tgindex
East Gojjam Zone Education Departmen

East Gojjam Zone Education Departmen

Статистика

ይህ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ከትምህርት ባለድርሻዎች ጋር መረጃ የሚለዋወጥበት ቻናል ነው።

Последний пост
19 авг. 2024 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
2 560
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
 
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
8 465
20 постов
Вовлечённость
330,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 19 июл. 2023 г.10 тыс165

    https://drive.google.com/file/d/1gKavfQLWpZEHd-SPNEJ7k_W8XFU02w68/view?usp=drive_web

  • 18 июл. 2023 г.15,8 тыс57из Yohannes Sewnet

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 июл. 2023 г.15,8 тыс2752

    видео или голосовое, без подписи

  • 22 июн. 2023 г.11,7 тыс10459

    15/10/2015 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ2015/2016 ዓ.ም የወረዳ ወረዳ ዝውውር ያገኙ መምህራንን የላክን መሆኑን እያሳወቅ ተገቢ ቅሬታ ያላቸው መምህራን በዝውውር መመሪያችን መሰረት በየወረዳቸው ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ለክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና የቅ/ዝግጅት ስራ ውይይት ተካሄደ በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል የክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና ኦረንቴሽን ከአጋር አካላት ጋር ሰኔ 7/2015 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ውይይቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን የምክክሩ ዓላማ በእየጊዜው በአፈታተን ስርዓት ውስጥ የሚስተዋሉ ልዩ ልዩ ግድፈቶችን ለማረቅ እንዲያመች ነው ካሉ በኋላ በተለይም ባለፈው ዓመት የነበረው የፈተና ስርዓት በተማሪዎቻችን ላይ የተስተዋለው የስነ ምግባር እና የሞራል እንከን የዞናችንን ህዝብ ባህልና እሴት የማይመጥን ክስተት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የደብር ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ይኸይስ ሃረጉ ዶ/ር “ጊዜና ተስፋ የተማሪ ትልቁ ሃብት ነው” ጊዜው አሁን በእጁ የያዘው የሚጠቀምበት ማንም የማይነጥቀው፤ ተስፋው ደግሞ ወደፊት አሻግሮ የሚያየው እድል መሆኑን ገልጸው በ2014 የነበረው የፈተና አፈጻጸም በተፈታኞች የነበረው የስነ ልቦና መዋዠቅ ወይም መንዘቃዘቅ እንዲሁም የስነ ምግባር መዛነፍ የእውቀትና የጽንሰሃሳብ አለመዋቀር ይህም የኩረጃ ባህል ጎልቶ መታየቱ፤እንዲሁም በወሬ ወይም አሉባልታ መፈታት ትልቁ የፈተና አስተምሮት የነበረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የ21ኛው ክ/ዘመን የፈቀደውና የፈለገው እንዲሁም የሚጠይቀውን ተግባር ለመፈጸም ከተሰብሳቢው ትልቅ ቁምነገር እንደሚጠበቅ አጽንዖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የዞኑ ትምህርት መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ ደመላሽ ታደሰ የ2014 ዓ/ም የፈተና አፈጻጸም የተዘጋጀውን ሰነድ በማቅረብ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የዞናችንን ገጽታ ሊያሻሽል በሚችል መልኩ ለመስራት በስነምግባር፣ስነልቦና እና በሞራል የታጀበ ዜጋ ለመፍጠር መስራት ይገባል በማለት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

  • እንዴት አመሻችሁ ወገን? ~~~ በቀሪ ጊዜያት የትምህርት ስራዎቻችንን ውጤት ሊያመጣ በሚያስችል መልኩ ለመምራት ያመች ዘንድ በየሳምንቱ የማይቆራረጥ የሪፖርትና የመረጃ ቅብብሎሽ ማድረግ ግድ ይላል። በዚህ መሰረት ሁሌም በየሳምንቱ ሀሙስ  እስከ 10:30 ብቻ በዋትስአፕ እና በቴሌግራም በተቀመጠው ቢጋር መሠረት መረጃ መስጠት የግድ ይላል። የሪፖርት ማድረጊያ ቢጋር፤ ~~~ 1. የትም/ቤቶች መሠረተ ልማት ማሟላት ያለበት ሁኔታ፤ ~በህ/ብ ተሳትፎ የሚገነቡ ግንባታዎች፤ ~በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚገነቡ ግንባታዎች ፤ ~ትም/ቤቶችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ እየተሠሩ ያሉ ስራውች፤ 2. የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት የተከናወኑ ተግባራት፤ 3. የትም/ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተሠራ ስራ ~ትም/ቤቶችን ደረጃ 4 የማድረስ ስራችን ~ደረጃ 1ትም/ቤቶችን በሙሉ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ፤ 4. የጎልማሶች ትም/ት አፈፃፀም ~የጎልማሶች መሠረታዊ ትም/ት አሠጣጥ፤ ~የብርሃን ምዘና ምዝገባ አፈፃፀም 5. የተማሪ ማቋረጥና ማሳለስ ለመከላከል እየተሠራ ያለ ስራና የተገኘ ውጤት፤ 6. የኢንስፔክሽን ስራ ያለበት ሁኔታ፤ 7. የጥናትና ምርምር ሲንፖዚየምና የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ኢግዚቪዥን ማካሄድ፤ 8. ወረዳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ ፕሮግራም በማስኬድ ንቅናቄ የመፍጠር ስራ ያለበት ሁኔታ የሚሉትንና ሌሎችም ተግባራት ካሉ በመጨመር ሁሌም በየሳምንቱ ሀሙስ እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ ብቻ ሪፖርት እንዲደረግ ከአደራ ጋር አሳስባለሁ። ማሳሰቢያ :- የመምሪያው ቡድን መሪዎች ከተቀመጠው ተግባር አኳያ በየቡድናችሁ የሚመለከታችሁን ተግባራት ክትትል በማድረግ የተጠናከረ ሳምንታዊ ሪፖርት በቴሌግራም መላክ የማይቋረጥ ተልዕኮ ስለሆነ በቅርበት እና በትኩረት አመራር ስጡበት !! " በጋራ ጥረታችን ወደ ቀደመ ከፍታችን !!"

  • видео или голосовое, без подписи

  • CamScanner 04-28-2023 10.38.pdf

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የዘጠና ቀናት እቅድ በማስተዋወቅ ሂደት ገቢራዊ ሆነ የመጪዎቹ ዘጠና ቀናት እቅድ ለትምህርት መምሪያ ሰራተኞች ገለጻ ተደረገ፡፡ አቶ ጌታሁን ፈንቴ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የቀጣይ ሶስት ወራት እቅድ ሲያስተዋውቁ ያለፉትን ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም እርካብ በማድረግ ነው ፤ያለፉት ወራት እቅድ አፈጻጸም ለክልሉ ከፍተኛ ግብዓት ሰጥቷል ያሉት ሃላፊው ለሚቀጥሉት ዘጠና ቀናት ነጸብራቅ ሆኗል በማለት አክለዋል፡፡ ይህንንም በተጋጋለ መንፈስ መቀጠል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ እቅዱ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አስጨርሶ ማስመረቅ፤የት/ቤት ደረጃ ማሻሻል፤የተማሪ አሳላሽን በቅርበት መከታተል፤የት/ቤቶችን አቅም ማጠናከር እና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በመሳሰሉት አምስት ዋና ዋና የትኩረት አምዶች ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም እያንዳንዳቸው በጣም ሰፊ ጽንሰ ሃሳብ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሁሉንም ተግባራት መፈጸም የሚያጠነጥነው በተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ላይ ስለሆነ የተማሪዎች አሳላሽና አቋራጭን ለመቀነስ፤ የእለት ውሎን ከ95% በላይ ማድረግ ፤ በዚህ ዓመት የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የተጣለውን ግብ ለማሳካት ስራ መስራት፤ በ9 ወረዳዎች እዲስ እየተገነቡ ያሉ 11 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በተመደበው 389836477 ብር በጥራትና በፍጥነት ማስጨረስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፕሮጀክቶች በአልማ፣ በክልል ባለሃብቶችና በማችንግ ፈንድ እየተገነቡ ቢሆንም በግንባታው ከፍተኛውን ድርሻ ለያዘው አልማ የተለየ አድናቆት እንዲቸረው ምስል ፈጥረዋል፡፡

  • видео или голосовое, без подписи

  • እንዴት ናችሁ ወንድም፤እህቶቼ እንዲሁም የስራ አጋሮቼ..!? ~~ እንደሚታወቀው በዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ ለፈተና በማዘጋጀት የተሻለና ቀዳሚ ውጤት ማስመዝገብ አለብን ብለን ተግባብተን ወደ ስራ ገብተናል። በዚህ መሰረት በርካታ ወረዳዎችና አስፈታኝ ት/ቤቶች በሚገርም የስራ ተነሳሽነትና የኃላፊነት ስሜት ተግባሩን እየመሩ ይገኛሉ። በዚህም ልዩ የድጋፍ ፕሮግራም ማለትም:- - በተመረጡ መምህራን፤ - የተመረጡ የትምህርት አይነቶች፤ - ለመምህራን ማበረታቻ በጀት ተመድቦ፤ - የራሱ ፕሮግራም ወጥቶለት፤ - በማታ እና በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም ተማሪዎቻቸውን በተሟሟቀ መንገድ ለፈተና እያዘጋጁ ይገኛሉ።እጅግ እናከብራችኋለን፤ጠንክሩልን እንላለን !! በተቃራኒው ደግሞ በተለመደው መንገድ የሚጓዙና የተለመደውን  ጅምላ የቲቶሪያል በመስጠት ተማሪዎችን እያገዝን ነው በሚል ራሳቸውን፤ህዝባቸውን እንዲሁም ተማሪዎቻቸውን በሚያታልል መንገድ ተግባር የሚፈጽሙ ጥቂት ወረዳዎችና ት/ቤቶች መኖራቸውን ታዝበናል። ነገርዮሹ ሁሉ "ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥስ" እንዳይሆንብን የተሰጠውን ዞናዊ አቅጣጫና ተልዕኮ ለምን እናንጠባጥባለን? እኩል መፈጸምስ ለምን አቃተን? ሌሎቹ የሰሩትን ስራ እኛ ለምን አልሰራንም? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሳችን በመጠየቅ ጉድለቶችን ፈጥነን ማረም ግድ ይለናል። የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችንን በአግባቡ አዘጋጅተን የማሳለፍ ያለማሳለፍ ጉዳይ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ ተራ አጀንዳ ሳይሆን የህዝባችንን ሞራል የማስጠበቅ፤ያለማስጠበቅ እንዲሁም የክብር ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ አንስተን መክረንበታል። ስለሆነም "ልዩ ድጋፍ ምንድነው?" የሚለውን ነገር በት/ቤቱ ከሚገኙ መምህራንና ሰራተኞች ጋር በአግባቡ መክሮ ተገቢውን አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደስራ መግባት ግድ ይለናል። ቀጣይ ሳምንት ጀምረንም 12ኛ ክፍል አስፈታኝ የሆኑ ት/ቤቶችን ምልከታ እናደርጋለን።በምልከታችንም ለተማሪዎች እየተደረገ ያለውን የልዩ ድጋፍ ፕሮግራም እንጎበኛለን(በተለይ የማታ እና የቅዳሜና እሁድ ትምህርቱን) አሰጣጥ በአግባቡ እንፈትሻለን። & የተማሪዎቹን የDRS ምዝገባ በጣም በጥንቃቄ ሰርተን በአጭር ቀን እናጠናቅ!! ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችንም የሚደረገው ልዩ ድጋፍ በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናክሮ እየተሰጠ መሆኑን ወረዳዎች ቸክ አድርጉ፤ከተማሪዎች የዕለት ውሎ መቀነስ ጀምሮ መታረም ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ ታዝበናል። በጥቅሉ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በአይነቱ ልዩ የሆነ የቅድመ-ዝግጅት ስራ ሰርተን አስደማሚ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሌም ሳንዘነጋ እንስራ።አጠቃላይ ሃገራዊና ክልላዊ ውድድሩ በእጅጉ የከረረ ነው፤በውድድር መሸነፍ ደግሞ ምን ያህል አንገት እንደሚያስደፋ እናውቃለን፤አንገታችንን ቀና ለማድረግ ደግሞ ዛሬውኑ የሚሰጠንን አቅጣጫ ተቀብለን ሳናንጠባጥብ እንፈጽም፤ስኬት ማስመዝገብ ደግሞ እንችላለን !! " በጋራ ጥረታችን ወደ ቀደመ ከፍታችን !!"

East Gojjam Zone Education Departmen — tgindex