ዐምደ ሃይማኖት
Статистика- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 180
- 1/48двое суток
- 206
- 1/72трое суток
- 222
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
የሥራ ማስታወቂያ 👇👇👇 የስራው ዓይነት :- Type writer ወንድማችን ዲ/ን ዮናታን መርእድን ያነጋግሩ 0994026877 ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
ዛሬ ከመርሐግብር በኋላ እህታችን አለም አስጨናቂ ቤት ገንፎ ስለተጠራን ተሰብስበን እንሔዳለን ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
🎯የክፍያ መጠን ዝርዝር ለወጣት፦ 50 ብር ለታዳጊ፦ 30 ብር ለማዕከላውያን፦ 10 ብር ማሳሰቢያዎች 🎯 አባላት ክፍያ ለመፈጸም ሲመጡ የክፍያ ደብተራቸውን መያዝ እንዳይረሱ ተገልጿል። 🎯 በተጠቀሱት የክፍያ ቀናት ወር በገባ(በመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት) ውስጥ ያልከፈለ አካል 10 ብር ቅጣት ይጣልበታል። የክፍያ ጊዜ፣ ቦታ እና አድራሻ 📅 የክፍያ ጊዜ፦ ወር በገባ በመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት ውስጥ 📍 ቦታ፦ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ወይም በአስተባባሪዎች እጅ የክፍያ አማራጭ ፦ ገንዘቡን በጥሬ( cash )ወይም በE birr [ +251949583325 ] ምህረት አለማየሁ በሚለው ይላኩ " ሲልኩ Screenshot ያንሱ !! " ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
ወርሃዊ መዋጮ ያልከፈላቹ በዚህ ክፈሉ 094 958 3325 (ምህረት አለማየሁ) ኢ ብር ወጣት 50 ብር ታዳጊ 30 ብር ማዕከላውያን 10 ብር ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
ኑ ለቤተክርስቲያናችን ፣ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ፣ ለሐገራችን ፣ ለቤተሰባችን ፣ ለራሳችን እንጸልይ “አሁንም፥ አምላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደሚሆነው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡ፥ ጆሮችህም የሚያደምጡ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ።” 2 ዜና 6:40 ጸሎት ክፍል ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
እንኳን ለጾመ ፍልስታ አደረሳችሁ አደረሰን ይህን ፆም ለመጀመሪያ ጊዜ የፆሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የፍስልታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 ድረስ ያለው ነው፡፡ ይህም ፆም የእመቤታችን ትንሳኤና ዕርገት መታሰቢያ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን አሰተምሮ መስረት እመቤታችን በጥር ወር 21 ቀን በ49 ዓ.ም በ64 አመቷ አርፋለች፡፡ ሐዋርያትም በድኗን ሊቀብሩ ወደ ጌቴ ሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሳስተው በእሳት ሊያቃጥሏት ሲሉ መላዕክት አስክሬኗን ወስደው በገነት አኑረዋታል፡፡ በነሐሴ ወር አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምሕላ ተቀብሯል፡፡ በዚህ የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያው ቶማስ አልነበረም እመቤታችንም በተቀበረች በሶስተኛው ቀን እንደልጅዋ ተነስታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ህንድ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ያገኛታል፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቻለሁ ብሎ ከደመናው ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናናችው ከእርሱ በቀር ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያት እንዳላዩ ነገረችው፡፡ ለምስክር እንዲሆነውም ሰበኗን ሰጥታው አረገች፡፡ ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ሚስጥሩን ደብቆ አይደረግም ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር ›› አላቸው እነርሱም ለማሳየት መቃብሩን ሲከፍቱ አጧት ለምስክር ይሁንህ ብላ የሠጠችውን ሰበኗንም አሳያቸው እነርሱም ሰበኗን ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደየ ሐገረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡ በዓመቱ ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ሳናይ ይቅርብን ብለው ከነሐሴ ጀምረው ሱባኤ ገቡ ከነሐሴ 14 ቀን ትኩስ በድን አድርጎ ጌታችን ሰጥቷቸው ከቀበሯት በኋላ በነሐሴ 16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም መንበር አድርጎ አቁርቧቸዋል እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችን በረከት ለማግኘት ትፅማለች በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህ ፆም በተለይ ሕፃናት ያከብሩታል በዚህም 15 ቀን ፆም የማይፆም የማይቆርብ ሕፃን የለም፡፡ የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው ብዙ ምዕመናን ቤታቸውን እየዘጉ በየቤተ ክርስቲያኑ ሱባኤ ገብተው በፆም በፀሎት ይሰነብታሉ፡፡ ፆሙም የሚፈታው በትንሳኤዋ መታሰቢያ ዕለት በነሐሴ 16 ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት የረድኤት የንሰሐ የምህረት ያደርግልን ወላዲተ አምላክ ማርያም ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ትስጠን ታሰጠን አሜን!!! መልካም ሱባኤ! ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
የሥራ ማስታወቂያ 👇👇👇 የስራው ዓይነት :- ስፒከር ማከራየት ደሞዝ:- በስምምነት የስራ ቦታ:- ከዚራ የስራ ሰዓት:- በቢሮ ሰዓት እኅታችን እድላዊት ተክሌን ያነጋግሩ 0914966847 ይቀላቀላሉን 👇👇👇 https://t.me/amdehaymanot1213
በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ለአርባ ዐመታት በጉባኤ መምህርነት እና በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ ከዚህ ዐዓለም ድካም አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው ብፁዕ አቡነ በርቶሎሜዎስ በመሩት ሥርዓተ ጸሎት ግብዓተ መሬታቸ ተፈጸመ። "መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት = ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ሰው ማን ነው?" መዝ. ፹፰፡፵፰ የሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ አጭር የሕይወት ታሪክ ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ ከአባታቸው አቶ አማረ በርሀ እና ከእናታቸው አብርሀት ንጉሥ በትግራይ ክፍለ ሀገር በማይጨው ወረዳ ልዩ ስሙ ኮረም በተባለ ቦታ በ1933 ዓ/ም ተወለዱ፡፡ ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ በተወለዱበት ቦታና በአጎራባች ባሉ አብያተ ክርስቲያናት የቃልን ትምህርት ጨምሮ ከፊደል እስከ ንባብ ያለውን ትምህርት በወቅቱ ከነበሩ መምህራን ተምረዋል። በመቀጠልም በ1950 ዓ/ም የቅኔን ትምርህት ተምረው ተቀኝተዋል። በመቀጠልም በራያ ዓዘቦ ከየኔታ ወልደ ሰንበት የቅኔን ትምህርት አደላድለዋል። ከዚያም በመነሣት በቀድሞው አጠራር ወደ ጎጃም ጠቅላይ ግዛት በማምራት በሞጣ፣ በዋሸራ፣ በጎንጅ፣ በጽላሎ ከነበሩ ከነበሩ ታላላቅ የቅኔ መምህራን ዘንድ ቅኔን ከነአገባቡ በመማር በቅኔ መምህርነት ተመርቀዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ ካላቸው የትምህርት ፍላጎት የተነሣ ወደ ታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ በመሄድ በመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ ተመርቀዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ በቅኔና በመጻሕፍት ትርጓሜ በመምህርነት ተመርቀው ትምህርታቸውን በአግባቡ ካጠናቀቁ በኋላ በ1978 ዓ/ም የፍቅር ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ድሬዳዋ ከተማ በመምጣት በርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በቅኔና በመጻሕፍት ትርጓሜ መምህርነት ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ ብቁ አገልግሎታቸው ታይቶ በ1987 ዓ/ም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ኀላፊ ሆነው ተመድበዋል። በወቅቱም አጎራባች በሆነችው በሐረር ከተማ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሐድሶን እናከናውናለን የሚሉ ከሓድያንና መ*ናፍ*ቃን በቤተ ክርስቲያን ላይ ከውስጥና ከውጪ በመሆን ከፍተኛ ወረራ ለማድረግ ሙከራዎችን ባደረጉበት ጊዜ ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ በታጠቁት የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍ የመናፍ*ቃንን ምንፍ*ቅና ይቈርጡ ዘንድ ከየካቲት 1/1987 ዓ/ም እስከ ሠኔ 30/1987 ዓ/ም ድረስ ለ5 ወራት ያህል በልዩ ልዩ ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲያገለግሉ በሐረር ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኀላፊ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በመቀጠልም ከሐረር ሐገረ ስብከት ተመልሰው የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር ሆነው ተመድበዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ የአባ እንጦንስና የአባ መቃርስ አሰረ ፍኖትን በመከተል በ1998 ዓ/ም የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜን ባስመሰከሩበት በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ከታላቁ ሊቅ ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሥርዐተ ምንኵስናን ተቀብለዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል ፍጹም ውጤታማ አገልግሎታቸው ታይቶ የድሬዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ ሆነው ተመድበውም አገልግለዋል። የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቃውንት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ሆነውም ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ እስከ በዕርግና ምክንያት ታመው ማስተማር እስካልቻሉበት ድረስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሙሉ ዐቅማቸው አገልግለዋል። ብዙ ዲቆናትን፣ ቀሳውስትን፣ ቆሞሳትንና ጳጳሳትንም አፍርተዋል። ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የቅኔና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ መምህር ሆነው ከመመደባቸው ባሻገርም በመልካም ፈቃደኝነት በመልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም እንደ አንድ አገልጋይ በመሆን በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌልና በትርጓሜ መጻሕፍት አገልግለዋል። ከታመሙበት ዕለት ጀምሮም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ሲያደርግና ሲያሳክማቸው የቆየ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውም እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ካጠገባቸው ባለመለየት ልዩ አስተዋፅኦን አድርገዋል። ነገር ግን ለ14 ወራት በሕክምና ሲረዱ ቢቆዩም ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር ፹፰፡፵፰ ላይ "መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት = ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ሰው ማን ነው?" እንዳለ በተወለዱ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ለሐምሌ 25 አጥቢያ ከሌሊቱ 8 ሰዓት 2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ዐርፈዋል። ሥርዐተ ማኅሌት ተቁሞ ሥርዐተ ፍትሐት ሲከናወን ዐድሮም ሐምሌ 26/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ ፫ ሰዓት ላይ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሠናያት ኀይለ ማርያም ገብረ ሚካኤል፣ የየክፍሉ ኀላፊዎች፣ የድሬዳዋ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሓፊዎች፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና መላው የድሬዳዋ ከተማ ማኅበረ ምእመናን በተገኙበት የታላቁ ሊቅ፣ በላዔ መጻሕፍት፣ መዝገበ ትሕትና፣ መፍቀሬ ሰብእ፣ ተሓራሚ፣ መናኝ፣ ባሕታዊ የሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል አማረ ግብአተ መሬት ከ፵ ዓመታት በላይ ባገለገሉበት በድሬዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ተፈጽሟል። © የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በቲክቶክ ገጻችን ያጋራነውን ይመልከቱ ላይክ ሼር ኮፒሊንክ ሪፖስት በማድረግ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ https://vt.tiktok.com/ZS4SW376v/
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи