው ቆይታ ወቅት ገልፀውልናል፡፡
ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም የሚወጣው እንቁጣጣሽ ሎተሪን በመቁረጥ በቤትዎ ድርብ በዓል ያክብሩ፡፡ እንቁጣጣሽ ሎተሪ …… ህይወትን ቀያሪ ዕድልን ………… አብሳሪ፡፡ አዲስ ዓመት ደርሶ……. የሚያደላድለው ይቁረጡ እንቁጣጣሽ…. ብዙ አማራጭ አለው፡፡
በአርሲ አዳባ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሎ ዩሱፍ በቆረጡት 49ኛ ዙር አድማስ ዲጅታል ሎተሪ በ2ኛ ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል፡፡ አቶ አሎ በግል ስራ ዘርፍ በኤሌክትሮኒክስ ንግድ የሚተዳደሩ ሲሆኑ በደረሳቸውን ገንዘብ ቤት ለመግዣ እንዲሚያውሉት ገልፀውልናል፡፡
በጉጉት የሚጠበቀው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቆርጠዋል? የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ2019 በጀት ዓመት ያዘጋጀውና ከፍተኛ ሽልማቶችን የያዘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በገበያ ላይ ነው፡፡ በአቅራቢያዎ ካሉ የሎተሪ አዟሪዎች በመቁረጥ ዕድልዎን ይሞክሩ ፡፡ በ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊየን ብር በ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊየን ብር በ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊየን ብር በ4ኛ ዕጣ 2 ሚሊየን ብር በ5ኛ ዕጣ 1 ሚሊየን ብር እና ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች ይዟል ፡፡ መልካም ዕድል ! የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 50 በገበያ ላይ ነው ይቁረጡ! በማንኛውም ቦታና በማንኛውም ሰዓት የእጅ ስልክዎን በመጠቀም 605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም ቴሌ ብር በመጠቀም በ10 ብር ይቁረጡ፡፡ አሁኑኑ ይቁረጡና ዕድለኛ ይሁኑ፡፡ በ1️⃣ኛው ዕጣ 4️⃣ ሚሊየን ብር በ2️⃣ኛው ዕጣ 2️⃣ ሚሊየን ብር በ3️⃣ኛው ዕጣ 1️⃣ሚሊየን ብር እና ሌሎች ዕጣዎችን ይዟል ፡፡ መልካም ዕድል! የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
በምስራቅ ሸዋ የአዱላላ ነዋሪ የሆነው ወጣት አቡ ቦጋለ በቆረጠው 49ኛ ዙር አድማስ ዲጅታል ሎተሪ በ3ኛ ዕጣ የ1 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኗል፡፡ ወጣት አቡ በትምህርት ቤት ውስጥ IT ባለሙያ ሲሆን በደረሰው ገንዘብ ከሙያው ጋራ ተያያዥ የሆነ ሥራ ለመስራት እንዳሰበ በቢሮአችን በነበረው ቆይታ ወቅት ገልፆልናል፡፡
በአርሲ ሄጦሳ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ደሜ አለማየሁ በቆረጡት ሚሊየን ሎተሪ በ6ኛው ዕጣ በግማሽ ቲኬት የ2 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል፡፡ ወ/ሮ ደሜ የቤት እመቤት ሲሆኑ የደረሳቸው ገንዘብ ቤት ለመግዣ እንደሚያውሉት በቢሮአችን በነበራቸው ቆይታ ወቅት ገልፀውልናል፡፡
የባህርዳር ነዋሪ የሆኑት አቶ ዜና ገ/መስቀል በቆረጡት ዝሆን ሎተሪ በ2ኛ ዕጣ የ3 ሚሊየን ብር እድለኛ ሆነዋል፡፡ አቶ ዜና በማሽነሪ ንግድ የተሰማሩ ሲሆን የደረሳቸውን ገንዘብ የባንክ ዕዳቸውን ለመክፈል እንደሚያውሉት በቢሮአችን ቆይታ ገልፀውልናል፡፡
የሐዘን መግለጫ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የቀድሞ የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መዓዛ ቅጣው በህልፈተ ሕይወታቸው የተሰማንን ልባዊ ሐዘን እንገልጻለን። ወ/ሮ መዓዛ ቅጣው ለኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በትጋትና በታማኝነት ለ 19 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን በተቋሙ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ አስቀምጠዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ቀደም ብለው ከታዩ ሴት አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። ዛሬ እኛም እርሳቸው በጣሉት ጠንካራ መሠረት መነሻ በማድረግ የጀመሩትን ድርጅታዊ ራዕይና ተግባር በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል እንሰራለን፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። ልዑል እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን፡፡
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
+4
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በንቃት ተሳትፏል። በዚህ መርሃ ግብር የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች በመሳተፍ ለአረንጓዴ፣ ንጹህና ዘላቂ ኢትዮጵያ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክብርት ቤዛ ግርማ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለትውልድ የሚተላለፍ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ “ዛሬ የምንተክለው ዛፍ የነገን ሕይወትና የአገራችንን ዘላቂ እድገት የምንገነባበት መሠረት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዋና ተልዕኮው ጎን ለጎን ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለማህበራዊ ኃላፊነት ያለውን ቁርጠኝነት በቀጣይነት ያጠናክራል። #አረንጓዴአሻራ #ለአረንጓዴኢትዮጵያ #የኢትዮጵያሎተሪአገልግሎት #GreenLegacy
አድማስ ዲጅታል ሎተሪ መደብ 049 ዛሬ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል::