ነጭ ሳር ካምፓስ ተማሪዎች ህብረት (አ.ም.ዩ)
Статистика☞ይህ በአ.ም.ዩ የነጭ ሳር ካምፓስ ተማሪዎች ህብረት ቻናል ነው። [በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ] ☞This is the official Nech Sar Campus Students' Union Telegram channel(AMU) ➡️መረጃ እና አስተያየት ለማድረስ 👇👇👇👇👇👇👇 @NSSU_AMU_bot 🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕 ላይ ✍️ይፃፉልን።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 811
- 1/48двое суток
- 929
- 1/72трое суток
- 1 002
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ታሪካዊ የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ በሕክምና ትምህርት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት ዘርፍ አብሮት ለሰራውና የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከተው ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ታሪካዊ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም አካሂዷል። በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢንጂነር አብደላ ከማል ባስተላለፉት ዋና መልዕክት፣ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዋነኛ የመማሪያ፣ የምርምር እና የተግባር ልምምድ (Attachment Site) ሆኖ በመቆየት ብቁ ሐኪሞችንና የጤና ባለሙያዎችን ለማፈራት ላደረገው በዋጋ የማይተመን አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት የተደረገው የባለሙያዎች ሽግግር የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት የሚያቆም ሳይሆን፣ በዩኒቨርሲቲው እና በአጠቃላይ ሆስፒታሉ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት መካከል ያለው አጋርነትና ትብብር በቀጣይም በተሻለ ጥራትና አቅም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢና የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለዩኒቨርሲቲው የጤናና ሕክምና ትምህርት የተግባር ልምምድ ማዕከል በመሆን ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል። የተደረገው የባለሙያዎች ሽግግር የሕብረተሰቡን አገልግሎት ሳይጎዳ መከናወኑ አርአያነት ያለው መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም በጋራ ሥራዎች ላይ ትብብሩ እንደሚቀጥልና ለዚህም የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ደስታ ጋልቻ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የሁለቱን ተቋማት ታሪካዊ የትብብር ጉዞና የደረሱበትን የዕድገት ምዕራፍ በሰፊው አብራርተዋል። ዶ/ር ደስታ እንዳመለከቱት፣ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ተቋም ለተቋም ምንም ዓይነት የጽሁፍ ውል ሳይኖር የሆስፒታሉ ባለሙያዎችን እንደ እንግዳ መምህርነት ሲጠቀም የቆየ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ የልምድ ልውውጥ በማድረግ በተዘጋጀ የጋራ መግባቢያ ስምምነት (MOU) መሠረት የተቀናጀና ስልታዊ ሥራ ሲከናወን ቆይቷል። ዩኒቨርሲቲውም ከአገልግሎት ማግኘት ባሻገር ለሆስፒታሉ እንደ አልትራሳውንድ፣ አልጋዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች እና ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁሶችን በድጋፍ ሲያቀርብ መቆየቱን አወስተዋል። ዶ/ር ደስታ አክለውም የማስተማሪያና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ ከታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተኝቶ ሕክምናን ጨምሮ ሰፊ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ፣ የሥራ መስተጓጎል እንዳይፈጠር በተዋቀረው የ"Exit Strategy" ኮሚቴ ምክረ-ሐሳብ መሠረት ውጤታማ የሥራ ሽግግር መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በልዩ ሁኔታ ስምምነት ከተደረገባቸው አገልግሎቶች (እንደ ፊስቱላ እና ፕላስቲክ ሰርጀሪ ያሉ) በስተቀር ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል መጠቃለላቸውን አስረድተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ ዶ/ር አዲሱ ተስፋዬ በበኩላቸው ለተደረገው ታሪካዊ የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዶ/ር አዲሱ ሁለቱ ተቋማት ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ውስጥ እጅግ ውጤታማና ፍሬያማ የጋራ ሥራዎችን ማከናወናቸውን ገልጸዋል። አክለውም የተደረገው የሥራና የባለሙያዎች ሽግግር የማህበረሰቡን የሕክምና አገልግሎት በማይጎዳና በማያስተጎጉል መልኩ መጠናቀቁን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ላደረገው በዋጋ የማይተመን ድጋፍ አመስግነው ይህ ስልታዊ አጋርነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና እንደማይቋረጥ አረጋግጠዋል። በታሪካዊው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ቦጋለ ገብረማሪያም፣ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጳውሎስ ታደሰ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡- ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/ ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/ ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
видео или голосовое, без подписи
🌟 ነፃ የሕክምና ምርመራ እና የምክር አገልግሎት ጥሪ! 🌟 በ"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" መሪ ቃል፤ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሙሉ በነሐሴ ወር የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎት ይሰጣል። 📅 የአገልግሎት መበሰሪያ ቀን እና ሰዓት፦ነፃ አገልግሎቱ ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል። 📌 አስፈላጊ ማሳሰቢያ፦ይህ ነፃ አገልግሎት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት የሕክምና ዓይነቶች ብቻ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከተጠቀሱት ውጭ ያሉ ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶች በነፃ አገልግሎቱ ውስጥ አይካተቱም። ✨ በነፃ የሚሰጡት አገልግሎቶች ፦ የስኳር እና የደም ግፊት ምርመራና የምክር አገልግሎት የቆዳ እና አለርጂ ምርመራ የዓይን ምርመራ የሥነ-አእምሮ ምርመራና ምክር የተላላፊ በሽታዎች ምርመራ (HIV፣ Hepatitis፣ TB፣ Syphilis) የቅድመ ካንሰር ምርመራ (የጡት እና የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ) በተጠቀሱት አገልግሎቶች ለመጠቀም ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ጀምሮ ወደ ሆስፒታላችን በአካል በመምጣት ይጠቀሙ!
ነጭ ሳር የነሃሴን ወር ምትቆዩ የነጭሳር ካምፓስ ተማሪዎች ከታች ባለው ቦት ሙሉ ስም ና ID no department ላኩልኝ የነጭሳር ካምፓስ የተ/ህብረት ጽ/ቤት "We are here to serve students!" ➡️መረጃ ጥያቄ እና አስተያየት ለማድረስ @NSSU_AMU_bot ላይ ✍️ይፃፉልን
видео или голосовое, без подписи
" የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ይሰጣል " - ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። መረጃቸውን ወደ ሲስተም ያላስገቡ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ መረጃ የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡ በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸው በተማሩበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
እዚ ሊስት ውስጥ ስማቹ የሌለ እና ኣከውንታቹ ከተሳሳተ እንዲሁም non cafe መሆን የምትፈልጉ ካላቹ እስከ ነገ ተማሪዎች አገልግሎት በአካል በመገኘት Report ማረግ ትችላላቹ። ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር ማረግ አይረሳ
ነጭ ሳር ካምፓስ ተማሪዎች ህብረት (አ.ም.ዩ) pinned a file
በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ቤት መመለስ የማትችሉና ባለፈው ባወጣነው ማስታወቂያ መሰረት የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ጥያቄው ተቀባይነት ያገኘው ቀድመው የመጡ የ50ዎቹ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው እስኪጠናቀቅ ነጭ ሳር ካምፓስ የምትቆዩ ይሆናል ::
Share 'student_registry_updated.xlsx' እዚ List ውስጥ ስማቸጀ ኖሮ ግን ወደቤት የተመለሳቹ ካላቹ ከታች ባለው bot አሳውቁን። እናመሰግናለን የነጭሳር ካምፓስ የተ/ህብረት ጽ/ቤት "We are here to serve students!" ➡️መረጃ ጥያቄ እና አስተያየት ለማድረስ @NSSU_AMU_bot ላይ ✍️ይፃፉልን
የዛሬው የምረቃ ሥነ ሥርዓት በከፊል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи