tgindex
𝗢𝗳𝗳𝗶𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗔𝗵𝗺𝗮𝗿𝗶𝗰 𝗤𝘂𝗼𝘁𝗼𝘀 ❤️

𝗢𝗳𝗳𝗶𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗔𝗵𝗺𝗮𝗿𝗶𝗰 𝗤𝘂𝗼𝘁𝗼𝘀 ❤️

Статистика

💜𝗕𝗲𝘀𝘁 𝗔𝗺𝗵𝗮𝗿𝗶𝗰 𝗤𝘂𝗼𝘁𝗼𝘀 ⓔ︎ⓝ︎ⓙ︎ⓞ︎ⓨ︎ 😉 💬𝗝𝗼𝗶𝗻 & 𝗦𝗵𝗮𝗿𝗲💬 💭 📩cross 🧣𝗳𝗼𝗿 𝗔𝗻𝘆 𝗰𝗼𝗺𝗺𝗲𝗻𝘁👇 https://t.me/ahmaric_queto

Последний пост
12 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Криптовалюты (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
2 178
−9 за 3 дн.
Сутки
−4
−0,18%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
2 747
20 постов
Вовлечённость
126,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 💕የረፈደ ፍቅር💕 ክፍል ፊ ከተማው በሰው እና በመኪና እየተተራመሰ ነው እንደሁልጊዜው ድድ ማስጫ ላይ ከጓደኞቼ ተቀምጬ የምታልፈውን ሴት እየለከፍኩ ነው ንጉሥ እባላለሁ ጀለሶች ኪንግ እያሉ ነው የሚጠሩኝ በህይወቴ ምንም አጥቼ አላውቅም የሀብታም ልጅ ባልሆንም ተቀማጥዬ ነው የምኖረው ምክንያቱም ከአያቴ ጋር ነው ያደኩት ያሰደጉኝ ደግሞ ጎረቤቶች ናቸው ሁሉም ይወዱኛል ቆንጆ ና ቄንጠኛ ዘናጭ ወንድ ነኝ…

  • 7 апр.1 20367

    💕የረፈደ ፍቅር💕 ክፍል ፩ ከተማው በሰው እና በመኪና እየተተራመሰ ነው እንደሁልጊዜው ድድ ማስጫ ላይ ከጓደኞቼ ተቀምጬ የምታልፈውን ሴት እየለከፍኩ ነው ንጉሥ እባላለሁ ጀለሶች ኪንግ እያሉ ነው የሚጠሩኝ በህይወቴ ምንም አጥቼ አላውቅም የሀብታም ልጅ ባልሆንም ተቀማጥዬ ነው የምኖረው ምክንያቱም ከአያቴ ጋር ነው ያደኩት ያሰደጉኝ ደግሞ ጎረቤቶች ናቸው ሁሉም ይወዱኛል ቆንጆ ና ቄንጠኛ ዘናጭ ወንድ ነኝ ሴቶችን ጀንጅኜ ፍቅር ሲይዛቸው ማየት ያዝናናኛል የሚገርመው ሳልጠይቃቸው ነው ስልካቸውን የሚሰጡኝ ስለቁንጅናዬማ ተዉት ያደንቁኛል ዛሬም አዲስ ሴት ከተገኘ ብለን ተቀምጠናል በነገራችን ስራ አለኝ ግን አልሰራም ቦዘኔ ነኝ አንዳንዴ ግን የታክሲ ተራ ላይ እሰራለው ዛሬ ከ➎ጓደኞቼ ጋር ተቀምጠን እያወራን ነበር ያው የፈረደበት ኳስ ነው በመሀል አማን የሚባለው ጓደኛችን "ያቻት የባለፈዋ ልጅ መጣችላቹ"አለን ባለፈው እኔ ተራ ላይ ስሰራ እነአማን ሊያወሯት ሲሉ ውሻ አርጋቸው የነበረች ሴት ናት እኛም ወሬአችንን አቆምን ቤልም ኪንግ አሳሯን አብላልኝ አለ እኔ እንዲሁም ጠንካራ ሴት ትመቸኛለች እናም ከተቀመጥኩበት ድንጋይ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ እና "እሙዬ ማማ"ብዬ ጠራሗት እሷ ግን ዞራ ሳታየኝ በዝግታ እየተራመደች ነበር ደረስኩባትና ምነው ስጠራሽ አልኳት ወሬ ለመጀመር ያክል ልጇትም ፊቷን አጨማዳ "ታውቀኛለህ"አለች አይኗን አፍጥጣ እኔም  ፈገግ ብዬ እንተዋወቃ ኪንግ እባላለሁ አልኳት"እሺ ንጉስ አሁን ጊዜህን አትግደል"አለችኝ ስሜ በአፏ ሲጠራ አሰጠላኝ እኔም አልተዋወቅም እያልሽኝ ባልሆነ አልኳት ልጅቷም አዎ እያልኩህ ነው ነቄ ነህ ማለት ነው ብላኝ የሞላ ታክሲ ውስጥ ገባች እኔም እልህ ተያያዘኝ ደስ ይሉኛል ሴቶች አጉል ሲኮሩ፡፡እኔም ጓደኞቼ ጋር ሄድኩኝ ከእነሱም ጋር ተሳስቄ እንደተለመደው ሲመሽ ቤቴ ገባሁ ጠዋት ስነሳ አያቴም የለችም ደጀሰላም ትሆናለች ብዬ ቁርሴን ድስት ጠርጌ በላውና ሻይ ልጠጣ እነ እማማ የሺ ጋር ሄድኩኝ የሳቸው ሻይ እኮ የቀመሰ ነው የሚያውቀው ያው ሰፈራችን ፍቅር ነውና የኔ የሚባል ነገር የለንም ሻዬ ጠጥቼ ከአንዱ ጓደኛዬ ጋር ተራ ላይ ሄድን ሁለት ታክሲ ከሸኘው በሗላ የትላንትናዋ ልጅ መጣች አሁንማ ስልኳን እቀበላት ብዬ ሰላም ቆንጆ ብዬ አብሪያት መሄድ ጀመርኩ ግን አታወራም ብዙ ለፈለፍኩኝ ዝም አለች ያምሻል እንዴ አልኳት በብስጭት ዝም አለችኝና ቆማ በአንድ እጇ እጄን በሌላኛው ራሷን አጥብቃ ይዛ ቆመች ሙድ ነው እንዴ አልኳት ዝም አለችና መንገዱ ላይ ተዘረጋች ኧረ ትወና ይሄ ሁሉ የእኔን ሀዘኔታ ለማግኘት ነው አልኳት ምንም ድንጋጤ ሳይሰማኝ ግን እሷ የምሯን ነበር ሰውነቴ የተሳሰረው ከአፍንጫዋ ደም ሲፈስ ነው መጮህ አልችልም ምን አይነት እርዳታ እንደሚሰጥ ምን አውቄ ያ  ቆንጆ ፊቷ በደም ተለውሷል እጇ ተዘረጋግቷል ስሟን እኮ በመላ አላውቀውም....    🎉ክፍል፪ ይቀጥላል🎀 ይቀጥላል like. Share ቤተሰብ✨ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️           👇👇👇👇 @https://t.me/ahmaric_quotes @https://t.me/ahmaric_quotes ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

  • йоС пОдписи

  • ♥️ ፅናት ♥️...!!! . . 🥀..ክፍል 5..🥀 . . ከ አልጋዋ እንድትነሳ እረድቷት ወደ እህቷ ወሰዳት።ደረጃውን እየወጡ ሳሉ ዶክተሩ  "እየውልሽ አንቺ በጣም ስለተጨነቅሽ ላሳይሽ ብዬ ነው እንጂ አይፈቀድም እህትሽን ከ ግማሽ ሰአት በኋላ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እንወስዳታለን" አላት። ፅናት "ምን እህቴ አትሞትብኝም አደል? "አለችው። ዶክተሩ አዘነ ግን ፈገግ ብሎ "አታስቢ ምንም አትሆንም የህክምና ወጪዋንም የገፍታሪው ወላጆች ናቸው የሚችሉት" አላት። ፅናት እሺ ብቻ ብላው መሄድ ጀመረች ትንሽ ኮሊደሩን እንዳጋሙሱ ነይ እዚህ ነው አላት።     ፨ክፍሉ ደረሱ በፀሎት  ያለችበት ፤ በፀሎት  የተኛችበት ፤በፀሎት የምታቃስትበት ክፍል  ዶክተሩ" ደረሰናል ይህኛው" ነው።  አላት ለፅናት እንድትገባ እየጠቆማት ፅናት ለመግባት ፈራች ክፍሉ ብትገባ የእሪሳ ሳጥን ውስጥ እህቷን የምታያት መሰላት። ውስጧ መግባትን ቢፈልግም እግሮቿ ግን ፍፅሞ አልቻሉም። ዶክተሩ ከትከሻዋ ገፋ ገደፍ አድጎ ሊያስገባት ሞከረ።   ፨ ፅናት ግን  "አይ አይሆንም፤ በጭራሽ አይሆንም" አለች። ዶክተሩ ግራ ተጋባ "ምኑ" አላት።ፅናትም የዶክተሩን ሁለት እጆች ይዛ " እህቴ በህይወት አለች አደል?"፤ ምንም አልሆነችም አደል? "አለችው። ዶክተሩ "አዎ አታስቢ! ነይ ገብተሽ እያት" አላት። ፅናት እንደምንም እግሮቾን ጎትታ  ገባች።     ፨ እህቷን ስታያት በጣም ደነገጠች። በደፈረሱ አይኖቿ ለእህቷ በድጋሜ፤ አለቀሰችላት ፤ አዘነችላትም። ዶክተሩ የፅናትን ፊት ሲያየው እሱም በጭራሽ ውስጡን አጀግኖ መቆየት አልቻለምና አለቀሰ እንባ አፈሰሰ። ፅናት ዶክተሩን አየችና "እንዴ  ለምን ታለቅሳለክ ስለማትድን ነው?" አለችና ዶክተሩ ፊት ላይ አፈጠጠች። ዶክተሩ ውብ አይኖቿ አፈዝዘውት በአትኩሮት ያያት ጀመር።  ፅናት ግራ ገባት ዶክተሩ በመጨረሻ ወደ እራሱ ተመልሶ እራሱን ታዘበ በብላቴና እና በታናሽ ታናሹ አይን መማረኩን እሱንም አስገረሞታል። ደንገጥ ብሎ "አይ አይ እንደዛ አደለም አታስቢ ደና ትሆናለች" አለና ሁለት መዳፎቹን አይኖቹ ላይ አርጎ ሽቅብ አንገቱን አድረጎ "ኡፍፍፍፍፍ" አለ።       ፨ፅናት ወደ እህቷ ተጠጋች መንካትም ፈራች እጇን ወደ በፀሎት ሰደደችው ግን መንካት አልቻለችም። እጆን መልሳ ፊቷን አዙራ በሩን ጓ አድርጋ ወጣች። ዶክተሩ ወደ በፀሎት ተጠጋ በፀሎት እግሯ ወደላይ በጅብሰን ታስሯል የወደቀችው የትምህርት ቤቱ መናፈሻ ሳር ላይ በመሆኑ እግሯን የፓርኩ አጥር ስለመታት እግሯ ተጎድቷል። ፊቷ ምንም አልሆነም ጭንቅላቷ ግን ተመቷል። ጭንቅላቷ ላይ የተጠመጠመው ፋሻ እንዳለ ሆኖ ፊቷ ግን ውብ ነው። ዶክተሩ "እነዚህ ልጆች ከምን ቢፈጠሩ ነው እንዲህ ውብ የሆኑት?" አለ ድምፅ አውጥቶ።       ፨ከዛ ክፍሉን ለቆ ወጣ። ይህ ከሆነ ከግማሽ ሰአት በኋላ የሆስፒታሉ ዶክተር እና ነርሶች በፀሎትን ኣፕራሲዮን በማድረግ ላይ ናቸው። ፅናት ግን ተኝታለች ዶክተሩ። የእህቷ ኣፕራሲዮን ከ ግማሽ ሰአት በፊት እንደሆነ የነገራትን ዘንግታ ሳይሆን ሳታስበው ነው። የትግስት ኣፕራሲዮን ጊዜ 8 ሰአት የሚፈጅ በመሆኑ ግማሽ ሰአት ከፈጀ በኋላ ፅናት ከእንቅልፏ ባነነች ከ አልጋዋ ተነስታ ኮሊደሩን እየተደገፈች ፣ እየተጓዘች በድጋሜ እራሷን ስታ ወደቀች።      ፨ያያት ሰው አልነበረም ከትንሽ ቆይታ በኋላ የአንድ ሴት ወደ ኮሊደሩ ስትመጣ አየቻት። ሴቲቷ አልጮከችም በቀስታ ወደ ፅናት ከሄደች በኋላ ፅናትን ተሸክማ አቅራቢዋ ወዳለው የአግዳሚ  መቀመጫ ወንበረ ላይ አስተኝታ  የፅናትን መንቃት መጠባበቅ ጀመረች። ፅናት ግማሽ ሰአት  አስቆጥራ ነቃች ስትነቃ የአንድ ሰው ታፋ ላይ ጋደም ብላለች። ቀስ ብላ ቀና ለማለት ስትሞክር አቅም አጥሮ አቃታት ። ሴቲቷ "ተኒ አዎ ተኒ መተኛት ፈረተሽ ነው አትፍሪ የአሁኑን መተኛት ከፈራሽ ለዘላለም መተኛትን እንዴት ልትቀበይው  ሚጢጢዋ" አለቻት ፀጉሯን እያሻሸች።       ፨ ፅናት ደነገጠች ቀስ ብላ በድጋሜ ለመነሳት ስትሞክር ተሳካላትና ቀና አለች። ይህቺን ሴት ፅናት ታውቀዋለች  ይንን ፊት የት እንዳየችውም  በጭራሽ ልትዘነጋው አትችልም ይህቺን ሴት የምታውቃት የእናት እና የአባትዋን መቃብር ለማየት ከ እህቷ ጋረ ስትመጣ ሁሌም ባይሆን በብዛት ታያታለች። ሁሌም በእጆቿ አበባ ይዛ መቃብሮቹ ጋር ትበትናለች። ሽቶም ትነፋባቸዋለች ፅናት ይህቺን ሴት በጣም ትፈራታለች። ፊቷ ልክ እንደ ቆንጆ እንጀራ ምልክት አለው። ፀየም ያለች እና ፀጉሯን የተከረከመች ናት ሁሌም የምትለብሰው ልብስ ጥቁር ግን ፅዱ ነው ጠረኗ መቃብሮቹን የምትቀባው ሽቶ ነው። አቋሞ ቀጠን ያለች እና እጅና እግሮቿ እረጃጅም ናቸው።           ፨ፅናት እና በፀሎት የሚፈሩት ሴት እሷን ሲያዩ ሞት ትዝ የሚላቸው ሁሌም ነው። ፅናት ፈራች የእህቷ በፀሎትን  የሞት መረዶ ልትነግራት የመጣች መሰላት። ከሴቲቱ ላይ ተፈጨረጭራ ተነስታ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብላ አንገቷን ደፍች እጆቾን ቆላልፋ በታፋዎቾ መሀል አረገቻቸው ። ሴቲቱ እጆቿን ወደ ፅናት እጆች ሰዳ ከታፍዋ ፈልቅቃ ያዘቻቸው ፅናት ፈራች። ሴቲቱ የቀኝ እጃን ወደ ፅናት አገጭ ሰዳ ቀና ካረገቻት በኋላ "ምነው  ፈረተሽ ነው? አይዞሽ አትፍሪ! ያሰብሽውን እና ለእሱ የምትጨነቂለትን ሰው እንደማታጪ ተስፋ አደረጋለው" አለቻት።         ፨ የሴቲቱ አይን ከ ፅናት አይኖች ጋር ተገጣጥመው ተፍጠጡ ፅናት አይኗን ስታየው ድንገት ደነገጠች ደርቃ ቀረች የልብ ምቷ ጨመረ ልቧ መታ እንደጉድ ድው ድው ድው ድውው። ሴቲቱ የፅናትን ድንጋጤ አስተውላለች "ምነው ለምን ደነገጥሽ?"  አለችና እጆን ከፅናት እጅ እና አገጭ አነሳች። ከዛም የቀኝ እጆን ወደ ፅናት ዘረግታ "እንተዋወቅ  ሚጢጢዋ ሊባኖስ እባላለው" አለቻት። ፅናት የሊባኖስን እጅ በአይኗ አተኩራ አየቻቸው። "ያንቺ ስም ማነው?" አለቻት። ፅናት እረብትብት አለች። እጆቿን በቀስታ ወደ ሊባኖስ እጃች ወስዳ አጣመረቻቸው ከዛም የፅናት ትንፋሽ ተቆራረጠ "እኔ የእኔ የእኔ ስም ደሞ ፅፅፅፅፅፅፅናትትትትት ይባላል"። አለቻት ሊባኖስ "እሺ የተጨነቅሽ ትመስያለሽ ሚጢጢዋ ፅናት መጣው ውሀ ይዜልሽ" አለችና ሄደች።        ፨ ሊባኖስ ከመቀመጫዋ ስትነሳ አንድ ደብተር ነበር። ሊባኖስ ከሄደች በኋላ ፅናት ጠጋ ብላ እጇእየተንቀጠቀጠ ደብተሩን አነሳችው። የደብተሩ የመጀመሪያ ገልፅ ላይ "በትልቁ ሞት ህይወት ነው! ህይወት ሞት ነው!?" ይላል ይቀጥላል like. Share ቤተሰብ✨ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ 👇👇👇👇 @https://t.me/ahmaric_quotes @https://t.me/ahmaric_quotes ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

  • ♥️ ፅናት ♥️...!!! . . 🥀..ክፍል 4..🥀 . . ፨ፅናት ከፍዘቷ ስትነቃ ጩከቷን አቀለጠችው ፤አለቀሰች ውስጧ በሀያሉ ታመመ። በአንድ ሲኮንዶች የተለያዩ አስቀያሚ ስሜቶችን  ውስጧ አስተናገደ "አንቺም ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው በፀሎቴ፤ እህቴ አንቺም አንቺም አንቺም እንደ አባባ እና እማማ ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው?፤ አይ አይሆንም እባክሽ" የሚሉ ቃላቶችን ከሲቃ ጋር አጓረፈቻቸው።       ፨ የበፀሎት የጭንቅላት ደምም ለጉድ ጎረፈ አወይ ስቃይ! አወይ ሀዘን! በቃላት የማይገለፅ ሀዘን ፣የውስጥ ህመም ፣እረ ስንቱን በለጋ እድሜዋ አስተናገደች። አንፑላንስ መጣ፤ አንፑላንስ ጮከ ፤በፀሎትንን ይዘዋት በቃሪዛ ወደ ህክምና ጣቢያ ከነፉ ፅናትም እንድትገባ ባይፈቅዱላትም ታግላና አልቅሳ እንደምንም  ገባች።    ፨ በስተመጨረሻ  ሆስፒታል ደረሱ ያኔ ፅናት ከመኪና ወረዳ የድረሱልኝ ጩከቷን ከ አንፖላንሱ ጋረ አቀለጠችው። ሆስፔታሉ በፅናት እና በአንፖላንሱ ድምፅ ታጀበ። ተጨማሪ ነረሶች መተው በፀሎትን ሆስፒታል አስገቧት ፅናት ውስጧ ተሸበረ ፈራች ውይይይ በቃ በጣም ጨነቃት። ምስኪኗ ትንሽየዋ ፅናት እራስዋን ሳተች።        ፨ የነቃችው በነጋታው ጠዋት 1:30 ላይ ነበር። አይኗ ደብዘዝዝ አለባት ከዛም እይታዋ ተስተካከለ። 1:30 አለች። ስአቱን ያወቀችው ባለችበት ክፍል ውስጥ በተሰቀለ የግድግዳ ሰአት ነው።ስትነቃ መጀመሪያ የጠራችው የእህቷን ስም ነበር። "እህቴ በፂዬዬ፤ እህቴ በፀሎቴ " ሲቃ በተሞላበት  እና እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ድምፅ ከዛ እንባ በድንቡሽብሽ እኛ በጥቂቱ ውረጭ በመታው ፊቷ ወረደ።        ፨ያለችበት ክፍል በድንገት  ተከፍቶ አንድ ዶክተር እና ፖሊስ እህቷን ከገፈተራት ልጅ አባት ጋረ ገቡ። ፅናት ሰውየውን ስታየው ፊቷ ተቀያየረ እንባ እና ንዴት ተናነቃት አትችልም እንጂ ተነስታ ብታፈራረጠው እና የምትወዳትን እህቷን አስነስታ የገፈተራትን ልጅ እስከ አባቱ ከዛ ፎቅ ወረውራ ብትገላግላቸው ደስታዋ ነው። ፅናት የወረዋሪው ልጅ አባት ላይ አፈጠጠች። ፖሊሱ ወደ ፅናት ተጠግቶ የተፈጠረውን ነገር ለመናገር አሁን ዶክተሩ መልካም ጤንነት ላይ ናት ስላለ ቃልሽን ትስጫለሽ።" አላት።       ፨ ፅናት አሁንም አይኗን ከ ወረዋሪው ወላጅ ላይ  አልነቀለችም የፓሊሱን ንግግረ ስምታ ይሆን?  ማንም አያውቅም አሁን አይኖን ዞርም ሳታረግ "ዶክተር እህቴ እንዴት ናት?" አለች። ዶክተሩ ፅናት የወረዋሪውን አባትን  እያየች እሱን መጠየቋ ግራ ቢያጋባውም "አታስቢ ደና ናት" አላት። ከዛም የገፍታሪው ልጅ አባት ሹክክ ብሎ ከ ክፍሉ ወጣ።     ፨ዶክተሩ በፅናት ፊት ላይ የሚያየው እልህ እጅግ አስገረመው አስደነገጠውም ህፃንነቷን አይቶ ንግግሯን እና ሁኔታዋን ሲያይ ገረመው።ፓሊሉ ፅናት እንድትነሳ ክንዷን በመያዝ "ቀስ ብለሽ ተነሺና  ወደ ፓሊስ ጣቢያ እንሂድ" አላት። ዶክተሩ ፅናትን ሲያያት ሁኔታዋ ጥሩ ስላልነበረ "እዚህ መሆን አይችልም?" አለ። ፅናት ክንድ  ላይ ያረፈውም የፓሊሱን እጅ ያዝ አረጎ ፖሊሱም አንዴ ፅናትን አንዴ ዶክተሩን እያየ እሺ ጥሩ ብሎ እጁን ከፅናት ክንድ ላይ አንስቷ ወደ ውጪ ወጣ።         ከቆይታ በኋላ ፖሊሱ ከመርማሪው ጋራ መጣ።        ፨መግቢያ በሩ ላይ ያለውን ወንበር ይዞ ፅናት ከተኛችበት አልጋ አጠገብ ተቀመጠ። ዋና መረማሪ ፖሊሱ የፅናትን ሆዷ ላይ ያጣመረችውን  እጅ አንስቶ በእጁ ያዘው ፈገግ ለማለት እየሞከረ "እንደተጎዳሽ ይገባኛል ፤ስለ እዚህ ነገር አውርቼ ባረብሽሽም ምርጫዬ ነበር ግን በተቻለሽ አቅም የምጠይቅሽን ሁሉ መልሽልኝ አላት። እጅ እጇን እያየ ፅናት አገጯን በመነቅነት እሺታዋን ገለፀችለት።     ፨ መረማሪው የድምፅ መቅጆዎን ካመቻቸ በኋላ ፅናትን አየት አረጎ  የድምፅ መቅጃውን ከማብራቴ በፊት ሁሉም እንዲወጡልሽ ከፈለግሽ ላስወጣልሽ እችላለው አላት። ፅናም "አይ አይሆንም በተለይ የአላዛር አባት እንዲኖረ እፍልጋለው ልጁ ያረገውን ነገር መስማት አለበት" አለች።መረማሪ  ፓሊሱ ወደ ፖሊሱ ዞሮ ሽቅብ እያየው "የአላዛረን አባት አስገባው" ብሎ ለፓሊሱ ትዛዝ አስተላለፈ ። ፓሊሱም "እሺ አለቃ እንዳልክ ይሁን "ብሎ ሊጠራው ከክፍሉ ወጣ። ፨ ፅናት "እሱ ሳይመጣ ምንም ማለት አልችልም አልፈልግምም" አለች። ዋና መረማሪ ፓሊሱም "እሺ ጥሩ እንዳልሽ ይሆናል" አለ። ከዛም ዝም ተባባሉ ፓሊሱ ግን ፅናትን በግረምት እያያት ነበረ። እሷም ጨረፍ አረጋ እያየችው ቆየች። ዶክተሩ በአትኩሮት ሁኔታውን ማየት ተያይዞታል ድንገት ፓሊሱ ከአፉ የሆነ ቃል ወጣ "ውብ ነሽ"  የሚል።       ፨ ፅናት ደነገጠች በእረግጥ ይህ ቃል ለእሷ አዲስ አደለም ያያት ሁሉ የሚላት ነገር ነው። በድንገት በሩ ተከፈቶ የአላዛረ አባት እና ፓሊሱ መጡ። መረማሪው "እሺ አሁን መቀጠል እንችላለን የተፈጠረውን ሁሉ ንገሬኝ  ዝግጁ ነሽ አደል? " አላት። ፅናት የአላዛርን አባት በእልህ እያየች "አዎ በሚገባ" አለች።     ፨ይህን ስትል አይኗ በሚጥሚጣ የተለወሰ እረጎ መስሎ ነበር። ልክ እንደ ውስጧ ደፍረሶ ነበር። መርማሪው የድምፅ መቅጃውን አበራው። ፅናት መናገር ጀመረች። "ትናት ትናት ትናንትትትት እህቴ ደና ነበረች።እኔም እንደዛው ሰረተፈኬት ተስቷኝ ከትምህርት ቤቱ አንደኛ እንደወጣው ሳውቅ ለእህቴ ላሳያት ፍለኩ በጣምምም ፈለኩ የመማሪያ ክፍላችን ፎቅ ሾር ሆኔ ጠበኳት እስክትመጣ በጣም ጎጉቼ ነበረ። በጣም በጣም በጣም በመጨረሻ መጣች። እህቴ መጣችልኝ" አለችና ፈገግ አለች።      ፨ ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሁሉ እያለቀሱ እና በፅናት የቃላት አጠቃቀም ተገረመው ነበረ። ፅናት ስታወራ አፉዋን የድምፅ መቅጃው ላይ አይኗን ደሞ የአላዛር አባት ላይ አድረጋ ነበረ። ለተወሰነ ሲኮንድ ፀጥ ብላ በድጋሜ ወሬዋን ቀጠለች።  "ከዛማ እህቴ ስትመጣ የምስራቹን ነግሬያት ገና ፍገግ እንኳን ለማለት ሳይፈቅድላት አላዛር! አላዛር! አላዛር! የኔን እህት፣ የኔን ፋና፣ የእኔን ሁሉ ነገረ ከ 2ተኛ ፎቅ ወረወራት"።ብላ ተንሰቀሰቀች።      ፨መረማሪው የድምፅ መቅጆውን አቋረጦ ፅናትን ሊያባብላት እጁን ወደ አንገቷ ሲያረገው ፅናት እጁን ይዛ "እንዳታባብለኝ በቃ ሁላችሁም ውጡ" አለች።በቃላቷቾ ክብደት ሁሉም ተገረመዋል። እድሜ ሳይሆን ኑሮ የሰውን ጭንቅላት  እንደሚያበስለውም ተረድተዋል። ሁሉም ተከታትለው ክፍሉን ለፅናት ትተውላት ወጡ።      ፨ፅናትም ለብቻዋ ክፍልሉ ውስጥ በሀዘን ቁረምት ብላ ቀረች። አይኗን የግድግዶ ሰአቱ ላይ ተከለች የግድግዳ ሰአቱን ወደ ጊዜ ሰአት ቀይራ  ከዛም ተነስታ በጣቶቾ አዙራ መቀየረን ተመኘች። ይህን ጊዜ ወይ ወደ ኋላ መልሳ በእህቷ ፍንታ እሷ ለመሆን አልያም ደሞ አሳልፍ እህቷም ደና ሆና መኖርን አለመች። ፅናት ወደ እራስዋ ተመልሳ ፈገግ ብላ "የሞኝ ምኞት ሞኝ ነሽ ፅናት " አለች።      ፨ እንዲህ ከእራሷ ጋር  የማይሆን ግን ቢሆን የሚያስደስታትን እያሰበች በማሰቧ እየተገረመች  እንቅልፍ ጥሏት  ሰአታት ነጎዱ።ከእንቅልፏ የነቃችው ዶክተሩ ሾለ ጤንነቷ ሊያረጋግጥ ሲመጣ ነበረ። ዶክተሩ "እንዴት ነሽ አሁን" አላት። በውስጧ "ምን እንድመልስለት ጠብቆ ነው?አለችና ለእሱ ግን  "ደና ነኝ" አለችው።  ዶክተሩ "እሺ ጥሩ" ብሎ ሙቀቷን እየለካት ፅናት ዶክተሩን "ዶክተር" አለችው ልስስስ ባለ አንደበት።  "አቤት"  አላት እሱም ረጋ ባለ ድምፅ  "እህቴን ማየት እፍልጋለው" አለችው። ዶክተሩ አልተቃወማትም።" እሺ  ብቻ ነው ያላት".ይቀጥላል @https://t.me/ahmaric_quotes

  • ..♥️ ፅናት ♥️...!!!            .            .            . 🥀..ክፍል 3..🥀 . . #Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!! . . አዘጋጅ እና አቅራቢ :- #ከደራሲያን_አለም የቴሌግራም ቻናል✍ . . ፨በሚኖሩበት አከባቢ ያሉ ስዎች እነ ፅናት ስፈራቸውን ሲቀላቀሉ  በስው ህይወት ገብቶ ማውራት ባይመቻቸውም የእነ ፅናት ነገረ ግን ስለሚገረማቸው ሁሌም ይንሾካሾካሉ ፤ያወራሉ "እንዴት ከአንድ ሞነክሴ ጋረ ሁለት ሙስሊም ይኖራል?" ብለው የመጀመሪያ ስሞን ያወሩ ነበረ። ከዛ በሳምንቱ ፅናት፣በፀሎት እና የእድሜ ባለፀጋዋ ሞነክሴ ቤተ ክረስቲያን ጠዋት ጠዋት ተሳልመው መምጣት ሲጀምሩ  የሰፈሩ ስው ዕርስ  ቀይረው "ቆይ ሙስሊም ካልሆኑ ለምን ይጠመጥማሉ?"ብለው ማውራት ጀመሩ ።      ፨በእዚህ ወሬ የሰፈሩ ነዋሪ በጠቅላላ በእየግሉ ወሬ ተነበየ "ይህንን ሻረፕ የሚጠመጥሙት ቡዳ ስለሆኑ ነው"። ቤተ ክረስቲያንም የሚሄዱት ለታይታ ነው እንደው ፈጣሪን አይፈሩም? " አሉና  ወሬውን ነዙት። ከአመት በኋላ የእድሜ ባለፀጋዋ ህመማቸው ፀንቶባቸው የአልጋ ቁራኛ ሆኑ።በፀሎት እና ፅናት እኒን ሴት ሀኪም ቤት እንደምንም ደጋግፈው ወሰዶቸው። ከ15ቀናት በኋላ ኑ እና ውጤቱን ትስማላቹ ብሎ ዶክተሩ በስጣቸው ቃል መሰረት በ15ቀኑ ሄዱ። ዶክተሩ አዋቄ ሰው እንዲጠሩ ቢጠይቃቸውም በፀሎት ስላሉበት ነገር ምንም ሳይቀር ነግራው አሳመነችው።   ፨ የሰሙት ዜና ልብ ሰባሪ ነበረ። ሴትየዋ ያለባቸው ችግረ ከደም ጋረ የተገናኘ በሽታ ነውና በሽታው በሙሉ በስውነታቸው ተሰራጭቶል  በህይወት ለትንሽ ጊዜም ቢሆን  ለመቆየት መዳኒት ያስፈልጋቸዋል። መዳኒቱን ለመግዛት ደሞ በሳምንት 10 ሺ ያስፈልጋል የሚል ዜና ነበረ። ይህንን መረዶ  ከሰሙ በኋላ ሁሉም ተረበሹ። በነጋታው በፀሎት ተነስታ ወዳከራዩት ቤት ሄደችና ቤቱን እንዲገዟት ጠየቀቻቸው።     መጀመሪያውም እንግዛው ሲሉ ስለነበረ ሳያቅማሙ እሺ አሉ።      ፨ ተከራዮቹ ባልና ሚስት ናቸው  በቅረቡ ነው ከአሜሪካ የመጡት። ከዛም ባልየው ለበፀሎት አንድ ነገረ ጠየቃት  እሷ ህፃን ብትሆንም ግን በሳል ሀይምሮ ነው ያላት። "ቆይ እንዴት ነው የምትሽጭልን አንቺም ልጅ እህትሽም ልጅ" አላት።  በፀሎትም "አሁን በእራሳችን ስምምነት እንፈጠር እናንተ የቤቱን ብረ ስጡኝ እና ቤቱን ኑሩበት። እኔ 18 አመት ሲሞላኝ ደሞ በፊረማዬ አረጋግጥላችዋለው" አለች። ስውየው ይህ ቃል የወጣው ከብላቴና ልጅ ነው ለማለት ተቸገረ። የሆነ ሰው በይ ብሏት እንጂ በፀሎት ወሬዋን ቀጠለች ከእድሜ ባለፀጋዋ ጋር በተስማሙት መስረት እንግዲህ 500,000 ብር ነው ስትል ሰውየውም "ጥሩ የተስማማውት ስለማምንሽ ሳይሆን ብታጭበረብሪ እንደምይዝሽ እና እንደምገልሽ ስለማውቅ ነው" አላት። በፀሎትም "ማንም ባለጌ እና አጭበረባሪ አርጎ ስላላሳደገኝ አታስብ" አለችው። ስውየው በአነጋገሯ ከመገረም ጋር ተስማማ።       ፨ ከዛ ስውየው በሶስተኛው ቀን 500,000 ብረ ስጣት። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ለወራት በእዚህ ብረ ሴትየዋን ማስታመም ጀመረች። መዳኒቱን  ቢወስዱም ግን በሽታቸው ገፈቶ። ይህ በእንዲ እንዳለ ከ6 ወር በኋላ ለወረ የተገዛላቸውን እንኳን መዳኒት ሳይጨረሱ ነው ፅናትና በፀሎት  ከትምህርት ቤት ሲመጡ አልጋው ላይ አይናቸው ፈጦ ያገኟቸው። በሰአቱ በፀሎት  እና ፅናት ባዩት ነገር ተደናግጠው ሲጮሁ የሰፈሩ ሰው ተሰብስበው  መጥተው ሴትየዋን ገናዥ መጥቶ ከገነዛቸው በኋላ በፁሎት  ካስቀመጠችው የቤቱ ብረ ለገናዡ ከፈለች።ለንፍሮ እና ለሊሎች ነገሮች ከአስቀመጠችው ብረ እያወጣች ተጠቀመች። ብሩ  ከየት መጣ ብለው የስፈሩ ስው በፀሎትን  ቢጠይቆት እና ቢያንጓጥጧት ቤታችንን ሽጭኤ ነው አለቻቸው።      ፨የሰፈሩ ነዋሪ ደሞ "አይ አይ በጥንቆላ ያጠራቀሙት ነው" ብሎ ፈረጀ።በፀሎት እና ፅናት ይህንን የሰፈር ወሬ ባልስማ እያለፉ ቆዩ። የሆነው ሆኖ የእድሜ ባለፀጋዋን ነገረ እና ሀሜት በተቀላቀለበት መልኩ ቀበሯቸው። የአባታቸው እህት በለቅሶ ሳምንት መጥታ እንደ ማንኛውም ሰው ደረሳ ሄደች።የሰፈሩ ስው ከሰልስቱ በኋላ ቤታቸው ድረሽም አላሉ።እንደውም ይበልጥ ይሸሻቸው እና ያረቃቸው ጀመር። ፨በሳምንቱ "እናታቹ ለፅናት ክርስትና የተበደረችውን ብር መልሱልን እስካሁንም ዝም ያልኳቹ ብረ የላችሁም ብለዬ ነበረ። አሁን ግን ቤታችሁን ስለሸጣቹ መክፍል ትችላላቹ" አሉዋቸው።በፀሎት በጣም ተበሳጨች "እንዴት መጀመሪያ 'ፈጣሪ ያፅናቹ' ሳይሉ ሾለ ብድረ ያወራሉ"አለች።አበዳሪውን እስከ አፍጫቸው ተናግራ የብረ መጠኑን ጠይቃ  ሰጠቻቸው። ከዛም የማታቃቸው ስዎች ሁሉ እየመጡ የአባታቹ እዳ አለባችሁ እያሉ ወሰዱ።       ፨በፀሎት በተለይ የመጀመሪያው ሰውየው ከሆደ በኋላ ጨሰች። ተንገበገበች ፣ተቃጠለች ፣እረረረረ፣ ድብን አለች። በእዚህ ጊዜ ትንሾ ፅናት "ተረጋጊ እህቴ እንኳንም የሰውዎችን እዳ ከፈልን አሁን ነፃ ነን።ሁሉንም  ተረጃቸው እስካሁን ታግሰውናል ሊላ ሰው ቢሆን እንዲ ጊዜ አይሰጠንም ነበረ"።  አለቻት።  በፀሎት በፅናት ንግግር በጣም ተደመመች የማፅናኛ ቃላቶቾ ሁሌም እያስገረሙ ያፅናኗታል።በፀሎት  ፅናትን እቅፍፍፍ  አረጋ በሁለቱም በኩል ጉንጮቾን ሳመቻቸው።  "ውይይይይ የኔ ሚጢጢ እህቴ ስወድሽ እኮ ያልሽው እውነት ነው"  አለቻት እና ፈገግ ብላ  "ፈጣሪ ያውቃል ለእኛ ጥሎ የማይጥለን አምላክ አለ" አለች። "ልክ ነሽ፤ አንችም ልክ ነሽ" ተባብለው ተቃቀፉ።     ፨ፅናት እና በፀሎት  እረዥም ደቂቃዎች ተቃቅፈው ከቆዩበት ፅናት ቀናብላ "እህቴ" አለቻት። በፀሎትም "ወዬ" አለች። ፅናት በድጋሜ ጥምጥም ብላ አቀፈቻት እና "ጭንቀትን ከሚያስረሱ ትልልቅ እና ዋና ከሚባሉት መካከል መተቃቀፈ እንደሆነ ታውቄያለሽ?"አለቻች።በፀሎትም  ግርም እያላት "አይ እህቴ ይህንን ደሞ ከየት ስማሽ" አለቻት። ፅናትም "ሬዲዮ ላይ ስምቼ ነው"። አለችት። በፀሎት "ውይይይይ የእኔ ውድ ምረጥ አኮ ነሽ"። አለችና አቅፋ ሳመቻት።    ፨ ከሳምንት በኋላ  ሁለቱም ወደ ትምህረታቸው ተመለሱ። በፀሎት 10 ፅናት ደሞ 5ተኛ ክፍል ደረሰዋል።ጊዜ ሄደ ህይወትም ከነ ክብደቷ  በእራስዋ መንገድ ተመመች። ፅናት እና በፀሎት የሁለተኛ ሴሚስተረ ውሰጤታቸውን ለመቀበል ትምህረት ቤት ናቸው። ወረፋ ይዘዋል  ማንም እነሱን ወላጅ አምጡ አይላቸውም ምክንያቱም ችግራቸውም ስለሚያውቁ። ፨ፅናት ውጤቷን ተቀብላ ከፎቁ ወረዳ እታች እህቷን እየጠበቀቻት ነው። ወደ ፎቁ አይኗን ቀይሳ  ሰርተፊኬቷ ላይ የተፅፈውን እጅግ አስደማሚ ውጤቶን ልታሳያት። ከብዙ ጥበቃ ግን ከትንሽ ደቂቃ በኋላ በእስተመጨረሻ እህቷ በፀሎት ሁለተኛ ፎቅ ደረጃ እየወረጀች አየቻት። ከዛም ጠራቻት። በፀሎት ቁልቁል እህቷን ስታያት ፅናት ጮክ ብላ "እህቴ አንደኛ ወጣውልሽ" አለቻት።     ፨በፀሎትም ፈገግ ብላ  ጓበዝ የእኔ ልዩ" ብላ ሊላ ልታወራው ያሰበችውን ሳጨረሽ አንድ ቀልዱ እንጨት እንጨት የሚል ልጅ ትግስትን ታግሎ ወደ ታች ወረወራት ፅናት ባየችው ነገረ ደረቃ ቀረች። ተማሪው ፣አስተማሪው ፣ብቻ ትምህረት ቤት የሚስሩ እና ያሉ ሁሉ በፀሎት ባወጣችው የጩከት ድምፅ ተደናግጠው ወጡ። . . 🥀..ከ 150 Like ቡሀላ ክፍል 4 ይቀጥላል ..🥀          ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ 👇👇👇👇 @https://t.me/ahmaric_quotes @https://t.me/ahmaric_quotes ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

  • ክፍል 3 እንዲለቀቅ ምትፈልጉ ሟር እና 100 like አድርጉት 🙏

  • ❤️….. ፅናት…….❤️ 🌹🌹🌹 ክፍል 2 🌹🌹🌹 https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk . .            ..የሆነው ሆኖ ለፅናት ክረስትና ቀን ጠዋት የድግሱን ብረ ውሽማሽ ነው የስጠሽ ብሎ ለክፏት ወጣ።እናትየው ሁሌም መልስ አትሰጠውም የህይወቷን ምእራፍ በትንሿ ልጇ ፅናት ብላ ስይማዋለች።በእዚህ መሰረት የመጨረሻ ልጆ ስም ሴት ከሆነች ፅናት እላታለው ብላ አባ ስለነበር።ስትወልድ ሴት ልጅ ወለደች።ይህቺ ልጅ ለህይወቴ ፅናት ናት አንቺንም በህይወት አቆይቶኝ እንድወልድሽ ስለፀለይኩ ነው በፀሎት ያልኩሽ ብላ ለበፀሎት ይህንን የነገረቻት።ገና በእረግዝናዋ ስአት ነበር። በፀሎት በሳል ጭንቅላት ስላላት እናታቸው ሲከፈትም ስትደሰትም የምታማክራት ለበፀሎት ነው።የፅናት ክርስትና በአል አክብረው ጨረሱ።       አመሻሽ ላይ በመጠጥ እራሱን የሳተው አባታቸው እናትየውን ይመጣና በተገረዳደፈ አንደበት በቆመበት እየተንገዳገደ"ስሚ አንቺ ቆይ እንዴት ተበድረሽ ትደግሻለሽ።ሀሀሀ ውይ ውይ ማለቴ ከውሽማሽ ተቀብለሽ ለነገሩ ለልጁ ያልሆነ ብር ይህቺም ደሞ ከእሱ ነው የወለድሻት አደል እሺ እሱስ ይሁን ይህንን ውበትሽን ለማውጣት ጥረሽ ተሳክቶልሽ ወንድን ማሽካርመምሽስ?"አለ።እናታቸው አለም ፀሀይ ምንም ትንፈሽ ሳታወጣ ጥበብ አብዝቶ የስጠው ስአሊ የሳለው  የሚመስል ውብ እና ትልልቅ አይኖቿን እያንከራተተች ታየው ጀመረ።      ፨እናታቸው አለም ፀሀይ እንደ ስሟ ፀሀይ ናት። ውበቷን ማንም ሊክደው አይችልም ውበት ከደም ግባት ጋረ ያደላት ቁመተ መለሎ ስውነቷ ለመንካት የሚያሳሳ የእግረ እና የእጆ ውበት የፀጉሯ እረዝመት እና ጥቁረት ተዳፋቷ በራሱ ወንድን ለማማለል በቂ ነው።በዛ ላይ ፀባይዋ ትህትናዋ እና ድምፆ ውብ ነው።ነገረ ግን ከትዳሬ ውጪ ወደ ውጪ ያለች እመቤት ናት። አባትየው በጩከቱ መልስ ስላልስጠችው በመናደድ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ በነበረውን ቢላ አንስቶ ፊት ለፊቱ በፋዘት ከምታየው ውቧ ሚስቱ አለም ፀሀይ ላይ ፤ የልጆቹ እናት ላይ የያዘውን ቢላ በረዥም እና ቀይ አንገቷ ላይ ሰካው።      ፨ ይህንን ተደብቃ ስታይ የነበረችው በፀሎት  በህፃን አይምሮዋ ያለ አቅሟ ማየት የሊለባትን ያየችው በፀሎት  ጩከቷን አቀለጠችው። ጓረቤት ተስበሰበ አባታቸው እራሱንም ጎረቤቶቹ መጥተው ከመያዙ በፊት እራሱ አንገት ላይም ወግቶ እራሱን አጠፋ። ጎረቤቶች በሩን በረግደው ገብ ፅናት መኝታ ቤት ሆና ይህንን ክስተት አይታ የገባት ይመስል እሪሪሪ ማለቷን ቀጠለች። ግን ከበፀሎት ውጪ ማንም ልብ አላላትም በፀሎት ከተደበቀችበት ሶፋ ሮጣ ወደ እህቷ ሄደች።ከእህቷ ጋረ አልጋ ላይ ወጥታ ጭብጥ ብላ ተቀምጣ ማልቀስ ጀመረች።ፅናት አልቅሳ አቅሟን ስታጣ ዝም አለች።ትግስት ግን ተንቀጠቀጠች።     ፨በእዚህ መልኩ ነበረ ወላጅ አልባ የሆኑት። ከዛማ በጎረቤት ጥሪ መሰረት ፖሊሶች መጡ።በነጋታው ፓሊሶች በፀሎትን ፓሊስ ጣቢያ ወስደው በህፆናት ሳይካትሪስት የተፈጠረውን እንድትናገረ አደረጉዋት።ያንን ቀን የተሰማትን ነገረ መግለፅም መረሳትም አትችልም ላይጠፋ በህሊናዋ ተቀረጿልና።      ፨የእናታቸው  ሰልስት ካለፈ በኋላ የአባታቸው እህት ጓዟን ጠቅልላ ገባች። ይህቺ አክሰታቸው ባልም ሆነ ልጅ እንዲሁም ፈላጊ ወንድ የላትም ፀባይዋ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ።ቤታቸው ገብታ አብራቸው መኖረ ስትጀምረ የበፀሎት እና የፅናት ህይወት ሲኦል ሆነ።አባት እና እናታቸው ሙሉ ንብረታቸውን በልጇቻቸው ያረጉት ፅናት ከተወለደች ከሳምንት በኋላ ነው። ይህ ንብረት ልጆቻቸው 18 አመት ከሞላቸው ሙሉ ንብረቱን እንዲወረሱ የሚል ውል ነው። በእረግጥ ሀብታም አደሉም በስማቸው አንድ ቤት ብቻ ነው የነበረው አባታቸው ነው ይህንን ያረገው። አክስታቸው እናት እና አባታቸው ያወረሷቸውን ውረስ አሳዳጊ ነኝ በማለት ልትወረስ ብትጥረም ችሎቱ ውሳኔዋን ውድቅ አረጎባታል የአክስታቸው ስም ድንቄ ይባላል።ፅናት ካደገች በኋላ ሁለቱንም ማሰቃየት ጀመረች።      ፨ይህንን ያዩ ተከራይ የነበሩት የእድሜ ባለፀጋ አክስታቸውን ከሰው በፍረድ ቤት ክረክር ከእዛ ቤት አስወጧት።ይህን ሲያረጉ የሰፈሩ ሰውም ለምስክርነት ቀርበው ነበር። ያኔ በፀሎት10 ፅናት ደሞ 5 አመታቸው ነበረ።ከዛማ ከእኒ የእድሜ ባለፀጋ ጋረ መኖረ ጀመሩ።በፀሎትም አክስቷ ያስቆረጠቻትን ትምህረት አስቀጠሏት። ከ2 አመት በኋላም ፅናትን ከቆሎ ትምህረት ቤት አስወጥተው አንደኛ ክፍል ወስገቧት። ሁለቱም ትምህረታቸውን በሰረአቱ መማረ ጀመሩ።ከቀናት በኋላ የእድሜ ባለ ፀጋዋ ሴት በእረጅና እቤት መዋል ጀመሩ።የጡረታ ብራቸውም ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ ተቋረጠ።     ፨ከዛም ሂሩት ከትምህረት ስትመለስ በዳቦ የሚሰሩ ምግችን እየሽጠች መተዳደር ጀመሩ።እንዲህ እየኖሩ እኒ የእድሜ ባለፀጋ በህመም አልጋ ላይ ዋሉ።እሳቸው ለማሳከም ቤታቸውን መሸጥ ቢፈልጉም 18 አመት ስላልሞላቸው መሽጥ አልቻሉም በእዛ ምክንያት እቃቸውን ጥቂት አስቀረተው ሸጡ ቤታቸውንም አከራይተው እነሱ የጭቃ ቤት ተከራዩ። ፨ እነ ፅናት ከእዛን ቀን ጀምሮ በጭቃ ቤታቸው ኑሮን ተያያዙት።የሚኖሩበትን ቤት ላየው ተመልካች ህፃናት ለጨዋታ ብለው እንደነገሩ የሰሩት የመጫወቻ ቤት ይመስላል።የፅናት ታላቅ  እህት በፀሎትም የእድሜ ባለፀጋዋን እና ፅናትን መንከባከብ ጀመረች። ከትምረህት ቤት  ከቤት ወደ ሾል ከስራ ወደ ጥናቷ እና እህቷን እና የእድሜ ባለፀጋዋን መንከባከብ የቀን ተቀን ስራዋ አደረገችው። የምትሰራው ሾል ቀለል ያሉ ምግቦችን በመዘፋዘፊያ ይዛ ዞራ መሽጥ ነው።      ፨መኖሬያ ስፍራቸው  ሴተኛ አዳሪ፣ ዱረዬ እና የጎዳና ተዳዳሪ ይበዛበታል። በፀሎት እና ፅናት ሁልግዜም ፊታቸው ላይ ሻርፕ ሳይጠመጥሙ አይወጡም ካለ አይናቸው ምንም የሚታይ ገልፅ  የላቸውም። የሚለብሱት ልብስ በጣም የተንጓተተ ግን ደሞ የፀዳ ነው።ቤታቸውን አከራይተው እዚህ መረጋጋት ፣ ዝምታ እና  እራስን ማዳመጥ ከማይቻልበት  ሰፈረ ከገቡ በኋላ ነው መሸፋፈን የጀመሩ . ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ 👇👇👇👇 @https://t.me/ahmaric_quotes @https://t.me/ahmaric_quotes ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ . . . . 🥀. ማክሰኞ ማታ 2:00 ክፍል 3 ይቀጥላል ………

  • ❤️❤️ፅናት❤️❤️ 🌹🌹 ክፍል 1 🌹🌹    ፨" የከተማ ገጠር  ውስጥ መኖር እኮ ከባድ ነው"። አለች ፅናት እንደ ልማድዋ በእጅ የምትያዘዋን ሬዲዮ ለመስራት እየታገለች። እንዲ ስትል ዊልቸር ላይ የተቀመጠችው ማየት የተሳናት ታላቅ እህቷ በፀሎት  "እንዴ ፅናቴ አሁን የምንኖረው ከተማ አደል እንዴ ደሞ አነጋገረሽ ሁለት መልክ ያዘ" አለቻት። ፅናትም "አይ ፀሎትዬ ባክሽ አንዳንዴ የሌለ ነገረ ያናዝዘኛል መሰለኝ"። አለችና ሬዲዮኑን መታ አረገችው እሱም በዱላ ይሰራ ይመስል መስራቱን ቀጠለ።           ፅናት  "ውይ ይሄ ፕሮግም አላመለጠኝም" አለችና ሬዲዩኑን ወደ ጆሮዋ አስጠጋችው። እንደው ወደ ጆሮዋ ማስጠጋት ልምድ ሆኖባት እንጂ የሬዲዮኗ ድምፅ ከእነሱ ቤት አልፎ ጎረቤት ይሰማል። ጓረቤት የላቸውም እንጂ ቢኖራቸው ኖሮ!..  ሬዲዮኑ ውስጥ አንድ ጓረናና ድምፅ ያለው ተወዳዳሪ የሊለው ደራሲ ሾለ ድረሰቱ ምረቃት ለድረሰቱ ምረቃት በተዘጋጀው  መድረክ ላይ ቆሞ የሚናገረ ይመስላል።        የእነ ፅናት ቤት ሪዲዮኑ ውስጥ ከሚያወራው ሰው በቀር ምንም አይስማም ይህ ታዋቂ ደራሲ ከታዳሚዎች ጭብጨባ በኋላ ወሬውን ቀጠለ። "ሰላም ጤና ከአክብሮት ጋረ ይድረሳቹ። ሾለ መፅሀፌ ከማውራቴ በፊት ሾለ ድረሰት አንዳንድ ነገረ ልበላቹ። ሁላችንም እዚህ አለም ላይ ስንኖር የፈጠረን አምላክ አለ ብለን በማሰብ ነው። እና ለምሳሌ አውሮፕላን የስራው ስው ከወፍ ነው የአሰራር ብልሀቱን የተማረው ፤መኪና የስራው ስው ከስው ውስጣዊ ሆድ እቃ አካል ተነስቶ ነው መኪናን የስራው፤ኧኧኧኧ ሊሎችም እንደዛው ደራሲም ከህይወት በመነሳትና  እና ፈጠረን ካለው ፈጣሪ ህይወትን በመውሰድ ነው የሚደረሰው።    ልዩነቱ ፈጣሪ የፈጠረቻው ፍጥረታት በእውን አሉ እኛ የፈጠረኛቸው ደሞ በምናብ አሉ። እኒን ምናባችን ውስጥ ያሉትን ስዎች በአካል ማምጣት በጭራሽ አንችልም።ኧኧኧኧ ለምሳሌ እኔ በምፅፈው ድረሰት ውስጥ 3ሜትረ ቁመት ያላት እምምምም ፤ ፀጉሯ እስከ እግረ ጥፍሯ የሚደረስ እእእእ፤ አፈንጮዋ በጣም ትንሽ፤ አይኗ በጣም ትልልቅ፤ እጅ እና እግሯ የአራስ ህፆን መጠን ያላቸው፤ እእእእእ ስትሄድ አንካሳ ሴት በምናቤ ፈጥሬ መፃፍ መብቴ ነው።        ፨ታዲያ እኔ መብቱ የግሌ ነውና  ብገላትም ፣ባኖራትም፣ ባሳምማትም፣ ባድናትም ፣ባስቆዝማትም፣ ክፉ ባረጋትም፣ ደግ ባረጋትም ፣መብቴ ነው። በተቃራኒው ቁመቷንም አጭረ አረጌ ፁጉሯን ረዥም ማረግ መብቴ ነው ብዙ አፈቃሪ ወንድ ወይም ወንድ የማይጠጋት ማረግም የእኔ ውሳኔ ነው። በእረግጠኝነት ይህቺ የነገረኮችሁን ሴት በምናባቹ አስባችዋታል ግን በአካል የለችም።       ፨እኔ በምናቤ የሳልኳትን ስው እንኳን እሷኑ አምጣ ብትሉኝ አላመጣም። ግን በሀሳባቹ አኑሬያታለው ምክንያቱም የእኛ ስልጣን እዚህ ድረስ ስለሆነ ነው። ፈጣሪ ግን ካሻው አሁን በእዚህ ስአት ከሁለት ቁመት አብዝቶ ከነሳቸው ስዎች መጀመሪያ የገለፅኩላችሁን 3ሜትረ ቁመት ያላትን እንስት ፈጠሮ እና ህይወት ስጥቶ ማኖረ ይችላል።እኔም የሆነ ደራጃ ድረሰ መሄድ እችላለው። ፈጣሪ በአንድ እንስት መሀፀን ውስጥ ይህቺን ሴት ሲፀንሰሰ እኔ በሀሳቤ ይህቺን ሴት ፀነስኩ ይባል። ታዲና ይህቺ ሴት ፈጣሪ በውልደት ወደ እዚህ አለም ሲያመጣት እኔ የእሱ ተፈጣሪ ደሪሲ ደሞ ይህቺን ሴት በምናቤ አረግዤ በብእሬ እወልዳታለው።      ፨ እኔም ሀሳቤን እሷም  በእኩል ህመም እናስተናግዳለን። ይህንን ካልኩ ዘንዳ ሾለ ድረስቴ አንዳንድ ነገረ ልበላቹ ያው ይህ መፅሀፈ በእውነቱ ብዙ ዋጋ አስከፈሎኛል። ውስጡ ያለውን  ሀሳብ ትወዱታላቹ ብዬ አስባለው አመስግናለው"። ሲል የታዳሚ ጭብጨባ አጀበው።     ፨ በመሀል የሙዚቃ መሳሪያ ድምፅ ገባና የፕሮግራሙ አቅራቢ ሰው አመስግኖ ተባባሪ አቅራቢውም "አብራችሁን እንድትቆዩ በአክብሮት እንጋብዛለን" አለች። ወዲያው  የሙዚቃ ክላክሲካል ተስማ። እረዥም ደቂቃዎች ካስቆጠረ በኋላ የፕሮግራሙ መሪ ድምፅ ተሰማ "ተመልሰናል አድማጭ ተመልካቾቻችን አሁን በመቀጠል የደራሲ መሀመድ ሳላዲን ባለቤት የሆነችው ወይዘሮ ከድጃ ኢብራሂም  ንግግረ እንድታረግልን በማክበር እንጋብዛታለን" አለ ወንዱ አቅራቢ። ከዛ ጭብጨቦ ተከተለ መድረግ ላይ  እንድትወጣ አበረታቶት። ጨብ ጨብ.......... ጨብ ጨብብብብብብብብብብ የደራሲ መሀመድ ሳላዲን ሚስት በሙዚቃ እና በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ እየሄደች ይመስላል።ከደቂቃዎች በኋላ መድረክ ላይ ወጥታ ወደ ማይኩ ተጠጋች          " ሰላም እንዴት ቆያቹ"         አለች። ከዛን በኋላ ጭብጨባ አጀባት። እሷም "በመጀመሪያ ፣በመሀል  እና በመጨረሻም ጥሉ ለማይጥለን አምላክ አልሃምዱሊላህ እኔ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ማሚዬ ሁሌም ጥሩ ሾል ለመስራት እንደጣረ ነው። እሱ ለእኔም ለልጆቹም እንዲሁም በዙሪያው ላሉ ስዎች ሁሉ ጥሩ ሰው ነው።ይህ የፆፈው መፅሀፍም በህይወታቸው ተስፋ ለቆረጡ ስዎች የህሊና ብረታት ይሆናል። ይህ መፅሀፈ በቃ አንብባቹ ተረዱት ምንም ማለት አልችልም አመስግናለው" አለች።       ሁሉም አጨበጨብ ሴቷ የፕሮግራም አቅራቢም "እናመስግናለን ወይዘሮ ከድጃ ፣ተመልካቾቻን እና አድማጮቻችን ፍቅረን እና ስላምን እንዲሁም ደስታን እንዲሰጣቹ እየተመኘን ፕሮግራማችንን በእዚሁ እንደዘጋለን" አለች። ወንድ አቅራቢውም "መልካም ጊዜ ስናይ እለታትን እንድታሳልፉ እንመኝላችዋለን" አለ። እና ፕሮግራሙ አበቃ።     ፨ፅናት "ውይይይ ደስ አይሉም በፀሎቴ እንዲህ አይነት ፍቅረ ሲኖረ አለ እንጂ የእኛ አባት" አለችና አንገቷን አቀረቀረች። ፅናት አባት እና እናቷን በፎቶ እንጂ በአካል ያየቻቸው ማስታወስ በማችልበት የጨቅላ እድሜዋ ላይ ነው በፀሎት ግን በትንሹ ታስታውሳቸዋለች። እሷም "እውነትሽን ነው ፅናቴ የእኛ አባት እኮ በጭራሽ ሰው አይደለም" አለች። ሁለቱም አይምሮ ውስጥ የአባታቸው እረኩስት ታወሳቸው።   ፅናት እህቷ በፀሎት  በነገረቻት መሰረት በፀሎት ደሞ አይኗ ባየው መሰረት አስታውሰው ፊታቸው ጭር አለ።በፀሎት በሀሳብ ጭልጥ አለች።ያሰብት ሾለ እናታቸው የሙት ቀን ስለሚወዶት እናታቸው አስቃቂ ግድያ እና ሾለ ገዳዩ አባታቸው ነበር።      ፨ጊዜው 11 አመታትን አስቆጥሯል።እናታቸው ያኔ ፅናትን ወልዶ አራስነቷን ጨረሳ የፅናት ክረስትና በአል የተከበረበት ጊዜ።በፀሎት ያን ጊዜ 5 አመቷ ነበረ። በጊዜው የፅናት የክረስትና ቀን ስለሆነ ሁሉም ደስተኞች ነበሩ።እናታቸው ከስፈራቸው ባለ ሀብት ገንዘብ ተበድራ በደመቀ መልኩ አክብራው ነበረ።  አባታቸው ለድግሱ አልገኝም ብሎ ወደ እህቱ ቤት ሄደ። የአባታቸው እህት የስይጣን አለቃ ባህሪ ያላት ሴት ናት። አባታቸው እናታቸውን ካገባ በኋላ "ሚስትክን ከሊላ ወንድ ጋረ አየዋት እሷ  በጭራሽ ላንተ ፍቅር የላትም" በማለት በመከረችው መስረት በፀሎት ሆዷ ውስጥ እያለች ልጅቷ የኔ አደለችም በማለት ይነዘንዛት እና ይጨቃጨቃት ነበረ። . . 🥀..ከ 150 ላይክ በሗላ ክፍል 2 ይቀጥላል ……..           .           . 𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 @ahmaric_quotes @ahmaric_quotes

  • ❤️❤️ ፅናት ❤️❤️ አዲስ ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለድ..❤️ እንጀምራለን 👍 SHARE እያረጋቹ ♥️ 🙏                  .                  .                  . 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹                  .                  .                  . ከፍቅር ታሪክ የቴሌግራም ቻናል 𝐉𝐨𝐢𝐧 በማለት ራሶን በጣፋጭ ትረካዎች ዘና ያድርጉ ..♥️✨                  .                  .                  . .............................................................. .............................................................. ..............................................................                  .                  .                  .              𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗   ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ 👇👇👇👇 @https://t.me/ahmaric_quotes @https://t.me/ahmaric_quotes ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

  • እና እስቲ በቻላቹት መጠን Channelችንን ለወዳጃቹ ሟር ሟር በማድረግ አበረታቱን 🙏 እኖዳቹዋለን

  • ውድ የChannel ቤተሰቦቻችን በቅርቡ ወደ ድሮ Post ልንመለስ ነው እና እስቲ መመለሳችንን የምትፈልጉ በimoji አሳዩን 👇

  • Hello family 👋

  • 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes

  • 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes

  • 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes

  • 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes

  • ዛሬ አንድ ነገር ልንገራችሁ። በእግዚአብሔር በጣም ከፍቶኛል ። ዛሬ ማታ አዲስ ታሪክ እንደምጀምርላችሁ ነግሪያችሁ ነበር አደል። እና ባለታሪኳ ሂሩት ትባላለች የስራ ባልደረባዬ ናት ውበቷን ወጣትነቷን ችግር ያረገፈባት ሴት ነበረች። ታሪኳን ቁጭ አድርጋ ነገረችኝ ለምን አትፅፊውም የኔ ህይወትኮ አንድ ፊልም ይወጣል የስንቱን እየፃፍሽ የኔን ምነው ዝም አልሽ እስኪ አፈምሽኝ አለችኝ። እየተሳሳቅን በቃ ቀጣይ ያንቺን ታሪክ ነው ምፅፈው ብዬ ቃል ገባሁላት ልክ ፅጌሬዳን እንደጨረስኩ ዛሬ ማታ የሷን ታሪክ ክፍል አንድን ልለቅላችሁ ነበር እንደምትወዱት እንደምትማሩበት አሷን ለማግኘት እንደምትጓጉም ጭምር እርግጠኛ ነበርኩ። ዛሬ በጠዋት ተነስቼ ለባብሼ ወደ ቢሮ ሄድኩኝ። ስገባ ሰላም ነበር ሁሉም እየተሳሳቀ እየተጨዋወተ የራሱን ወሬ እያወራ  ወደ 3 ሰአት አካባቢ ላይ ግን አንዳንድ እያሉ ወደበረንዳ እየወጡ ማልቀስ ጀመሩ ነገሩ አልገባንም ነበር ጠጋ ብለን ምን እንደተፈጠረ ጠየኳቸው ሂሩት አርፋለች አሉኝ። ማለት አልኳቸው ምክንያቱም ሀሙስለት ቁጭ ብለን ምሳ በልተናል ቁጭ ብለን ስለታሪኳ አውርተናል ደስ የሚል ነገር ላይ ስለሆነች ቀጣይ የህይወት መስመሯን ለመቀየር እንዳሰበች ነግራኛለች። ትንሽ ህመም እየተሰማት ስለነበርም የአቡነሀራ ድንግልን ፀበል እንደምሰጣትም ቃል ገብቼላት ነገ ላቀብላት ነበር ታሪኩን ፅፈሽ እስክትጨርሺ የኔም ህይወት ስለሚቀየር መጨረሻው ቆንጆ ይሆንልሻል አለችኝ። ግን እኔ ታሪኳን መፃፍ ሳልጀምር የሷ ታሪክ ተፈፀመ ። በቃ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላቅም በቃ ለዚህ ህይወት ነው ምንባክነው በቃ ከፍቶኛል 😔 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes

  • йоС пОдписи

  • 😔 🔍Join our second Channel🔎           @ahmaric_quotes