Tamene Mengste Wube
Статистикаአገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም ኢትዮጵያዊ ሆነን—የሚያግባባ አናጣም! ዕወቂው ዐለሜ...! ኢትዮጵያዊ መሆን—የውርስ እንቁጣጣ በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ... |ታመነ መንግሥቴ ውቤ—አባ ወራው| ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል እና ጥበብ እናወጋለን! ጀበናዋ ተጥዳለች! ፍንጃሎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም! ክሕሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ። ትውልድ❤
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 35
- Всего постов
- 43
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 91
- 1/48двое суток
- 104
- 1/72трое суток
- 112
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📍 <<አገራችን የባሕር በሮቿን ከማጣቷ የተነሳ ደርሶባት የነበረውን ስቃይና ችግር ከዛሬውም ሆነ ከወደፊቱ ትውልድ አንድም ኢትዮጵያዊ ሊረሳው አይችልም ።>> ቀ.ኃ.ሥ፣ ሕዳር 3፣ 1954 ዓ.ም አሰብ
መቼም የዋድላ ደላንታው ልጅ ከሽመልስ አብዲሳ የበለጠ ጥላቻ አልዘራም። «እንከባበር» ማለትን እንደ ጥላቻ ተቆጠርከው ሰብሉን በሚሊዮኖች በቀል ተባዝቶ ታጭደዋለህ። «ትንሽ ከፊት ሲሆን አገር ያሳንሳል»—እንዲል አማራ🥰 ንግግሩ ይሄ https://www.facebook.com/share/r/1Eyj2LsM6h/ ነው።ከዐውዱ ውጭ ተጠቅመው ወንድማችንን 'እንኳንም ታሰረ' እያሉ ያውለበልቡታል። አዎ ለገዳዮችህ የበዛ ጥላቻ ከሌለህ ግፋቸውን አትመክትም። ባይዜ ሕዝብ የሚጠላ ፖለቲከኛ ደሞ ያስጠላኛል።ለምን የወለጋ ኦሮሞ ይጠላል? አጋቹን ግን ተባብረን እንጠላለን። «ይሄው ነው!»
ቅድ ለታ— ጡዘት እሚባል ጭፈራ ቤት ገብቼ ነበር።ሁለት ሃስትል ጠጣሁ።እንዲህ ያለ ገላ በቅርበት ዐየሁ። በቃ😂
«እናትዋ»🙁
«ጮቄ አለምአቀፍ የልብስ ብራንድ እንዲሆን በቃ እግዚአብሔር ገልጦልን እየሰራን ነው ። በቃ ይኸ ሁሉ የእርሱ ስራ ነው የኔ አይደለም ። እግዚአብሔር በእኔ ላይ አድሮ መቸ ነው ስራ የሚሰራ ብላችሁ ፀልዩ ። እሱ ሲፈቅድ ሁሉም ነገር እንደ ጮቄ ተራራ ወደ ከፍታ ይሄዳል ። ያለሱ ፈቃድ ውለን ማደርም አይቻልም ። ሁሌም ለሚደረግላችሁ ነገር አመስግኑ 🙏❤🙏❤🙏❤»
«አለን፤አለን»😂 ምን አለ ያረጋል ነኝ🥰
ይገምቱ፤ይሸለሙ🥰
«የኢትዮጵያ ባል የኢየሩሳሌም እጮኛ»—ይል ነበር ካሳ። እሰቡት መላ ኢትዮጵያን እኮ አላገባትም።ሙሉ ድንግልናዋን አልወሰደም🙁 እኔ አደለሁም ይሄን እምል🤫 ጂጂ ናት። «ያገቡሻል ይፈቱሻል አሁንም ድንግል ነሽ!» ብላ አለች። ካሳ 'ድንግል' ኢትዮጵያን በደንብ ሳ'ዳ ኢየሩሳሌምን ሊያገባ ጫፍ እንደደረሰ ይናገር ነበር አሉ። ምናብ...👏 ልጁም የእኛ፣ዓላማው(ባንዲራው)ም የእኛ፣ከተማዋም እጮኛችን ጄሩሳሌም ናት—አሉ። እኔ ላግባት እንዴ🤔?
«ጨሰ አቧራው ጨሰ ጨሰ አቧራው ጨሰ ጨሰ አቧራው ጨሰ» 😂
«አሰብ ጠረፉ ላይ ካልተሰራ ቤቴ ፣ ወንድም አልወለደች መካን ናት እናቴ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹» ገገአ
ምን ትላላችሁ🥰?
«ጀግናው በላይ በላይ ኮስትር አሰኘኝ!»
ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ናት ብለን ካመንን ወይም ደግሞ ኢትዮጵያውያን አጠቃላይ ብሔር ብሔረሰቦች በኢትዮጵያ አንድነት አምነው፣ አሁን ባለው ሕገ-መንግሥት ተስማምተው አብረው ለመቀጠል የሚወስኑ ከሆነ፤ አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ናት። መሰረታዊ ነገሩ ይህ ነው። ሕገ-መንግሥቱም በዋናነት የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሆኗን ነው፤ ልክ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ አማርኛ እንደሆነው ሁሉ:: ነገር ግን በዚህ ሰሞን እንደሚሰማው፣ አንዳንድ ክልሎች «አዲስ አበባ የኛ ሆና በሕገ-መንግሥት ውስጥ ትጠቀስልን» እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ ሁሉም ክልሎች ጥያቄ ማንሳት ይችላሉ። በተለይ ደግሞ ወደ ታሪክ ከሄድን የዚች ከተማ መሥራቾች የአማራ ነገሥታት ተብለው መከራቸውን የሚያዩት ናቸው። ሸገር የነ አጼ ልብነ ድንግል፣ የነ አጼ ዳዊት ከተማ ናት። ወደ ቅርቡ ከመጣን ደግሞ አሁን ያለችዋን ቅርጿን የሰጧት እቴጌ ጣይቱና አጼ ምኒልክ ናቸው። እነዚህ ነገሥታት ከአማራ ጋር ስለተገናኙ ወይም የአማራ ነገሥታት በመባላቸው ሕዝቡ እስካሁን ድረስ መከራ እና ሰቆቃ የሚያይባቸው ሰዎች ናቸው። ከተማዋ «የማን ናት?» ወደሚል ንትርክ ከወረደች እና ከኢትዮጵያ ዋና ከተማነቷ ዝቅ ብላ በብሔር መመዘን ከተጀመረ በዋናነት የዚች ከተማ ባለቤት አማራ ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም አዲስ አበባን የከበበው የሸዋ አካባቢ ዞሮ ዞሮ ከአማራ ጋር የተገናኘ ጥልቅ የታሪክ ቁርኝት አለው። አሁን ባለው የብሔር ስብጥር እና የፖለቲካ መስፈርት ከተሄደ ከተማዋ የአማራ ናት እያልኩህ ነው። ስለዚህ ይህ የብሔር ጥያቄና ንትርክ ቢቀርብን ይሻላል። በአንድነት ብንቀጥል ይበጃል። አዲስ አበባ «ኢትዮጵያ» በሚለው ታላቅ አስተሳሰብ ጥላ ሥር የመላ ኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ሆና ብትቀጥል እወዳለሁ።
የሙሉ ጊዜ ሥፖንሰራችን🥰
ትናንት ባጋራሁት የ ዘካባ ምሥል እና ጽሑፍ አስተያዬት መሥጫ ሥር ብሎም በግል “ከአገር ወጣህ ወይ? ፤ ኡጋንዳ ገባህ ወይ? ጮቄ ገባህ ወይ?» እያላችሁ ጠይቃችሁኛል። መልሴን እነሆ🤝 እኔ ጋዜጠኛ ነኝ።የትም፣መቼም፣በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆኘ የሰዎችን አሳብ ለማንጸባረቅ ነው—ሞያውን የተማርኩት። ሥለሆነም በሚሊዮኖች ሕይወት ላይ ሥለሚወስነው ዘመነ ካሴ ባውቄ የተባለ ሰው አሳቦች ለመፃፍ የግድ አገሬን መልቀቅ፣ጫካ መግባት ወይ ሰማይ መውጣት የለብኝም። ሶ...! በአገሬ መዲና ነኝ። እንዲህ ያለ ነገር ሲደጋገምብኝ ለአሳብ ነፃነቱ ሕይወቱን የገበራት የኦሮሞይቱ ልጅ አጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ ተናግሯታል የምትባል አሳብ እየተደጋገመች ታቃጭልብኛለች። ሐጩ'ኮ ምን አለ🥰? ፕሮፌሠር መረራ ጉዲና በቄሮ አመጽ ጊዜ አግኝተውት ነው አሉ።ከፖለቲከኞች በላይ ለኦሮሞ ወጣቶች ትግል ድምጽ እንደሆነ ነግረውት በመጨረሻ «ግን ተጠንቀቅ—ኦፌጊ» አሉት። አጫሉም መለሰ🙁 «ደሞ ለመዝፈን ጫካ መግባት አለብኝ እንዴ?» ሀጫሉ እንደተናገረው ከአገሩ ሳይወጣ፤ጫካ ሳይገባ ማለት ያለበትን ብሎ ግፈኞች ሲተኩሱበት ጥይቱን ተቀብሎ በአሳብ አሸንፏቸው አርፏል። እኔም የሱ ወንድም«ደሞ ለመፃፍ ኡጋንዳ መግባት አለብኝ እንዴ?»🙁 እያልኩህ ነው። ሕግ አክብሬ እሠራለሁ።ተዚያ ወዲያ ለሚመጣው ሁሉ አለሁ። «ዘጠኝ ሞት መጣ ቢለው 'አንዱን ግባ በለው'» እንዳለው አማራ👏
እንኳን ለዚህ በቃህ ታላቅ ወንድማችን🥰
«አሙን አሉ አሙን አሉ ተዋቸው ይሙን ቢፈሩን አደለ ቢጠረጥሩን!» አማራ🥰
ከዚህ ሰው አሳቦች አንድ ነገር ይገዛኛል።እሱም ፋኖ ነጋሽ መሆን አለበት የሚለው ነው። መንገሥ ማለት ቀኃሥን መሆን አደለም።ገበሬ፣የፋብሪካ ሠራተኛ፣የታክሲ ሹፌር፣ወታደር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሜዳ ላይ በአግባቡ ተወዳድሮ መሪ መሆን ይችላል ማለቱ ነው። ገና ቦሌ ሳለሁ 2016 ዓመተ ምኅረት ላይ ሲናገረው ሰምቸው ምችት ያለኝ አሳቡ ነው። ገበሬን ሥልጣንህ አደጋ ውስጥ ሲወድቅ «ፋኖ ተሰማራ» ብለህ አስገድለኸው ልዡን ጽንፈኛ ብለህ ከሥልጣን ዕድል መከልከል ኢ ፍትሐዊነት ነው። ለኢትዮጵያ የምመኝላት ዴሞክራሲ ሁሉንም ሰው የአገር መሪ መሆን እንደሚችል እንዲሰማው የሚያደርግ እድል ነው። እኛን የአገው ምድር ገበሬዎችን ልጆች 'ፍትሕ' ባልን 'ጽንፈኞች' ሥትሉን የቀማችሁን ይሄን ዕድል ነው። እናም ፋኖ አገር የመምራት መብት እንዳለው፣አራሽ፣ቀዳሽ፣ተኳሽ ብቻ እንዳልሆነ +ነጋሽ መባል እንዳለበት የተስማማን ጊዜ ሰላም የሚወርድ ይመሥለኛል። በዚህ ከተስማማችሁ ላደራድራችሁ—የምር😂 ሽማግሌ አትናቁ፤ ተኦባሳንጆ አናንስም🥰
«ልጆች አሉኝ፣ በዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ። የእኔ እኩዮች አብዛኞቹ በትግል ስም ተሰውተዋል። የታሠሩም አሉ። በመውለዴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ምናልባትም ወደፖለቲካው ዓለም ዘልቄ ከገባሁ መውለዴ ይበልጥ ደስተኛ ያደርገኛል ብዬ አስባለሁ፣ ምክንያቱም አገራችን ውስጥ ወጣት ፖለቲከኛ ስትሆን ማንኮ’ላሸት የተለመደ የመንግስት ተግባር ነው። ልጅ ለመውለድ ብቻ ባይሆን እንኳን ወ’ሲብ ጸዴ ነገር ነው። ከእኩያህ ጋር ይጥማል፣ ሌላ ለየት ያለ ዓለም ነው። የወ’ሲብ አድማ የፌሚኒስቶችን አሳብ ደገምኽምብኝ! ትውልዱን አታስንፉት፣ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ስትወልድ የነበረው ሞልቶላት እና ደልቷት አልነበረም። ትከሉ እያልኩህ ነው አለቃ፣ በመትከል እናንሰራራ¡🤣 ትቀልዳለህ እንዴ ባሻ፣ ወ’ሲብን ያህል ነገር አድማ ስትል ትንሽ እፈር እንጂ በእውነት😂» ባለፈ ለማግባት አትሯሯጥ ላልኩበት ጡፌ የተሰጠኝ የመልስ ምት😭
በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል ተከሰሰው ከ3 ዓመት በላይ በእስር ላይ በሚገኙ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ የመንግሥት የይቅርታ ሰነድ መቅረቡ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አማካኝነት የቀረበው ይህ የይቅርታ ሰነድ፤ ተከሳሾቹ ለተፈጠረው ቀውስ እና ውድመት ኃላፊነት እንዲወስዱ፣ የፖለቲካ አቋማቸውን ወንጀል አድርገው እንዲቀበሉ እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን እንዲያወግዙ የሚጠይቁ ቅድመ ሁኔታዎችን ያካተተ ነው። አብዛኞቹ ተከሳሾች ሰነዱን የፈረሙ ቢሆንም፣ 30 የሚሆኑ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ግን "ያልፈጸምነውን ወንጀል አምነን አንፈርምም" በማለት ለመፈረም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። እነዚህ ተከሳሾች መንግሥት "ወንጀለኛ ነን ብላችሁ እመኑ" በሚል ቅድመ ሁኔታ ይቅርታ ከሚል፣ ክሱን በፖለቲካዊ ውሳኔ አቋርጦ እንዲፈታቸው ጠይቀዋል። የሕግ ባለሙያዎች በበኩላቸው በሕጉ መሠረት ይቅርታ መጠየቅም ሆነ መስጠት የሚቻለው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት በተወሰነባቸው ላይ ብቻ በመሆኑ፣ ገና በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ያሉ ተከሳሾችን ከእስር ለመልቀቅ ትክክለኛው ህጋዊ መንገድ "ክስ ማቋረጥ" እንደሆነ ያስረዳሉ። #አማራ #ፍትሕ #ጋዜጠኞች #ፖለቲከኞች #የይቅርታ_ጥያቄ #ኢትዮጵያ