Damot Media / ዳሞት ሚዲያ
Статистикаአማራ በክንዱ ነፃነቱን ያረጋግጣል ! የአሸናፊወች ልጆች ነንና እናሸንፋለን ! ለመልዕክቶቻችሁ(....)
- Последний пост
- 31 мар.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🛑 አስቸኳይ የደህንነት ማሳሰቢያ:-ለሁሉም የፋኖ አመራሮችና አባላት በጦርነት ታሪክ ውስጥ ትልቁ አደጋ ከጠላት ፊት ለፊት የሚሰነዘር ጥቃት ሳይሆን፣ ከውስጥ የወጡ ሚስጥሮች የሚፈጥሩት ቀዳሚ ጥቃት ነው። ከመስመር ወጥተው ለጠላት እጃቸውን የሚሰጡ ግለሰቦች (በተለይም አመራሮች) የሚከተሉትን ስልታዊ መረጃዎች ለጠላት የመስጠት ዕድላቸው 100% መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይገባል:: * ስትራቴጂካዊ ሰነዶች፡ የወደፊት ዕቅዶች፣ የድርጅት ምስጢሮችና የውጊያ ስልቶች። * የመሬት ላይ እንቅስቃሴዎች፡ የመደበቂያ ቦታዎች፣ የሰራዊት መተላለፊያ መስመሮች እና የከተማ ውስጥ አባላት የኮድ ስሞች። * የፋይናንስ ምንጮች፡ የገቢ ማሰባሰቢያ ስልቶችና ደጋፊዎች። * የአመራር ሚስጥሮች፡ የዋና ዋና አዋጊዎች ስልክ ቁጥር፣ የግል ድክመቶችና የመንቀሳቀሻ ሽፋኖች። * ተጋላጭነቶች፡ ሊመለመሉ የሚችሉ አባላት ማንነትና ድክመታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች። 🛡 መወሰድ ያለባቸው አስቸኳይ እርምጃዎች አንድ አባል ወይም አመራር ከድርጅቱ ወጥቶ ለጠላት እጁን ሲሰጥ፣ ተቋሙ "የመረጃ ሽብር" ውስጥ ከመግባቱ በፊት የሚከተሉትን የመከላከያ እርምጃዎች በፍጥነት መተግበር አለበት፦ * የመረጃ ግምገማ (Damage Assessment): የከዳው ግለሰብ የሚያውቃቸውን ሚስጥሮች በሙሉ ቁጭ ብሎ መዘርዘርና ጠላት በእነዚህ መረጃዎች ምን ሊያደርግ እንደሚችል መተንበይ። * ፈጣን ለውጥ (System Reset): ግለሰቡ የሚያውቃቸውን የመገናኛ ኮዶች፣ የመተላለፊያ መስመሮችን፣ የጥበቃ ሽፋኖችን እና የከተማ ውስጥ አባላትን አድራሻ በአስቸኳይ መቀየር። * ውስጣዊ ምርመራ (Internal Intelligence): ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ታጋዮች በፍጥነት በመጠየቅ፣ ግለሰቡ ከመክዳቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ እና የወሰዳቸውን መረጃዎች መለየት። * የንቃት ጥሪ (High Alert): መረጃው በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አባላት ጠላት መረጃውን ተጠቅሞ ድንገተኛ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሚችል አውቀው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማዘዝ። "የከዳው ግለሰብ የጠላት መሳሪያ ነው፤ መረጃው ደግሞ የጠላት ጥይት ነው። ጥይቱ ሳይተኮስብን ኢላማችንን እንቀይር!" ድል ለአማራ ህዝብ!!
ሰበር መረጃ!! በ5 አቅጣጫ ለወረራ የተነቃነቀው ጠላት ተደመሰሰ!! ዛሬ መጋቢት 19/2018 ዓ.ም የማዕከላዊ አርማጭሆ ከሞችንና አካባቢዎችን ለመውረር ከዳንሻ በመነሳት ከሶስት ተከፍሎ 🔸1ኛው ግዙፍ ኃይል ከሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ተነስቶ በአሸሬ ዶጋው በኩል በማድረግ ወደ ወረዳዋ ከተማ ማሰሮ ደንብ ለመዝለቅ የተነቃነቀ ሲሆን፣ ከ700 ሰራዊት በላይ 2 ዙ-23 2 ሞርተር የታጠቀ ሌሎች ሞተራይዝድና የቡድን መሳሪያዎችን ጨምሮ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ኃይል ነው። ይህ ግዙፍ ኃይል በለሊት ተጉዞ ዶጋው አካባቢ ጉልት ጎጥ እንደደረሰ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አፋብን በላይ ዕዝ ፬ኛ ደጃዝማች ኮር ረመጡ ደጀን ክ/ጦር ሬጅመንት 2 እና ዘራይ ክ/ጦር ሬጅመንት 1 በመጣመር ባደረሱበት ጥቃት ➧ከ60 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ➧ 01 3F ወታደራዊ ተሽከርካሪ ተማርኳል፣ ➧ 01 ብሬን የቡድን መሳሪያ፣ ➧ 02 አርባ ጎራሽ ክላሽ የጦር መሳሪያ፣ ➧ 02 M14 የጦር መሳሪያ፣ ➧ ከ27 በላይ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ተማርኳል፣ ➧ ደመቀ የተባለ ለዓመታት በህዝብ ላይ ግፍና በደል ሲያደርስ የነበረ የወረዳ ሚሊሻ ኃላፊ ተደምስሷል፣ ➧ በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን የጦር መሳሪያ ተተኳሽ፣ በዚህ ግንባር የደረሰበትን ምት ተቋቁሞ ከጀግናው ሰራዊታችን ፊት መቆም የተሳነው ጠላት ዶጋው ወደተሰኘች አነስተኛ ከተማ አፈግፍጎ የተደመሰሰበትን ኃይል እየቀበረ ጊዚያዊ የመስፈሪያ ቀጠናውን ዶጋው አድርጎ ተመክቶና ተመክቶ የወረራ ዕቅዱ መክኖበት ይገኛል። 🔸2ኛው ከዳንሻ የተነሳ ወረራ ከሰሜን ምስራቅ ዳንሻ ተነቃንቆ ወደ ሙዓት አድጊ የተሰኘ አነስተኛ ከተማ አቋርጦ የአንገረብ ወንዝን በመሻገር ዶጋውንና ደለሳን በግራ በኩል በመተው ከማሰሮደንብ አብርሃ ጅራ መተላለፊያ መስመርን ማዕሪሽ የተሰኘ ቦታ የሚቆርጥ ወራሪ ሰራዊት ሲሆን ሰፊ የሰው ኃይል አሳትፎ ማዕሪሽን ንጋት አካባቢ ከተቆጣጠረ በኃላ ማሰሮ ደንብና ጋብላን ከኃላ ቆርጦ የወገንን የኃይል አሰላለፍ ሚዛን ለማዛባት ሙከራ አደረገ። ወቆይታ በኃላ ረፋድ አካባቢ ወደ ጋብላ ከተማ ለመነቃነቅ ሲሞክር የአርበኞች ክ/ጦር ሁለት ሬጅመንቶች፣የተከዜ ክ/ጦርና የጎቤ ክ/ጦር ሬጅመንቶች በጋራ በወሰዱት ፀረ ማጥቃት ከቁጥሩ በውል ያልታወቀ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ወደፊት አቅዶት የነበረው ማጥቃትም ህልም ሁኖበት ተገድቦ ወደ ኃላ ተስቦ ራሱን ለማትረፍ የመረጠውን ወታደራዊ መሬት ለመከታና ከለላ ተጠቅሞ እንዲገደብ ተገዷል። 🔸3ኛው ጠላት በተመሳሳይ ከሰሜን ምስራቅ ሶሮቃ ተነስቶ ዶጋው እንደደረሰ ወደ በደዊ በማቅናት የማሰሮደንብን ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ቆርጦ ለመያዝ ተልዕኮ የተሰጠው ኃይል በጫካ ሳይታይ በለሊት በመንገድ መሪ ተመርቶ ገስግሶ የነበረ ጠላት በአፋብን በላይ ዕዝ የደጃዝማች 4ኛ ኮር አይንድ ሬጅመንት በደዊ አካባቢ ተመክቶ ዕቅዱ ከሽፎ ሊመለስ ግድ ሁኗል። 🔸 4ኛው የጠላት ስምሪት ከሳንጃ ከተማ ተነስቶ በወይደንባህ በኩል ተጉዞ የተንፈልን ዳገት ዘልቆ ቀጥታ ወደ ማሰሮደንብ እንዲገባ ተልዕኮ የተሰጠው ጠላት ገስግሶ ነበር። ፊትለፊት ገዥ መሬት ተቆጣጥሮ የነበረው የረመጡ ደጀን ሬጅመንት 1 ሰራዊት ተንፈል ሚካኤል ላይ ጠብቆት የነበረ ቢሆንም .... 🔸 5ኛው የጠላት የወረራ ዘመቻ አቅጣጫ ከሳንጃ ከተማ ተነስቶ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ በጫቆና ጠባሪ በመዞር ፉጨናን ተቆጣጥሮ ማሰሮደንብን ለመክበብ የተነቃነቀው ጠላት ቢሆንም.... የደጃዝማች 4ኛ ኮር የጦር ጠበብት አዋጊዎች በወሰዱት የወታደራዊ ዘመቻ የወታደራዊ ሳይንስ ብልጫ የኮሩ የተመደቡ ሬጅመንቶች ከመከላከል በፍጥነት ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ከኃላ ትቶት የመጣውን የታች አርማጭሆ ዋና ከተማ ሳንጃ ከተማ የመሸገውን ጠላት በማጥቃት ከተማው የመሸገውን የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት መምታትና ዋና ቤዙ ላይ አደጋ መጣል ተችሏል። በዚህ ግንባር የተመታና የተማረከ ሰብዓዊና ቁሳዊ የጠላት ኪሳራ በውል አይታወቅ እንጅ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። ከሳንጃ ተነስተው በወይደንባህ ተነንፈልና በጫቆ ጠባሪ ለማጥቃት ተነቃንቆ የነበረ ጠላት ከሳንጃ በደረሰለት የድረሱልኝ ጥሪ የወረራ ዕቅዱ መክኖ ወደሳንጃ ከተማ መሪዎችን ለማትረፍ ሲብረጀረጅ እንዲመለስ ተገዷል። የሳንጃ ከተማ ምሽግ መደፈርን ተከትሎ ከሙሴባምብ ፈረስ መግሪያ የተነሳው የጠላት ኃይል ወደ ሳንጃ ተወርውሮ ለመድረስ ሙከራ ቢያደርግም ሳንጃ ለመሸገው የጠላት ግሪሳ በተግባር ሳይደርስለት ቀርቷል። ዛሬ መጋቢት 19/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ አርማጭሆና በታች አርማጭሆ ከተማ የተደረገው ውጊያ የጠላት ሰራዊት በግፍ የረገፈበት ሲሆን በተለይም የካባቢው ተወላጅ ከሃዲ የሰላም አስከባሪ ታጣቂዎችን ከፊት በማሰለፍ "የዘንዶ ጉድጓድ በሞኝ እጅ ይለካል" እንዲሉ ከፊት አሰልፈው ጭዳ እንዲሆኑ የተፈረደበት ዕለት ሁኖ አልፏል። ለከሃዲ ሚሊሻና ለብርሃኑ ጁላ ግብስብስ ጀንበር ፅልመት ሲውጣት ለልማደኞቹ አፋብን በላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር ሰራዊታችን የድል ወጋገን በመላው አርማጭሆ በርቶ ውሏል። በነጭና ጥቁር የዓይን ቀለም መካከል ነጥለው የሚመቱት የተመሰከረላቸው የደጃዝማች 4ኛ ኮር ሰራዊት ዓባላት በምሽግም ከምሽግ ውጭም ከአንገት በላይ የዓብይ አህመድን ሰራዊት ጭንቅላት ሲያፈርጡት ውለዋል። ህልውናችን በአርበኝነታችን!! ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ቴዎድሮስ ዕዝ በርካታ ቦታዎች ላይ ጠላትን ደመሰሰ። _____፩ ደባይ ጮቄ ወረዳ ቁይ ከተማ 206ኛ እና 201ኛ ኮር በመቀናጀት በቁይ ከተማ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ 59 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲደመሰሱ 29 ሚኒሻና ፖሊሶች መገደላቸው ተረጋግጧል። በቴዎድሮስ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ፻ አለቃ አበበ ሰውመሆን መሪነት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ቁይ ከተማን በመክበብ ከንጋቱ 11:30 በተጀመረ ውጊያ ቁይ ከተማን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር በአረመኔው ሰራዊት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመክፈት 59 (ሀምሳ ዘጠኝ) የ75ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት አባላት በተደረመሱ ምሽጎች ውስጥ ተገድለዋል። በግራሮ፣ በቴ/ሙ/ኮሌጅ፣ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፣አሞራ ገደል የነበሩ ተደራራቢ ጠንካራ ምሽጎች በተሰበሩበት አውደ ውጊያ በርካታ ወታደራዊ ድሎች ያስመዘገበው ቴዎድሮስ ዕዝ ጠላት የሚመካበትን የአሰንዳቦ የቁም ምሽግ በመደረማመስ ፦ ብሬን 2 (ሁለት) ስናይፐር 1 (አንድ) ክላሽ 51 (ሀምሳ አንድ) የቃታ መሳሪያ 8 ( ስምንት) ካዘና 13 (አስራ ሶስት) ቦምብ 21፣ቁጥሩ ያልታወቀ ተተኳሽና ወታደራዊ ቁሳቁሶች የተማረኩ ሲሆን፦ 59 የአረመኔ ሰራዊት 25 ሚኒሻ 4 ፖሊስ 2 ካድሬዎች ተገድለዋል። 35 ቁስለኛ አካላቸው በጥይት ሀሩር የተበሳሳ ሲሆን 2 (ሁለት) ፓትሮሎች ተቃጥለዋል። ኢንስፔክተር የፀዳው ወልዴ ወንጀል መከላከል ኃላፊ፣ ነግሬው ሰውነት፣ ካሳ ታምሩ እና ምኔ ሰውነት የተባሉ የአረመኔው ሰራዊት ወታደራዊ አመራሮች ከተገደሉት ውስጥ በፊት አውራሪነት ሲቀመጡ ሁለት መቶ አለቆች ከተገደሉ የጦር መኮንኖች መካከል ይገኙበታል ። በዚህ ጠንካራ ፍልሚያ የ206ኛ ኮር እና የ201ኛ ኮር የጦር አመራሮች የክ/ጦር መሪዎች ጋር በመናበብ ውጊያውን ከጠላት ጋር እየተፋለሙ መርተውታል። _______፪ ሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ ከማስመረቁ ማግስት ከክፍለ ጦሩ የተሰባሰበ ኃይል ጋር በሸበል በረንታ ወረዳ መርገጭ ንዑስ ከተማ ከአገዛዙ የጠላት ኃይል ጋር ከባድ ውጊያ በማድርግ በርካታ የጠላትን ኃይል በመደምሰስ እና በማቁሰል ዛሬም የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች ታሪክ ሰረቷል። በዛሬው እለት በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ከተማን ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድርስ የአገዛዙ ካንፖችን ሙሉ በሙሉ በመቅጣጠር ለአገዛዙ መንገድ መሪ የነበሩ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ እና የአገዛዙ ቅጥርኛ አራጅ የመከላከያ ሰራዊትን ሲደመስስ በርካቶች ቁስለኛ ሆነው በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ። በሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ 64ኛ ክፍለ ጦር በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ንፁስ ከተማ መሽጎ የሚገኘውን ካንፕ ለአራት ሰዓታት ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ከ40 በላይ የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥርኛ ሰራዊት ሲደመሰስ 20 ከበላይ የጠላት ኃይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድርግ 10 መሳሪያ ገቢ አድረጓል። በመርገጭ ከተማ በተደረገው ውጊያ ከተደመሰሱት እና ከባድ ቁስለኛ ከሆኑት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ውስጥ:- 1ኛ.ሚሊሻ 10 አለቃ ባየ ገዛኸኝ የሸበል በረንታ ሚሊሻ ፅ/ቤት ቤት ም/ል ኃላፊ የተወገደ 2ኛ.ፖሊስ አሸናፊ ብሬን ተኳሽ የተወገደ 3ኛ.ፖሊስ ጀማል የተወገደ 4ኛ.ፖሊስ እስማየል የተወገደ 5ኛ.ፖሊስ ሞላ መርጃ ደህንነት የተወገደ 6ኛ.ፖሊስ ሰይድ የተወገደ 7ኛ.ሚሊሻ ትልቁ ጠጋነህ ነጠርጌ ቀበሌ የተወገደ 8ኛ.ሚሊሻ አንለኝ ንጉሴ የተወገደ 9ኛ. ሚሊሻ አቃተ መረከቡ የጁ ባይሌ ምረኮኛ 10ኛ.ሚሊሻ ዝናው ብርሃኑ ውራጌ ቀበሌ ቁስለኛ 11ኛ.ሚሊሻ ስለሽ አሻግሬ ኃናማሪያም ቀበሌ ከባድ ቁስለኛ 12ኛ.ሚሊሻ ቄስ ፍቃዱ የተባሉ ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ሌሎች በስም ያልዘረዘናቸው የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ መርገጭ ጤና ጣብያ እና የዕድውኃ የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል ገብተው በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠናል። _____፫ ምዕ/ጎጃም ወምበርማ ሽንዲ ከተማ ወገዳድ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በቀን 16/2018 ዓ.ም የአገዛዙ ፀረ አማራ ሠራዊት ከመሸገበት ምዕ/ጎጃም ወምበርማ ሽንዲ ከተማ ወደ ወገዳድ የገጠር ቀበሌ ከሌሊቱ 7:00 ሠዓት ጀምሮ የተለመደ የጥፋት በትሩን ህዝባችን ላይ ለማሳረፍ ተንቀሳቅሷል። ነገር ግን ቴዎድሮስ ዕዝ ክንደ ነበልባሎቹ 88ኛ ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ወንበርማ ወረዳ ወገዳድ ቀበሌ ልዩ ስሙ አምበስ ጋማ የተባለ ቦታ ላይ ከአገዛዙ ወራሪ ሀይል ጋር በተደረገው ትንቅንቅ በርካታ የጠላት ሀይል ተደምስሷል። ክንደ ነበልባሎቹ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር እና የቴዎድሮስ ዕዝ ኮማንዶ ዩኒት ሀይል ከጠላት ጋር በቦንብ የታጀበ የእጅ በእጅ አውደውጊያ እስከ ምሽቱ 2:00 ያደረገ ሲሆን ጠላት መመለሻ አጥቶ የድረሱልኝ ጩኸት አሰምቷል። ጠላት ሙትና ቁስለኛውን አምበስ ጋማ ተራራ እና ወገዳድ ቤተክርስቲያን ታቅፎ በከበባ ያደረ ሲሆን ሌላ ተጨማሪ ሀይል ከቲሊሊና ከቡሬ በዛሬው ዕለት በማስመጣት አስከሬንና ቁስለኛ ሲያመላልስ ውሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የወንድማዊና ጓዳዊ አንድነት ፕሮግራም ሁለተኛው መድረክ በሸዋ ሰማይ ስር ተካሄደ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) መመስረቱን ተከትሎ በወረኃ የካቲት መጨረሻ ላይ በሸዋ የሚገኙት ሁለቱ ዕዞች የአንድነት ጉዟችውን ያሳዩበት የመጀመሪያውን የአንድነት መድረክ የአፋብን አሳምነው ዕዝ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች በየካኪት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛው መድረክ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች የተገኙት የሁለቱም የዕዝ መሪዎችና ልዑካን ቡድን በተገኙበት የአማራው የመጀመሪያ የሸዋ አንድነት በደማቅ ሁኔታ ፕሮግራሙ ተካሒዷል። የሁለቱ ወንድማማች ዕዞች ሁለተኛው መድረክ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም "አንድ ሆነን የህዝባችንን የህልውና አደጋ እንቀለብሳለን!" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ በተዘጋጀው የአንድነት መድረክ ላይ የአፋብን ፖሊት ቢሮ አመራሮች፣ የሁለቱም ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮርና የክፍለጦር አመራሮች፣ የፋኖ ሰራዊት አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክላስተር አመራሮች፣ የአርበኞች ፋኖ ጦር ሰራዊት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት በአይነቱ ለየት ያለ የሸዋ ወንድማዊ አንድነት መድረክ ፕሮግራም ተካሂዷል። የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ አርበኛ መከታው ማሞ እና የአንድነት አመቻች ኮሚቴው ሰሞኑን ለተከታታይ ቀናት በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች የሸዋ አንድነቱን ሂደት የማስረዳት ሰፋፊ መድረኮች የተካሔዱ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም የተጀመረውን የሸዋ ወንድማዊ አንድነት መድረክ የሚያጠናክር ሁለተኛው መድረክ ተካሂዷል። አርበኛው በመክፈቻ ንግግሩ ይሕን የሸዋ አንድነት ይመጣ ዘንድ ከሀገር ውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ፣ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎ ቤተ አምሓራ እና በሸዋ የሚገኙ የትግሉ ደጋፊዎችና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሸዋ አንድነት በሀሳብም ሆነ በአካል ለተሳተፉ ታላቅ ምስጋና በማቅረብ የህይዎት መስዋዕትነት ተከፍሎበት የመጣውን አንድነት በየደረጃው የሚገኝ አመራርና ሰራዊታችን እንዲሁም የማህበረሰባችን ክፍል አጥብቆ በመያዝ የግል ፍላጎታቸውን ካነገቡ ፀረ አንድነቶችን በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ መልዕክቱን አስተላልፈዋል። የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ሳብሳቢ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረገው የመክፈቻ ንግግር "ከመቅረት ማረፈድ ይሻላልና" እኛ የሸዋ ወንድማማቾች በተለያዩ ጎራ በተሰለፍንበት ወቅት ለመደበኛ ጠላታችን ሰፊ ክፍተት በመፍጠራችን የበደልነውን ህዝብ ለመካስ በርካታ ስራዎችን በጋራ ሰርተን እንድናሳይ ሲል ለመላው የአማራ ፋኖ አባላትና ለመድረኩ ታዳሚዎች መልዕክቱን አስተላልፏል። በመድረኩ ላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሸዋ ወንድማዊ አንድነትን በማስመልከት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኀላፊ አርበኛ አበበ ሙላቱ መድረኩን በተሳካ ሁኔታ የመራው ሲሆን የዕዙ ወታደራዊ ኪነት ቡድን የመድረኩ ድምቀት በመሆን የተለያዩ ትምህርት አዘል መልዕክቶችን የአባቶቻችንን ጥበብ ተላብሰው ለታዳሚው አስተላልፈዋል። ድል ለአፋብን!! ድል ለአማራ ህዝብ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
⚠ ከፍተኛ ከሆነ ባለስልጣን የውስጥ አርበኛ (ቀኘ) የደረሰኝ መረጃ ነው። ለሁሉም ማህበረሰብ የሚጠቅም ስለሆነ ሼር አድርጉት። "በዚህ ሳምንት 14 ተሳቢ ፈንጅ በመከላከያ ታጅቦ ከጅቡቲ ወደ አ/አበባ ገብቷል።የፎቶ ማሰረጃ አለ። በተለይ ለሰዎች ለተሽከርካሪ ፈንጅዎች ናቸው። 2. የመከላከያ እና የፈደራል ፖሊስ ደረቅ ሬሽን (ብስኩት) ክምችት ዝቅተኛ ነው።ከፍተኛ የመከላከያ እና የፌደራል(በተለይ የወንጀል መካላከል ክፍል opration ላይ ያሉ) ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ናቸው።አስቸኳይ ስብሰባም አድርገዋል ።ስብሰባው ትንሽ ቁልፍ አመራሮች ያሉበት ሚስጥራዊ ስብሰባ ነው።አብይም በዙም(zoom) ሳይሳተፍ አልቀረም።ለስብሰባው የዙም ዝግጅቶች ያደረጉ ሰዎች መረጃው ነግረውናል። 3.ሌላ በዚህ ሳምንት የ intelligence ስብሰባ ነበር። በስብሰባው ለረጅም ሰአት(3-5) የፈጀ ሲሆን አጀንዳው ፅንፈኛው የሚል ነበር። በዚህ ዙሪያ የአማራ ተወላጆች በከፈተኛ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸውና አጠራጣሪ ነገር ካለ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ትዕዛዝ ወረዷል። ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ቦታዎች መጨረሻ ላይ በቁጥር እዘረዝራለውሁ። 4. ሌላው የአማራ ሆቴሎች፣ፀጉር ቤቶች ኬክ ቤቶች፣አልጋ ቤቶች ምሽት መዝናኛዎች የ intelligence ምድባ ተደርጎባቸዋል። ሰዎችን ለመገመት በሚያሳስት መንገድ ተመድበዋል።መደበኛ የክትትል ሰዎች(ከዚህ በፊት በህብ/ቡ የሚታወቁ) እንዳሉ ሆነው ሌላ አዲስ በተለያየ ዘዴ እንዳይታወቁ አሳሳች በሆነ መንገድ ነው የተመደቡት። ለምሳሌ የtiktok content creater መስለው፣የቀን ስራ አገናኝ መሥለው፣ካሜራ ማን መስለው፣ የቀን ሰራተኛ መስለው፣ሊስትሮ መስለው፣በየመኖሪያ ቤቱ የtv ,የstove ,ምጣድ ና ሌሎች የጥገና ባለሙያ , home care የጤና ባለሙያዎች, ዘበኞች, ልብስ ሰፊዎች የራይድ ሹፌሮች በተለያየ በማይገመት መልኩ የተለያዩ የስለላ መሳሪያዋች ይዘው ከ20 ቀን ከፍተኛ ስልጠና በመውሰድ ነው ወደ ስራ የገቡት።አብዛኛው ክትትሎች ሴቶች ሲሆኑ በብዛት አማርኛ( የአማራ ተወለጆች) በደንብ መናገር የሚችሉ ናቸው። 4.social media (tiktok,WhatsApp ሌሎችም ,) ላይ ድጋፍ ለፋኖ የሚሰጡትንም በlive,profile ላይ በመግባት ፎታቸውን በመለየት ያሉበትን ቦታ(በተለይ አ/አ) በመለየት ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተቋቋመ የuniversity ተማሪዎች,የICT በያሉበት በቅርቡ ስልጠና ጨርሰው ወደ ስራ ይገባሉ።ይህ በሁሉም የአማራ ክልል ስራ ይጀምራሉ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለታል። 5. ሌላው ሚስጥራዊ የደህንነት ስብሰባ ማለትም በመካላከያ,ፌደራል ፖሊስ, አዲስ አበባ, ብሔራዊ ደህንነት, የኦሮሚያ ክልል የኢንተልጀንስ አጠቃላይ መረጃ ሪፖርት መሠረት ከ5000 በላይ የፋኖ ፣350 የኤርትራ ፣2500 የትግራይ , የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት 700 ወጣቶችና ሀገር አፍራሽ በሚል በቁጥጥር ስር ውለው በዙሪያቸው ማን እንዳሉ ጭምር አሰቃቂ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። በምርመራ አካላቸው የጎደሉ የሞቱ የተረሸኑ ደብዛቸው የጠፉ አሉ።የምርመራ ቦታዎች ቢሾፍቱ ,ሞጆ, ሆለታ ዙሪያ እና የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ናቸው። ከተቻለ በፎቶ አያያዝልሃለው።ይህንን ምርመራ ቡድን የሚመሩት የመከላከያ አባሎች,የICT ቴክኒካዊ ባለሙያዎች ,የ psychology ባለሙያዎች አሉበት። 4.ሌላው በየ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያዎች ከፍተኛ የሆነ ቁጥር የአማራ,የትግራይ እና የኤርትራ ተወላጆች በቁጥጥር ይውላሉ።እነዚህ መጠነኛ ምርመራ የሚደረግባቸው ፍ/ቤት የሚቀርቡ ናቸው። ለምሳሌ ለልደታ ፍ/ቤት ,የካ ለሚ ኩራ,ጦር ሀይሎች አካባቢ(ቶታል አካባቢ) ባሉ ፍረድ ቤቶች በእያንዳንዱ ቀን (ከሰኞ እሰከ አርብ)ምን ያህል ወጣት እንደሚንገላታና እንደሚሰቃይ በተጨባጭ ገብተው(2:30-11:00 ሰአት) ማየት ይቻላል። ማንኛውም ሰው (ጋዘጤኞች ሌሎችም ገብቶ መታዘብ ይቻላል። 5. ከላይ እንገለፅኩት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቦታዎችን በተለይም አማራዎች ኤርትራዎች,ትግሬዎች የሚኖሩባቸው ተብለው የተለዪ ናቸው።እነርሱም ክፍለ ከተማዎች ናቸው 1.ለሚ ኩራ ክ/ከ (በብዛት ኤርትራዎች በቁጥጥር የዋሉበት።ክትትል እንዲደግበት ብዙ የ intelligence ክትትሎች ተመድበዋል። 2.ሰሚት, መገናኛ ኮሚሽን ዙሪያ 3.ቂርቆስ ክ/ከተማ (አማራዎች ና ትግሬዎች more target) 4.የካ ክ/ከተማ የተለያዩ ስራ የሚሰሩ ሆቴሎች , ባለሱቆች,ጫት ቤቶች ,መታወቂያ ቀይረው የሚሰሩ ኤርትራዎችና ትግሬዎች more target ናቸው። 5.ንፍስ ስልክ ክ/ከተማ በተለይም ኤርትራዎች ሆቴል አልጋ ይዘው የሚኖሩ red line 6. አማራዎች በከፍተኛ ሁኔታ ክትትል የሚደረግባቸው ቦታዎች ዘነብወረቅ,አውቶብስ ተራ,ጀሞ 2ና,3, አየር ጤና ሀናማርያም , ፍየል ቤት ,ቤተል አካባቢ, ሰንዳፋ, ቦሌ,የካ አባዶ , ሳሪስ,ቃሊቱ, ኮልፌ,እና ሌሎች ያልተጠቀሱ ሲሆኑ ክትትሉ ከሀብታም እሰከ የቀን ሰራተኛ ,ከመንግስት ሰራተኛ(የወረዳ ሰራተኞች) እሰከ ነዋሪዎች ያጠቃልላል።የሚመራውም ከፍተኛ አመራሮችና ሚስጥራዊ በሆነ ልዩ ስልጠና ነው። በመጨረሻ አያንዳንዱ የምሰጥህ መረጃ በጥንቃቄ ከበርካታ ሰዎች(ዳኞች, ፖሊስች,የክትትል ሰዎች, ከመከላከያዎች) ለረጅም ጊዜ የተሰበተበ በሰነድ ማስረጃ የተሠበሰበ ነው።የዶክመንት መረጃ አለ ግን ቢወጣ አደጋ ስለሚያመጣና ተጋላጭነቱና ለመለየት ቀላል ስልሆነ only text copy ብቻ ልልክ ተገድጃለው። በተለይ የአማራ, የትግረይ ,የኤርትራ ተወላጆች በዙሪያቸው ያለን ሰዎች,ጓደኞች የስራ ባልደረቦች እና ሌሎች ሰዎች በንቃት በመከታተል ራሳቸው እንዲጠብቅ, በወቅታዊ ሁኔታ ምንም አይነት መረጃ ከማውራትም ከመስጠትም እንዲቆጠቡ።ማንንም ማመን አይገባም።"
በቃሊቲ ማ/ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በቂ ሕክምና ለማግኘት እንዳልቻሉ ተገለፀ ፤ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በኩላሊት ሕመም የተነሳ በከፍተኛ ሕመም ላይ እንደምትገኝም ተሰምቷል። ለእስረኞች የጤና አገልግሎት መስጠት ምንም እንም እንኳ የመንግስት ቀጥተኛ ኃላፊነት መሆኑ እና አድሎአዊ ድርጊት የተከለከለ ስለመሆኑ በሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ሕጎች የተገለፀ ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም። የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21(1) እስረኛ መሆን ማለት ሰብአዊ ክብርን የመነፈግ ማለት እንዳልሆነ በመግለጽ “በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ሰዎች በሙሉ እንዲሁም ጥፋተኛ ተብለው በቅጣት ላይ ያሉ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን በሚያከብር መንገድ የመታከም መብት አላቸው” ይደነግጋል። የፌዴራል እስረኞች አያያዝ ደንብ ቁጥር 138/2007 ይህ ደንብ በ2007 የወጣ ሲሆን፣ እስረኞች በጾታ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም በዜግነት ሳይድሉ እንዲታከሙ ያዛል ። ይሁን እንጅ በተለይም በአማራነታቸው የተነሳ ወደተለያዩ የፌደራል ማ/ቤቶች ተወስደው የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ሕክምናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያገኙ አለመሆኑን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ለፍ/ቤት አቤቱታዎችን ሲያቀርቡ ይደመጣል። የጤና ባለሙያዎች ሳይቀር ክሊኒካዊ ነጻነታቸው እየተነጠቀ የሕክምና ውሳኔዎችን በህክምና ምክንያቶች ብቻ ከመወሰን ይልቅ በእስር ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ፖለቲካዊ ጫና ሲቀለበሱ ይስተዋል። የፍ/ቤት ትዕዛዝን በተገቢው ሁኔታ ባለመፈፀምም ጭምር ሕሙማን እንዳይታከሙ ማድረግ የተለመደ ሆኗል። አንድ ተጠርጣሪም ሆነ የተፈረደበት ሰው መሰረታዊ የሆነ አለማቀፋዊ የሆነ ሕክምና የማግኘት መብቱን በመግፈፍ መቅጣት ትልቅ ኢሰብአዊ የሆነ ወንጀል ነው። ይህን መሰረታዊ የሆነ ሕክምና የማግኘት መብት ከተነፈጉት መካከልም በቃሊቲ ማ/ቤት የሚገኙ በአማራነታቸው የተነሳ ያለፍትህ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ሴት የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ይገኙበታል። ከእነዚህም መካከል ፦ 1) ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ፣ 2) ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ፣ 3) አለም በድሉ ፣ 4) ሕይወት አለማየሁ እና 5) ሀሊማ መሀመድ 6) የዋስትና 150 ሽህ ብር ተጠይቃ ደጋፊ ባለማግኘቷ ለመክፈል ባልቻለችው መቅደስ አለሙ እና በሌሎችም ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል ተጠቃሽ ነው። መንግስታዊ የሆነ የዘር ፍጅትና የጦር ወንጀል እየተፈፀመበት ስላለው የአማራ ሕዝብ ድምፅ በመሆኗ እንደ ወንጀል የተቆጠረባት መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ለገጠማት ከፍተኛ የሆነ የዐይን ሕመም ከብዙ ጩኸት ፣ ልመና እና አቤቱታ በኋላ ሕክምና ለማግኘት መቻሏ ይታወቃል ፤ መጠነኛ መሻሻል ብታሳይም አሁንም በክትትል ላይ ትገኛለች። በተመሳሳይ የግፍ እስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ከብዙ መዘግየት በኋላ የግል ሕክምና ማግኘቷ ተገልጧል ፤ ጋዜጠኛዋ ሁለት ኩላሊቷ መጎዳቱ በሀኪም ተረጋግጧል። መጋቢት 10/2018 ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት በመሄድ የግፍ እስረኞችን የጎበኘው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ እንደገለፀው የእስረኞቹ የጤና ሁኔታ አሳዛኝና አሳሳቢ ነው። ጋዜጠኛ ገነት አስማማውም የኩላሊት ጠጠር ነው የተገኘባት። ለመኝታ የሚሆን ደረቅ ፍራሽ እንዲገባላት ፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥላትም መጠየቁ ተገልጧል። 3) ሌላኛዋ የግፍ እስረኛ አለም በድሉም ሕክምና ለማግኘት በተደጋጋሚ ብታመለክትም የተሻለ ሕክምና እንድታገኝ አልተፈቀደላትም። ዳኑ የአጥንት ሕክምና ሄዳ አስቸኳይ ሕክምና ማግኘት ባለመቻሏ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። 4) ሕይወት አለማየሁ እና ሀሊማ መሀመድ በከፍተኛ ሕመም ላይ ይገኛሉ። ሁሉም ከሰብአዊነት አንጻር አስቸኳይና የተሻለ ሕክምና የማግኘት መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል። ይህ ይሆን ዘንድ ደግሞ የሰብአዊ መብት እና የሚዲያ ተቋማት በቃሊቲ ማ/ቤት እና በችሎት እየተገኛችሁ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ተጠይቋል። አቢይ አህመድ በሚመራው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በአማራ ማንነታቸው ብቻ ከየ ስራ እና መኖሪያ ቤታቸው እየታፈኑ በተለያዩ የፌደራል ማ/ቤት ያለፍትህ እየተሰቃዩ የሚገኙ በትንሹ ከ300 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ከእነ ቤተሰቦቻቸው ሁለንተናዊ የሆነ ወገናዊ ድጋፍና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ግልጽ ነው። (አውሎግሶን አንድነት ፣ መጋቢት 11/2018)
እየመጣን ባጫዬ!💪😃
አፋብን ሸዋ ደራ! ከአዲስአበባ 95 ኪሜ ርቀት ላይ! በሻሻ ወ ጁላ ሂሳቡን ስራዉ 😃
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንኳን ለኢድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። በተለይም ስለ ሕዝባችሁ ነፃነት ስትሉ ለነፍሳችሁ ሳትሳሱ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ከምትከፍሉት መራር ዋጋ ጎን ለጎን ይህን ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በጸሎት ያሳለፋችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎቻችን ከፈጣሪ ዘንድ እዝነትና በረከት ለሚታደልበት የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የአማራ ሕዝብ ላለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ከደረሰበትና አሁንም እየተፈጸመበት ካለው መንግሥት-መር የጅምላ እልቂትና ጭፍጨፋ እንዲሁም የሀብትና ንብረት ውድመት ውስጥ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዩ ወገናችን ከፊት ተሰላፊ ነው። ወገኖቻችን በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ አማራ-ጠል እሳቤ ባነገቡ ቡድኖችና የጸረ-አማራነት ትርክትን ሥጋ አልብሶ በሚንቀሳቀሰው አገዛዝ በሚፈጸምባቸው ጭፍጨፋ በርካቶች ሕይወታቸው ተቀጥፏል፣ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ለከባድ ማኅበራዊ ምስቅልቅል ተዳርገዋል። በዚህ ጸረ-አማራ እሳቤ በሚመራው ሥርዓት የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ጥቃት ተባብሶ በመቀጠሉ ዛሬም በሞት አፋፍ የሚገኙ ወገኖቻችን እልፍ ናቸው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከተፈጸመባቸው ጭፍጨፋ እንደ እድል ተርፈው፡ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ፡ ከሞት ያልተናነሰ ኑሮን እያሳለፉ ይገኛሉ። ወገናችን በዚህ መከራ ውስጥ ሆኖም ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በዱዓ በማሳለፍ የጽናት ተምሳሌትነቱን እያሳየ ነው። በመከራ ውስጥ ሆኖም ለፈጣሪው መገዛትን፣ ጽናትን፣ አሸናፊነትን፣ ትዕግሥትንና ጥበበኝነትን ከወለደው ሕዝብ የወረሰው የአማራ ፋኖ፡ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የመከራ ቀንበር ይሰብር ዘንድ ሐቅን ከነፍጥ ጋር አንግቦ በድሉ ዋዜማ ላይ ይገኛል። የአማራ ፋኖ እያደረገ ባለው ትግል ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ታድጎ ሕልውናቸውን ማስከበር፣ ለተፈፀመው እልቂትና በደል ፍትሕና ርትዕ ማስፈን፣ እንዲሁም ወገኖቻችን በገዛ አገራቸው በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሀብትና ንብረት ማፍራት የሚችሉበትን ሥርዓት ማንበር፡ የትግላችን ቀዳሚ ዓላማና ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ግባችን ነው። ለዚህ ታላቅ ዓላማ ስኬት ሕዝባችን፡ በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ፡ ትግሉን በባለቤትነት ከመምራት፣ ከመታገል ጀምሮ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ፣ የሐሳብና የመረጃ እገዛ በማድረግ እንዲሁም በዱዓ በመርዳት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ቅዱስ ቁርኣን "እናንተ ያመናችሁ ሆይ፡ በትዕግሥትና በሶላት ታገዙ፡ አላህ በእርግጥ ከታጋሾች ጋር ነውና" ("ያ አዩሀለዚነ አመኑ ስተዒኑ ቢሷብሪ ወሷላህ፣ ኢን-አላሀ መዐ-ሷቢሪን") ሲል ያስተምራል። በእርግጥም ሐቅን ከነፍጥ ጋር ያነገበው የሕልውና ትግላችን፣ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ንቁ ተሳትፎ ዛሬ በድሉ አጥቢያ ላይ ደርሷል። ነገ የህልውናን ትግላችን በነፃነታችን ሲረጋገጥ በዓሉን በሚመጥን ሁኔታ በአደባባዮቻችን እስከምናከብር በዚህ መከራ ውስጥ ሁናችሁ እያከበራችሁ ላላችሁ ህዝባችን እና ሰራዊታችን ድርጅታችን አፋብን መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል። በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢድ-ሙባረክ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ!
без подписи
ሌላ የብስራት ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ [መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም] ዘመቻ አርበኛ ውባንተ አባተ ፪ኛ ዓመት መታሰቢያ ከራሥ ጋይንት እሥከ ደራ-ሐሙሲት በደቡብ ጎንደር ቀጣና እና አዋሳኞች የሚንቀሳቀሱት የበላይ ዘለቀ ዕዝ፣ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እንዲሁም የምኒልክ ኮሮች በጋራ አቅደው ዛሬ አነጋግ ላይ የጀመሩት ውጊያ ጠላት በደቡብ ጎንደር ቀጣና ያሰማራውን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ እና ሎጅክስቲክሱን በመማረክ በድል በመከናወን ላይ ነው። በራሥ ጋይንቱ ነፋሥ መውጫ ከተማ፣ በጉና በጌምድሩ ክምር ድንጋይ ከተማ፣ በፋርጣው ጋሳኝ ከተማና በደራው ሐሙሲት ከተማ የተከማቸውን የጠላት ሰራዊት እኔ ቁሳቁስ ዒላማ አድርጎ በተካሄደው ማጥቃት በሁሉም ከተሞች የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በጥበበኛው በሰራዊታችን ክንድ ፍርስርሱ ወጥቷል። በዚህ ውጊያ:- ፩)/ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር:- ከባሕር ዳር በ30 ኪ.ሜ ርቀት ያለችው ደራ ሐሙሲት ከተማ ፣ ወንጨጥ ሚካኤል፣ ይዘት እና ቦምባት የመሸገውን የአገዛዙ ሰራዊት፤ ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ጋሳኝ ከተማን አልፎ ወደ ክምር ድንጋይና ራሥ ጋይንት ሊያልፍ የነበረውን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በመበታተን፦ ✅ 09 ብሬን ✅03 ዲሽቃ ✅ 120,000 በላይ ተተኳሽ ✅453 Ak-47 ክላሽ ✅135 የአድማ ብተና ምርኮኛ ✅251 የተደመሰሰ ✅07 RPG ከነሙሉ ተተኳሹ ✅ከ10+ ፓትሮሎች ✅28 ሎጀሥቲክ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ✅51 የሬዲዮ መገናኛ ራዲዮ ✅በርካታ የጭሥ ቦምቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርኳል። ፪) አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ንፋስ መውጫ ከተማ እና ጉና በጌምድር ክምር ድንጋይ ከተማ ላይ ወታደራዊ ጥበብ የተሞላበት የከተማ አውደ ውጊየ በማድረግ ጠላት ላይ ከፍተኛ ምት በማሳረፍ:- ✅03 ዲሽቃ ✅10 ብሬን ✅500+ ክላሽ ኮፕ ✅65 አብራራው ✅13 አይኮም የመገኛ ሬዲዬዎች ✅01 FSR መኪና ፣ 05 ፖትሮል መኪኖች ✅ ከ100 ሺህ በላይ የተለያዩ ተተኳሾች ገቢ ሆኗል። ✅ከ 100+ በላይ የአድማ ብተና አመራርና አባላት የብልጽግና ካድሬ አመራሮች እና ሚሊሾች ሲማረክ ከፍተኛ ኃይሉ ደግሞ ሙት ሆኗል ። ፫) ምኒልክ ዕዝ የ303ኛ ኮር 81ኛ፣ 16ኛ ክፍለ ጦሮች እና የ106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር በደቡብ ጎንደር ጋይንት ንፋስ መውጫ ከተማ ላይ በሚገባ ተመትቷል:: በዚህ አውደ ውጊያ የምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር እና የ106ኛ ደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች የተገኘ ምርኮ:- ✅ 183 ከተለያዬ አሐድ የተውጣጣ የጠላት ሰራዊት ✅ አንድ ብሬን ✅ 2468 የብሬን ተተኳሽ ✅ 151 ክላሽ ✅ 8780 የክላሽ ተተኳሽ ✅ 267 የእጅ ቦምብ ✅ በርካታ የደረትና የወገብ ትጥቅ እንዲሁም ወታደራዊ አልባሳት የተማረከ ሲሆን ከ200 በላይ አድማ ብተና፣ ፖሊስና ምሊሻ ተደምስሷል። በአጠቃላይ ዛሬ መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም እስካሁን በተካሄደው ውጊያ:- ➫ 6 (ስድስት) ድሽቃ፣ ➫ 20 (ሃያ) ብሬን፣ ➫ 1104 (አንድ ሺ አንድ መቶ አራት) ክላሽ፣ ➫ 15 (አስራ አምስት) ፓትሮል፣ ➫ 29 (ሃያ ዘጠኝ) ሌሎች ተሽከርካሪዎች፣ ➫ ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ የክላሽ፣ የብሬን እና የዲሽቃ ተተኳሾች፣ ➫ 64 (ስልሳ አራት) መገናኛ ራዲዮኖች፣ ➫ 65 (ስልሳ አምስት) አብራራው ጠመንጃ፣ ➫ 500 (አምስት መቶ) በላይ የእጅ ቦንቦች፣ ➫ 418 (አራት መቶ አስራ ስምንት) ሰራዊት መማረክ ተችሏል። በዚህ ውጊያ 651 (ስድስት መቶ አምሳ አንድ) በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል። በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶችም ገቢ ተደርገዋል። ይቀጥላል...
без подписи
без подписи
ጎንደር