tgindex
Ethio Fm 107.8

Ethio Fm 107.8

Статистика

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
48
Всего постов
59
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
18 505
+7 за 3 дн.
Сутки
+3
+0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 671
40 постов
Вовлечённость
9,0%
к подписчикам
Постов в день
6,9
всего 59
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
по 11 постам
1/24сутки в ленте
1 151
1/48двое суток
1 319
1/72трое суток
1 422

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 46342

    የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጥብቅ አሳሰበ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አንድ ወር መሙላቱን አስመልከቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መልዕክት ማምሻውን አስተላልፏል ። ኮሚሽኑ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ ላለፉት ሰላሳ ቀናት የተካሄደው የምክክር ሂደት ስኬታማና አዲስ የምክክር ባህል እንዲዳብር መሰረት የጣለ እንደነበር ገልጿል። ይሁን እንጂ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረና ተፈጥሯዊ የሆኑ አለመግባባቶች ማጋጠማቸውን ጠቁሟል። በተለይም ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በስም ያልጠቀሳቸው ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላትና አንዳንዶች ሲል የገለጻቸው የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው ብሏል። ስለሆነም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑና በስፍራው ከሚገኙ ህጋዊ መገናኛ ብዙኃን ከሚወጡ መረጃዎች ውጪ ያሉ ሀሰተኛወሬዎችንእንዳይከታተል፣የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል። በመጨረሻም ኮሚሽኑ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት በሚፈፅሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህ ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

  • 14 авг.2 074414

    ግምታዊ የግብር አሰባሰብ ሂደት ከልክ በላይ ግብር ሊያስከፍል እንደሚችል ተጠቆመ በግምታዊ ግብር አጣጣል ሂደት የግብር ከፋዮች ከልክ በላይ ግብር ሊጣልባቸው እንደሚችል የሕግ ባለሙያዉ አቶ ዮሴፍ ወርቀልኡል ገልጸዋል። አቶ ዮሴፍ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በግምታዊ ግብር አጣጣል ሂደት የግብር ከፋዩ የመስሪያ ቦታ፣ አካባቢው እና የቤቱ ስፋት ታይቶ ግብር የሚጣልበት ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ የሰነድም ሆነ ሌሎች ማስረጃዎች ባለመኖራቸው፤ ግብር ከፋዮች ከልክ በላይ የሆነ ግብር ሊጣልባቸው እንደሚችልም አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማግኘት ያለበትን ገቢ ላያገኝ እንደሚችል አንስተዋል። ይሁን እንጂ የግብር ከፋዩን ትክክለኛ ገቢ የሚያሳይ የሂሳብ መዝገብ ወይም ሌላ ተጨባጭ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ ግምት ለስህተት ተጋላጭ በመሆኑ ከልክ በላይ ግብር ሊጣል እንደሚችል አቶ ዮሴፍ ገልጸዋል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤የቀን ገቢ ግምት በዘፈቀደ የሚወሰን እንዳልሆነ እና እንደ እርሳቸው ገለጻ የንግዱ ዘርፍ፣ የንግድ ቦታው የሚገኝበት አካባቢ፣የቦታው ስፋት፣ በአካባቢው በተመሳሳይ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች እና የሚይዟቸው ዕቃዎች ዋጋ ታይተው ግምቱ እንደሚሰላ አንስተዋል። አቶ ሰውነት እንደገለጹት፤የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ሽያጫቸው ከ2 ሚሊየን ብር በታች ሲሆን፤እነዚህም ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ እንደማይገደዱም እና የቀን ገቢ ግምት እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል። ይህም በተጨማሪ የገበያ ዋጋ ጥናት ተካሂዶ እንደሚፈጸም ገልጸዋል። አቶ ሰውነት አክለውም በተመሳሳይ የንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የተለያየ የቀን ገቢ ግምት ሊደረግላቸው እንደሚችልም እና ይህም ከንግድ ቦታው አካባቢ እና ከቦታው ስፋት አንጻር እንደሚወሰን አብራርተዋል። በግምታዊ ግብር አሰባሰብ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ያለው ግብር ከፋይ በተቀመጠው የይግባኝ አቀራረብ ሂደት መሠረት ቅሬታውን ማቅረብ እንደሚችል አቶ ሰውነት ገልጸዋል። በመሆኑም የግምታዊ ግብር አሰባሰብ ሂደቱ በተጨባጭ መረጃና ጥናት እንዲደገፍ፣ ግብር ከፋዮችም የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ትክክለኛ ገቢያቸውን ማሳየት የሂደቱን ፍትሐዊነት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል። ሰላማዊት ዲታ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

  • 14 авг.1 7915
  • 14 авг.1 5953

    በከባድ ዝናብ አማካኝነት ጃፓን ውስጥ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ተባለ በምስራቅ ጃፓን ቺባ ግዛት ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን፤ አምስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የጃፓን ባለሥልጣናት ‹‹ታይቶ የማይታወቅ›› ሲሉ የገለጹት ዝናብ፤ ከ20 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቀንስ፣ 7 ሺህ ተጓዦች ደግሞ በቶኪዮ ናሪታ አየር ማረፊያ በአንድ ሌሊት በረራቸው እንዲዘገይ አድርጓል። ይህ የጎርፍ አደጋ የተከሰተው በዚህ ሳምንት በጃፓን እና በአጎራባች አገሮች ውስጥ ተከታታይ አውሎ ነፋሶች ከተከሰቱ በኋላ ነው። የጃፓን የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ እንደገለጸው፤የቅርብ ጊዜውን የጎርፍ አደጋ ያመጣው ወደ አገሪቱ ምሥራቅ የሚፈሰው ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር ሲሆን፤ይህም ከላይ ካለው ቀዝቃዛ አየር ጋር ተዳምሮ የከባቢ አየር ሁኔታን እጅግ ያልተረጋጋ ያደርገዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። የአብስራ ተስፋሁን ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

  • 14 авг.1 74022

    በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወነው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም 1.3 ሚሊዮን ገደማ ህጻናትን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ   በፕሮግራሙ አምስት አንኳር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ የተሰራ ሲሆን፣ ከ5 ሺህ በላይ የሰለጠኑ ባለሙያዎች የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም ለትውልድ ግንባታ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ 1 ሺህ 155 የህጻናት ማቆያዎች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።   ድጋፍ ለሚሹ አያሌ እናቶችና ህጻናት ተከታታይ የአልሚ ምግብና የህክምና ክትትል ከመደረጉም በላይ፣ ህጻናቱ በጨዋታ መልክ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ።   ይህ ፕሮግራም ለወላጆች እፎይታን፣ ለህጻናት ደግሞ ብሩህ ተስፋን ማብሰራቸው በጥናት መረጋገጡ ተጠቅሷል።     ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

  • 14 авг.1 7723

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 7783

    የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦችን የሚያጣጥም የ120 አባላት ስብስብ ማቋቋሙን አስታወቀ   የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከስምንቱ የአጀንዳ ቡድኖች የተሰበሰቡ ምክረ ሃሳቦችን እርስ በእርስ የሚጋጩ ነገሮች እንዳይኖሯቸው የማጣጣም እና ድግግሞሾችን ወደ አንድ የማምጣት ሀላፊነት የተጣለበት የ120 አባላት ስብስብ ማቋቋሙን ገለጸ።   የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ እንደተናገሩት፣ ይህ ስብስብ ኮሚሽኑ አጠቃሎ ለሚያቀርበው የምክረ ሃሳብ ሰነድ ወጥነት እንዲኖረው የሚያስችል ስራ ይሰራል።   ለእያንዳንዱ ስምንት አጀንዳ ቡድን 15 ያህል አባላት የተመረጡ ሲሆን፣ እስከ መጪው ሰኞ ድረስ የማጣጣም ስራቸውን አጠናቀው በጋራ ማረጋገጫ ስርዓት አልፎ ለ500 አባላት የውይይት ቡድን ለተጨማሪ አስተያየት እንደሚያቀርቡ ተገልጻል።   በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከታቀዱት ስራዎች መካከል ሶስት አራተኛ ያህሉን ማጠናቀቁንና ሁሉም ተመካካሪ ቡድኖች በቀረቡት ምክረ ሐሳቦች ላይ ተስማምተው መፈረማቸውን አስታውቋል።   ከሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ ዋናውን ጉባኤ በመክፈት የተጀመረውና በስምንት አጀንዳዎች ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የምክክር ሂደት፣ በዛሬው እለት 30ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ኮሚሽኑ ሂደቱን በተቀመጠለት ጊዜ ሰሌዳ አጠናቅቃለሁ ብሏል።   ቁምነገር አየለ    ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.2 099104

    ገዳ ባንክ የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታና የሥነ-ሕንፃ ጥበብ የሚያዘምን የዋና መሥሪያ ቤቱን ዲዛይን ይፋ አደረገ አዲስ አበባ በከፍተኛ የከተማ መዋቅር ለውጥና በዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ግንባታ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ገዳ ባንክ የከተማዋን የነገ ገጽታ ታሳቢ ያደረገ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ የዲዛይን ውድድር አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል። ባንኩ ይፋ ያደረገው ይህ ዲዛይን የኪነ-ሕንፃ ጥበብን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ያቀናጀ ሲሆን፣ ለከተማዋ የሥነ-ውበት ዕድገትም የራሱን አሻራ እንደሚያሳርፍ ተገልጿል። የገዳ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ቡሉቶ እንደገለጹት፤ ባንኩ የወደፊት የዕድገት ምዕራፉንና የፋይናንስ  ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን የፈጠራ ደረጃ ታሳቢ ያደረገ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ የዲዛይን ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል። በውድድሩም የከተማዋን የሥነ-ሕንፃ ከፍታ የሚመጥኑና የባንኩን መለያ እሴቶች የሚያንፀባርቁ የፈጠራ ውጤቶች ቀርበዋል። ከ38 በላይ አማካሪ ድርጅቶች ሰነድ ገዝተው የተሳተፉበት ይህ ውድድር፣ በዘርፉ በታወቁ ገለልተኛ ዳኞች ጥብቅ ምዘና ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፣ 18ቱ ተወዳዳሪዎች መስፈርቱን አሟልተው ማቅረባቸው ተገልጿል። አቶ ወልዴ ቡሉቶ አሸናፊውን ዲዛይን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ሕንፃው የ‘ስማርት’ ግንባታ መስፈርቶችን የሚያሟላ፣ የአካባቢ ጥበቃንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ያገናዘበ እንዲሁም ለሰራተኞችና ለደንበኞች ምቹና አነቃቂ የሥራ ምህዳር የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል። ይህ የሕንፃ ዲዛይን ውድድር መጠናቀቅ ባንኩ ወደ ቀጣዩ የዕድገት ምዕራፍ ለመሸጋገር እያደረገ ያለው ዝግጅት አካል መሆኑ ተመላክቷል። ባንኩ ይህንኑ ስትራቴጂያዊ ግብ ለማሳካትና ካፒታሉን በማጠናከር በገበያው ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ አዳዲስ አክሲዮኖችን ለባለሀብቶችና ለህዝብ ክፍት ማድረጉን ገልጿል። ይህም ባንኩ ወደ ኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለመቀላቀልና የባለአክሲዮኖችን ድርሻ ይበልጥ ተጠቃሽ ለማድረግ ለጀመረው ሥራ እንደ መነሻ የሚታይ መሆኑ ተጠቁሟል። በዕለቱ በተካሄደው የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ የባንኩ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት፣ በከተማዋ የፈጠራና የኪነ-ሕንፃ ሥራዎች ላይ የሚደረጉ መሰል ውድድሮች የሀገሪቱን የሥነ-ሕንፃ ጥበብ ደረጃ እንደሚያሳድጉት ገልጸዋል። ገዳ ባንክም ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በመገንባትና አገልግሎቱን በማዘመን የባንክ ተደራሽነትን የማስፋፋት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ልዑል ወልዴ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.1 9042
  • 13 авг.2 094179

    በአዲስ አበባ የትራፊክ ሕግ ጥሰት ከ1.5 ሚሊዮን ማለፉ ተገለጸ   በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  በሚተላለፈው ታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ከተመዘገቡት ጥሰቶች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሶ ማለፍ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱም ተመልክቷል። ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ሕግን አለማክበር ለሕይወትና ንብረት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አሳስበው፤ የቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ ግን አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ይገኛል ብለዋል።   በዚሁ መሠረት በ2017 ዓ.ም 4መቶ11 የነበረው የሞት አደጋ በ2018 ዓ.ም ወደ 3መቶ82፤ የከባድ አደጋዎች ቁጥር ደግሞ ከ1 ሺህ9መቶ85 ወደ 1ሺህ8መቶ65 ዝቅ በማለት የ1መቶ20 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል። በአንጻሩ ቀላል አደጋዎች ከ1መቶ15 ወደ 7መቶ35፣ የንብረት ጉዳቶች ደግሞ ከ34 ሺህ84 ወደ 34 ሺህ7መቶ2 ከፍ ብለዋል።   በመጨረሻም አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ሕግን በማክበር ማሽከርከር እንዳለባቸው እና የሰው ሕይወትና ንብረትን ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል። ሳራ ዮሐንስ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.56удалён 13 авг.

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.1 90652

    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከታቀዱት ስራዎች መካከል ሶስት አራተኛ ያህሉን ማጠናቀቁን ገለጸ ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ ለረጅም ጊዜ ሲደከምበት የቆየው የዚህ የምክክር ሂደት ውጤት በቅርቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንደሚሆንና አብዛኛው የዝግጅትና የውይይት ስራ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጿል። በሂደቱ ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች በተመለከተም፤ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸውን ቅሬታዎች በተዘረጋው የቅሬታ መፍቻ ስነ-ስርዓት መሠረት በጥንቃቄ እየተመለከተ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አክሎም “በውይይቱ ሂደት ውስጥ አለመግባባቶችና ግጭቶች መኖራቸው አልተካደም፤ ይሁን እንጂ እነዚህ አለመግባባቶች መኖራቸው የሀገራዊ ምክክሩን አስፈላጊነት ይበልጥ የሚያጎላው ነው” ብሏል። አክሎም ልዩነቶቹ በውይይትና በመደማመጥ ተፈትተው ወደ ጋራ መግባባት መደረሱ ለሂደቱ ስኬታማነት ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጿል። በትላንትናው ዕለት እናት ፓርቲ እና አብን የጉባኤው ሂደት የገዢው ፓርቲን ፍላጎት ለማስፈጸም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው ሲሉ ቅሬታ አቅርበው ነበር። አብን ጉባኤው ከተጀመረ በኋላ አዳዲስ ተመካካሪዎች ግልጽ ባልሆነ መንገድ መጨመራቸውንና የገዥው ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ የሥራ ቡድኖች እየገቡ ጫና መፍጠራቸውን ተቃውሟል። ኮሚሽኑ በታዩ ግድፈቶች ላይ አፋጣኝ ማስተካከያ ካላደረገም ራሱን ከጉባኤው እንደሚያገል ማስጠንቀቁ ይታወሳል። እናት ፓርቲ በበኩሉ፤ በምክክሩ ላይ አብላጫውን ቁጥር የያዙት የገዥው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በመሆናቸው ሂደቱ "ቀድሞ የተወሰነ ውሳኔን ቅቡልነት እንዲኖረው የማድረግ ሥራ ነው" ሲል አጣጥሎታል። በተጨማሪም ጉባኤው ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን ዋና ዋና መገለጫዎቿ ለድርድር የቀረበበት መድረክ ሆኗል ሲል ከሷል። ለዓለም አሰፋ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.1 6311
  • 13 авг.1 7452

    የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከታሪፍ በላይ የተወሰደ ከ680 ሺህ ብር በላይ ለተሳፋሪዎች አስመለሰ   በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ እና የመንገድና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል፣ ባለፉት 10 ወራት ከሕጋዊ ታሪፍ በላይ ከተሳፋሪዎች የተሰበሰበ 680 ሺህ ብር ማስመለስ ተችሏል።   የከተማ አስተዳደሩ መንገድና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት በአካባቢው የሚሰጠው የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሕግና ሥርዓትን የተከተለ እንዲሆን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።   የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘነበ ዘለቀ ከደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በበጀት ዓመቱ ከሕዳር ወር ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ከሕጋዊ ታሪፍ በላይ ተጨምሮ ከተሳፋሪዎች የተሰበሰበውን 680 ሺህ ብር በማስመለስ ለተገልጋዩ ማኅበረሰብ መመለሳቸውን ገልጸዋል።   ኃላፊው አክለውም፣ ከታሪፍ በላይ የማስከፈል ሙከራዎችን እና በሌሊት የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጉዞዎችን ለማስቀረት ከአጎራባች ዞኖች የትራንስፖርት አካላት ጋር በቅንጅት የመሥራት እንቅስቃሴ ተጀምሮ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።   በመጨረሻም፣ የተሳፋሪዎችን መብት ለማስከበርና ጤናማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስፈን የሕብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ መሆኑን አቶ ዘነበ ጠቁመው፣ ማኅበረሰቡ የሚያደርገውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸው ተዘግቧል።   ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.1 4962
  • 13 авг.1 6301

    በጃፓን ከወረቀት የቀጠነ እና በስስነቱ አቻ ያልተገኘለት ቸኮሌት ይፋ ተደረገ ጃፓናዊው የጣፋጭ ምርት አዘጋጅ ማቴ በጥቅል የቸኮሌት ወረቀት መልክ የተሰራና 0.03 ሚሊሜትር ብቻ ስፋት ወይም ውፍረት ያለው ‹‹ኮርቴክያ›› የተሰኘ ለየት ያለ የቸኮሌት ጣፋጭ ለገበያ አቅርቧል። በ2024 ስራ የጀመረው እና በቶኪዮ ጃፓን የሚገኘው ማቴ ቦቴጋ ዴል ቾኮላቶ በዓለም ቀጭኑን ቸኮሌት በማዘጋጀት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ እውቅናን አትርፏል። በጣሊያንኛ «የዛፍ ቅርፊት» የሚል ትርጉም የተሰጠውና «ኮርቴክያ» የተሰኘው ይህ ታዋቂ የቸኮሌት አይነት፤ በ0.03 ሚሊሜትር ብቻ የሚዘጋጅ በመሆኑ የኢንጂነሪንግ ድንቅ ስራ ተደርጎ ተቆጥሯል። በጣሊያን ሀገር ጥንታዊ የቸኮሌት አሰራር ዘይቤ የተነሳሳው ኮርቴክያ፤ከአካባቢው የመሳሪያ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ለአንድ ዓመት ተኩል ገደማ ጥናትና ምርምር ከተደረገበት በኋላ በተሰራ ልዩ ማሽን የታሸና የተጠቀለለ ነው። ምንም እንኳን ተመሳሳይ ማሽኖች በሌሎች የዓለም ክፍሎች ሊኖሩ ቢችሉም፣ እንደ ኮርቴክያ ያለ እጅግ ቀጭን የቸኮሌት ሽፋን ማዘጋጀት የሚችል ማሽን ግን እስካሁን አልተገኘም። የ«ማቴ» መስራች ማቴኦ ዋና አላማ፤በአፍ ውስጥ ሲገባ ወዲያውኑ የሚቀልጥና ቀደም ሲል ተደርሶበት የማይታወቅ አዲስ የቸኮሌት ጣዕም ተሞክሮን ለደንበኞች ማቅረብ እንደሆነ ተገልጿል። ቸኮሌት በአፍ ውስጥ ሊቀልጥ ሲል የተለየ ጣዕም እንደሚሰጥ የሚታመን ሲሆን፣«ማቴ» በየምግቡ ላይ ይህንን ልዩ ስሜት ለማቅረብ አልሞ የተነሳ ነው፡፡ ይህንን 0.03 ሚሊሜትር ውፍረት ያለው የቸኮሌት ሽፋን የዛፍ ቅርፊት በመሰለ ቅርፅ በመጠቅለል በአፍ ላይ ሲያርፍ ወዲያውኑ የሚቀልጥና አዲስ የምግብ አቀራረብ ስሜትን የሚፈጥር ልዩ የጣፋጭ አይነት መፍጠር ተችሏል። ኮርቴክያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ተቀባይነትን ካገኘ በኋላ ብዙዎች ተመሳሳይ ምርት ለማዘጋጀት ቢሞክሩም፣ ቸኮሌቱን ለማዘጋጀት የሚያገለግለውማሽን በቶኪዮ በሚገኘው የማቴ ቦቴጋ ዴል ቾኮላቶ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ልዩ መሳሪያ በመሆኑ እስካሁን ተመሳሳይ ምርት ማዘጋጀት አልተቻለም። ሀና ሰይፉ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም

  • 13 авг.1 4011

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.1 5002
Ethio Fm 107.8 — tgindex