tgindex
ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

ኢትዮ የህግ አገልግሎት/Ethio Legal Service

Статистика

ጠቃሚ እና አዳዲስ ህጎችን እዚህ በነፃ ያግኙ

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 425
+36 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
572
24 постов
Вовлечённость
40,1%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
189
1/48двое суток
216
1/72трое суток
233

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 👆👆👆 አዲሱ የመንግስ ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 የተደነገጉ ወሳኝ ሕጎች #​በአዲሱ_የፌዴራል_ሲቪል_ሠራተኞች_አዋጅ_ቁጥር1353/2017 አንቀጽ 11 መሠረት የሠራተኞችን ደመወዝ እና ተያያዥ መብቶች አስመልክቶ የሚከተሉት ወሳኝ ሕጋዊ ድንጋጌዎች ተቀምጥዋል፦ ​📌 1. የደመወዝ ክፍያ ጊዜ ሰሌዳ (አንቀጽ 11/1/) ​ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በየወሩ መጨረሻ (ቀነ 30) ለሠራተኞች ደመወዝ የመክፈል ግዴታ አለበት። ​የወር ደመወዝ እንደ መደበኛ የሠራተኛ ጥቅም በመሥሪያ ቤቱ በዘፈቀደ ሊዘገይ ፈጽሞ አይችልም። ​📌 2. የደመወዝ መቆረጥ ወይም መያዝ ገደብ (አንቀጽ 11/2/) ሠራተኛው በሕግ የተፈቀደ መሠረት ሳይኖር በዘፈቀደ ደመወዙ ሊቆረጥ አይችልም! ደመወዝ ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ የሚችለው፦ 📌​ሠራተኛው በፈቃዱ በጽሑፍ ሲስማማ፣ 📌​በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሰጥ፣ ወይም 📌​በሌላ ሕግ የተደነገገ መሠረት ሲኖር ብቻ ነው። ​📌 3. የመቆረጫ መጠን ገደብ (አንቀጽ 11/3/) 👉​በየትኛውም ምክንያት ቢሆን በየወሩ ከሠራተኛው ደመወዝ ሊደረግ የሚችለው የቅነሳ መጠን ከደመወዙ አንድ ሦስተኛ (1/3) መብለጥ የለበትም። 👇👇👇 https://www.facebook.com/100065172933419/posts/1429891099193308/?app=fbl

  • без подписи

  • አባትነትን ማረጋገጥ vs የመካድ ክስ! **** አባትነትን ማረጋገጥ vs የመካድ ክስ ሠ/መ/ቁ 215765 /የላልታተመ/ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አባትነት በፍርድ ሊነገር የሚችልበትን ዝርዝር ድንጋጌዎች የያዘ ሲሆን በቅድሚያ አባትነት ከህግ ግምት የሚመነጭ በህግ ግምት የሚረጋገጥ ነው፡፡ በዚህ አኳኋን በጋብቻ ጊዜ ወይም ጋብቻ ሳይፈፅሙ እንደባልና ሚስት አብረው በሚኖሩ ጊዜ መወለድን በማሳየት በህጉ ግምት የሚረጋገጥ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ከዚህ በቀር የጋብቻ ግንኙነት ወይም በህግ የታወቀ ግንኙነት ሳይኖር የተወለደን ልጅ አንድ ሰው አባት ነኝ በሚል በፅሑፍ ያወቀ እንደሆነ በዚሁ ሥርዓት አባትነትን ማረጋገጥ የሚቻል ስለመሆኑ በህጉ የተመለከተ ሲሆን ከላይ በተቀመጡት ሁኔታዎች በማይሸፈኑ በአዋጁ አንቀፅ 143 የተዘረዘሩት  ምክንያቶች  ባጋጠሙ  ጊዜ  እንደ  ሶስተኛ  የአባትነት  ማረጋገጫ  መንገድ  አባትነት  በፍርድ የሚነገርበት አግባብ ተደንግጓል፡፡  የመካድ ክስን በተመለከተም የቤተሰብ ህጉ በህግ እውቅና የተሰጣቸው ግንኙነቶች (ጋብቻ እና ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖር) ለመጠበቅና በዚህ ግንኙነት ጊዜ የተወለዱ ህፃናት ያለአባት እንዳይቀሩ በማሰብ በግንኙነቱ ጊዜ የተወለደው ህፃን አባት የሚባለው ከእናቱ ጋር በግንኙነቱ አብሮ ያለው/የነበረው ሰው ስለመሆኑ የህግ ግምት ይወስዳል፡፡ ይህም ቢሆን ግምቱ ቀሪ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ህጉ አስቀምጧል፡፡ ይህ  መንገድ  ልጅን  መካድ  (disowning)  ይባላል፡፡  (የተሸሻለው  የቤተሰብ  ህግ  ከአንቀጽ  167 –  179 ይመለከቷል)፡፡ ከህጉ መገንዘብ እንደሚቻለው የመካድ ክስ ተጠቅሞ የአባትነት ሸክምን በፍርድ ማስወገድ የሚችለው በህግ ግምት አባት ነህ የሚባል ሰው (ወይም ወራሾች) ነው፡፡

  • አዳዲስ የጊዜ ገደቦች አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ዐዋጅ ቁጥር 1410/2018 ከሚደነቅባቸው አንዱ ነገር ብዙ አዳዲስ የወንጀል ፍትሕ ሂደት የጊዜ ገደቦችን መደንገጉ ነው:: ከእነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹን እንጠቃቅሳለን::👴🏽 1. የተጨማሪ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በአንድ ጊዜ እስከ 14 ቀን ሊፈቀድ የሚቻል ሲሆን አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ግን #በማናቸውም ምክንያት ከ4 (አራት) ወር ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ትደንግጓል::  አንቀጽ 119(2) ይሁንና ወንጀሎች ቀላል፣ መካከለኛ እና ከባድ ተብለው የተከፋፈሉ እንደመሆኑ አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮም በዚህ አግባብ ቢከፋፈል ጥሩ ነበር::👴🏽 2. የወንጀል ምርመራው ተጠናቆ በዐቃቤ ሕግ ክስ እስኪመሠርት ያለው የመሸጋገሪያ ጊዜ ቀጠሮ በመደበኛነት እስከ 20 ቀን ሆኖ በአጠቃላይ ግን ከ 34 ቀን ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 119(4)፣ 197(1)፣ 198(2) * የጊዜ ገደቡ የሚሠራው ተጠርጣሪው ተይዞ ያለ ከሆነ ብቻ ነው:: 3. ፍርድ ቤት በዐቃቤ ሕግ የተመሠረተን መደበኛ ክስ አይቶ ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: አንቀጽ 232 (1), (2):: በዚህ መሠረት:- *ቀላል ክሶች=3 ወር (+45 ቀን) ማለትም በአጠቃላይ በ4 ወር ከ15 ቀን ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው:: *መካከለኛ ክሶች =6 ወር (+3ወር) ማለትም በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው:: *ከባድ ክሶች=12 ወር (+6ወር) ማለትም በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ከ6 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው:: ~ያልገባኝ በእነዚህ የጊዜ ገደቦች ውስጥ ውሳኔ ካልተሰጠ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው ነው—ዳኛው መዝገቡን ባለበት ይዘጋል ቢባል ጥሩ ነበር::🙄 4. በዋስትና በመስጠት፣ በመከልከል ወይም በተፈቀደ የዋስትና ዓይነት ወይም መጠን ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ብይኑ በተሰጠ በ20 ቀን ውስጥ ነው:: *ይህ እንኳን ከጊዜ ገደብ አኳያ አዲስ አይደለም—ከነባሩ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 75(1) ጋር ተመሳሳይ ነው:: ይሁንና የዋስትና ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በይግባኙ ላይ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ተደንግጓል:: አንቀጽ 152(1), 153 *ይሁንና በተለይ በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 66 ሥር ማናቸውም ፍ/ቤት የዋስትና ጉዳይ ሲመጣለት በ48 ሰዓት ውስጥ መወሰን አለበት ከሚለው አኳያ ሲታይ አዲሱ ሕግ ያዘገየዋል:: 5. ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: ይህም ፍ/ቤት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ ከሰጠ በኋላ ግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየታቸውን አጠቃለው ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ፍ/ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ አለበት ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 301(1) 6. በዋናው የወንጀል ጉዳይ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት ጊዜ ፍርዱ፣ ውሳኔው፣ ብይኑ ወይም ትእዛዙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተደንግጎአል:: አንቀጽ 332(4) *ይህም በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 187 (1)፣ (2) መሠረት ይግባኝ ለማለት የሚፈልግ አካል ለይግባኝ የመዝገብ ግልባጭ እንዲሰጠው ውሳኔው በተሰጠ 15 ቀን ውስጥ ለወሰነው ፍ/ቤት ማመልከቻ የማቅረብ እና እና የውሳኔ ግልባጩ በደረሰው 30 ቀን ውስጥ ይግባኝ  የማከፈት በድምሩ የ45 ቀን አሳሳች አሠራርን ቀሪ የሚያደርግ ነው:: ስለሆነም የወንጀልና የፍ/ብሔር ይግባኝ አቀራረብ የጊዜ ገደብ ተመሳሳይ ሆነ ማለት ነው:: 7. የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ 90 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተደንግጎአል:: አንቀጽ 344(3)   *ያው በቀድሞው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ኮድ ውስጥ ባለመጠቀሱ ምክንያት ለፎርማሊቲ ያህል አዲስ ነው ብለን ጠቀስነው እንጂ በተግባር አዲስ አይደለም:: 8. የፍ/ቤት መጥሪያ ከቀነ ቀጠሮ 10 ቀን በፊት እንዲደርስ ተደንግጓል:: ማለትም የዐ/ሕግ ክስ ማመልከቻ ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ክስ ለማንበብ ከያዘው ቀን አሥር (10) ቀን ቀደም ብሎ ለተከሳሽ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 214(3) እንዲሁም የተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ፍ/ቤቱ የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ከቀጠረበት ቀን አስቀድሞ ከ10 ቀናት በፊት ለዐ/ሕግ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 288(2) 9.  የግል አቤቱታ (private prosecution) እንዲያቀርብ በዐ/ሕግ የተፈቀደለት ሰው ፈቃዱን ባገኘ 15 የሥራ ቀን ውስጥ ክሱን አዘጋጅቶ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ አለበት። በመሆኑም ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክስ ማቅረብ አይችልም:: አንቀጽ 200(3) 10. የግል የወንጀል ምርመራ አቤቱታ (complaint) የሚያቀርብ ሰው አቤቱታውን ባቀረበ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ለመርማሪ ፖሊስ ካላስረዳ የግል አቤቱታው ይሠረዛል:: አቤቱታው ከተሠረዘ በኋላ በጉዳዩ ላይ ድጋሚ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 64(4) 11. በልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በመደበኛነት ከሦስት ወር አይበልጥም:: ይሁንና በዚህ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በማንኛውም ምክንያት ከ12 ወራት ሊበልጥ አይችልም:: አንቀጽ 105 (1)፣ (2)፣ (3) 12. የጥፋተኛነት ድርፍር (Plea bargaing) ማድረጊያ ጊዜም ተገድቧል:: ማለትም ዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጣመ በስተቀር ዐ/ሕግና ተከሳሹ (ጠበቃው) የጥፋተኛነት ድርድር ለማካሄድ ከተስማሙበት ቀን ጀምሮ 45 (አርባ አምስት) ቀናት ውስጥ ድርድሩ መጠናቀቅ አለበት፡፡ አንቀጽ 175(4) *"ከዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ድርድሩ እስከመቼ እንደሚራዘም ቁርጥ ገደብ ቢቀመጥ ሸጋ ነበረ:: 13. ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ የሚቀርብ አቤቱታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት:: አንቀጽ 221 *ይህ ጊዜ ከቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 198 ጋር ተመሳሳይ ነው:: ይሁንና በቀድሞው ኮድ የአንድ ወሩ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ተከሳሹ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንደተሰጠበት ካወቀበት ቀን አንሥቶ ሲሆን በአዲሱ ኮድ ግን በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንዲሰጥበት ያደረገው ምክንያት ከቀረበት ወይም ከተወገደበት ቀን ጀምሮ ነው:: *በነገራችን ላይ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት በመታየት ሂደት ላይ ያለ (ፍርድ ያላገኘ) ከሆነ ተከሳሹ በማንኛውም ጊዜ ክርክሩን መቀላቀል ይችላል:: ማለትም ፍ/ቤቱ በሌለህበት ጉዳዩን ለማየት ብይን (Ex parte ruling) ስለሰጠሁ ወደ ክርክሩ መግባት አትችልም ሊለው አይችልም:: አንቀጽ 218(4) * አደራ! ተከሳሽ በሌለበት (trial in absentia) የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 218-222] እና ተከሳሽ ባለበት (trial in praesentia) ታይቶ የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 353-357] የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸውና አይቀላቀል:: በዚህ መሠረት ተከሳሽ ባለበት ታይቶ የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ (review of judgement) ለመጠየቅ የሚቀርብ አቤቱታ የመጨረሻው ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል:: አንቀጽ 355(1) ምንጭ፣ Lawyer Hailu Hasena

  • በፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ  77 እስከ 80 መሠረት የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የባለትዳሮቹን ስምምነት፣ የልጆችን ጥቅም እና የንብረት ክፍፍልን በመመርመር የፍቺ ውሳኔ ይሰጣል። 1. የስምምነት ፍቺ ምንድን ነው? የስምምነት ፍቺ ማለት ባልና ሚስት በራሳቸው ፈቃድ ጋብቻቸውን ለማፍረስ ተስማምተው ለፍርድ ቤት በጋራ ማመልከታቸው ነው። የዚህ ዓይነቱ ፍቺ  ማን ጥፋተኛ እንደሆነ አይከራከሩም።የትዳሩ መቀጠል እንደማይቻል ይስማማሉ።በንብረት፣ በልጆች ጥበቃና ቀለብ ላይ ስምምነት ያቀርባሉ። 2. ለበስምምነት ፍቺ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች ሀ. የሁለቱም ነጻ ፈቃድ ስምምነቱ ያለ ማስገደድ፣ ያለ ዛቻ እና ያለ ማታለል መሆን አለበት። ለ. የጽሑፍ ስምምነት ሐ. ስምምነቱ ሕጋዊ መሆን ስምምነቱ ሕግን የማይጥስ፣የሕፃናትን ጥቅም የማይጎዳ እና የሞራል ሥርዓትን የማይቃረን መሆን አለበት። 3. የስምምነቱ ይዘት በአብዛኛው የስምምነት ሰነዱ የሚካተቱት፦ ሀ. ጋብቻው እንዲፈርስ የሁለቱም ፈቃድ ለ. የጋራ ንብረት ክፍፍል ሐ. ዕዳ ካለ አከፋፈሉ መ. የልጆች ጥበቃ (Custody) እና የልጆች ቀለብ ሠ. የልጆች ጉብኝት (Visitation) ረ. ሌሎች የገንዘብ ወይም የቤተሰብ ጉዳዮች 5. ፍርድ ቤቱ ስምምነቱን ሊቀበል የማይችልባቸው ሁኔታዎች ሀ. ስምምነቱ በማስገደድ ከተፈጸመ። ለ. የሕፃናትን መብት ከጎዳ። ሐ. ሕግን ከተቃረነ። መ. አንዱ ባለትዳር በትክክል ካልተረዳው። 6. የፍቺ ውጤቶች ፍቺው ከጸደቀ በኋላ፦ ሀ. ጋብቻው ይፈርሳል። ለ. የጋራ ንብረት ይከፈላል። ሐ. የልጆች ጥበቃ ይወሰናል። መ. የልጅ ቀለብ ይወሰናል። ሠ. እያንዳንዱ በሕግ መሠረት እንደገና ማግባት ይችላል።

  • የቤት ሽያጭ ውል እንዲፈፀምልኝ የሰበር ውሳኔዎች? እና ዳኝነት መጠየቂያ ፎርም 1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የማይንቀሳቀስ ንብረት (ቤት) ሽያጭ ውል በህግ የተደነገገውን የይዘት እና የቅርጽ (Form) ማዕቀፍ ካሟላ እና ወገኖች ውሉ መኖሩን ካልካዱ ውሉ እንዲፈጸም (ጸንቶ እንዲቀጥል) የሚወስን ሲሆን፣ በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ ወይም ህጋዊ መስፈርት ያልተከተለ ከሆነ ግን እንደ ረቂቅ (ህጋዊ እውቅና እንደሌለው) ይታያል። የሰበር ውሳኔዎች ዋና ዋና ሐሳቦች የውል መኖር አለመካድና መታዘዝ፡ የቤት ሽያጭ ውል መፈጸሙ በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል በፍጹም የማይካድ ከሆነ እና ውሉ ሊፈጸምበት የማይችልበት አንዳች ህጋዊ ምክንያት ከሌለ፣ በዚህ መልክ ወይም የይዞታ ማስተላለፍ ፎርም ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም በሚል ብቻ ውሉ ውድቅ ሊደረግ እንደማይገባ የሰበር አሰራሮች ያሳያሉ። የውል ማረጋገጫና ፎርም (Form): የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1723 እንደሚያዝዘው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ በውል አዋዋይ ፊት መፈጸም አለበት። ነገር ግን በሰበር ውሳኔዎች (ለምሳሌ በሰ/መ/ቁ 99124 እና መሰል መዝገቦች) እንደተገለጸው ግራ ቀኙ ወገኖች ውሉን ፈጽመው ገንዘብ ተቀባይ መهاኑና ንብረቱ መሸጡ ታውቆ ሳለ፣ የፎርም ግድፈትን ብቻ ምክንያት በማድረግ ሻጭ ውሉን ክዶ ቤቱን ለመውሰድ የሚያደርገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ተወስኗል። የቀብድ ጉዳይ እና የውል ማረረጋገጫ፡ በሰበር ጥራዞች (ቅፅ 7 የሰ/መ/ቁ 26996) እንደተተነተነው በውሉ ላይ በግልጽ የቀብድ ክፍያ መፈጸሙ ከተጠቀሰ ውሉ በህግ ፊት ለመኖሩ በቂ ማረጋገጫ ይሆናል። የቀብድ ክፍያ በግልጽ ካልተጠቀሰ እና በህጉ መንገድ ያልተመዘገበ ከሆነ ግን ህጋዊ የቤት ሽያጭ ውል አለ ለማለት አስቸጋሪ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

  • የግብር ቅሬታ ማመልከቻ ፎርም! 1. የቅሬታ አቅራቢ መረጃ ሙሉ ስም፦ __ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፦ __ አድራሻ፦ __ ስልክ ቁጥር፦ __ የንግድ ሥራ ዓይነት፦ _ የንግድ ፈቃድ ቁጥር፦ ____ 2. ቅሬታው የሚመለከተው ጉዳይ የግብር ዓይነት፦ ___ የግብር ዘመን፦ ___ የግብር ማስታወቂያ/ውሳኔ ቁጥር፦ ___ የተጠየቀው የግብር መጠን፦ ___ብር የሚከራከሩበት መጠን፦ _ ብር 3. የቅሬታው ዝርዝር የቅሬታው ምክንያት፣ የተፈጠረው ሁኔታ፣ የግብር ባለሥልጣኑ የወሰነው ውሳኔ እና ቅሬታ እንዲቀርብ ያደረገው ምክንያት በዝርዝር ይጻፍ፦ 1. 2. 3. 4. 5. 6. 4. የቅሬታ አቅራቢው ጥያቄ የተጣለብኝ የግብር ግምገማ/ውሳኔ እንደገና እንዲመረመር፣ የተሳሳተው የግብር ስሌት እንዲስተካከል እና በሕግ መሠረት ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጠኝ እጠይቃለሁ። 5. የተያያዙ ሰነዶች ☐ የግብር ማስታወቂያ/ውሳኔ ቅጂ ☐ የንግድ ፈቃድ ቅጂ ☐ TIN ሰርተፊኬት ☐ የሂሳብ ሰነዶች ☐ ደረሰኞች ☐ ሌሎች፦ ___ 6. ማረጋገጫ እኔ ከላይ የገለጽኩት መረጃ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጣለሁ። የአመልካች ስም፦ __ ፊርማ፦ __ ቀን፦ ____ #የግብር ባለሥልጣን የሚሞላው ክፍል የቅሬታ መለያ ቁጥር፦ __ የተቀበለው ባለሙያ፦ ___ የተቀበለበት ቀን፦ __ የምርመራ ውጤት፦ ____ የተሰጠው ውሳኔ፦ _ የኃላፊ ስምና ፊርማ፦ ___

  • የፅሁፍ  ውል ሳይኖር ገንዘብ አበድረው ሰው አልመልስ ብሎዎታል??? የሰበር መ/ቁጥር 31737 ቅፅ 5  የብድር ውል በፅሁፍ እንኳን ባይኖር​ በስልክ ወይም በቃል በተደረገ ስምምነት ገንዘብ በባንክ ገቢ የተደረገ እንደሆነ ለማስረዳት በቂ ነው። ጠበቃ  እና የህግ አማካሪ በላይ ተፈራ 0943192020/ 0921452273 ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሰጥተናል። ውሳኔውን አስፈላጊ ከሆነ እናያይዛለን :: ብዙ ጊዜ በወዳጅነት፣ በዘመድ አዝማድ ወይም በጓደኝነት መካከል። "ውል ምን ያደርጋል? እንተማመናለን" በሚል ያለ ጽሑፍ ስምምነት ገንዘብ እናበድራለን። ነገር ግን ገንዘቡ በሚፈለግበት ጊዜ አለመመለስ ብቻ ሳይሆን "አልተበደርኩም" የሚል ክህደት ሲያጋጥም ምን ማድረግ ይቻላል? ​1. ከ500 ብር በላይ በጽሑፍ መሆን አለበት! በኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2472 መሠረት ከ 500 የኢትዮጵያ ብር በላይ የሚደረግ የብድር ውል በጽሑፍ ሊደረግ እንደሚገባ ያዝዛል። ነገር ግን የጽሑፍ ውል አለመኖሩ ብድሩ አልተሰጠም ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ፍርድ ቤት ሲቀርብ የማስረዳት ኃላፊነቱን (Burden of Proof) ያከብደዋል እንጂ! ​2. የጽሑፍ ውል ሳይኖር እንዴት ማስረዳት ይቻላል? ያለ ውል የተሰጠ ገንዘብን በተዘዋዋሪ ማስረጃዎች ማስረዳት ይቻላል፦ ​📱 የባንክ ማስተላለፊያ ደረሰኝ (Bank Transfer): ገንዘቡን በባንክ አስተላልፈው ከሆነ ትልቅ ማስረጃ ነው። በተለይ የማስተላለፊያ ምክንያት (Reason) የሚለው ቦታ ላይ "ብድር" የሚል ተጽፎ ከሆነ የበለጠ ያጠናክረዋል። ​💬 የዲጂታል መልእክቶች (SMS, Telegram, WhatsApp): ተበዳሪው ገንዘቡን ስለመቀበሉ ወይም ለመክፈል ጊዜ ሲጠይቅ የላካቸው የጽሑፍ እና የድምፅ መልእክቶች በማስረጃነት ይያዛሉ። ​👥 የሰው ምስክር እና የቃል እምነት: ገንዘቡ ሲሰጥ የነበሩ ምስክሮች ወይም ተበዳሪው በፍርድ ቤት ቀርቦ "አዎ ተበድሬአለሁ" ብሎ ማመኑ (Admission)። ​⚖️ ያለ አግባብ ማበልፀግ (Unjust Enrichment): በህጉ መሠረት አንድ ሰው ያለበቂ ህጋዊ ምክንያት የሌላውን ሰው ገንዘብ ወስዶ መበልጸግ አይችልም። ተበዳሪው ገንዘቡን በስጦታ ወይም በዕዳ ክፍያ መልክ ማግኘቱን ካላስረዳ የመመለስ ግዴታ አለበት። ​💡 ምን ማድረግ ይገባል? ​የዕዳ አምኖ መቀበያ ውል ይፃፉ፡ ወደ ህግ ከመሄዶ በፊት ከሰውየው ጋር ተነጋግረው የነበረውን ዕዳ አምኖ የሚፈርምበትን ሰነድ ማዘጋጀት። ​የይርጋ ጊዜን ያውቁ፡ ብድር ከተሰጠበት ወይም እንዲመለስ ከተጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ በጣም መዘግየት መብትዎን ሊያሳጣዎት ስለሚችል በጊዜ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ። ​👉 ባጭሩ፡ ያለ ውል ማበደር ያስቸግራል እንጂ መብትን ሙሉ በሙሉ አያሳጣም! ​(ለወዳጅ ዘመዶ እንዲደርስ #Share በማድረግ ያጋሩት! Web site 👇👇 https://www.google.com/url?sa=t&source=web&rct=j&opi=89978449&url=https://ethiolegalservice.com/&ved=2ahUKEwjj_vWZ4ZqWAxXl0AIHHXxmF7YQFnoECBAQAQ&sqi=2&usg=AOvVaw2nXlkb6eJHdGTNYRZ2TWxn

  • #አንድ ሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል ? #በ 48 ሰአት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አለው።  ፖሊስ ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ያላግባብ ቢያስረው ግለሰቡ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ #ይችላል????  ሌላው ደግሞ ፖሊስ ፍረድ ቤት በ48 ሰአት ውስጥ አቅርቦት ዋስትና ተፈቅዶለት ፖሊስ  በዋስትናው መሰረት ሳይፈታው ቢቀር ግለሰቡ ምን ማድረግ ይችላል ???? አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ  ምን ማለት ነው? *** ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እና ሁኔታዎች በወንጀል ተጠርጥረው ለእስር ሊዳረጉ ይችላሉ ። በወ/ስ/ስ/ህግ ሆነ በህገ _መንግስቱ ከተረጋገጡ መብቶች መካከል በ 48 ሰዓት ዉስጥ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት መቅረብ ይገኝበታል ። ይህ ሳይሆን ሲቀር ተጠርጣሪዉም ሆነ የእርሱ ተወካይ ያለ አግባብ መታሰራቸው ቀሪ እንዲሆን ወይም የአካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ። Habeas Corpus  የሚለው ቃል የላቲን ሲሆን " Show me the body "  የሚል ትርጓሜ አለው ። በዚህ ስርዓትም የታሠረዉን ግለሰብ ያሰረው አካል የማቅረብ ወይም  " to produce the body " ግዴታ አለበት ። የዚህ ዓይነቱ ክስ በየትኛው ፍርድ ቤት ይቀርባል ? በአዲሱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/13  አንቀጽ 5 (1) (ኘ ) መሠረት አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ይቀርባል ። በህገ _ መንግስቱ ምዕራፍ 3 ላይ የተዘረዘሩት መሠረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችን ለማስከበር ፍርድ ቤት ለመታየት ብቁ የሆኑ ጉዳዮችን ለመዳኘትም በዚሁ አዋጅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑ ተሰጥቷል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለ አቤቱታ አቀራረቡ የፍትሐብሔር ስነ _ ስርዓት ህጋችን ምን ይላል ?

  • የባል እና ሚስት ፍቺ እና የንብረት ክፍፍል የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ሊከናወን የሚችለው ጋብቻው ሲፈርስ ብቻ ነው! [የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ፣ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የመዝገብ ቁጥር 143/2017] ​የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክርክር ሊቀርብ እና በፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊሰጥበት የሚችለው በባልና ሚስት መካከል ያለው ጋብቻ ሲፈርስ ብቻ ነው። የባልና ሚስት ጋብቻ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች በባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ላይ የሚያደርጉት ክርክር እና የሚሰጡት ውሳኔ የሕገ-መንግሥቱን አንቀፅ 34 የሚጥስ ነው። ባልና ሚስት ወይም ከሁለቱ አንዱ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት መብትን ለማስከበር ከሌሎች 3ኛ ወገን ጋር የሚያደርጉትን ክርክር፣ ንብረቱ የባልና ሚስት ወይም የ3ኛ ወገን መሆን አለመሆኑን ብቻ በመወሰን ክርክሩን መቋጨት አለባቸው እንጂ አልፈው የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር በማድረግ የሚሰጡት ውሳኔ ከሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 34 ጋር የሚቃረን ነው። jura legal update እንደለጠፉት የፌደራል የቤተሰብ ህጋችንን ለማግኘት 👇👇👇 https://www.facebook.com/100065172933419/posts/1426293199553098/?app=fbl

  • ስም ለውጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ካልፀደቁ በቀር የሕግ ውጤት ከማይኖራቸው ጉዳዮች አንዱ የስም ለውጥ ነው። የግል ወይም የቤተሰብ ስም መቀየር .የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 32 እስከ 46 ሰዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች .የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የፍርድ ቤት ማመልከቻ ሂደት .የስም ለውጥ በፍርድ ቤት ከተፈቀደ በኋላ ብቻ በመንግስት መዝገቦች ይመዘገባል። ለምሳሌ: መታወቂያ : የመንጃ ፍቃድ : ፖስፖርት : የትምህርት  ማስረጃዎች ........

  • የልጅ ቀለብ ይቆረጥልኝ ዳኝነት ጥያቄ ፍርድ ቤቶች በክረምትም  ሆነ በመደበኛው የስራ ጊዜ ሳይቋረጥ የሚያስተናግዱት ዳኝነት ጥያቄ ጊዜ የማይሰጠው እና አንገብጋቢው የህፃን ልጅ ቀለብ ይቆረጥልኝ ዳኝነት ነው፡፡ የልጅ ቀለብ ይቆረይልኝ አቤቱታ እና መመሪውን ከታች ካለው የቴሌግራም ሊንክ ያገኙታል፡፡ የቀለብ አወሳሰን መመሪያ መርሆች 💥የልጅ ቀለብ በዋናነት የህፃናት ጥቅምን ቀዳሚ ማድረግ አለበት።ቀለብ ሰጪዋች ወላጆች በሚሆኑበት ጊዜ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ልጆቻቸውን የማሳደግና የመንከባከብ ሕጋዊ ሐላፊነታቸውን እንደገቢያቸው መጠን የሚጋሩት ይሆናል። 💥የልጅ ቀለብ በሚወሰንበት ሂደት ወላጆች ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም በየትኛውም ሁኔታ ግን ለልጅ ቀለብ የመስጠት ግዴታን የሚያግድ መሆን የለበትም። 💥የልጅ ቀለብ አወሳሰን የልጅን መሠረታዊ ፍላጎቶችን ልዩ ወጪዎች ታሳቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ከወላጆች አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ከሆነ ልጁ የዚህ ገቢ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል።ከዚህ በተጨማሪም ልዩ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን ሕፃናት ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታል።

  • https://www.facebook.com/reel/27671100752558879/?app=fbl በኢትዮጵያ የታክስ አይነቶችን በዝርዝር

  • https://www.facebook.com/100065172933419/posts/1423023836546701/?app=fbl

  • 1 авг.9901322

    186 ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ የፍትሀብሄር ክሶች ፡፡ በቀጣይ ለእያንዳንዱ የክስ አይነቶች ሳምፕል ክስ እናዘጋጃለን ::

  • 30 июн.1 27169

    1/ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚመጣን ሃላፊነት በመጀመሪያ ጥፋት በእስራት የሚያስቀጣውን ድንጋጌ የሰረዘው፣ 2/ ታክስ ከፋይ ተቋማት ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቅርበው መፍትሄ ማግኘት እንደሚችሉ፣ 3/ በልዩ እና አስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር አዲስ በኦዲት ወቅት ያልቀረበ ማስረጃ ለቅሬታ ሰሚ ሆነ ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ ማቅረብ የሚከለክል  እና መሰል አዳዲስ ድንጋጌዎች የተካተቱበት የታክስ አስተዳደር አዋጁ ማሻሻያ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ውብሸት ካሳሁን 👆 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን የፌደራል ታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ --------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 23 ፣ 2018 ዓ.ም፤‎ አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገው የመረጃ ጥራትን ለማሳደግና በመረጃ መሰብስብ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለማረም እንዲሁም ለስህተቱ መነሻ የሆኑ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ገልጸዋል፡፡ ታክስ ከፋይ ተቋማት የተወሰነባቸው የታክስ ክፍያ ላይ ቅሬታ ማሰማት ከፈለጉ ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቅርበው መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ አዋጁን ለማሻሻል ሌላው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። አሁን የተሸሻለው  ‎አዋጁ አስር ዓመታትን አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን የገለፀው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተሸሻለው አዋጁ የበለጠ የፌደራል ታክስ አስተዳደር ስርዓትን የበለጠ  የሚያምን ይሆናል ብለዋል፡፡ ምክርቤቱ በረቂቅ አዋጁ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

  • 6 июн.1 27869

    ባንኮች የግለሰቦችን አካውንት ለማገድ ስልጣን አላቸው ????? በቅርቡ ባንኮች የግለሰቦችን (የደንበኞቻቸውን) አካውንት እያገዱ  በግለሰቦች ላይያላግባብ  እንግልት እና ኪሳራ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ባንኮች የደንበኞቻቸውን አካውንት ለማገድ የሚያበቃ በህግ ስልጣን ተሰጥቶዋቸዋል ወይ???? የመኒ ላውንደሪ አዋጅ ቁጥር 780  በብሄራዊ ባንክ አቃጅ ቁጥር 1356/13  እና መመሪያዎች ን መሰረት በማድረግ  የግለሰቦችን አካውንት አገድን ይላሉ፡፡ በተለይ መመሪያ ቁጥር 4/2021  አጠራጣሪ  ግብይት ካለ ባንኮች የግለሰቦችን አካውንት ማገድ እንደሚችሉ ተደንግጓል፡፡  ነገር ግን ባንኮች የግለሰቦችን አካውንት ሲያግዱ ያለምንም ገደብ የተሰጣቸው ስልጣን አይደለም፡፡ አካውንት ሊታገድ የሚችለው ለተወሰኑ ቀናቶች ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 780  ከብሄራዊ ፋናንስ ኢንተለጀንስ ቢሮ አካውንት እንዲያግዱ ትእዛዝ ከመጣላቸው  ከ 3 ቀን ላልበለጠ ለማገድ ይችላሉ እንዲሁም በሌሎች  አዋጆች መመሪያዎች ቢበዛ ከ 10 ቀናት ላልበለጠ ለማገድ ከሚችሉ በቀር  ባንኮች የግለሰቦችን አካውንት ለማገድ ስልጣን የላቸውም፡፡ ግለሰቦች የባንክ አካውንታቸው ከላይ ከተገለፀው ውጭ ያላግባብ ባንኮች ያገዱ ከሆነ  በፍትህ ስርአቱ በፍርድ ቤት እግድ እንዲነሳላቸው እና አካውንቱ በመታገዱ ምክኒያት  ለደረሰ ኪሳራ  ካሳን የጠበቃ አበል ለዳኝነት የተከፈለ ክፍያን እና የተለያዩ ወጪዎችን ባንኮች እንዲሸፍኑ ግለሰቦች ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ በላይ ተፈራ 0943192020 https://www.facebook.com/100065172933419/posts/1372617664920652/?app=fbl

  • без подписи

  • በአዋጁ አንቀጽ 10 ስር የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤትነትን በተመለከተ የተጣሉ ገደቦች ተዘርዝረዋል። በአዋጁ አንቀጽ 10(1) መሠረት የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የማይችልባቸው ልዩ ቦታዎች እና የድንበር አካባቢዎች የድንበር ላይ ሕዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ከግምት በማስገባት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል። ሌላኛው ገደብ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በመንግሥት ቀጥተኛ ድጎማ ለዜጎች በሚሰሩ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የማይችል ሲሆን ነገር ግን ይህ ገደብ የፌደራል ወይም የክልል መንግሥት በግል እና መንግሥት አጋርነት ወይም በተመሳሳይ የቤቶች ልማት ማእቀፍ፣ ወይም ለትርፍ ዓላማ ገንብቶ ለሽያጭ የሚያቀርባቸውን ቤቶች አያካትትም (አንቀጽ 10(2) እና(3))። ሌላው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋም ወይም ምንጭ ገንዘብ መበደር ወይም ካፒታል ማሰባሰብ አይችልም (አንቀጽ 10/4/)። በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በማናቸውም ሁኔታ በአንድ ጊዜ የሚኖረው የመኖሪያ ቤት ቁጥር አንድ ሲሆን ሚኒስቴሩ ከአገር ጥቅም አንፃር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ይህን ቁጥር በመመሪያ ማሻሻል ይችላል (አንቀጽ 6/2/)፡፡ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ የውጭ አገር ዜጋ ግዴታዎችን በተመለከተ በአዋጁ አንቀጽ 9(1) መሠረት የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ ሕጎች በኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ የተጣሉ ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡ በተጨማሪም ባለመብት ለመሆን የሚያስፈልግ አነስተኛ የገንዘብ መጠን ማሟላት፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስፈልጉ የሊዝ፣ የቤት ግዢ፣ የግንባታ ፈቃድ ወይም የመጀመሪያው ዓመት ተያያዥ የመንግሥታዊ አገልግሎት ክፍያዎችን በኢትዮጵያ ተቀባይነት ባለው የውጭ ገንዘብ እኩል ምንዛሪ ብቻ መክፈል፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን በሊዝ መሬት የሚያገኝ ከሆነ አጠቃላይ የሊዝ ዋጋውን በአንድ ጊዜ የመክፈል ግዴታዎች አሉበት (አንቀጽ 9/2/)፡፡ ከፍ ሲል የተጠቀሱት መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ገደቦች ቢኖሩም ከመኖሪያ ቤት ባለቤትነት መብት ጋር በተያያዘ በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተለየ መብትና ግዴታን ከሚያስቀምጡ አገራት ለሚመጡ የውጭ ዜጎች በእንካ-ለ እንካ (Reciprocity) መርህ መሠረት በአዋጁ ላይ ከተመለከተው የተለየ መብት የሚሰጥ ወይም ግዴታን የሚያስቀምጥ አሠራር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ሊወሰን እንደሚችል በአንቀጽ 11 ስር ተደንግጓል፡፡ መተጨማሪም አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት በመኖሪያ ቤት ላይ የሚኖር መብት ቀሪ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እና አሠራሮች እንደአግባብነቱ በዚህ አዋጅ መሠረት የውጭ አገር ዜጋ በመኖሪያ ቤት ላይ በሚኖረው የባለቤትነት መብት ላይም ተፈፃሚ ይሆናሉ (አንቀጽ 12)፡፡ ማጠቃለያ በአጠቃላይ አዋጁ የውጭ አገር ዜጎች በሕጋዊ መንገድ የቤት ባላቤት የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ረገድ ከሚኖረው ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ባሻገር የውጭ አገር ዜጎች የቤት ባለቤት ለመሆን ሕገወጥ መንገድ እንዳይከተሉ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

  • የውጭ አገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት የሕግ ማዕቀፍ መግቢያ መጠለያ የሰው ልጆች ከሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱ ነው። በዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት የቃል ኪዳን ሰነዶች እንዲሁም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ዜጎች የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ ንብረት የማፍራት መብታቸው እውቅና ተሰጥቶታል። እንደመኖሪያ ቤት የመሳሰሉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እና ከአንዳንድ የንብረት መብት አይነቶች ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ዜጎች ከውጭ አገር ዜጎች ጋር ሲነፃፀር ላቅ ያለ መብት አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ መዋለ ነዋያቸውን፣ እውቀታቸውን እና ሙሉ ጊዜያቸውን በዚች አገር ላይ የሚያፈሱ የውጭ አገር ዜጎች የአገሪቱን ዜጎች መኖሪያ ቤት የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ እንደመኖሪያ ቤት ያሉ መሠረታዊ ፍላጎቶችን የሚያገኙበትን የሕግ ማዕቀፍ መኖር ጠቃሚ በመሆኑ በአገራችን የውጭ አገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት የሕግ ማዕቀፍ በአዋጅ ቁጥር 1388/2017 ተደንግጓል። በዚህ ጽሑፍ የውጭ አገር ዜጋ ምንነት፣ የውጭ አገር ዜጎች የቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ የውጭ አገር ዜጋ መብቶች እንዲሁም የተጣሉ ገደቦች እና ግዴታዎችን በአጭሩ እንዳስሳለን። የውጭ አገር ዜጋ ማን ነው? በአዋጅ ቁጥር 1388/2017 አንቀጽ 2(1) መሠረት የውጭ ዜጋ ማለት ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን (ትውልደ ኢትዮጵያዊ) ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ነው። ከዚሁ የአዋጁ ትርጓሜ እና የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ከወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 ድንጋጌ መረዳት እንደሚቻለው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሰዎች ምንም እንኳን የሌላ አገር ዜግነት ቢኖራቸውም እንኳን ለዚህ አዋጅ ዓላማ ሲባል እንደውጭ አገር ዜጋ የማይቆጠሩ ሲሆን በተጨማሪም የውጭ ዜጋ የሚለው ሐረግ የተፈጥሮ እና የሕግ ሰዎችን የሚያጠቃልል ነው። የውጭ አገር ዜጎች የቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች በአዋጁ አንቀፅ 7 መሠረት የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆነው የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች ሲያሟላ ነው፡- ስም፣ ዜግነት እና ሌሎች ማንነትን የሚገልፁ ሕጋዊ ሰነዶችን ማቅረብ፣ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስፈልግ አነስተኛ የገንዘብ መጠን ለማሟላት የሚያስችል በቂ አቅም ያለው መሆን፡- ከአዋጁ አንቀጽ 6(1) መረዳት እንደሚቻለው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በዚህ አዋጅ መሠረት የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሊዝ ሙሉ ዋጋውን ጨምሮ ለአንድ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሙሉ ዋጋ ወይም ለመኖሪያ ቤት ግዢ የሚመድበው አነስተኛ የገንዘብ መጠን ከ150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ) የአሜሪካን ዶላር ያነሰ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት የውጭ ባለሀብት ተብሎ የተቆጠረ ማንኛውም ሰው ከፍ ሲል የተገለፀውን አነስተኛ የገንዘብ መጠን መመደብ ሳይጠበቅበት የአንድ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚችል ሲሆን ነገር ግን ከአንድ በላይ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚችለው ከፍ ሲል የተገለፀውን የሊዙን ሙሉ ዋጋ ጨምሮ በሕጉ የተገለፀውን አነስተኛ የገንዘብ መጠን መመደብ ሲችል ብቻ እንደሆነ ከአዋጁ አንቀጽ 5(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። ሌላው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ገበያ ወቅታዊ ሁኔታን፣ የከተሞች የመኖሪያ ቤቶች አማካይ ዋጋን፣ የውጭ አገር ዜጎች በመኖሪያ ቤቶች ገበያ ያላቸውን የተሳትፎ መጠን እና የአዋጁን ዓላማ ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ምክንያቶችን እንደአስፈላጊነቱ መሠረት በማድረግ እንዲሁም የክልሎችን እና ከተሞችን የእድገት እና ልማት ደረጃ ታሳቢ በማድረግ በዝርዝር ጥናት ላይ በመመስረት የአነስተኛ ገንዘብ መጠኑን ከፍ ወይም ዝቅ የሚያደርግ፣ የእያንዳንዱን የሊዝ ቦታ ወይም ቤት ስፋት እንዲሁም የሊዝ ይዞታዎችን ወይም ቤቶችን አጠቃላይ ቁጥር የሚወስን መመሪያ ሊያወጣ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 6(3) እና (4) ተደንግጓል። የወንጀል ታሪክ የሌለው መሆን፡- በአዋጁ መሠረት የመኖሪያ ቤት ባለቤት ከመሆን የሚከለክሉ ወንጀሎች እንዲሁም ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ ከአገር ሰላም፣ ደኅንነት፣ ጸጥታ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ምንጭ ወይም ዝውውር ጋር የሚያያዙ የክልከላ ገደቦች ዝርዝር የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል። ከአገር ሰላም፣ ደኅንነት፣ ጸጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ የክልከላ ገደብ የሌለበት መሆን፣ ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ፍቃድ ማግኘት፡- ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ እንዲሰጠው የሚፈልግ የውጭ አገር ዜጋ የፈቃድ ይሰጠኝ ማመልከቻውን በአካል ወይም ሚኒስቴሩ በሚያደራጀው የድረ-ገጽ ሥርዓት አማካኝነት ለሚኒስቴሩ ማቅረብ አለበት (አንቀጽ 13/2/)፡፡ ሚኒስቴሩም የቀረበለትን ማመልከቻ በመመርመር ማመልከቻው በቀረበ በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን ያልተሟሉ ጉዳዮች እንዲቀርቡ ከወሰነም ይህንኑ እንዲፈፅም ለአመልካቹ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ መግለፅ አለበት፡፡ በዚህም መሠረት ተሟልቶ በቀረበ ማመልከቻ ላይ ማመልከቻው ተሟልቶ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል (አንቀጽ 14)፡፡ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ የውጭ አገር ዜጋ መብቶች በአዋጁ አንቀጽ 8(1) መሠረት የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት የመኖሪያ ቤት ባለመብት ለሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተሰጡ የንብረት መብቶች ይኖሩታል፡፡ ሆኖም ለግለሰብ ወይም ለቤተሰብ መኖሪያነት የማከራየት መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ መኖሪያ ቤቱን ለንግድ ዓላማ ማዋል የተከለከለ ነው። በተጨማሪም ራሱ እና ቤተሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖሩ የሚያስችል አግባብነት ባለው አካል የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ መብት፣ ለራሱ እና ለቤተሰቡ የመግቢያ ቪዛ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ መመላለስ እንዲችሉ የሚያደርግ አግባብነት ባለው አካል የሚሰጥ እስከ 5 ዓመት የሚያገለግል የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ የማግኘት መብት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ እና አሠራር መሠረት ከመኖሪያ ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የሚያገኘውን የኪራይ ወይም የሽያጭ ገቢ በወቅቱ ተመን በውጭ ምንዛሪ ወደ ውጭ አገር የማስተላለፍ መብት ይኖሩታል። በሌላ በኩል ደግሞ አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት ለኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የመስጠት ኃላፊነት ያለው ተቋም በዚህ አዋጅ መሠረት በሚኒስቴሩ ፈቃድ ለተሰጠው እና ሕጋዊ ውል ለፈፀመ የውጭ አገር ዜጋ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀጽ 17)፡፡ የመኖሪያ ቤት ባለቤት በሚሆን የውጭ አገር ዜጋ ላይ የተጣሉ ገደቦች እና ግዴታዎች