tgindex
Последний пост
25 окт.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
706
−1 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
670
21 постов
Вовлечённость
94,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ትራምፕ የጋዛ ጦርነት አሁን እንዲቆም ለምን ወሰኑ? በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ጥቁር ጠባሳውን ያሳረፈው የጋዛ ጦርነት አብቅቷል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ በወራሪው ፂዮናዊ አልፎ አልፎ ቢገረሰስም ከሞላ ጎደል እንደፀና ነው። የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ አግቷቸው የነበሩትን ፂዮናዊያን እየለቀቀ እና በምላሹ በበደል እስር ሲማቅቁ የነበሩ ፍልስጤማዊያንን ነፃ እያወጣ ቀጥሏል። አሁን ውስን የታጋቾች ሬሳ በፍርስራሽ ስር በመሰወሩ አድካሚ ፍለጋ ከመደቀኑ የዘለለ ስምምነቱን ሊያሰናክል የሚችል ከባድ ፈተና ያለ አይመስለም። ይህ ስምምነት የአሜሪካው ፕሬዝዳን ዶናልድ ትራም የፂዮናዊያን ታጋቾች እንዲለቀቁ እና ሙታኑ እንዲመለሱ የጊዜ ገደብ ካስቀመጡ እና ጦርነቱ በፍጥነት እንዲቆም ከመጠየቃቸው ጋር የተያይዞ የመጣ እንደሆ እሙን ነው። ታድያ ትራም ወደ ስልጣን ከመጡ ወራት ካለፉ በኋላ በዚህ ሰአት ስለምን የጋዛ ጦርነት እንዲቆም ፈለጉ የሚለው ጥያቄ ሊሰመርበት የሚገባው እንደሆነ አምናለው። አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ዶናልድ ትራም የጦርነት ሂደቱ እንዲቋጭ የፈለጉበት ብዙ ምክኒያቶች ቢኖሩም በዋነኛነት አምስት መሰረታዊ ምክኒያቶች እንዳሉ ያምናሉ። 1⃣ የመጀመሪያው ምክኒያት በጋዛ እየተካሄደ ያለው አጥፊ ጦርነት ከሚካፈሉት አካት አልፎ በረሀብ እያረገፋቸው ያሉ ህፃናት እና አረጋዊያን የፂዮናዊዋን ሀገር እጅጉን እንድትጠላ ማድረጉ ነው ይላሉ ተንታኞቹ። እንደሀገር ብቻ ሳይሆን እንደዜጋም በየሀገራቱ የተበተኑት ፂዮናዊያን በግልሰብ ደረጃ ከአለም እየተተፉ ሄደዋል። ይሄ ደግሞ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ መጠልሸት እና የስም መጉደፍ መዳረጉ ዶናልድ ትራምፕን አሳስቧቸዋል። በጊዜ ሂደት ስትራቴጂካዊ አጋራችን የሚሏት ወራሪ ሀገር ዲፕሎማሲ መበላሸቱ ተመካከለኛውን መስራቅ አቅጣጫ መልክ እንዳይቀይረው ሰግተዋል። «እስራኤል» ይሏት ሀገር አሜሪካ በመካከለኛው መስራቅ የከፈተቻት ኤምባሲ እንደመሆኗ የርሷ ስም መጠልሸት ለሀገራቸው መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ አያጡትም። 2⃣ ሌላኛው የጦርነቱ መቋጫ ምክኒያት ተብሎ የሚነሳው ደግሞ የፂዮናዊያን አጋር የሚባሉ አውሮፓዊ ሀገራት ለፍልጤም ሀገርነት እውቅና መስጠታቸው ነው። እንደ ፈረንሳይ ፣ እንግሊዝ ፣ ካናዳ ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎችም የአውሮጳ ሀገራት ለፍልጤም ሀገርነት እውቅና መስጠታቸው ነገሮች ምን ያህል ወደ ቁልቁለት እየተንደረደረ ለመሆኑ አመላካች ነው ይላሉ የዚህ እያታ ደጋፊዎች። ስለዚህ ፂዮናዊነትን ለመታደግ ጦርነት ከማስቆም እና «እስራኤል» ራሷ በራሷ ከማጣፋት መታደግ ለትራምፕ አማራጭ የነበረው ጉዳይ አይደለም። 3⃣ በሶስተኛነት ለጋዛ ጦርነት ማቆም እንደምክኒያት ሊጠቀስ የሚችለው የኳታር ድብደባ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁ የአሜሪካ አየር ሀይል መቀመጫ የሆነችው ኳታር በ«እስራኤል» ድብደባ ማስተናገዷ አሜሪካንን በስሱም ቢሆን ሳይጎረብጣት አልቀረም። በርሷ ፈቃድ የተፈፀመ ቢሆን እንኳ ጥበቃ አደርግልሻለው ያለቻት ሀገር ስትወቀጥ አይታ ዝም ማለቷ ክብሯን ዝቅ የማድግ ያህል ሸምቅቋታል። በተጨማሪ አረባዊያን ሌሎች አጋሮችን ወደ ማማተር መገደዳቸው ለዛሬም ባይሆን ለረዥም ጊዜ ሀሚያመጣው ጉዳት መኖሩ አያጠያይቅም። የሱዑዲ እና የፓኪስታን ስምምነት በግንባር ቀደምትነት እዚህ ቦታ ሊጠቀስ ይችላል። 4⃣ የ«እስራኤል» መረን የለቀቀ እርምጃ ከጋዛን ፣ ኢራንን ፣ የመንን ፣ ሶሪያን ፣ ሊባኖስን አልፎም ኳታር መድረሱ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ምቾት የነሳ እንደሆነም የሚናገሩ አይጠፉም። ምክኒያቱም በአለም ላይ ያለው አንድ ጉልቤ እንደሆነ ሁሉም ሀገራት እንዲያምኑ ይፈለጋል። እሷም አሜሪካ ብቻ እና ብቻ ናት። ይሄንን እሳቤ ሊያዛባ የሚችል ማንኛውም አካል እጅ  ይቆረጣል። የ«እስራኤሉ» ጠቅላይ ሚኒስቴር ደግሞ ይሄንን እያከበረ አልነበረም። እንደውም የአሜሪካንም ገዢ እስኪመስሉ ድረስ በሀገሪቱ ፖሊሲ ላይ ተቆልለዋል። እንደ ትራምፕ ያሉ ኩራት ያረሰረሳቸው መሪ ደግሞ አሁንም ሀያሉ ቃል የርሳቸው እንደሆነ ለማሳየት ይፈልጋሉና ጦርነት በቀጥታ ተሳትፈው መደምደም ባይችሉ እንኳ የመጨረሻ ቃላቱን የሚተነፍሱለት እርሳቸው እንደሆኑ ማሳየት ይፈልጋሉ። 5⃣ ከሁሉም ምክኒያቶች በበለጠ የጋዛ ጦርነት ተቋጭቶ እንዲታይ ያበቃው የትራምፕ ነጋዴነት ባህሪ እንደሆነ ይነገራል። ሰውየው ማንኛውም ነገር ሲፈፅሙ ልክ እንደ ነጋዴ ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው የዋጋ ድርድር እያደረጉ ነው። በተለይ ደግሞ ስም እና ዝና የሚደራርብላቸው ንግድ ይመቻቸዋል። ትራፕ ለ«እስራኤል» ሲሉ «የሚታለብ ላም» ያሏቸውን ዓረቦች ማጣት አይፈልጉም። ከዚህም በላይ ደግሞ በማያበቃ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ተጠልፈው በቻይና ፣ ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ የሚተበተበውን ሴራ ችላ እንዳይሉ እጅጉን ይሰጋሉ። ለዚህም ሲባል ነው ከአፍጋኒስታን ፣ ከኢራን እና የመን ጦርነቶች በፍጥነት አፈትልከው ሀይላቸውን የሰበሰቡት። በዚያ ላይ የቻይና አውዳሚ የኢኮኖሚ ጦርነት ሲታሰብ በዚህ ሰአት የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ጦርነት ሊያስከፍል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሲያስቡት ብርክ ይነሳቸዋልና በተቻላቸው የማይቀር ወደ ሚመስለው የቻይና እና አሜሪካ ጦርነት ሀሳባቸውን እና ሀይላቸውን መሰብሰብ ይፈልጋሉ። ለማንኛውም የትራምፕ አስተዳደር የነጋዴነት ባህሪ ሰፋ ያለ ትንታኔ ስለሚያሻው ምናልባት በሌላ ጊዜ እንመለስበት ሆኖ ለጋዛ ተበዳይ ወንድሞቻችን ስለተፈጠረው ሰላም አላህ የሞላ ምስጋና እያደረስን አጭር መጣጥፋችንን እንቋጫታለን። ሰላም👋

  • ሙታንን መሳደብ ሙታንን መሳደብ በህይወት ያሉ ወዳጆቻቸውን «አዛ» ከማድረግ የዘለለ ቅንጣት ትርፍ አይኖረውም። ሙእሚኖችን «አዛ» ማድረግን በተመለከተ ደግሞ ቁርአን ግልፅ የሆነ አቋም አለው። እነሆ قَالَ الله تَعَالَى: وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ بِغَيْرِ مَا اكْتَسَبُوا فَقَدِ احْتَمَلُوا بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُبِينًا [الأحزاب:58] «እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡» (ሱረቱል አሕዛብ 58) በጥቅሉ ሙእሚኖችን ማስቸገር ክልክል መሆኑን ከመናገሩ በተጨማሪ ሙታንን መሳደብ በስነምግባር ፀያፍ ከመሆን ባሻገር የአላህ መልእክተኛ ትእዛዝም መጣረስ ነው። እዚች ጋርም ማስረጃ እንጠቅሳለን عن عائشة -رضي الله عنها- قالت: قال رسول الله ﷺ: لا تسبوا الأموات، فإنهم قد أفضوا إلى ما قدموا[1]، رواه البخاري እናታችን ዓኢሻ (ረዐ) እንሳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፦ «ሙታንን አትሳደቡ እነርሱ በእርግጥም ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ተጠግተዋል።» ቡኻሪ ዘግበውታል ሙስሊሞች እንዲህ ካለው ነውረኛ ተግባር ከቅርቡም ሆነ ከሩቁ ራሳቸውን ማቀብ ይኖርባቸዋል። ሌሎችን የምናስተናግድበት መንገድ ልክ እኛ ልንስተናገድበት በምንወደው ሁኔታ ይሁን። የኛ ወዳጅ ሲሰደብ እንደምንጠላው የሌሎች ወዳጆችን መስደብ እንፀየፍ! የኛ ወገን ሞት እንዲያገኘው እንደማንወድ ሁሉ ለሌሎች ሞትን አንመኝ! የራሳችን ሰው ሲሞት እንደማንስቅ በሌሎች ማለፍ አንሳለቅ! የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ያስተማሩንም ይህንኑ ነው፦ وعنْ عبدِاللَّه بنِ عَمرو بن العاص رضي اللَّه عنْهُمَا قالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ: المُسْلِمُ منْ سَلِمَ المُسْلِمُونَ مِنْ لِسَانِهِ ويدِهِ، والمُهَاجِرُ منْ هَجَر مَا نَهَى اللَّه عنْهُ متفقٌ عليه ዓብደላህ ብን ዓምር ብን ዓስ (ረዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፦ «ሙስሊም ማለት ከእጁ እና ምላሱ ሙስሊሞች ሰላም የሆኑለት ነው። ሙሀጂር ማለት ደግሞ አላህ ከከለከለው የተሰደደ ነው።» (ቡኻሪ እና ሙስሊም) በሌላ ሐዲሳቸው፦ وعنْ عبدِاللَّه بنِ عَمرو بن العاص رضي اللَّه عنْهُمَا قال رسولُ اللَّه ﷺ: مَنْ أحبَّ أنْ يُزَحْزحَ عَنِ النَّارِ، ويَدْخَل الجنَّةَ، فلتَأتِهِ منِيَّتُهُ وهُوَ يُؤمِنُ باللهِ واليَوْمِ الآخِرِ، وَلْيَأتِ إِلَى النَّاسِ الَّذِي يُحِبُّ أنْ يُؤْتَي إليْهِ رواه مسلم ዓብደላህ ብን ዓምር ብን ዓስ (ረዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፦ «ከእሳት ተፈልቅቆ ጀነት መግባት የፈለገ ሰው ሞቱ እስክትመጣ ድረስ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሆኖ እና ሰዎች ዘንድ የሚያመጣው ነገር እርሱ ጋር እንዲመጡበት በሚፈልገው መልኩ ሆኖ ይሙት።» (ሙስሊም ዘግበውታል) እነዚህ ሁሉ መረጃዎች እንዳሉ ሆነው ሙታን ጋር የሚደረግ ግብግብ ፀያፍ የሚያደርጋቸውን የተወሰኑ ነጥቦች እናሳያችሁ 1️⃣ ለስድብ እና ውግዘት ምላሽ መስጠት የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ያለ ሰው መስደብ ከቆይታ በኋላ እንኳ ለተውበት እና ይቅርታ ለመጠየቅ የማይቻልበት አደገኛ ሁኔታ ይፈጥራል። እንደሚታወቀው በሰዎች ላይ ድንበር ማለፍ ተውበት የተሟላ የሚሆነው የሰዎቹን ሀቅ ማካካስ ወይም ይቅርታ መጠየቅ ሲገኝ ነው። ከሞተ ሰው ደግሞ ይህንን ማድረግ አይቻልም። 2️⃣ ሙታን ሰዎችን መራገም እና በሞታቸው መፈንደቅ በሞቱት ሰዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳይ አያስከትልም። ሆኖም በወዳጆቻቸው ዘንድ ጥላቻ እና መከፋትን ይፈጥራል። ከአእምሮ ይልቅ ስሜትን ፣ ከምክኒያት ይልቅ እልህን በሰዎች መካከል በማንሰራፋት መለያየት እና መከፋፈልን ያንሰራፋል። 3️⃣ ሙታንን መዝለፍ ከተሳዳቢው ከፍ ብሎ የሙስሊሞችን ክብር እንደ ኡማ የሚያጎድፍ እና በሌሎች እምነት ተከታዮች ዘንድ ክፉ ተደርጎ እንዲሳል የሚያደርግ ነው። እዚህ ጋር የሙናፊቆች አለቃ ዓብደላህ ብን ኡበይ ብን ሰሉል በሞተ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ያሳዩት መለሳለስ ጥሩ ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለው። የሙናፊቆች አናት ብን ሰሉል በአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ልብስ መከፈኑን ምን ያህሎቻቹ ታውቁ ይሆን? 4️⃣ በሰዎች ነውር እና ክፉ አጋጣሚዎች ላይ መንጠልጠል ከራስ ነውር መዘናጋት እንደሆነም አለመዘንጋት መልካም ነው። በመጨረሻም ታላቁ መልእክተኛ (ሰዐወ) ያሉትን ብለን እንሰናበታችሁ عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ: صَعِدَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الْمِنْبَرَ فَنَادَى بِصَوْتٍ رَفِيعٍ، فَقَالَ: «يَا مَعْشَرَ مَنْ أَسْلَمَ بِلِسَانِهِ وَلَمْ يُفْضِ الإِيمَانُ إِلَى قَلْبِهِ لاَ تُؤْذُوا الْمُسْلِمِينَ، وَلاَ تُعَيِّرُوهُمْ، وَلاَ تَتَّبِعُوا عَوْرَاتِهِمْ، فَإِنَّهُ مَنْ تَتَبَّعَ عَوْرَةَ أَخِيهِ الْمُسْلِمِ تَتَبَّعَ اللَّهُ عَوْرَتَهُ، وَمَنْ تَتَبَّعَ اللَّهُ عَوْرَتَهُ يَفْضَحْهُ وَلَوْ فِي جَوْفِ رَحْلِهِ»، رواه الترمذي ብን ዑመር (ረዐ) እንዲህ ይላሉ "የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሚንበር ላይ ወጥተው ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲሉ ተጣሩ፦ «በምላሳቹ ሰልማቹ እምነት ልባቹ ያልዘለቀላቹ ስብስቦች ሆይ! ሙስሊሞችን አታስቸግሩ! አታነውሯቸው! ንራቸውን አታነፍንፉ! የሙስሊም ወንድሙን ነውር የተከታተለን ሰው አላህ ነውሩን ይከታተልበታል! አላህ ነውሩን የተከታተለበት ሰው ደግሞ የመጓጓዣው ሆድ ውስጥ ቢገባ እንኳ ያዋርደዋል!» ቲርሚዚይ ዘግበውታል

  • видео или голосовое, без подписи

  • 29 мая 2025 г.1 0543из Mohapharm

    видео или голосовое, без подписи

  • ፈረንጆች peace deal እና peace process የሚሉ ሁለት ሀገረጎች አሏቸው። Peace deal ሊስማሙ ከፈለጉት አካል ጋር ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው በአጭሩ የሚቋጩት የሰላም ስምምነት ሲሆን peace process የሚሉት ደግሞ ረዥም ጊዜ በስምምነት ሂደት በማድከም ጊዜ የሚገዙበት እንዲሁም ተቀናቃኞቻቸውን በስብሰባ ብዛት የሚያሰለቹበት/ከጥያቄው እንዲያፈገፍግ የሚያደርጉበት ሂደት ነው። ብዙ ጊዜ የፍልጤም ጥያቄ በሁለተኛው ሂደት ውስጥ ወጥቶ አያውቅም። ለዚህ ጥሩ ማሳያ ደግሞ ያሲን ዓረፋት ናቸው። በስብሰባ እና በጊዜ ደክመው ለእስራኤል የተባለች አሸባሪ የሀገርነት እውቅና የሚሰጥ ስምምነት እንዲፈርሙ ሆነዋል። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው። ጊዜያት ሲረዝም የሙስሊሞች ደም ቀለል ሆኖብን ስለቅድስት ምድራችን ከማበሰብ እንዳንዘናጋ። አላህ ከተበደሉ ወንድሞቻችን ጋር ይሁን።🤲

  • ይህ የሶሪያዊ ስደተኛ ታስታውሱታላቹ? 2015 ላይ ነበር ከቤተሰቡ ጋር ጦርነት ሸሽተው ወደ ቱርክ እየተሰደዱ የነበረበት ታንኳቸው ሰምጦ የሞተው። ከርሱ ጋር አባቱም በዚሁ አደጋ ህይወቱ አልፎ ነበር። የዚህ ሚስኪን የ3 አመት ህፃን ቀብር ስርአት የተፈፀመው በዛሬው እለት ዙልቂዕዳ 21 ቀን ነበር።

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 📜 እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱የአውሮፓዊያኑ ስብራት😱 ቀኑ ዙልቂዕዳ ሀያኛው እለት ፤ አመቱ ደግሞ 1441 ላይ ያሳያል። በአወሮጳዊያኑ ካላንደር 2020 ማለትም አይደል? አለም ሁሉ አይኑን በጊዜው አስጨናቂ ከነበረው ኮሮና ወረርሽኝ ላይ አንስቶ  በቱርክ ሀገረ መንግስት ፕሬዝዳን ረጀብ ጠይብ ኤሮዶጋን ላይ አድርጓል። ከ83 አመታት በኋላ የማይነካውን ነክተው የማይደፈረውን ደፍረው የዜና አውታሮች መነጋገሪያ ሆነዋል። ጀርመን አሌክትሪክ ካልጨበጥኩ ፤ ፈረንሳይም ራሴን ሲጥ ካላደረኩ የሚመስሉ መግለጫዎችን ይወረውራሉ። ለነገሩ አይፈረድባቸውም። የልእልናቸው ማክተሚያ የሆችው ኮንስታንቲኖፕል "ኢስታምቡል" ከወደቀች በኋላ የክብራቸው አሻራ የሆነችው «አያ ሶፊያ» ዳግም ወደ መስጂድነት እየተመለሰች ነው። አታቱርካዊ ብለው የተዋት ሀገር ዳግም ኢስላማዊ እየሆች ሲያዩ ምን ይበሉ ታድያ? የሀገሪቱ ፕሮዝዳንት የመክፈቻ ቁርአን የሚያነበቡበት እና ሙፍቲዋ ሰይፍ ተደግፈው ኹጥባ የሚያደርጉበታ ጉድ ያላት ሀገር ሆናለች ቱርክ!! አዎን! ከሶሀቦቹ ጀምሮ ብዙ መስዋእትነት ተከፍሎባት ፤ ነብያዊ ትንቢት የተሰጠባት የኢስታንቡል ከተማ ንጉሶቿን የምትሾምበት ፤ ስልጣንም የምታከፋፍልበት ስፍራ ዛሬ ከ83 አመት በኋላ ዳግም ወደ መስጂድነት ተለውጧል። ክስተቱ ልክ ያ…ኔ ሙሐመድ አልፋቲሕ ኢስታምቡል (ኮንስታንቲኖፕል)ን ሲከፍት የነበረው አይነት ንዝረት በመላው የአውሮፓ ሀገራት ተረጭቶ አንቀጥቅጧቸው ያለፈው ልክ እንደዛሬው ባለው የዙልቂዕዳ 20ኛው እለት ነበር።

  • 📜 እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱ደም የጠማው መስቀል😱 ልክ የዛሬ 930 አመት አስቀድሞ በዓረቦቹ የቀን መቁጠሪያ ዙልቂዕዳ 19 ላይ ፈረንሳይ በአውሮፓ አሉ የተባሉትን ጉልቤ ጄኔራሎች ሰብስባ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትመክራለች። የስብሰባው መሪ ደግሞ አባ ኡርባን ሁለተኛ ናቸው። በካቶሊክ እምነት ዘንድ የጊዜው የመጨረሻውን የጵጵስና መንበር የጨበጡ ሰው ነበሩ። ታድያ በእኒህ ትልቅ የሀይማኖት ሰው በእለቱ እየተሰበከ የነበረው መዋደድ እና መቀራረብ እንዳይመስላችሁ። ይልቁንም በአለም ላይ እጅግ ብዙ የሰው ልጆችን ህይወት የቀጠፈውን የ«መስቀላዊ ዘመቻ» ወይም በተለምዶ የመስቀላዊያኑ ጦርነት እየተባለ የሚጠራውን ፍጅት ስለመቀስቀስ እንጂ። አባ ኡርባን የአውሮፓ ጉልቤ ወታደሮችን ሰብስበው «ጣኦታዊ» ባሏቸው ሙስሊሞች ላይ ዘመቻ እንዲደረግ ቀሰቀሱ። ከዚያም አልፈው ይህንን ዘመቻ የሚሳተፍ የትኛውም ሰው ወንጀሉ ሙሉ በሙሉ እንደሚሰረይለት ቃል ገቡ። ያመነው ስለእምነቱ ሲል ያላመነው ደግሞ በሩቅ ምስራቅ ያለው የገዘፈ የሀብት እና የስልጣኔ ክምር ለመቀራመት አሰስ ገሰሱን ጭኖ የቁድስ ከተማን ለመውረር ፊቱን ወደ ዓረቡ አለም አዞረ። ይህ ጦርነት ለዘመናት ንፁሀንና ከዘማች ሳይለይ በመስቀል ስም ደም እያፈሰሰ እ/አ/አ ከ1095 እስከ 1272 ድረስ ማብቂያ ያላገኘ ፍጅትን አስከትሏል። ታድያ ይህ የመስቀላዊያኑ ዘመቻ እንዲካሄድ አባ ኡርባን ቅስቀሳ ያደረጉት ልክ በዛሬዋ የዙልቂዕዳ 19ኛው እለት መሆኑን ባሰብን ጊዜ በታሪክ የኋሊት ልንመልሳችሁ ወደድን።

  • 📜 እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱አይነ ስውሩ ፈረሰኛ😱 ገና ስሙ ሲነሳ የፊርዓውን ወንበር ተረካቢዎች እንዲርዱ የሚያደርግ ግዙፍ ስብእና ገንብቷል። ከኖረባት የግብፅ ከተማ አልፎ አለም ላይ ስመገናና ለመሆን የበቃው የሁለት አይኖቹ ብርሀን ከመሰለባቸውም ጋር ነበር። የታሪክ ምሁራኑ እንደሚሉት ከሆነ አንደኛዋ አይኑ ብርሀን የተነፈገችው ገና የ13 አመት ታዳጊ እያለ ሲሆን የቀረችው አንድ አይኑ ደግሞ በ17 እድሜው ርቃ ኮብልላለች። የምናወራው የኸጢቦች አሚር ፤ የኢማሞች አውራ እና የሚንበሩ ፈረሰኛ ስለሆነው ዓብዱልሐሚድ ኪሽክ ነው። ኪሽክ እአአ በ1933 በግብፅ የተወለደ ሲሆን አስር አመት ሳይሞላው የቁርአን ሒፍዙን አጠናቆ የአዝሀር ዩኒቨርሲቲን እንደተቀላቀለ ይነገርለታል። በታሪካዊው አዝሀር ዩኒቨርሲቲ ቆይታ ሁሉ በሚያመጣቸው ውጤቶች የአንደኝነትን ደረጃ ተነጥቆ የማያውቅና በተለይም የ«ነሕውና ሰርፍ» አስተምህሮ ላይ የሸኾቹን ምትክነት በመያዝ ለተማሪዎች የማብራራት እንድል ያገኝ እንደነበርም ይወሳል። ይህ ጉምቱ ስብእና የህይወቱን ማንነት የለወጠችው የኹጥባ ሚንበር ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘው ገና የ12 ታዳጊ እያለ ነበር።በ1961 ከአዝሀር ዩኒቨርሲቲ «ኡሱለ ዲን» ፋካሊቲ ተመርቆ በመስጂደ ሰሐን ከዚያም በመስጂድ መኑፊያ ያገለገለ ሲሆን ከ1962 ጀምሮ ደግሞ በመስጂድ ዓይነል ሐያት ረዥሙን የኸጢብነት ዘመኑን አሳልፏል። ጊዜው እንደ ዓብዱናስር እና አንዋር ሳዳት ያሉ እንኳንስ ለመተቸት ይቅርና ቀና ብሎ ለማየትም የሚያስፈሩ አምባገነኖች የነገሱባት ነውና ኪሽክ በዚህን ያህል ድፍረት ፀንቶ ይቆያል ብሎ ማሰብ ከባድ ነበር። ሆኖም አ/ሐሚድ በሀሪቱ ላይ ኢስላማዊ ስርአትን ለመደምሰስ የተሸረቡ ሴራዎችን ሁሉ በኹጥባ ቢንበሩ ላይ አንገቱን ቀና አድርጎ በመተች ግምቶች ፉርሽ አድርጓቸዋል። ኪሽክ አይደፈሩም የተባሉ ከገረሰሰባቸው ጉዳዮቹ መካከል የፍልስጤም ሉአላዊነት የከዳውን ካምፕ ዴቪድ ስምምነት ፤ የዳዕዋ ሰራተኞችን ለማሸማቀቅ በሰይድ ቁጥብ ላይ የተወሰደውን የሞት ቅጣት ፤ ኢስላምን በሶሻሊስ ለመበረዝ የሞከረውን ነጀብ መህፉዝ ድርሰት ወዘተ… ይገኙበታል። ኪሽክ የኢስላምን እውነተኛ ቅርፅ ለማስጠበቅ ባደረገው ተጋድሎ በ1965 ፣ በ1981 እና 1982 ለእስር የተዳረገ ሲሆን በአካላቱ ላይ ግልፅ ምልክት የሚያሳይ ያህል የከፋ እንግልት እና ስቃይ እንዲደርስበት ተደርጓል። በስተመጨረሻም ከ1982 በኋላ ከመስጂድ ኢማምነቱ እና ኸጢብነት እንዲታገድ በመደረጉ ህይወቱን በኢስላማዊ ድርሳናት ላይ አድርጎ ከ100 በላይ መፅሀፎችን በመፃፍ እስከህልፈተ ህይወቱ ድረስ ቆይቷል። ሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ኪሽክ በረጀብ ወር በእለተ ጁሙዓ 1417 ሂጅሪያ ለባለቤቱ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) በህልሙ ከዑመር ብን ኸጧብ ጋር ሆነው መጥተው ጀናዛውን ሲያጥቡት እንዳየ ከነገራት በኋላ የቀብሊያ ሰላት ሱጁድ ላይ እንዳለ ነፍሱ ወደ አኼራ ከነፈ። ይህ ታላቅ ዓሊም እና ኸጢም ይህችን ምድር የተቀላቀለው ልክ በዛሬዋ እለት ዙልቂዕዳ 14 ቀን 1351 ሂጅሪያ ላይ ነበር። የሚንበሩን ፈረሰኛ አላህ በሰፊው ጀነቱ እንዲያንፈላስሰው የምንግዜም ምኞታችን እና ዱዓችን ነው።

  • 📜 እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱የኺላፋ ስርአቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተበደረ😱 የዑስማኒየ ኺላፋ ለ600 አመታት ፀንቶ የቆየ ቢሆንም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከውጫዊ ያልተቋረጡ ጦርነቶች እና ውስጣዊ አመፆች ምክኒያት መዳከም የጀመረበት ጊዜ ነው። ከጦርነቶቹ ባሻገር የእንገሊዛዊያኑ የአስተሳሰብ ወረራ በሀገሪቱ ላይ እጁንና እግሩን አስገብቶ ፖለቲካዋን በማተረማመስ የአቅሙን ሁሉ እየተውተረተረ ይገኛኝ። ሱልጣን ዓብዱልመጂድ ብን መሕሙድ አንዴ በሀይማኖት ስም ሌላ ጊዜ ደግሞ በግዛት ጥያቄ እየተሳበበ የሚቀሰቀስበትን የማይጠፋ የሚመስል ነበልባል ከዚህም ከዚያም እያለ ያበርዳል። ሀገሪቱ ፅንታ እንድትቆይ ፤ የኸሊፋ ስአቱም እንዳይናጋ ያለየሌለ ሀይሉን ሁሉ ተጠቅሞ የሩሲያ እና ፈረንሳይን ቅጥ ያጣ ጣልቃ ገብነት ለማስታገስ የጦር ሰራዊቱን በግንባር አሰልፎ እስከመጨረሻው ጠብታ ይፋለማል። እንደሚታወቀው ጦርነት የጥይት መወራወር ብቻ ሳይሆን የሀገርን ኢኮኖሚ ፤ የመሰረተ ልማት እና ሰላም እጅጉን የሚፈታተን ጠባሳ መጣሉ የማይቀር ነውና የኡስማኒው ኺላፋ የኋሊት የጎን ውጋት የሆነበትን እና በዘመነ ዓብዱልሐሚድ ሁለተኛ ጊዜ ሀገሪቱን ይበልጥ እንድትመሳቀል ያደረገውን የእንግሊዛዊያኑን ብድር የወሰደው በዚህ ጊዜ ነበር። ምንም እንኳ ዑስማኒያ ስርአት ግዛተ ሰፊ እና በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች ብትሆንም ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጦርነት ለማጠናቀቅ ከእንግሊዝ ሀገረ መንግስት የመጀመሪያውን ከሀገር ውጪ የተገኘ ብድር ልክ በዛሬው እለት ዙልቂዕዳ 13 ቀን 1271 ሂጅሪ ላይ ብድር ወስዳለች። ብድሩ 5ሚሊዮን የወርቅ ሳንቲሞች ሲሆኑ በየጊዜው 5 በመቶ ወለድ እንዲታሰብበትም ለስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ይህች እለት በዘመነ ኺላፋው ላይ የመጀመሪያውን የኢኮኖሚ ነፃነት ለመነጠቅ የረዳች የታሪክ እጥፋት ናት ብንል ማጋነን ያለበት አይመስለኝም። ዙልቂዕዳ 13 ቀን1271 አመተ ሂጅራን በዚህ አስታወስናት።

  • 📜📜 እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱ታላቁ ክህደት😱 በአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ታሪክ ውስጥ እጅ የበዙ መናፍቃን እና ሀገራቸውን የከዱ ግለሰቦች ታይተዋል። ሆኖም በታሪካቸ ወሳኝ የሚባል ግንባር ላይ በዚህ ደረጃ ተከድተዋል ብሎ ለማሰብ ግን የሚከብድ ይመስለኛል። ነገሩ እንዲህ ነው የቁረይሽ ጎሳዎች እያደገ የመጣውን አዲስ ሀይል ከመዲና ነቅለው ለመጣል ለብቻቸው እንደማይሳካላቸው ስለገባቸው ጥምር ጦር አደራጅተው ክተት ብለዋል። በጊዜው በዓረቢያ ግዛት ታይቶ የማይታወቅ ቁጥር ያዘለ ሰራዊት አሰልፈውም የኢስላም ስም ዳግም በግዛቱ እንዳይነሳ ተማምለው ወደ መዲና እየገሰገሱ ነው። ግዜው 5ኛው አመተ ሂጅራ ላይ ያሳያል። ግና በስብስቡ ብዛት እርካታ ያልተሰማቸው ቁረይሾች ከመዲና ግዛትም ጥምር ጦሩን የሚቀላቀል ከዳተኛ እያፈላለጉ ኖሮ የበኒ ነዲር አይሁዳዊያን ከጎናቸው ማሰለፍ ተሳካላቸው። በኑ ቁረይዟዎች ግን ለጊዜውም ቢሆን ለመስማማት አልፈቀዱም። ይልቁንም መዲና ከተመሰረተው አሰላለፍ ጋር በመሆን ሀገሪቱን እንደሚከለከሉ ቃል ተጋብተዋል። ሙስሊሞች ገጥሟቸው የማያውቅ የሰራዊት ብዛት መዲናን ለማውደም እየገሰገሰ መሆኑን ሲሰሙ የመውጫ ቀዳዳ ለማበጀት ቁጭ ብለው የጦር መከላከያ መንገዶችን ያሰላስላሉ ፤ ይማከራሉ ፤ ይወያያሉም። በስተመጨረሻም በሰልማን አልፋሪሲ ጠቋሚነት ሀገሪቱ ዙርያ ቁፋሮ እንዲከናወን ከስምምነት ተደርሶ ሁሉም ረሀቡን ካንጀቱ እየደባበሰ የመዲናን ዙርያ በቁፋሮ ያካልሏት ያዙ። ይህ ሁሉ ሀገር የማፅናት እና እምነትን የማስከበር ትግል ሲያደርጉ ግን እንዲህ ያለው ክዳት ከጀርባችን ይኖራል ብለው ጭራሹኑም አላሰቡም ነበር። የሆነው ሆኖ ግዙፉ ሰራዊት አጋሰሱን ጭኖ መዲና ደረሰ። ግና ባልጠበቀው ሁኔታ የመከላከል ስልት ደንቃራ ስለገጠመው ሀገሪቷን ከቦ ከማስጨነቅ የተለየ ግዙፍ ፍልሚያ ለማድረግ አልቻለም። በመሆኑም አሁንም ተጨማሪ ሀይል አስፈላጊ ነው ወደሚለው  ሀሳብ መሄድ በከሀዲያኑ ሰራዊት ታመነበት። ግን ከመዲና ውጪ ሳይሆን ከመዲና ግንባር ነው ሀይሉ የተፈለገው። ይህንን ክዳት ከመዲና የሚፈፅም ከተገኘ የሙስሊሞች ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው። ከውጪ በከበባ የታጠረችው ከተማይቱ ከውጥ ደግሞ በክዳት ትታመሳለች። ያኔ የሙስሊሞች ግዛት ያከትምለታል። ይህንን የክህደት ድራማ እንዲያቀነባብር የተመረጠው ከአመት በፊት በሙስሊሞች እዝነት የተለቀቀው የበኒ ነዲር ጎሳ ባላባት ሑየይ ብን አኽጠብ ነበር። የእናት ጡት ነካሽ የሆኑት አይሁዳዊያኑ ከመዲና ግንባር ቀድመው እንደሚገነጠሉ እቅድ ተይዞላቸዋል። የሆነውም አልቀረም። በኑ ቁረይዟዎች ሀይል አሰላለፉን አይተው ሙስሊሞችን ከዱ። ከዚያም አልፈው የስለላ እና የጦር ዝግጁቱን ከመዲና ውስጥ ቁጭ ብለው በግንባቸው እንደተከለሉ አጧጧፉት። አላህ ያለው ሌላ ሆነና የአሕዛብ ዘመቻ የታሰበለትን ውድመት ሳያደርስ ሲበታተን ተራው የከዳተኞቹ በኒ ቁረይዟ መሆኑ አልቀረለትም። እናም ልክ በዛሬው እለት ዙልቂዕዳ 12, ቀን 5ኛው የሂጅራ መቁጠሪያ ላይ በኑ ቁረይዟዎች እንዲከበቡ በታላቁ መልእክተኛ (ሰዐወ) ትእዛዝ ተላለፈ።

  • ሰበር ዜና በካሽሚር ግዛት በተፈፀመው የጎብኚዎች ግድያ ጋር ተያይዞ ወደ ጦርነት የገቡት ሁለቱ ጎረቤታማች ሀገሮች በዛሬው እለት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን የአለም ሚዲያዎች በፊት ገፃቸው ላይ እያስነበቡ ይገኛሉ። እአአ በ1947 ወደ ሁለት ሀገርነት የተቀየሩት ሀገራቱ የጃሙ ካሽሚር ግዛት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ለግጭት እና ለጦርነት የተዳረጉ ሲሆን በያዝነው የአፕሪል ወር ውስጥ ዳግም ወደ ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል። ጦርነቱ በ«ባይሳራን» በተባለ ሸለቆ ላይ በተከሰተ ድንገተኛ ጥቃት የተቀሰቀሰ ሲሆን በቦታው ከ26 ሰዎች የማያንሱ ንፁሀን መገደላቸው ተገልፁዋል። በዚህም የተነሳ ህንድ ጥቃቱ በ«ፓኪስታን ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች የፈፀሙት ግድያ ነው» ወደሚል ክስ እና የኢንደስ ወንዝ ስምምነት ወደ ማቋረጥ ገስግሳለች። የንግድም ሆነ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷንም በፍጥነት አቋርጣለች። ፓኪስታንም በምላሹ የንግድ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን የቆረጠች ሲሆን በ1972 በሀገራቱ መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት መፍረሱን ይፋ አድርጋለች። በፍጥነት የተጋጋመው የሀገራቱ ዲፕሎማሲ በህንድ አስጀማሪነት ወደ ጦርነት የተለወጠ ሲሆን ህንድ በአየር ጥቃት ብዙ ንፁሀን የሚኖሩበትን ቦታዎች እና መሳጂዶችን ጭምር በሚሳኤል እና በጀቶች አውድማለት። በዚህ ድብደባ ከ31 የማያንሱ ንፁሀን ሰዎች ህይታቸው የተቀጠፈ ከመሆኑም ባሻገር ከ5 በላይ ለጥቃት የተሰማሩ የህንድ ጀቶች በፓኪስታን መከላከያ መውደማቸው ተገልፁዋል። ፓኪስታንም በግዛቷ ውስጥ ለተፈፀመው የአየር ጥቃት በሚሳኤል ፣ ጀቶች እና ሳይበር ጥቃት የታጀበ መጠነ ሰፊ መለሶ ማጥቃት ካከናወነች በኋላ በትናንትናው እለት ሁለቱ ሀገራቶች በአሜሪካ ፣ ሳኡዲ እና ቱርክ አሸማጋይነት ተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል።

  • 📜📜እለቱ በታሪክ ገፅ📄 😱የ15 አመቱ ሙፍቲ😱 እለቱ በሂጅራ አቆጣጠር 724 ላይ ያሳያል። ከግብፅ መንደሮች አንዷ በሆነችው «በልቂኒያ» ውስጥ አንዲት እናት በተባረከው የረመዳን ወር ልጇን ልትገላገል በምጥ ስቃይ ሰውነቷ ይርገፈገፋል። ከብዙ ድካም እና እግልት በኋላ ድንቡሽቡሽ ያለ ወንድ ልጅ የ«ረስላን ብን ኑሰይር»ን ቤተሰብ ተቀላቀለ። ቤተሰቡ ቀድሞውንም በዒልም የደመቀ ፤ በተርቢያም የተኮተኮተ ነውና የአዲሱ ህፃን እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ብዙም አያዳግትም ነበር። እንኳንስ የረስላን ልጅ ሆኖ የበልቂኒያ መንደር መወለድ እንኳ በጊዜው የዲን እውቀት ለመሸመት ስኮላርሺፕ የማግኘት ያክል መታደል ነበር። ዘመናት አንድ ሁለት እንዳሉ አዲሱ ህፃን የሁለተኛውን ኸሊፋ ዑመር (ረዐ) ስም ተጎናፅፎ አደንበቱ እንኳ በልኩ ሳይፈታ የቁርአን ንባብን እንደንፁህ ኩሬ በጨቅላነቱ ተጎነጨ። ይህ በዘመኑ ብዙም ሰዎች የሚያደርጉት ስለሆነ የሰዎችን ትኩረት ላይስብ ይችል ይሆናል። ሆኖም ገና የ7 አመት ህፃን ሆኖ 30ውን ጁዝ ቁርአን በቃሉ ሸምድዶ በአንድ ትፋሽ ሲጨልጠው ግን የዑመር ብን ረስላን ነገር የዋዛ እንዳልሆነ እያሳበቀ መጥቷል። ዑመር እድሜው 12 እንኳ ሳይሞላ ለታላላቅ ዓሊሞች እንኳ ዳገት የሆኑት መፅሀፍ በልቦናው መሐፈዝ ተሳክቶለታል። ከነዚህም መካከል «አልሙሐረር» የተሰኘውን የኢማም አቡልቃሲም አራፊዒ የፊቅሁ ሻፊዒ መፅሀፍ ፤ «አልካፊ» የተሰኘውን የብን ማሊክ የዓረብኛ ሰዋሰው መፅሀፍ ፤ ኡሱሉል ፊቅህ ላይ የሚያጠነጥነውን «ሙኽተሰር ብን ሀጅብ» መፅሐፍ ፤ የኢማመ ሻጢቢይ የ7 ቁርአን አነባበብ ዘዴዎች የሚተነትን መፅሐፍ ወዘተ… ዑመር ብን ረስላን 12 አመት ሳይደርስ በልቦናው ከጠጣቸው ታላላቅ ድርሳናት ውስጥ ይጠቀሳሉ። አሁን በትንሿ የ«በልቂን» የዒልም መንደር ደፍሮ ዑመርን የሚያስተምር አልተገኘምና ወደ ግብፅ ዋና ከተማ ከአባቱ ጋር የእውቀት ፍለጋ ጉዞ አደረጉ። በዚያም በዘመኑ አንቱ ከተሰኙት እንደ «አቢ ሐያን» ፤ «አልመይዱሚ» እና «ሸምሰዲን አልአስፈሀኒ» ያሉ ምሁራን ዘንድ ቀርቦ ከእውቀት ባህሩ የቻለውን ያህል ዘገነ። እድሜው 15 አመት ሲሆን የታዳጊው ክብደት የገባቸው ሸይኹ አቢ ሀያን «ፈታዋ እንድትሰጥ ፈቅጄልሀለው» ሲሉ አበሰሩት። ልጅ ዑመር በበኩር እድሜ ያከማቸውን እውቀት ይዞ ወደ ህዝቡ ብቅ ሲል ብዙዎች እጃቸውን በአፍ የሚያስጭን አስደማሚ የእይታ እና የማብራራት አቅሙን ተመልክተው «በእርግጥም አላህ የ9ኛውን ክፍለ ዘመን ኢስላማዊ ተሀድሶ የሚያበስር ምሁር አዘልቋል።» እንዲሉ አስገድዷቸዋል። ይህ ታላቅ ዐሊም ካፈሯቸው ተማሪዎ መካከል «ብን ሐጀር አልዓስቀላኒ» አንዱ መሆናቸውን ስትሰሙ እናንተም መደነቃች እንደማይቀር አስባመው። ዑመር ብን ረስላን ወይም በሚታወቁበት መጠሪያቸው #ሲራጁዲን_አልበልቂኒ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ልክ በዛሬዋ እለት ዙልቂዕዳ 11ኛው ቀን 805 ሂጅሪያ ላይ ነበር። የአላህ እዝነት አይለያቸው።

  • ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ ተይዞ ከነብያችን (ሰዐወ) እንደተዘገበው «የዋሻውን ምእራፍ (ሱረቱል ከህፍን) በጁሙዓ እለት ያነበበ ሰው በሁለት ጁምዓዎች መካከል ብርሀን ይፈነጥቅለታል።» ኢማም አልሐኪም እና ኢማም አልበይሀቂ ዘግበውታል

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሸሂዱል አዛን በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጀግና ስም አድናን ማንዳሪስ ይባላል። አንዳንዶች «ሸሂዱል አዛን» እያሉ ይጠሩታል። ስያሜውን ያገኘው ያለምክኒያት አይደለም። በ1920ዎቹ መጀመሪያ የኸሊፋው ስርአት ከሀገረ ቱርክ ከተፈነቀለ በኋላ በቱርክ የሚኖሩ ሙስሊሞችን ለመታደግ ባደረገው ትግል እንጂ። በጊዜው ሀገሪቱ ሌላው ቀርቶ አዛን እንኳ በቱርክኛ እንዲፈፅሙ የሚያስገድድ ነውረኛ ህግ ደንግጋ ነበር። ለዚህ ሁሉ መሸማቀቅ የዳረጋቸውን የአታቱርክ ፓርቲ የሚቃወም  የመጀመሪያውን ፓርቲ የመሰረተው ዓድናን ማንዳሪን ከብዙ ትግል በኋላ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ቢሳካለትም ለሙስሊሞች በሰጠው የነፃነት ብርሀን አታቱርካዊያኑ ጥርስ ውስጥ መግባቱ ግን አልቀረለትም። በስተመጨረሻም አዛን በአረብኛ እንዲደረግ በመፍቀዱ የሸሪዓ መንግስት ለማቋቋም አስበሀል በሚል ማወናበጃ ከመንበረ ስልጣኑ በወታደራዊ ፍንቀላ ተወግዷል። ይህም አልበቃም ያላቸው ፈንቃዮቹ ሸንጎ አቋቋመው  በፍትህ አልባ ፍርድ እሱን ከነጓደኞቹ ህይወቱን እንዲነጠቅ ውሳኔ አስተላልፈወረበታል። ሴብቴምበር 17 , 1961 ምድረ ቱርክ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝባዊ ምርጫ ወደ ስልጣን የሰቀለችውን ጠቅላይ ሚኒስቴር በወታደሮቿ ሸምቀቆ አንጠልጥላ በአደባባይ ሰቀለች። አድናንም ለሙስሊሞች በታገለባት ሀገር የሰማእትነት ማእረግ ተጎናፀገባት። አላህ ሸሂድነቱን እንዲቀበለው ከልብ እንመኝለታለን።

  • видео или голосовое, без подписи

ethiomuslims — tgindex