Economics For All !!!
Статистикаይህ ቻናል ሲመሰረት ዋና አላማው የEconomics material ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ማጋራት እና ለሀገራችን ብቁ Economist መፍጠር ነው።
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 32
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 391
- 1/48двое суток
- 448
- 1/72трое суток
- 483
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#ጥቆማ በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ! የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም መራዘሙን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል። የትምህርት መስኮች ● Electrical Engineering ● Biotechnology ● Space Science ● Mechanical Engineering ● AI ● Nuclear engineering ያመልክቱ 👇 https://sitedu.info/admission/application መስፈርቶች ● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90% ● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል ● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል ● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ ● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ ውጤት ከ2017ዓ.ም ከተመዘገበው ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ20% ጭማሪ(እድገት) ተመዝግቧል። ተማሪዎችም ውጤታቸውን በሁለት አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:- ➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት 3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ ❷ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ 1) start የሚለውን ይጫኑ! 2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ 3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ 4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ ➌ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት 3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን 4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ 5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ 👉 2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።
📊 የኢኮኖሚክስ ሳይንስ እንደሚያረጋግጠው፣ ከፍተኛ የታክስ መጠን ከፍተኛ የመንግሥት ገቢ አያመጣም! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የኢኮኖሚክስ ሳይንስ የሚያስተምረው፣ የታክስ መጠንን መጨመር ሁልጊዜ የመንግሥትን ገቢ እንደማያሳድግ ነው። በተወሰነ ደረጃ ከተሻገረ በኋላ፣ በመጨረሻ ላይ ከፍተኛ የታክስ መጠን ከተወሰነው ተመጣጣኝ ደረጃ በላይ ሲጨምር፣ ምርትን፣ ኢንቨስትመንትን እና የታክስ መሠረቱን (tax base) በማሳነስ፣ በመጨረሻም የመንግሥትን የታክስ ገቢ እንኳን ይቀንሳል። ይህንንም ሐሳብ የላፈር ከርቭ (Laffer Curve) በግልጽ ያሳያል። ብዙ ሰዎች የመንግሥትን ገቢ ለማሳደግ ቀላሉ መንገድ የታክስ መጠንን መጨመር ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን የኢኮኖሚክስ ሳይንስ የሚያሳየው እውነታ ከዚህ የተለየ ነው። ስለዚህ ዘላቂ የመንግሥት ገቢ የሚገኘው ታክስን በማሳደግ ብቻ ሳይሆን፣ ምርትን በማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት፣ የታክስ ከፋዮችን በማበረታታት እና የበለጠ በማስፋት እንዲሁም የታክስ አስተዳደርን በማሻሻል ነው። የታክስ መጠን እስከ ተወሰነ ደረጃ ድረስ ሲጨምር የመንግሥትን ገቢ ሊያሳድግ ይችላል። ነገር ግን ከዚያ ገደብ በላይ ሲያድግ ውጤቱ በተቃራኒው ይሆናል። ምርት ይቀንሳል፣ ኢንቨስትመንት ይዳከማል፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎች ይቀንሳሉ፣ የታክስ ተገዢነትም ይወርዳል። በመጨረሻም የመንግሥት ገቢ ራሱ ይቀንሳል። 💼 ከፍተኛ የታክስ ጫና የድርጅቶችን የሥራ ወጪ ይጨምራል፤ ትርፋቸውን ይቀንሳል፤ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ያዳክማል። በዚህ ምክንያት አንዳንድ የግል ኩባንያዎች፣ የንግድ ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የአገልግሎት ድርጅቶች ሥራቸውን ያሳንሳሉ፣ ወይም ወደ ታክስ ጫና ዝቅተኛ ወደሆኑ አገሮች ሊዘዋወሩ ይችላሉ። ይህ ሀሳብ በተግባር እንዴት እንደሚታይ ለማሳየት፣ በአገራችን ከታወቁ የግል ድርጅቶች እና ኩባንያዎች ባለቤቶች አንዱ፣ በቢዝነስ ሥራቸው ላይ የደረሰባቸውን ከፍተኛ የታክስ ጫና እና ይህ ጫና በኢንቨስትመንት፣ በሥራ መስፋፋት እና በአጠቃላይ በቢዝነስ መንፈሳቸው ላይ ያሳደረውን የተስፋ መቁረጥ ተፅዕኖ ሲገልጹ እስቲ መጨረሻ ላይ ያያዝኩትን በተለያየ ሚዲያዎች እየተዘዋወሩ ያሉ ሊንኮችን ከፍተው ይመልከቱ። 📉 በተጨማሪም ከፍተኛ ታክስ አንዳንድ ንግዶችን ከመደበኛው ኢኮኖሚ ወደ መደበኛ ያልሆነ (Informal Economy) እንቅስቃሴ እንዲሸጋገሩ ወይም ታክስን ለመሸሽ እንዲሞክሩ ሊያበረታታ ይችላል። ይህ ደግሞ የታክስ መሠረቱን ያጠባል፤ የመንግሥት ገቢንም ይቀንሳል። 🌱 ስለዚህ የመንግሥት ገቢን በዘላቂነት ለማሳደግ መፍትሔው የታክስ መጠንን ያለ ገደብ መጨመር ሳይሆን፣ ፍትሃዊና ተመጣጣኝ የታክስ ሥርዓት መዘርጋት፣ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የንግድ ምቹ አካባቢን መፍጠር እና የታክስ አስተዳደርን ማዘመን ነው። የመንግሥት ገቢ የሚያድገው በከፍተኛ የታክስ መጠን ሳይሆን፣ በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በሰፊ የታክስ መሠረት፣ በከፍተኛ ምርታማነት እና በታክስ ከፋዮች እምነት ላይ ነው። የገለጹት ሐሳብ በኢኮኖሚክስ ውስጥ Laffer Curve ተብሎ ከሚታወቀው ጽንሰ-ሐሳብ ጋር ይዛመዳል። ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የሚያሳየው የታክስ መጠን ከ0% ወደ መጠነኛ ደረጃ ሲጨምር የመንግሥት ገቢ እንደሚጨምር፣ ነገር ግን ከአንድ የተመጣጠነ ደረጃ በላይ ሲደርስ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በመቀነስ የመንግሥት ገቢ እንኳን ሊቀንስ እንደሚችል ነው። የላፈር ከርቭ (Laffer Curve) ምሳሌ ይህ በታክስ ፖሊሲ ውስጥ ታዋቂ የሆነ ሀሳብ ነው። 📈 የላፈር ከርቭ (Laffer Curve) የመንግሥት ገቢ (Tax Revenue) ▲ │ │ ● │ ● ● │ ● ● │ ● ● │ ● │ ● │ ● └───────────────────────── ───────────────► 0% 50% 100% የታክስ መጠን (Tax Rate) የግራፉ ትርጉም 📢 0% ታክስ ⇒ የመንግሥት ገቢ = 0 📢 ታክስ ከ0% ወደ መካከለኛ ደረጃ ሲጨምር ⇒ የመንግሥት ገቢ ይጨምራል። ነገር ግን ታክስ ከመጠን በላይ ሲጨምር ኢንቨስትመንት፣ ሥራ ፈጠራ እና ምርት ይቀንሳሉ። 📢 ከ0% እስከ 50% (ምሳሌ) ⇒ የታክስ መጠን ሲጨምር የመንግሥት ገቢም ይጨምራል። 📢 ከ50% በላይ (ምሳሌ) ⇒ የታክስ ጫና ከመጠን ሲያልፍ ምርት፣ ኢንቨስትመንት፣ ሥራ ፈጠራ እና የታክስ ተገዢነት ይቀንሳሉ፤ በዚህም ምክንያት የመንግሥት ገቢ ይቀንሳል። 📢 100% ታክስ ⇒ ማንም ሰው ለመሥራት ወይም ለመንገድ ማስፋፋት ተነሳሽነት አይኖረውም፤ ስለዚህ የመንግሥት ገቢም ወደ 0 ሊጠጋ ይችላል። ማጠቃለያ የመንግሥትን ገቢ ለማሳደግ ዘላቂ መፍትሔ የታክስ መጠንን ያለገደብ መጨመር ሳይሆን፣ ምርትንና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ፣ የታክስ መሠረቱን የሚያሰፋ እና ፍትሃዊ የሆነ የታክስ ፖሊሲን መተግበር ነው። ከፍተኛ የታክስ መጠን በራሱ ገቢን አያረጋግጥም፤ ተመጣጣኝና ሳይንሳዊ የታክስ ፖሊሲ ግን የኢኮኖሚ እድገትንም ሆነ የመንግሥት ገቢን በዘላቂነት ሊያሳድግ ይችላል። #ታክስ #ኢኮኖሚ #ኢንቨስትመንት #ምርታማነት #የመንግሥት_ገቢ #የኢኮኖሚ_ፖሊሲ ┈┈┈┈┈┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈┈┈┈┈┈┈ ✍️ Anbessie Debebe
ሁላችሁም ለ2 ቀን የሚቆይ ነጻ የData የድምፅና የsms ስጦታ ተሰጧችኋል። ስጦታው 1.5GB data, 15 ደቂቃና 30 sms ሲሆን ከሀምሌ 17 ሌሊት 6 ሰዐት እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ይቆያል። ይህንን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የ2018 በጀት አመት ሪፖርት ባቀረቡብት ወቅት ነው።
ለዲግሪ እና ለፖስትግራዉደት (Undergraduate & Postgraduate) ተማሪዎች በሙሉ! ልባችሁን ይዝሩ 🎓✨ በመረጃ ትንተና፣ በፕሮፖዛል ዝግጅት ወይም በዳታ አናሊሲስ ላይ የጊዜ ጉድለት ወይም ችግር ያጋጠማችሁ ነው? የምትፈልጉት ምርጫዎች በእጃችሁ ላይ ናቸው! የፕሮፌሽናል እገዛ በሆነ መንገድ ጥራቱን የጠበቀና ፈጣን እገዛ እንሰጣለን። 🔹 የምንሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች (Services)፡ Research Proposal & Thesis፡ ከርዕስ መረጫ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ ሙሉ እገዛ Data Analysis፡ በ SPSS እና በ STATA ሶፍትዌሮች የተደገፈ ጥልቅ ትንተና Questionnaire Development፡ ትክክለኛና ሳይንሳዊ የመረጃ ሰብሰቢያ መጠይቅ ዝግጅት Term Papers & Semester Projects፡ በጥራት የተሰሩ የምደባ ስራዎች 🔹 የምናገኛቸው የትምህርት ዘርፎች (Departments)፡ ለፖስትግራዉደት (Postgraduate)፡ Project Management፣ MBA፣ Marketing Management እና ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች ለዲግሪ (Undergraduate)፡ Accounting፣ Management፣ Marketing እና ተያያዥ ትምህርቶች 💡 ለምን እኛን ይምረጡ? ታማኝነት፣ ጥራት እና ጊዜን መጠበቅ ዋና ዋና መለያዎቻችን ናቸው! ሳይቆጠቡ ዛሬውኑ ያግኙን። 👇👇 ለመገናኘትና ፈጣን ምላሽ ለማግኘት 👇👇 📞 ስልክ ቁጥር፡ 0911849500 📲 በቴሌግራም፡ @zegetah
ከላይ የቀጠለ ተጨማሬ ማብራሪያ #ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ላይ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ምን ይላሉ? ባለሥልጣኑ በመመሪያው አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ማሻሻያዎች ያደረገ ሲሆን፤ በረቂቅ ማሻሻያዎቹ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ መጠየቁ ይታወቃል። ማሻሻያዎቹ፦ በቀድሞው ዲፕሎማ / ከ12+2 /ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ አራት ስልጠና ተመርቀው ያጠናቀቁ ትክክለኛነቱ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ወይም በፌደራል ወይም በክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተረጋገጠ ኦሪጅናል የስልጠና ማስረጃ ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ኖራቸው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ የትምህርት ማስረጃ የሚረጋገጥላቸው፦ ሀ) ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፋ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡ ለ) ሆኖም ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ፩ (ሀ) የተጠቀሰው ቢኖርም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ የያዙ ባሉበት የትምህርት ደረጃ (BA, MA, and PhD) ላይ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው በያዙት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል። https://t.me/econ13 ሐ) ይህ መመረያ ተሻሽሎ በስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር ወይም ማንኛውም የሚመሰከተው አካል የሚያወጣውን የመግቢያ መስፈርት ብቻ ተከትሎ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር አለበት። በማሻሻያዎቹ ላይ አስተያየት ይስጡ 👇 https://forms.gle/ndRhodE2yoHSn2P5A https://t.me/econ13 ሊንኩን በመጫን አስተያየት መስጫውን ማግኘት ትችላላችሁ፤ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ ስትጨርሱ Submit የሚለውን በመጫን አስተያየታችሁን ይላኩ። https://t.me/econ13 በተጨማሪ ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት በባለሥልጣኑ ኢ-ሜይል አድራሻ Info@eta.et ላይ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ ተብሏል። https://t.me/econ13
እንደገና ፈተና አለ‼️ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የተመረቃችሁ ወይም የመውጫ ፈተና ሳትፈተኑ የዲግሪ ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ እንደገና የትምህርት ማስረጃችሁን ለማረጋገጥ ሲባል ሊፈተኑ ነው ተብሏል። በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት በኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ ላይ በተለቀቀው ሊንክ እየገባችሁ መሙላት ትችላላችሁ።
Ethiopian National Exit Exam 2018 E.C. / 2026 G.C. Results 🇪🇹🎓 • Total registered candidates: 237,460 • Students who did not sit for the exam: 32,432 • Students who failed: 155,336 • Students who passed: 48,692 Congratulations to all 48,692 graduates who passed the 2018 E.C. / 2026 G.C. Exit Exam! Your hard work paid off. 🎉 To those who didn’t pass this time — don’t give up. I’m wishing you success in advance for the second round. You’ve got this! 💪 And to the 32,432 candidates who were absent for various reasons — I encourage you to prepare well and come back stronger for the next exam. Your degree is worth it.
🔥Urgent For Graduates #Job_Portals ለኢትዮጵያውያን ለሥራ ፍለጋ የሚረዱ ድረገጾች እና ፖርታልስ (Portals) እንደሚከተለው ቀርበዋል። ‼️ብዙ የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት ⤴️ 1⃣. www.ethiojobs.net . 2⃣. https://dereja.com 3⃣. https://et.profdir.com/ 4⃣. http://Www.harmeejobs.com 5⃣. www.ezega.com 6⃣. www.employethiopia.com 7⃣. www.unjobs.org 8⃣.http://www.hawassaonline.com/jobs.php 9⃣.https://www.au.org/about/employment 1⃣0⃣. http://www.unicef.org/ethiopia/careers_12858.html 1⃣1⃣. https://www.et.undp.org/content/ethiopia/en/home/jobs.html 1⃣2⃣. www.ethiocv.net 1⃣3⃣. https://www.ethiopianreporterjobs.com/ 1⃣4⃣. https://ethioworks.com/category/addis-zemen/ 1⃣5⃣. https://www.geezjobs.com/ 1⃣6⃣. www.nilejobs.com
አብዛኞቻችሁ ማጭበርበሪያ ነው ወይም አይሰራም ብላችሁ ታምናላችሁ፤ ነገር ግን እመኑኝ፣ ሰዎች ለ3 ደቂቃ ያህል ደረጃዎቹን በመከተል ብቻ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እያገኙ ነው። ሁለቴ ሳታስቡ አሁኑኑ ገንዘብ ማግኘት ጀምሩ፤ ቦቱን ያስጀምሩ (start በሉ)፣ ከዚያም 4 ቻናሎችን ይቀላቀሉ (join አድርጉ) እና ሽልማትዎን ይቀበሉ። https://t.me/usdtxtrustwallte_tbbot?start=6762683037
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሰላም ሁላችሁም! ደህና ናችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በቀላሉ ገንዘብ ሊያገኙበት የሚችሉበት አዲስ ዕድል አግኝቻለሁ። በቀላሉ ሊንኩን በመጠቀም ይግቡ፣ ቦቱን (bot) ያግኙ፣ እና የተጠቀሱትን 4 ግሩፖች በመቀላቀል የሚጠበቁትን ቅደም ተከተሎች ያጠናቅቁ። 🎉 የ $2 USDT የእንኳን ደህና መጡ ቦነስ ያገኛሉ። ከዚያ በኋላ፣ የእርስዎን የማጋሪያ ሊንክ (referral link) ለሌሎች ያጋሩ እና ለእያንዳንዱ ለተሳካ ግብዣ $1 USDT ያግኙ። https://t.me/usdtxtrustwallte_tbbot?start=6762683037 ህጋዊ እና እውነተኛ ይመስላል፣ ስለዚህ ፍላጎቱ ካላችሁ ቀድማችሁ በመግባት ራሳችሁ ፈትሹት! https://t.me/usdtxtrustwallte_tbbot?start=6762683037
Mind test for refreshment! I am an English letter with 5 letter. if you remove the first letter, I become something u can drink. if u remove the second letter, I will become a place where people live. if u remove my third Letter, I will become a type of music. If u remove the 4th Letter, I will become something u use to write. If u remove the 5th Letter, I will become a number! So, what am I?
Dear Economics Exit Exam Candidates, Tomorrow is for relaxation, not pressure. ✅️ Avoid over reading and unnecessary tension. ✅️Give your mind time to relax and recharge. ✅️ Eat well and sleep well starting tonight. ✅️Build self-confidence and trust your preparation. ✅️Don't worry about the few topics you may have missed. ✅️Take breaks, an exhausted mind gets stuck during exams. Remember, the exam requires around 2 hours and 30 minutes of focused thinking, so save your energy for the exam room. 🎓 Wishing all of you the very best of the best. Believe in yourselves that you are ready.
‼️ዘመኑ ያመጣውን የAI ጎርፍ ተከትሎ ብዙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከዚህም ከዚያም "አዲስ AI ፈጠርሁ" እያሉ ዜና ሲያስነግሩ ይሰማል። Optimist ለመሆን እሞክራለሁ፣ አደንቃለሁ ግን ደግሞ ሙሉ የAI ቴክኖሎጅ በአንድ ሰው የሚሰራ የቴክኖሎጅ ውጤት አደለም። በየደረጃው ብዙ ሀብትና እውቀት የሚጠይቅ ቴክኖሎጅ ነው። ከየት ይጀምራል መሰላችሁ። የመጀመሪያው የኮምፒውተር መሰረተ ልማት ነው። ግዙፍ መረጃ የማሰላሰል አቅም ያላቸው የኮምፒውተር ሰርቨሮችና የኔትወርክ መሰረተ ልማት ያስፈልጋሉ። Data Center ማለታችን ነው። በሁለተኛ ደረጃ በሚሊዮን or ቢሊዮን ቴራባይት የሚገመት የዳታ ክምችት ያስፈልጋል። ሶስተኛ የዳታ ክምችቱን መሰረት አድርጎ በተሰራ አልጎሪዝም የሰለጠነ የAI ሞዴል ያስፈልጋል። በመጨረሻ ሞዴሉ ከሰው ጋር እንዲያወራ የሚያስችለው Interfacing ያስፈልጋል። API ይባላል። አንድ ግለሰብ ይህን ሁሉ አሟልቶ አንድ ቻትቦት ሊሰራ አይችልም። ነገር ግን እንደ ጎግልና Open AI ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ከላይ ያወራሁትን 3ቱን ደረጃዎች ከሰሩ በኋላ የመጨረሻውን interfacing በሽያጭ መልኩ ለሶስተኛ ወገን አልሚዎች (3rd party developers) ያቀርባሉ። ሶስተኛ ወገን አልሚዎች subscribe ያደረጉትን API በመጠቀም የራሳቸውን mobile app ወይም web app ሰርተው ያቀርባሉ። ይህን ነው እንግዲህ "እኔ ሰራሁት" የሚሉን። ከእነዚህ ሶስተኛ ወገን አፕሊኬሽኖች ጋር ስታወሩ የምትፀፃፉት ግለሰቡ ከሰራው app ጋር ይመስላል እንጅ ከጀርባ ሙሉ ለሙሉ ሰርቭ የሚደረጉት በጎግል ወይም Open AI ሰርቨሮች ነው። Subscription ካቆመ የነዚህ አፕሊኬሽኖች አገልግሎትም ያቆማል። 🤷♂️ ምን ለማለት ነው... እንደ አገርም እንደ ግለሰብም "በራስ አቅም ሰራን" እያልን ራሳችንን ባናታልል ባይ ነኝ። AI based app ሰራሁ ቢባል ኖርማል ነው ያስኬዳል። AIዩን ራሱን ሰራሁት ማለት ግን አይነፋም።
видео или голосовое, без подписи
አንድ ጥበበኛ ሰዉ እንደዚህ አለኝ.... 1. አንድን ሰው ተከታትለህ ከሁለት ጊዜ በላይ አትደውልለት። ካልመለሰ ለመልስ የሚከለክለው አስፈላጊ ጉዳይ እንዳለው አስብ። 2. የተበደርከውን ገንዘብ ባለቤቱ ከመጠየቁ በፊት መልስ። ይህ ታማኝነትህንና መልካም ባህሪህን ያሳያል። ይህ ለጥላ፣ ለብዕር ወይም ለምሳ ዕቃዎችም ይሠራል። 3. አንድ ሰው ምሳ ወይም እራት ሲጋብዝህ በሜኑ ውስጥ ያለውን በጣም ውድ ምግብ አትዘዝ። 4. “ገና አላገባህም?”፣ “ልጅ የለህም?”፣ “ቤት ለምን አልገዛህም?” ወይም “መኪና ለምን አልገዛህም?” የሚሉ የሚያሳፍሩ ጥያቄዎችን አትጠይቅ። ይህ የአንተ ጉዳይ አይደለም። 5. ከኋላህ ለሚመጣ ሰው በሩን ክፈትለት። ወንድም ይሁን ሴት፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ ሌላን በአክብሮት ስለተያዝክ አትቀንስም። 6. ከጓደኛህ ጋር ታክሲ ከተሳፈራችሁ እሱ ዛሬ ከከፈለ፣ ቀጣዩን ጊዜ አንተ ለመክፈል ሞክር። 7. የተለያዩ አመለካከቶችን አክብር። ለአንተ 6 የሚመስለው ከሌላው አቅጣጫ 9 ሊሆን ይችላል። 8. ሰዎች ሲናገሩ አታቋርጣቸው። ሙሉ በሙሉ እንዲገልጹ ፍቀድላቸው። 9. አንድን ሰው ካሾፍክበት እና እሱ ደስ ካላለው፣ ወዲያውኑ አቁም። ዳግመኛም አታድርገው። 10. አንድ ሰው ሲረዳህ “አመሰግናለሁ” ማለትን አትርሳ። 11. ሰውን በአደባባይ አመስግን፤ በግል ግን አርም። 12. በሰው ክብደት ላይ አስተያየት ለመስጠት ምክንያት አይኖርም። “በጣም ጥሩ ትመስላለህ” ብቻ በል። 13. አንድ ሰው በስልኩ ፎቶ ሲያሳይህ ግራ ወይም ቀኝ አትሸብልል። ቀጣዩ ምን እንደሆነ አታውቅም። 14. የሥራ ባልደረባህ ወደ ሐኪም ቀጠሮ እንዳለው ቢነግርህ፣ “ለምን ነው?” አትበለው። “ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለህ ብቻ ጠይቅ። 15. የጽዳት ሠራተኛን እንደ CEO በተመሳሳይ አክብሮት ያዝ። 16. አንድ ሰው በቀጥታ ሲያናግርህ ስልክህን ማየት ጨዋነት አይደለም። 17. እስኪጠይቁህ ድረስ ምክር አትስጥ። 18. ከረጅም ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ስትገናኝ፣ እድሜውን ወይም ደመወዙን አትጠይቅ። 19. በቀጥታ የማይመለከትህ ከሆነ በራስህ ጉዳይ ተጠመድ። 20. በመንገድ ላይ ከሰው ጋር ስታወራ መነጽርህን አውልቅ። የአክብሮት ምልክት ነው፤ የዓይን ግንኙነትም እንደ ንግግርህ አስፈላጊ ነው። 21. በድሆች መካከል ስለ ሀብትህ አትናገር፤ እንዲሁም ልጅ በሌላቸው ፊት ስለ ልጆችህ አትመካ። 22. ጥሩ መልዕክት ካነበብክ በኋላ “ለመልዕክቱ አመሰግናለሁ” ማለትን ልማድ አድርግ። ምስጋና የሌለንን ነገር ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ነው። ❤️♥️
ሳይንስና ማክሮ-ኢኮኖሚክስ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሀብት እድገት (Rapid Wealth Accumulation) እንዴት ሊከሰት እንደሚችል የሚያስረዱባቸውን ግልጽ ንድፈ-ሀሳቦች (Theories) እና አሰራሮችን እንድህ ያስቀምጧቸዋል። አንድ ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ሀብት ሲያፈራ ስናይ "እንዴት ሊሆን ቻለ?" ብለን መጠየቃችን አይቀሬ ነው። በኢኮኖሚክስ እና በቢዝነስ ሳይንስ ውስጥ ግን ይህ ድንገተኛ ተአምር ሳይሆን፣ የተወሰኑ ሳይንሳዊና ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ህጎች ሲገጣጠሙ የሚፈጠር ተጨባጭ ውጤት ነው ይለናል። ሳይንሳዊው እና የገበያው እውነታ ምን ይላል? ዋና ዋናዎቹን 4 ነጥቦች እንያቸው፦ 1. የሪስክ እና የትርፍ ቀመር (The Risk-Return Tradeoff Theory) 📊 በፋይናንስ ሳይንስ ውስጥ ትልቅ ህግ አለ፦ "ከፍተኛ ሪስክ ባለበት ቦታ፣ ከፍተኛ ትርፍ አለ።" በአጭር ጊዜ ውስጥ ሚሊየነር የሆኑ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ የስጋት ቀጠና ውስጥ የገቡ ናቸው። 👉 ለምሳሌ የሪል እስቴት እውነታወችን አስቀድሞ መተንበይ፣ በግንባታ (Construction) ዘርፍ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መረከብ ወይም የውጭ ንግድ (Import/Export) ላይ ሙሉ ካፒታልን መድቦ መስራት። 👉 ገበያው ሲሳካላቸው ትርፉ በአንድ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚበዛ (Exponential Growth)፣ ለሚያየው ሰው በአንድ ጀምበር የመነጠቅ ያህል ይፈጠራል። 2. የመረጃ አለመመጣጠን (ብልጫ) (Information Asymmetry) 💡 ይህ በኢኮኖሚክስ ለኖቤል ሽልማት ያበቃ ታዋቂ ቲዎሪ ነው። በገበያ ውስጥ ሁሉም ሰው እኩል መረጃ የለውም። 👉 አዳዲስ የመንግስት ፖሊሲዎች ሲወጡ፣ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ለውጦች (ለምሳሌ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያዎች) ሲደረጉ፣ ይህንን መረጃ ቀድሞ ተንትኖ የተረዳ እና ወደ ተግባር የቀየረ ሰው ገበያው ሳይነቃበት ትልቅ የሀብት እድል ይፈጥራል። 👉 መረጃን ቀድሞ ማግኘት እና የገበያ ክፍተቶችን (Arbitrage Opportunities) መጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ግዙፍ ትርፍ ያስገኛል። 3. የኔትወርክ ውጤት እና ሊቨሬጅ (The Network Effects & Leverage) 🌐 በዘመናዊው የቢዝነስ ሳይንስ፣ የሰው ጉልበትን ብቻ ተጠቅሞ በፍጥነት መበልጸግ አይቻልም። ፈጣን ሀብት የሚመጣው "Leverage" (ሌሎችን ነገሮች አባዝቶ መጠቀም) ሲቻል ነው። የካፒታል ሊቨሬጅ፦ የባንክ ብድርን ወይም የባለሀብቶችን ገንዘብ (Equity) ተጠቅሞ በትልልቅ ውሎች (Deals) ላይ መስራት። የኔትወርክ ሊቨሬጅ፦ እንደ ደላላ ወይም አስተሳሳሪ (Brokerage) በመሆን፣ በገዢና በሻጭ መካከል ያሉ ትልልቅ የቢዝነስ ኮንትራቶችን በማገናኘት በአንድ ውል ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ኮሚሽን በአጭር ጊዜ ማግኘት። 4. የገበያ ሞኖፖሊ እና ልዩ መብቶች (Market Monopoly Power & Economic Rent) 👉 አንዳንድ ጊዜ ፈጣን ሀብት የሚመነጨው በአንድ የተወሰነ የንግድ ዘርፍ ላይ ካለ ልዩ መብት ወይም የገበያ የበላይነት (Monopoly/Oligopoly) ነው። 👉 በአቅርቦት እጥረት ምክንያት ፍላጎቱ እጅግ ከፍተኛ በሆነበት ገበያ ውስጥ (ለምሳሌ እንደ ስንዴ፣ ብረት፣ ስሚንቶ ወይም ነዳጅ ያሉ ስትራቴጂካዊ እቃዎች) አስመጪ ወይም አከፋፋይ መሆን የቻሉ ሰዎች፣ የዋጋ መወሰን አቅም (Pricing Power) ስለሚኖራቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊገመት የማይችል የሀብት ክምችት ይፈጥራሉ። ሳይንሳዊው እውነታ የሚያሳየን፣ ፈጣን ሀብት ከስራ ውጭ በሚመጡ ሚስጥራዊ ምክንያቶች የሚፈጠር ሳይሆን፤ መረጃን ቀድሞ የመጠቀም፣ ከፍተኛ ስጋትን የመጋፈጥ፣ ካፒታልን የማባዛት (Leverage) እና የገበያ ክፍተቶችን የመሙላት ሳይንሳዊ ውጤት መሆኑን ነው።
የኦንላይን ፈተና ልምምድ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ! የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለዋናው ፈተና ራሳችሁን እንድታዘጋጁበት፣ የኦንላይን መለማመጃ ከነገ ግንቦት 07/2018 ጠዋት 3፡00 ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ፈተናውን ለመለማመድ ወደየ ክልላችሁ ሊንክ ከገባችሁ በኋላ፣User Name በሚለው ላይ በአድሚሽን ካርዳችሁ ላይ ያለውን ቁጥር በማስገባትና Password በሚለው ላይ 1234 በማስገባት ፈተናውን መፈተን ትችላላችሁ። ልምምዱን በስልክ፣ በላፕቶፕም ሆነ በኮምፒውተር ኢንተርኔት በመጠቀም መስራት ትችላላችሁ። ልምምዱ እስከ ፈተናው ዋዜማ ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።