tgindex
Berbir Mereja / በርብር መረጃ

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

Статистика

Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.

Последний пост
14:34
Последнее чтение
14:21
Постов за неделю
40
Всего постов
262
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
5 190
−8 за 4 дн.
Сутки
−4
−0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
765
40 постов
Вовлечённость
14,7%
к подписчикам
Постов в день
5,7
всего 262
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
635
1/48двое суток
727
1/72трое суток
784

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14:342491

    видео или голосовое, без подписи

  • 11:3842312

    የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የቀድሞው የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት አቶ ከቡር ገና "አዲስ አበባን ማን ይውሰዳት?" በሚል ርዕስ ባሰፈሩት የሙግት ጽሑፍ በሃገሪቱ የተጋረጡ እንደ ጦርነት፣ መፈናቀል፣ የኑሮ ውድነት እና ስራ አጥነት ያሉ ከበድ ያሉ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት የከተማዋ የባለቤትነት ጥያቄ አወዛጋቢ የፖለቲካ አጀንዳ መሆኑን ተችተዋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የአዲስ አበባን ሕጋዊ ስልጣን፣ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላትን ግንኙነት፣ ወሰን፣ ቋንቋ እና የፖሊስ ስልጣንን ጨምሮ በርካታ ህገ-መንግስታዊ ነጥቦችን መወያያ ማድረጉን ያነሱት አቶ ክቡር የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ የሁሉም ብሔረሰቦች የጋራ ጥረትና ድካም ውጤት እንጂ የአንድ ወገን የፖለቲካ ድል ወይም ሽልማት ሊደረግ እንደማይገባው አሳስበዋል። እንደ አቶ ክቡር ገና ገለፃ ኦሮሚያ ከከተማዋ ጋር የሚያያዝ ህጋዊ የታሪክ፣ የጂኦግራፊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄ ቢኖረውም፣ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ለነጠላ የፖለቲካ አካል አሳልፎ መስጠት የፌደራሊዝም ስርዓቱን ወደ ንብረት ክፍፍል ቀውስ ይከተዋል ይህም ሌሎች ክልሎች ተመሳሳይ ጥያቄ እንዲያነሱ በር ይከፍታል። አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መኖሪያ፣ ለኦሮሚያ ልዩ ግንኙነት ያላት፣ ለፌደራል መንግስቱ መቀመጫ እና የዜጎች መብት የተከበረባት ከተማ ሆና ካልቀረበች በስተቀር የባለቤትነት ሙግቱ ሌላ የብሶት እና የቅሬታ ምንጭ ከመሆን ያለፈ መፍትሔ እንደማያመጣ አስረድተዋል። @berbirmereja @berbirmereja

  • 11:244171

    видео или голосовое, без подписи

  • 11:244171

    видео или голосовое, без подписи

  • 11:2439911

    11 ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ተገጩ‼ 📌 3 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ‼ ​በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ አከባቢ ነሐሴ 9 ቀን ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ገደማ በደረሰ ከባድ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ4 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። ​አደጋው ከሐዋሳ ወደ ዓለታ ወንዶ በሚጓዝ የዶልፊን ተሽከርካሪ እና በተቃራኒ አቅጣጫ በሚጓዝ የኤፍኤስአር መኪና መካከል በተፈጠረ መጋጨት የተነሳ መንገድ ዘግተው በቆሙ ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ አንድ የሲኖትራክ መኪና ተደርቦ በመጋጨቱ የተከሰተ ነው።​በአጠቃላይ በ11 ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ደርሷል። @berbirmereja @berbirmereja

  • 19:536808

    ለሠላም ተስፋ ሰጭ መረጃ‼️ የፌዴራል መንግስት እና ህወሓት በናይሮቢ ሊወያዩ ነው ተባለ‼️ የፌዴራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች በሚቀጥለው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ ለዳግም ውይይት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል። 📌 በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ትግራይ አነፃራዊ ሰላም ሰፍኖ የቆየ ቢሆንም፣ በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ስምምነቱን በመጣስ ዳግም የጦርነት እንቅስቃሴ በመጀመሩ እና የትግራይ ህዝብ "ጦርነት ይበቃናል" ጥሪ በማቅረቡ ነው። 📌 ሂደቱን ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ዊሊያም ሩቶ፣ እና ኡሁሩ ኬንያታ ይመሩታል ተብሏል። 📌ከሰሞኑ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ "ከሕወሓት ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊደረግ አይገባም" በማለት መግለፃቸው የድርድር መንገድ መጀመሩን ጠቋሚ ነው በሚል ብዙዎች ሲገልፁ ነበር። 👉በየትኛውም መንገድ ይሁን ብቻ ጦርነትን የሚያስቀር ነገር ይፍጠርልን‼️ሠላም ለሀገራችን ሠላም ለህዝባችን‼️ @berbirmereja @berbirmereja

  • 18:287148

    🚨 ወታደራዊ ውጥረት፡ አሜሪካ አዲስ የጦር መርከብ ላከች፤ ኢራን ለከፋ ውጊያ እየተዘጋጀች መሆኑ ተሰማ! 🇺🇸🇮🇷 አሜሪካ በኢራን የወደብ መስመሮች ላይ የጣለችውን የባህር ከበባ አጠናክራ ለመቀጠል እና ለረጅም ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ የቆየውን «ዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን» የተሰኘውን የጦር መርከብ ለመተካት «ዩኤስኤስ ጆርጅ ዋሽንግተንን» ወደ ቀጣናው መላኳን ተከትሎ በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል ያለው ግጭት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር እንደሚችል ተገልጿል። ይህንን የኃይል ማሳያ ተከትሎ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚፈጠር አዲስ ወታደራዊ ግጭት ራሷን እያዘጋጀች ሲሆን፡ በተለይም የሮኬት እና የሚሳኤል አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ እና የሮኬት ማስወንጨፊያዎቿን በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ለመበተን በትኩረት እየሰራች ይገኛል። ከዚህ ቀደም በአሜሪካ እና በእስራኤል ከተፈጸሙባት ጥቃቶች በኋላ ኢራን የሚሳኤል ክማችቷን በከፍተኛ ደረጃ እንደገና የገነባች ሲሆን፡ የባሊስቲክ ሚሳኤል አቅሟንም ዋነኛ የመከላከያ ዋስትናዋ አድርጋ ትመለከተዋለች። የጦር መሣሪያዎቿን በሰፊው መበተኗም አሜሪካ በሚሳኤሎቿ ላይ ጥቃት ብትሰነዝር እንኳ የመልስ ምት የመስጠት አቅሟን ሙሉ በሙሉ እንዳታጣ ለማድረግ ይረዳታል ነው የተባለው። ዋሽንግተን የጦር መርከብ ለውጡ መደበኛ የታቀደ ስራ እንደሆነ ብትገልጽም፡ የፔንታጎን ባለስልጣናት ግን በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ከበባ ላለማቋረጥ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። @berbirmereja @berbirmereja

  • видео или голосовое, без подписи

  • 17:207044

    ምፅዋ በካርጎ አውሮፕላኖች ተጨናንቋል‼️ ሱዳን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ እያራገፈች ነው‼️ ጀነራል አል_ቡርሃን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ አውሮፕላን ማረፊያ በብዛት  እያራገፈ እንሚገኝ በሳተላይት ምስል ተረጋግጧል ። ከሱዳን ተነስተው በምፅዋዋ አውሮፕላን ማረፊያ ያረፉ በርካታ የጭነት አውሮፕላኖች ከባባድ መሳሪያዎችን፣ ተወንጫፊ ሚሳይሎችንና ጥይት እያራገፉ መሆናቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል። ከሱዳን በተጨማሪ ከቤላሩስ እንዲሁም ከኢራን የመጡ የጭነት አውሮፕላኖች ከሁለት ቀን በፊት ምፅዋ እንዳረፉ ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል። @berbirmereja @berbirmereja

  • ሆቴሎች የሀገሪቱን ባህልና ተፈጥሯዊ መስህቦች በሚመጥን መልኩ ሊገነቡ እንደሚገባ ተገለጸ በኢትዮጵያ የሚገነቡ ሆቴሎችና የቱሪዝም ማረፊያዎች የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ተፈጥሯዊ ገጽታ ባንፀባረቀ መልኩ ለጎብኚዎች ሳቢ ሆነው ሊገነቡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታወቀ፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትና የበርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያሳየች ነው ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የአለም አቀፍ የቱሪስት አስጎብኚዎች ፌደሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ አቶ ዮናስ ትኩ፤ ይህንን እድገት ታሳቢ ያደረጉ የሆቴል አዳራሾች በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዘው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ እንደ አክሱምና ላሊበላ ያሉ ታሪካዊ ቅርሶችን መነሻ ያደረጉ ግንባታዎች እንደነበሩ በማንሳት፤ አሁንም የሚገነቡ አዳዲስ ሆቴሎች በውጫዊ ቅርጻቸውና በውስጣዊ የማስዋብ ስራቸው የሀገሪቱን ባህል የሚያንጸባርቁ መሆን እንዳለባቸው አቶ ዮናስ ገልጸዋል፡፡ በሆቴሎች ውስጥ በሙያው ያልሰለጠኑ ሰራተኞች በከፍተኛ ቁጥር እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን አቶ ዮናስ ገልጸው፤ ይህም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጉድለት የሚያስከትል በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባና አገልግሎቱን ወደ አለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ሆቴሎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በመቅጠር በብቃት ሊመሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሆቴሎች የሰለጠነ የሰው ኃይል በመመደብ አገልግሎታቸውን ማዘመናቸው፣ የሀገር ገጽታ ግንባታን በማጠናከር እንግዶችን ለማስተናገድና የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ @berbirmereja @berbirmereja

  • ታሪካዊ የምስራች ለስፖርት ቤተሰቡ! ****** የዓለማችን ቁጥር አንድ ሊግ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ — አሁን በነፃ ወደ ቤትዎ ሊመጣ ነው! በኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ታሪክ ግዙፍ የስፖርት ሁነቶችን ለህዝብ በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆነው ሀገሬ ቴሌቪዥን፣ የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነፃ አየር ስርጭት (FTA) ብቸኛ ባለመብት በመሆን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል! ሀገሬ ቴቪ በቀጣዮቹ ሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ያለምንም ክፍያ የሚከተሉትን ድንቅ ዝግጅቶች በነፃ ወደ ቤትዎ ያደርሳል፦ 👉በሳምንት አንድ ጨዋታ፦ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ላይ የሚደረጉ የተመረጡ አጓጊ የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያዎች። 👉የሰኞ ምሽት ማጠቃለያ (Highlights)፦ የሳምንቱን ሙሉ ጨዋታዎች ግቦችና ምርጥ እንቅስቃሴዎች። 👉የረቡዕ ምሽት ዘጋቢ ፊልም (Documentary)፦ በፕሪሚየር ሊጉ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሳቢና ማረኪ ታሪኮች። 👉የአርብ ምሽት ቅድመ-ጨዋታ (Preview)፦ ሳምንታዊ የጨዋታዎች ትንተና እና ዝግጅት። ሀገሬ ቴቪ ይሄን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስርጭቱን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ተመልካቾች ያለምንም ክፍያ በቤታቸዉ በነፃ ያደርሳል። @berbirmereja @berbirmereja

  • "ባንዳ ለሆዱ ሲሞት እኛ ለሀገር ሉዓላዊነት እንሞታለን!"ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው አስተላላፊ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፦ ዋና ዋና ነጥቦች፦ የውጊያ ማርሽ ቀያሪው ሀይል - የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ለሀገር አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ሰጪ እና የጠላቶችን ስጋት አስቀድሞ የሚቀልብስ የመከላከያ ዋና ስትራቴጂካዊ መቺ ሀይል ነው! ህወሃትና ሻዕቢያ ጨምሮ በባዕዳን ስትራቴጂ ስር ተሰልፈው ኢትዮጵያን ለማዳከም የጠነሰሱት ደባ በሠራዊታችን ፅናት አየር ላይ ቀርቷል። ህወሃትና ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ሀገራችን የባህር በር እንድታጣ የሰሩ የክህደት ሃይሎች ናቸው። ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ እየተጠበቀች በጀመረችው የብልፅግና እና የእድገት ጉዞ ወደፊት ትቀጥላለች! ልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ለሀገር ውስጥ ሰላም ማፅናትና ለማንኛውም ጥቃት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ይገኛል። @berbirmereja @berbirmereja

  • ባህርዳር ስታዲየም‼️ ባሕርዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት። የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት። የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)  መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል። ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል። @berbirmereja @berbirmereja

  • ትራምፕ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን "የአሜሪካ ግዛት" ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ ​የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር እየተካሄደ ያለው ግጭት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት አድርገው ለማወጅ ማቀዳቸውን ገለጹ።  ​ትራምፕ በኒው ዮርክ ባደረጉት ንግግር፣ የአሜሪካ ባህር ኃይል በአካባቢው ላይ ሙሉ ቁጥጥር ማድረጉን ገልጸው፣ የባህር ሰርጡን በቅርቡ የአሜሪካ ግዛት እንደሚያደርጉት ተናግረዋል። በተጨማሪም አሜሪካውያን የነዳጅ ዋጋ በመጠኑ ቢጨምርም የኢራንን የኑክሌር ስጋት ለመግታት የሚከፈል አስፈላጊ ዋጋ እንደሆነ እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል። ​በሌላ በኩል የኢራን ባለስልጣናት ለትራምፕ ንግግር ፈጣን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የሆርሙዝ ሰርጥ በማህበራዊ ሚዲያ መልእክትም ሆነ በወታደራዊ ዛቻ ሊወሰድ እንደማይችልና ሁልጊዜም የኢራን አካል ሆኖ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። @berbirmereja @berbirmereja

  • በቅናት ስሜት የባሏን የቀድሞ ሚስት የ5 ዓመት ህፃን በመርዝ የገደለችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች አዳማ ከተማ መስተዳድር ቦኩ ሸነን ክፍለ አዋሽ መልካሳ ወረዳ አዋሽ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ሙሉ ሸዋ የተባለች ግለሰብ በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኝና በመምህርነት፣ ተቀጥራ ስትሰራ ነበር። የአዳማ ከተማ መስተዳድር ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ታምራት ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በምትሰራበት ትምህርት ቤት ከአንድ መምህር ትዳር መስርታ እንደነበረ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ የመምህርት ሙሉ ሸዋ ትዳር ልጅ መውለድ ሳይችሉ ከሁለት ዓመት በኋላ በባል ላይ ባደረበት የቅናት ስሜት  ምክንያት ፍቺ ፈጽሟል ።  በዚህም ትዳራቸው በፍቺ በ ከተጠናቀቀ በኋላ መምህርት ሙሉ ሸዋ  ወዲያው አዲስ የትዳር ሕይወት ውስጥ ትገባለች። በትዳሯ  የወንድ ልጅ እናት መሆን የቻለች ሲሆን በፍቺ ትዳሩን ያፈረሰው መምህር ደግሞ እዚያው ትምህርት ቤት ከአንዲት በረዳት መምህርትነት እና በተማሪዎች ምገባ የምታገለግል ጋዲሴ አመንቴ  ከተባለች ሴት ጋር  ትዳር ይመሰርታል። ይሁን እና በህጋዊ መንገድ የተፉታት መምህር እና የቀድሞ የትዳር አጋርዋ የቀድሞ የፍቅር ግንኙነታችን መቀጠል አለበት በማለት የማስፈራራት የመሳደብና የትንኮሳ ተግባር መፈፀም የእለት ተእለት ተግባሩ እንደሆነ ይናገራሉ ። መምህርት  ሙሉ ሸዋ ለባለቤቱ ለጋዲሴ ባለቤትሽ አንቺን አግብቶ እኔም የሚመስለኝን አግብቼ ልጅ ወልጄ እየኖርኩ ነው የኔ እና የእሱ ነገር ደግም በሠላም ፍቺው ተጠናቅዋል። ታዲያ ስወጣ ስገባ የሚያስቸግረኝ በማለት ድርጊቱን እንድታስቆምላት ትለምናለች። ጋዲሴ የተባለውን ሰምታ ባለቤቷን ስሞታ የቀረበበት ድርጊት እንደሚፈፅም ስትጠይቀው እሱ ደግሞ በተቃራኒው፣ እኔ እሷን  የሠደብኳት አንቺን ስታንቋሽሽ፣ ስትሠድብሽ፣ እንጂ ምን ያገናኘናል በማለት  በመካከላቸው የግጭት በር መክፈቱን ነው  ምክትል ኮማንደር ታምራት ጌታሁን የተናገሩት። ጋዲሴ በባለቤትዋ የተነገራትን የፈጠራ ታሪክ ሰምታ በከፍተኛ የበቀልተኝነት ስሜት ውስጥ ትገባለች።በዚህ ስሜት ውስጥ ባለችበት  ለመበቀል በማሰብ በዛው ትምህርት ቤት የሚማረው ልጇን ሚያዝያ 9 ቀን 2018ዓም  ለመምህርቷ ልጅ ኬና በመርዝ የተበከለ ሙዝ መመገቧ ተገልጿል። በዚህም የታዳጊው ህይወት በህክምና እርዳታ ቢታገዝም ማትረፍ ሳይቻል ይቀራል። የድርጊቱ መፈፀም ተመልክቶ ፖሊስ በወቅቱ የተለያዩ ማስረጃዎች አጠናክሮ ድርጊቱን ያጣራና ለአቃቢ ህግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ በከፍተኛ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል።  ክሱን የተመለከተው የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ጋዲሴ አመንቴ የተባለችው ተከሳሽ ምንም በማያቅና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለው ህፃን ልጅ በተመረዘ ምግብ ለሞት ማብቃት እጅግ ነውረኛ ጨካኝ እና ከባድ ቢያደርገውም ቀደም ሲል በነበራት ሕይወቷ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ባለመፈጸሟ  በድርጊቷ ክፉኛ መፀፀቷ እንደማቅለያ ተወስዷላት በ19 አመት እስራት እንድትቀጣ የተወሰነባት መሆኑን ምክትል ኮማንደር  ታምራት ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። @berbirmereja @berbirmereja

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ኤርዶጋን እስራኤል ፍልስጤምን ከአለም አቀፍ ትኩረት ለማስወገድ እየሰራች ነው አሉ። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን እንደተናገሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መንግስት ፍልስጤምን ከአለም አቀፍ አጀንዳ ለማስወገድ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል። ኤርዶጋን በአንካራ ከፍልስጤሙ አቻቸው ማህሙድ አባስ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኔታንያሁ መንግስት አላማ በአካባቢው የሚፈጠሩ ሁከት እና አዳዲስ ግጭቶችን በመጠቀም ፍልስጤምን የሰው ልጅ የጋራ አጀንዳ እንዳትሆን ማድረግ ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም፥ ምንም ያህል ቢጥሩም አይሳካላቸውም፤ ጥፋቷን በተመኙ ቁጥር የፍልስጤም ጉዳይ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ እያደገ ይሄዳል ሲሉ ተናግረዋል። ቱርክም ለፍልስጤም ሀገርነት ምስረታ ትግሏን እንደምትቀጥል ቃል ገብተዋል። የፍልስጤም ጉዳይ ጠበቃ በመሆን የሚታወቁት ኤርዶጋን፣ የኔታንያሁን መንግስት በተደጋጋሚ የተቹ ሲሆን፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል።በዌስት ባንክ፣ በሊባኖስ እና በሶሪያ ከተደረጉት ድርጊቶች ባሻገር የወረራና የማስፋፋት ፖሊሲዎችን እየተከተሉ ይገኛሉ ሲሉ ከሰዋቸዋል። አባስ ከዲፕሎማሲያዊ አማካሪያቸው ማጅዲ ኻሊዲ፣ ከደህንነት አዛዡ ማጄድ ፋራጅ እና ከከፍተኛው የፍልስጤም ባለስልጣን ዚያድ አቡ አምር ጋር በመሆን አንካራ ገብተዋል። የፍልስጤሙ መሪ አስፈላጊ እና አዎንታዊ ብለው በገለፁት የረቡዕ ዕለት ውይይታቸው፣ ከአንካራው ኤርዶጋን ጋር በመሆን በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። @berbirmereja @berbirmereja

  • видео или голосовое, без подписи

  • ፍጥጫ ውስጥ ገቡ‼️ አሜሪካ እና ቻይና በቢሾፍቱው ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ‼️ ​የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገነባው የ12.5 ቢሊዮን ዶላሩ የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በሁለቱ ሀያላን ሀገራት መካከል የጂኦፖለቲካዊ ፉክክር ማዕከል ሆኗል። ​ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት እንደዘገበው፤ የመንግስት ባለቤትነት ያላቸው የቻይና ኩባንያዎች የጨረታ ሂደቱን እየመሩ ቢሆንም፣ ዋሽንግተን እንደ ቦይንግ እና ጄነራል ኤሌክትሪክ (GE) ያሉ ግዙፍ የአሜሪካ ኩባንያዎች ኮንትራቱን እንዲያገኙ ከፍተኛ ግፊት እያደረገች ትገኛለች። ​ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋና የንግድ እና የጉዞ ማዕከል ያደርጋታል ተብሎ ይጠበቃል። @berbirmereja @berbirmereja

Berbir Mereja / በርብር መረጃ — tgindex