tgindex
አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

Статистика

Official Arbaminch University ® ማስታወቂያዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት! ሀሳቦች እና እንዲተላለፍላችሁ የምትፈጉት ነገር ካለ በ @newneway @firaK19 @miko1122 @ADA1249 ላይ ያግኙን፡፡ AMU Info ...... እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ ይደርሶታል፡፡ ።።ከተማሪ ለተማሪ።።: Arba_Minch_university

Последний пост
19 дек. 2024 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 702
+2 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 134
20 постов
Вовлечённость
165,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሃይድሮሊክ ቤተ ሙከራ Water Technology Institute: Hydraulic Laboratory @amucampus @firak19

  • በጫሞ ካምፓስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጫሞ ካምፓስ በ2017 ዓ.ም ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ የቢዝነስና አኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲንና የካምፓሱ ኃላፊ ዶ/ር መስፍን መንዛ ከዚህ ቀደም በተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በአብዛኛው አመርቂ ውጤት በማምጣት ማለፍ እንደቻሉ ገልጸው ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርታቸው እና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ መደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ተሻግረው መቀጠል እንዲችሉ እንደ ካምፓስ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግም ዲኑ ተናግረዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የኮሌጁ ዲን፣ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን፣ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የተማሪዎች ኅብረት እና የሰላም ፎረም አባላት የተገኙ ሲሆን የተማሪዎች የዲሲፕሊን ሕጎች፣ በሁሉም ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶች እና  በግቢው የሚኖራቸውን  ቆይታ በሚመለከት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብሩህ ተስፋ ማዕከል! የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት @amucampus @firak19

  • @amucampus

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለሪሚዲያል ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ሰጥቷል፡፡                       የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው ተማሪዎች የተሰጣቸውን መልካም ዕድል ሳያባክኑ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎች በኮሌጁ የሚኖራቸው ቆይታ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሲማሩ የቆዩትን ትምህርት የመከለስ ሥራ እንደሚሰራና ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ኮሌጁ የሚጠቅበትን እንደሚወጣ እንዲሁም ከተማሪዎቹ የላቀ ትጋት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተሰጠ ሁለተኛ ዕድል መሆኑን የገለጹት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲን ዶ/ር አድማሱ ጣሰው በበኩላቸው ተማሪዎች በሚኖራቸው የግቢ ቆይታ ቤተሰባዊ ግንኙነትን በማዳበር መብትን መጠቀምና ግዴታን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ብዝሃ ማንነት ያለበት ተቋም በመሆኑ ተባብሮና ተቻችሎ የመኖር ባህልን ማዳበር ከተማሪዎቹ እንደሚጠበቅም ም/ዲኑ አክለዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲሲፕሊን መመሪያዎች እና የተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍና እና የተማሪዎች ኅብረት የሚሰጡት አገልግሎት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በዕለቱ የኮሌጁን ዲን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንትና አባላት ተሳትፈዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብሩህ ተስፋ ማዕከል! የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት @amucampus

  • @amucampus

  • ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አዲስ ለተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ የመልካም ምኞት መግለጫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀዳሚ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን ገናና ስም ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተርታም ይመደባል ፡፡ለዚህም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የነበረው አመራር ጥንካሬ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበራችሁ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ልቆ እንዲወጣ፣ ሰላሙ የተጠበቀና ለሃገሪቱ የሰላም አምባሳደር ምልክት መሆን እንዲችል ለተማሪዎችም እንደመፈክሩ የብሩህ ተስፋ ማዕከል መሆኑ እንዲመሰከርለት ስላደረጋችሁ፣ የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች ህብረት በሙሉ አቅማችሁ በመደገፍ ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን አዲስ ለተመደባችሁ ለዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ይህን ግዙፍ ሃገራዊ ተቋም ለመምራት ዕድል ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን እንደተማሪዎች ህብረት  እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አብረናችሁ ለመስራት እና የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ተሰናድተናል። በተማሪዎች እና  በአመራሩ መሀከል ድልድይ በመሆን ፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን በማስጠበቅ ፣ የተቋሙን ሰላም በማስቀጠል በበለጠ ለመትጋት እንደተሰናዳን መግለጽ እንሻለን። በተለይም በአሁኑ ሰዓት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስገዝነት ለሚያደርገው ሽግግር የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ  እንደሚሻ የምንገነዘበው ነው። የትምህርት ዘርፉ ሪፎርምም ይኼንን ተልዕኮ ከግንዛቤ ያስገባ መሆኑን እናምናለን። የተማሪዎች ህብረትም የዩኒቨርስቲው ማህረበሰብ አስኳል እንደመሆኑ መጠን ከትላንት በተሻለ ትጋት ፤ ከአምናው በበለጠ ጥረት መስራት እንደሚገባንና የሚጠበቅብንን ለመከወን ፣ የተሰጠንን ተልዕኮ ለመተግበር እና ከተማሪዎች የሚነሱ ሀሳቦችን ለማስፈፀም ተግተን እንሰራለን፡፡ @amucampus

  • 20 дек. 2023 г.11,1 тыс7

    без подписи

  • 20 дек. 2023 г.10,8 тыс7

    без подписи

  • без подписи

  • 20 дек. 2023 г.11 тыс408

    без подписи

  • የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ፈረንሳይ ሀገር ከሚገኝ ‹‹Fund for Innovative Development (FID)›› ድርጅት ጋር በመተባበር በሚያከናውነው ‹‹Adoption of Rhizobium Inoculant Technology (ARIT)›› የተሰኘ የትብብር ፕሮጀክት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ‹‹Bio-Fertilizer›› ማምረት ላይ የለውጥ ማሳያ (Progress) ሪፖርትና የመስክ ምልከታ ታኅሣሥ 4/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ የምርምር ዳይሬክቶሬት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም በትብብር ፕሮጀክቱ ባቄላ፣ አኩሪ አተር፣ ቦሎቄ፣ ሽምብራ፣ አተርና ሌሎች ጥራጥሬዎች/Leguminous Plants/ ለማምረት የሚያገለግል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለሙከራ የሚመረትበትና ማዳበሪያው በማሳ ላይ በተክሎቹ ላይ የሚሞከርበት የምርምር ማሳያዎች የመስክ ምልከታ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ምርምሩን በማሳደግ ለአርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በተለያየ መልኩ ለማቅረብ እንዲሁም መሰል ምርምሮችንና ፕሮጀክቶችን ለማሳደግ እንደሚሠራ ዶ/ር ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የባዮሎጂ ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አሽናፊ ኃይሉ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በሁለት ዓመታት ቆይታ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የገጠሙ ችግሮችና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥ ብሎም በኮሌጁ ግቢ ውስጥ የተደራጁ የሙከራ ቦታዎችና መስክ ላይ ያሉ ምርቶችን በመመልከት ለቀጣይ ሥራ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችን ለማግኘት መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ ዶ/ር አሸናፊ በጥቂት በጀት ብዙ ተማሪዎችን በተግባር ማስተማር መቻሉና የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረት ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ ከሚቻልበት ደረጃ መደረሱ የፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸሞች መሆናቸውን የለውጥ ማሳያ ሪፖርቱና የመስክ ምልከታው ያሳያሉ፡፡ በአፈጻጸሙ እንደ ድክመት የተጠቀሱ ጉዳዮችን ለመቅረፍና በስፋት በማምረት ለማኅበረሰቡ ለማዳረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚሠሩ መሆኑንም ዶ/ር አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ፈረንሳይ ሀገር ካለ ድርጅት ጋር በጋራ እንደሚሠራና ሙሉ ወጪው በድርጅቱ እንደሚሸፈን ጠቅሰው እንደ ኮሌጅ መሰል የትብብር ሥራዎችን እናበረታታለን ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቶችን በየጊዜው የመገምገም ሥራ በዕቅድ ተይዞ የሚሠራ ነው ያሉት ዲኑ በለውጥ ማሳያ ሪፖርቱና በመስክ ምልከታው ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ ሥራዎች በፕሮጀክቱ እንደተሠሩ ማየት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተርና ተመራማሪ ቱማ አየለ መሰል ምርምሮችን የማከናወንና የምርምር ውጤቱን በሚገባ በመያዝ አባዝቶ ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ የማድረስ ሥራ ተጠናክሮ ቢሠራ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ብሎም ማዳበሪያ በውድ ዋጋ መግዛትን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ በኮሌጁ የባዮ ቴክኖሎጂ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በምርምር ሥራው ጥሩ ዕውቀትና ጠቃሚ ልምዶችን እንዳገኙ ገልጸው ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በዘርፉ ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ ሥራዎች ለመሥራት መነሳሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የጋሞ ዞን ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል አመራሮች፣ መምህራንና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ @amucampus @amucampus