tgindex
የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲ አሰሪዎች ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲ አሰሪዎች ፌዴሬሽን

Статистика

🔰We are the only Foreign Employment Associations Federation in Ethiopia 🌐 Gulf Aziz building 4th floor Room No. 404, Bole Medhanialem, Addis Ababa, Ethiopia ✍️ አስተያየት መቀበያ : @eoeaf2022bot ⚜️ Our Group : @eoeaf2022

Последний пост
26 сент. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 065
+1 за 2 дн.
Сутки
+2
+0,19%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 144
20 постов
Вовлечённость
389,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://vm.tiktok.com/ZMAPYH3hC/

  • *ጥብቅ ማሳሰቢያ* *ለኤጀንሲ ማህበራት እና ኤጀንሲዎች በሙሉ !!* በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የተሰማራችሁ ኤጀንሲዎች በሙሉ የኤጀንሲ ማህበር/ ፌደሬሽን አባል መሆናችሁን እና አለመሆናችሁን አባል ከሆናችሁ የየትኛው ማህበር አባል እንደሆናችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ግንቦት 18 እና 19ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንድታመጡ በማለት ዓርብ ግንቦት 15/2017ዓ.ም ከቀኑ 10:35ስዓት ላይ የወጣዉ ማስታወቂያ የማህበራት ህገ ደንብን ያልተከተለና ቀጥታ አባላትን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አግባብ ባለመሆኑ ማንኛውም የማህበርም ሆነ የፌደሬሽን አባል ጥያቄው ሊቀርብለት የሚገባው በተደራጀበት ማህበር በኩል ብቻ መሆን ሲገባው ይህ ሊሆን አልቻለም። ስለሆነም ማስታወቂያውን ካወጣው አካል ጋር ያካሄድ ስህተት መኖሩን ተነጋግረን እስክናስተካክል ሁሉም ማህበራት እና የኤጀንሲ ባለቤቶች ሪፖርት እንዳታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን። *ፌደሬሽን ጽ/ቤት*

  • በአዋጁ ዙሪያ ለመወያየት የተጠራው ስብስባ ሰዓት መቀየሩን ስለማሳወቅ : በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ለተሰማራችሁ አጠቃላይ ኤጀንሲወች በሙሉ በረቂቅ አዋጅ ላይ ለነገ አርብ ጠዋት ተቀጥሮ የነበረው ስብስባ በዛው ቀን ከሰዓት ወደ 8:00 ሰዓት የተዘዋወረ መሆኑን እና ቦታውም ያልተቀየረ መሆኑን እንገልፃለን:: ፌዴሬሽን ጽ/ቤት

  • በአዋጁ ዙሪያ ለመወያየት ተጠርቶ የነበረው ስብስባ ቀኑ መራዘሙን ስለማሳወቅ : 👇🏻በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ለተሰማራችሁ አጠቃላይ ኢጀንሲወች በሙሉ በረቂቅ አዋጅ ላይ ለነገ ተቀጥሮ የነበረው ስብስባ ለአርብ ጠዋት የተዘዋወረ መሆኑን እንገልፃለን:: ፌዴሬሽን ጽ/ቤት

  • አሰቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ! ለፌዴሬሽን አባል ማህበራትና ኤጀንሲዎች በሙሉ !! የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ላይ ሁሉም የኤጀንሲ ባለቤት ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት 4 ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት የውይይቱ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪ እንድናደርግ ተነግሮናል ።ይህ ስብሰባ በክብሪት ሚኒስትር የሚመራ ወሳኝ የረቂቅ አዋጅ የውይይት መደረክ በመሆኑ ሁሉም አመራርና አባል በዕለቱ በመገኘት የስብሰባው ተካፋይ እንዲሆን አክብሮታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት

  • https://youtu.be/oi2vynEuiq8?si=Be5XakLWb3X77jff

  • 23/01/2017 ዜና EOEAF የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽን የዜጎችን መብት ለማስከበር ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በውጭ ሀገር በስራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት እና ደህንነት ለማስጠበቅ ከዚህ ቀደም በጋራ አብሮ ለመስራት በመርህ ደረጃ ንግግር ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ዕለተ ሀሙስ መስከረም 2017 በኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ከሁለቱም በኩል የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የአለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ተወካይ፣ የተለያዩ የሚድያ ተቋማት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ነቢል መሀመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ፌዴሬሽኑ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በስራ የሚሰማሩ ዜጎች መብት፣ ክብር እና ደህንነት እንዲጠበቅ ለኤጀንሲዎች ከመንግስትና ከአለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ጠቅሰው በተለይ ፌዴሬሽኑ ከእነኝሁ የባለድርሻ አካላት ጋር የስነምግባር ደንብ አዘጋጅቶ እና አፀድቆ ኤጀንሲዎች ህግን፣ ዘርፉን በተመለከተ የወጣውን አዋጅ እና አለም አቀፍ መርሆዎችን በጠበቀ መልኩ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አስገንዝበዋል፡፡  ፕሬዝደንቱ አክለውም ፌዴሬሽኑ በዋናነት የአባላቶቹን መብት ከማስከበር ባሻገር የዜጎች መብት፣ ጥቅም እና ደህንነት እንዲከበር የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በዛሬው ዕለት የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም የዜጎችን መብት በማስከበር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ኮንፌዴሬሽኑ ለዜጎች የሰብዓዊ መብት መከበር ከሚሰራ ከየትኛውም ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት በርካታ ጥረት ሲደረግ የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ አክለውም ፕሬዝዳንቱ ይህ የመግባቢያ ሰነድ ወደ ትግበራ ሲገባ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የሚሰማሩ ዜጎች ከምልመላ ጀምሮ እስከሚሄዱበት የመዳረሻ ሀገራት እና ቆይታቸው ላይ በጋራ በሚመሰረተው የቅጥር እና የምልመላ አማካሪ ኮሚቴ (Migrant Workers Recruitment Advisory Committee) አማካኝነት መረጃዎችን በመሰብሰብ እና ልውውጥ በማድረግ የዜጎችን መብት ለማስከበር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ   ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽን ጋር  በጋራ መስራታቸው በርካታ ዜጎች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲሰማሩ ከማገዝ በተጨማሪ ዜጎች ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀምባቸው መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ የመግባቢያ ሰንዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት ጥምር ኮሚቴ በመመስረት እና   የጋራ አክሽን ፕላን በማውጣት ወደ ውጭ ሀገር በሥራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት ለማስከበር በርካታ ስራዎች እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡

  • без подписи

  • 6 сент. 2024 г.4 528111из MIDADONLINEINSTITUTE

    ዜና EOEAF ከ ነሀሴ 28/12/2016 ጀምሮ በሥራ ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ2016 የሥራ አፈፃፀምና ግምገማ መድረክ የፌዴሬሽኑ ቦርድ አባል እና የዓለም አቀፍ እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሰኢድ አህመድ ፌዴሬሽኑን ወክለው የተሳተፉ ሲሆን የውይይቱን መድረክ ጠቅለል አድረገው እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ የስራ እና ክህሎት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ እንደአጠቃላይ በውጭ ሥራ ሥምሪት ያሉብንን ችግሮችና መፍትሄዎች የዳሠሰ የውይይት መድርክ ነበር፡፡ ስብሰባው ሚኒስትሮችንና ሙሉ የመስሪያ ቤቱ የሥራ ሀላፊዎችና የክልሎችንም ያካተተ ስለነበር ከስልጠናና ሲኦሲ ፣ከሲስተም ችግር፣ ከሪፖርትና ከእገዳ ጋር የለውን የአሠራር ክፍተት እንዲሁም በቀጣዩ ለሚደረገው የውጭ ሥራ ስምሪት እቅድና አፈፃፀም ብሎም ያልተከፈቱ አዳዲስ አገሮችን ማስከፈትና የተሻለ ግብአት ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ በተለያዩ ባለሙያዎች ጥናት ቀርቦ የመፍትሄ አቅጣጫ የተመላከተበት መድረክና ክብርት ሚንስትሯ ሙፈሪያት ካሚልም ጠንከር ያለ መመሪያ የሰጡበት መድረክ ነበር፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ በውጭ አገር የሥራ ስምሪት የሚገጥሙንን ፈተናዎች ለመወጣት በጋራ መቆምን የተረዳንበት ልምድ ወስደናል፡፡ ስለሆነም እንደፌዴሬሽን አድነታችንን አጠናክርን ፊታችን ላይ ያለውን ኬላ በጋራ ማለፍ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት

  • ዜና EOEAF 9/12/2016 በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዘርፍ ለተሰማሩ በርካታ ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል:: የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽንን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈው ስልጠና የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋራ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን አላማው በውጭ ሀገር በስራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት, ጥቅም እና ደህንነት ለማስጠበቅ በሀገራት መካከል የሚፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ከዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ባለው ሂደት አለም አቀፍ ህጎችንና መርሆዎችን መሠረት ባደረገ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ከማስቻል በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማረጋገጥ ነው:: ይህ በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ከበርካታ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር በፈረመቻቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ዝግጅት, አተገባበር እና ክትትልን በመገምገም የተሻለ የዜጎችን ጥቅም የሚያስከብር ስምምነት በሚዘጋጅበት አግባብ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ውይይት ተጠናክሮ ይቀጥላል:: ፌዴሬሽን ጽ/ቤት

  • https://youtu.be/0crWwFR4g1o?si=N3Ldjrw7xeFycH4E

  • https://www.facebook.com/100078322869617/posts/pfbid02erX2oZqCgxjxfRmJviwK89JtMZHzwZPtfwHpuqAH2LErZequ8iaxekqbSLFmSqZXl/?sfnsn=mo

  • https://www.facebook.com/100078322869617/posts/pfbid0KuC8grhjteDchDjt4gDs12wzHN1bQxmUmVPDcZYmgbB12pENA5Qa9b2uZ32vsnn5l/

  • без подписи

  • ለተከበራችሁ በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት በአገናኝ ስራ ላይ የተሰማራችሁ የፌዴሬሽናችን መስራች የሶስቱም ማህበራት አባላትና በዘርፉ ለተሰማራችሁ ኤጀንሲዎች በሙሉ። በቅድሚያ የከበረ ሠላምታችን ይድረሳችሁ ለማለት እንወዳለን። በመቀጠልም ፌዴሬሽናችን ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኩዌት አቻው ጋር ባደረገው ውጤታማ ውይይት የዜጎች መብት ክብርና ደህንነት በተሻለ መልኩ ማስከበርን ጨምሮ እስከዛሬ ከየትኛቸውም የመዳረሻ ሀገራት ጋር ከተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እጅግ የተሻለ የኮሚሽን መጠን ላይ ስምምነት የተደረሰ መሆኑን ስንገልጽላችሁ ላቅ ያለ ደስታ እየተሰማን ነው። ፌዴሬሽናችን ከኩዌት አቻው ጋር በዚህ መልኩ የተሳካ ስምምነት ላይ እንዳይደርስ ማህበር ነን የሚሉ አንዳንድ አካላት የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል:: ይሁን እንጅ የሁለቱ አቻ ማህበራት አመራር በጋራ ቆመው በመታገላቸው ምክንያት ጥረታቸው የከሸፈ ቢሆንም ዛሬም በሁለቱ አቻ ማህበራት በኩል የተደረሰውን ስምምነት ጥላሸት ለመቃባትና በመድረክ የደረሰባቸውን ከባድ ሽንፈት ለመሸፈን በመሯሯጥ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ረገድ እንደ አንድ ስትራቴጂ ለመጠቀም እየሰሩ ያሉት ደግሞ በዘርፉ የተሰማሩ ኤጀንሲዎችን ስብሰባ በመጥራት የተሳሳተ መልዕክት የማስተላለፉ ጉዳይ አንዱ ነው። ሰለሆነም ለተከበራችሁ በዘርፉ ለተሰማራችሁ ኤጀንሲዎች በሙሉ በቅድሚያ ማስተላለፍ የምንፈልገው ፌዴሬሽናችን ከኩዌት አቻ ማህበር ጋር የደረሰው ስምምነትና በሂደቱ የነበሩትን ተግዳሮቶችን በዝርዝር የሚተነትን ጹሁፍ ከዚህ በታች የቀረበ ስለሆነ ሁላችሁም እንድታነቡት እየጋበዝን በዚሁ አጋጣሚም የፌዴሬሽኑ መስራች የሆኑ የሶስቱ ማህበራት አባላት ፍውቸር በተባለው ማህበር በተጠራው ስብሰባ ላይ ለመገኘት ግደታ የሌለባችሁ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን ። ፌዴሬሽኑ

  • በኢትዮጵያ እና በኩዌት መንግስት በኩል ኢትዮጵያዉያን ሰራተኞችን ወደ ኩየት ለመላክ ግንቦት ሰኞ 19 2016 ዓ.ም የተደረሰዉን ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ የዉጭ ሀገር ስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽን በጽ/ቤቱ ከኩዌት አቻ ማህበር ጋር የዜጎችን መብት ; ክብር እና ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም በዉጭ ሀገር ስራ ስምሪት የተሰማሩ ኤጀንሲዎችን ጥቅም ባስከበረ መልኩ የሁለትዮሽ ስምምነት አፅድቀዋል:: ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ለሁሉም በዉጭ ሀገር ስራ ለተሰማሩ ኤጀንሲዎች በቅርቡ በተከታታይ የምንለቅ ይሆናል:: ፌዴሬሽኑ

  • ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ** (ኢ ፕ ድ) ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል። በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ሕጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል። ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

  • без подписи

  • ለተከበራችሁ በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት በአገናኝ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ኤጀንሲዎች በሙሉ። በቅድሚያ የከበረ ሠላምታችን ይድረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።በመቀጠልም የ E -LM I S version Two ወደ ስራ ከገባ በኋላ ሚኒስቴር መ|ቤቱ የሰራተኛ ሀይልን ለኤጀንሲዎች ማከፋፈል የጀመረ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሂደትም ቀድሞ በኤጀንሲዎች እጅ የሚገኙ ቪዛ ያላቸውና ለቪዛ ፕሮሰስ የተመዘገቡ  ዜጎች ጉዳይ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ለፌዴሬሽናችን በርካታ ጥያቄዎች ቀርቧል። ፌዴሬሽናችንም በበኩሉ ጉዳዩ መፍትሔ ያገኝ ዜንድ  ከሚኒስቴር መ|ቤቱ ጋር ስፊ ምክክር አድርጓል ። በዚሁ መሠረትም Version TWO የጀመረ ቢሆንም በ Version One በእጃችሁ ላይ የነበሩና ቪዛ ያላቸው እንዲሁም ለቪዛ ፕሮሰስ የተመዘገቡ ዜጎች ከእጃችሁ እስከሚያልቅ ድረስ በ Verson Two ላይ መስተናገድ እንዲችሉ ስረዓት የተበጀለት መሆኑን አውቃችሁ እጃችሁ ላይ ያሉትን ዜጎች የፖስፖርት ቁጥርና የሌበር አይ ዲ በማመልካቻ ለስራና ክህሎት ሚኒስትር በማስገባት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደምትችሉ መግባባት የተፈጠረ መሆኑን  ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን:: ፌዴሬሽኑ

  • https://youtu.be/ZWyvluHhLRM?si=bACJIfGDl77XCaBg