tgindex
Asham TV | አሻም ቲቪ

Asham TV | አሻም ቲቪ

Статистика

እንኳን ወደ ይፋዊው የአሻም ቲቪ የቴሌግራም ገጽ በደህና መጡ:: የተለያዩ ትኩስ መረጃዎች እና ታማኝ ዜናዎችን ለማግኝት ገጻችንን ይከታተሉ ። አሻም ለሁላችን !

Последний пост
10 дек.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
19 532
−5 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 688
17 постов
Вовлечённость
34,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 дек.12,3 тыс20

    🔵ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ ቆይታለች፡፡ ይሁን እንጂ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋር አብራችሁ ለዘለቃችሁ ለውድ ተመልካቶቻችንና ተከታታዮቻችን ልባዊ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡ አሻም ለሁላችን!

  • 9 дек.9 2021

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 дек.8 80813

    🟡ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን፡- 🏷ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ  መግለጫ ድርጅታችን አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል በዜና አቅራቢነት እንዲሁም በቅርቡ በጣቢያችን ‹‹ሶፊ ሾው›› ሲል በሰየመው የመዝናኛ ዝግጅቱ  በአሻም የቴሌቪዥን እና በዩትዩብ ገፅ እያዘጋጀ ሲያቀርብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይህ በሆነበት ከትላንት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ስለ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር ሲፈጽም የሚያሣይ መረጃ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ሲዘዋወር ተመልክተናል፡፡ አሻም ይህንኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ጋዜጠኛው የተሰራጨውን መረጃ ተከትላ ስለ ተሰራጨበት መረጃ ሶፎኒያስን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቃለች፡፡ በዚህም ሶፎኒያስ <<አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ለማከም ፀበል ገብቻለሁ>> የሚል አጭር ምላሽ ከመስጠት ውጭ ተጨማሪ ያለው ነገር የለም። ስለሆነም አሻም ሚድያ ትሬዲንግ አ.ማ. የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ እንዲሁም የህብረተሰቡን እሴት እና ሃይማኖት ያከበረ የምትመራበት ኤዲቶሪያል አላት፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጠኛው የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እሴት፣ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖት የሚጻረር ተግባር ተሰራጭቶበት በመመልከቷ እጅጉን እያዘነች ድርጊቱ የሚዲያ ተቋሟን የማይወክል ይልቁንም በጽኑ የምታወግዘው መሆኑን ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሻም ሚዲያ ትሬዲን አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በፈጸመው ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት ጭምር የነበራትን የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማቋረጡዋን ለመግለጽ ትወዳለች፡፡ አሻም ለሁላችን!

  • 7 дек.5 8305

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 дек.5 8995

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 дек.4 2245

    ህዳር 28/2018 የአሻም የምሽት ዜና ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅ በተለያዩ መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 1628 ተማሪዎች አስመረቀ። ኮሌጁ በድረ ምረቃ፣ በቅድመ ምረቃ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንድሁም በሰርተፍኬት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ ህዳር 27/2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል አስመርቋል። ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅ ለ12ኛ ዙር ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ ከሲቪል አቪየሺን ባለስልጣን ባገኘው እውቅና መሰረት፣ በአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሺያን ያስተማራቸው የመጀመሪያ ተመራቂዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል። በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ኢንተርናሽናል ትሬድ እና ኢኮኖሚክስ እና ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (130 እጩ ተመራቂዎችን) ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም፤ አቬሽን ማኔጅመንት፣አካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ሆቴል ማኔጅመንት እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት (93 እጩ ተመራቂዎችን) በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በደረጃ IV በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ፍሮንት ኦፊስ፣ ሀርድዌርና ኔትወርክ ሰርቪስ፣ማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት ፣ነርሲንግ እና ፋርማሲ 1035 ሰልጣኞችን ማስመረቁ ተገልጿል። በተጨማሪም በሠርተፍኬት ስልጠና በኤርክራፍትና ሜንቴናንስ ቴክኒሻን (ፓወር ፕላንት፣ኤር ፍሬም፣አቪኦኒክስ)፣ ኤርላይን ካቢን ክሪው፣ ፍላይት ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና በቲኬቲንግና ሪዘርቬሽን ያሰለጠናቸውን 370 ሰልጣኞችን በጠቅላላ 1628 እጩ ተመራቂዎችን ተመርቀዋል ተብሏል። በቀጣይ ዘርፉን በማስፋት የነርሲንግ እና ፋርማሲ ፕሮግራሞች በኮሌጁ ለመስጠት መታቀዱ ተጠቁሟል። በብርሀን እሸቴ አሻም ለሁላችን !

  • 4 дек.6 0004

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 дек.6 0544

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 дек.4 1754

    የህዳር 25/2018 የአሻም የምሽት ዜና 🏷የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከሰክሰስ ፕላስ ጋር በመሆን ለአካል ጉዳተኞች 50 ዊልቸር አስረከበ። ሰክሰስ ፕላስ ከከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር በከተማዋ ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ በአለም ለ34ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአካል ጉዳተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል። በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የድርጅቱ አመራሮች ተገኝተዋል። የሰክሰስ ፕላስ ድጋፍ፣ አካል ጉዳተኞች በማህበራዊ ህይወታቸው በንቃት እንዲሳተፉ የሚያግዝ መህኑን የኦሮሚያ ክልል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሶ ቢቂላ ገልፀዋል። የሰክሰስ ፕላስ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍሬው መንገሻ በበኩላቸው፣ ይህ የዊልቸር ድጋፍ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም በየሦስት ወሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መርሃ ግብር አካል እንደሆነ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደምም ድርጅቱ በአዲስ አበባ እና በትግራይ ክልል ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ተመሳሳይ ድጋፎችን ማድረጉ ይታወሳል። ሰክሰስ ፕላስ የበጎ አድራጎት ድርጅት አካል ጉዳተኞች በተሟላ ሁኔታ ለህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን የበጎ አድራጎት ተግባር አበረታች መሆኑ ተገልጿል። በብርሀን እሸቴ አሻም ለሁላችን !

  • 3 дек.4 8812

    видео или голосовое, без подписи

  • 3 дек.4 6872

    የህዳር 24/2018 የአሻም የምሽት ዜና የዲፕሎሚቲክ ማህበረሰቡ ላይ ትኩረት ያደረገው ዲ ኔክስት ኢቭ ዲፕሎማት (De-Next-Ev Diplomat) ባዛር ተካሄደ። ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቭንትስ ከዲሊኦፖል ሆቴል እና ከኔክስት ፋሽን ዲዛይን ጋር በጋራ በመሆን የዲፕሎማቲክ ባዛር አካሂዷል። የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "ዲ ኔክስት ኢቭ የዲፕሎማት ባዛር"   በዲሊኦፖል ሆቴል ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ የዲፕሎማት ባዛር የተለያዩ የቆዳ ምርቶች ፣ ከከበሩ ማዕድን የተሰሩ ጌጣጌጦች ፣ የሀገር ባህል ልብሶች ፣ ከተፈጥሮ እፅዋት የተዘጋጁ የፀጉር ቅባቶችና የተለያዩ የእጅ ስራዎች ቀርበውበታል። ባዛሩን ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኢቭንት ከዲሊኦፖል ሆቴል እና ከኔክስት ፋሽን ዲዛይን ጋር በጋራ በመሆን እንዳዘጋጁት ተነግሯል። ባዛሩ ለሕዝብ አገልግሎት የተዘጋጀ በመሆኑ መግቢያ በነጻ መሆኑን ተነግሯል። በዚህ ባዛር ከተዘጋጁ መርሃግብሮች መካከል በኔክስት ፋሽን ዲዛይን የተዘጋጀ ዓመታዊ "አፋ አዋርድ" ይካሄዳል። ይህን ዝግጅት በዓመት ሦስት ጊዜ ለማካሄድ ዝግጅት እንዳለቀ የተገለፀ ሲሆን በአዲስ ዓመት፣ ገና እና ፋሲካ ሰሞንን ምክንያት በማድረግ በየጊዜው ይካሄዳል ተብሏል። የአዋርዱ አዘጋጅ ኔክስት ፋሽንና ዲዛይን ኮሌጅ፤ ለድምፃዊ ሀመልማል አባተ፣ መቅደስ ፀጋዬ ፣ ዮሀንስ ታጠቅ- ከጆኒ ቪዲዮ እና ሌሎችንም ሸልሟል፡፡ ኮሌጁ በተለያየ ጊዜ በሚያዘጋጀው የAFFA አዋርድ ለኢትዮዽያ ፋሽን አስተዋፅኦ ያደረጉ ታላላቅ ሰዎችን የሚሸልምበት ፕሮግራም ላይ ነው እውቅናውን የሰጠው። በብርሀን እሸቴ አሻም ለሁላችን !

  • 3 дек.8 1142

    видео или голосовое, без подписи

  • 3 дек.8 1332

    видео или голосовое, без подписи

  • 3 дек.3 9092

    ህዳር 24/2018 የአሻም የምሽት ዜና 🏷ያያ ዋሌት ከጤና ሚኒስቴር ጋር የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ፈፀመ። ያያ የክፍያ ስርዓት አክሲዮን ማህበር የጤና ክፍያዎችን በዲጂታል ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት ይፋ አድርገዋል። ስምምነቱ የተፈፀመው በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ እና የያያ ዋሌት ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮሃንስ በልሁ አማካኝነት ነው። ሁለቱ ተቋማት በጤና ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት ይፋ ያደረጉት አዲሱ ስምምነት ሆስፒታሎች እና ፋርማሲዎች ሁሉን አቀፍ በሆነ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት እንዲታገዙ በማድረግ የጤና አገልግሎትን ቀልጠፋ፣ ዘመናዊ እና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። ስምምነቱ በጤና ተቋማት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ የሚከናወኑ አሰራሮችን በመቀየር አስተዳደራዊ ጫናዎችን ለመቀነስ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። ያያ ዋሌት ተጠቃሚዎች በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ክፍያዎችን ለመፈፀም ያግዛል የተባለ ሲሆን፣ በሁሉም አማራጮች ውህደትን መፍጠር ያስችላል ተብሏል። ተቋሙ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጠው እና በባንኩ የሚተዳደር የዲጂታል መሳሪያ አውጪ ተቋም ነው። በብርሀን እሸቴ አሻም ለሁላችን !

  • Live stream finished (3 minutes)

  • Live stream started

  • ህዳር 16/2018 የአሻም የምሽት ዜና 🏷 ኢትዮጵያ በሀገራዊ  ሪፎርሙ ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡   🏷የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ከብሔራዊ ዲጂታል ሥነ-ምህዳር ጋር ለማዋሃድ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡ 🏷በኢትዮጵያ የፋሽን ዲዛይን ተቀባይነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ፡፡   🏷ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡ 🏷ታንዛኒያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት ምክንያት የነጻነት ቀን እንዳይከበር ሰረዘች፡፡ 🏷የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ቻድ እና ዮርዳኖስ 70 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ዕርዳታን አፀደቀ፡፡ 📶Live On Asham Tv Social Media 🔵 Facebook & 🔴 Youtube ቀጥታ ስርጭት በፊስ ቡክ እና በዩትዩብ ገጾቻችን ይከታተሉ https://www.youtube.com/ https://web.facebook.com/AshamMedia

  • Live stream finished (16 minutes)

  • Live stream started

  • ህዳር 15/2018 የአሻም የምሽት ዜና 🏷 ኢትዮጵያ በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ወቅት አመርቂ የሚባል የውይይት ጊዜ ማሳለፏ ተመላከተ፡፡ 🏷ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚን አስመልክቶ ስኬታማ ውይይት መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ተገለፀ፡፡ 🏷ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ከሚዲያና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተፈራረመ። 🏷ሆስፒታሉ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከህዳር 14 እስከ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡ 🏷እስራኤል በቤይሩት የሂዝቦላ ጦር መሪን ገደለች። 🏷በፓኪስታን የመከላከያ መስሪያ ቤት ውስጥ በአጥፍቶ ጠፊዎች 3 ሰዎች ሞቱ 📶Live On Asham Tv Social Media 🔵 Facebook & 🔴 Youtube ቀጥታ ስርጭት በፊስ ቡክ እና በዩትዩብ ገጾቻችን ይከታተሉ https://www.youtube.com/ https://web.facebook.com/AshamMedia

Asham TV | አሻም ቲቪ — tgindex