SMH General Construction
Статистикаበኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(Eng sintayehu melese) tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 988
- 1/48двое суток
- 2 278
- 1/72трое суток
- 2 457
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በብሎኬት ግንባታ ወቅት የቱምቢ (Plumb Bob) ትክክለኛ አጠቃቀም እና የሳይት ቁጥጥር! 🧐🏗️ በምስሉ ላይ እንደምናየው የብሎኬት ግንባታው በትክክል ወደ ላይ ቀጥተኛ (Plumb / Vertical) መሆኑን ለማረጋገጥ የቱምቢ(Plumb Bob) ልኬት እየተወሰደ ይገኛል። በቱቢ ልኬት ወቅት ትኩረት የሚሹ ቁልፍ ነጥቦች፦ 1. The Gap Requirement: በቱምቢው የታችኛው ነጥብ (Bob) እና በብሎኬቱ መካከል ትንሽ ክፍተት (ከ 1mm እስከ 2mm) መኖር አለበት — ቱምቢው ከብሎኬቱ ጋር ሙሉ በሙሉ ከተነካካ ልኬቱ ትክክል አይደለም። 2. Checking Top Block vs. Base: የቱምቢው የእንጨት/የላይኛው መደገፊያ ብሎኬቱ ላይ ሲያዝ፣ የታችኛው ተንጠልጣይ ነጥብ ከመሰረቱ (Base Course) ጋር የነበረውን አሰላለፍ መፈተሽ አለበት። 3. Regular Check: የቱምቢ ቁጥጥር ግንባታው አልቆ ሳይሆን በየተደረደረው የብሎኬት መስመር (In every course) መከናወን አለበት። በእርስዎ ሳይት ላይ ለብሎኬት አሰላለፍ Spirit Level ወይስ Plumb Bob (ቱምቢ) ይመርጣሉ? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!👇 https://t.me/ethioengineers1
DEFLECTION ምንድነው? 👉አንድ Beam ላይ Load ሲጫን Beam ቀድሞ ከነበረበት ቀጥተኛ ቅርጽ ይወጣና ይጎበጣል። ይህ የBeam ከOriginal Position የሚያደርገው የVertical Displacement Deflection ይባላል። Before Loading A ───────────────────── B After Loading A ────────╲____╱──────── B ↓ Deflection በተለምዶ δ ወይም y እንጠቀማለን። Units mm m በBuilding Design ብዙ ጊዜ mm ይጠቀማል። https://t.me/ethioengineers1
የኮንክሪት የውሃ ማፍሰሻ ቦይ (Concrete Roof Gutter) ውሃ እንዳያስተላልፍ የሚደረጉ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች! 🧐🌧️ በምስሉ ላይ እንደምናየው በቆርቆሮው እና በፓራፔት ግንቡ መካከል የኮንክሪት ቦይ (Concrete Gutter) ተሰርቷል። ይህ ቦታ በህንፃዎች ላይ ከፍተኛ የውሃ ሰርጎ የመግባት (Water Leakage) አደጋ ከሚፈጠርባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። በኮንክሪት ጋተር ስራ ወቅት ሊረሱ የማይገባቸው ነጥቦች፦ 1. Proper Slope/Fall: ኮንክሪቱ ውሃ እንዳያቁር ቢያንስ 1% እስከ 2% ተዳፋትነት (Slope towards downspout) ሊኖረው ይገባል። 2. Waterproofing Membrane: በኮንክሪት ቦዩ ላይ ጥራት ያለው የውሃ መከላከያ (App Waterproofing Membrane / Elastomeric Coating) መቀባት/መንጠፍ። 3. Flashing & Overlap: በቆርቆሮው እና በጋተሩ መካከል ያለው መጋጠሚያ ላይ ብረታዊ ፍላሽንግ (Metal Flashing) ገብቶ በቂ Overlap መኖሩን ማረጋገጥ። በእርስዎ ሳይት ላይ ለኮንክሪት ጋተር ውሃ መከላከያ Crystalline Coating ይመርጣሉ ወይስ Bituminous Membrane? https://t.me/ethioengineers1
በራፍት ፋውንዴሽን (Raft Foundation) ብረት ዝርጋታ ላይ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ነጥቦች! 🧐🏗️ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ወፍራም የታችኛ እና የላይኛ የብረት ንብርብሮች (Top & Bottom Rebar Mesh) በከፍተኛ ጥንቃቄ ተዘርግተው በማሰሪያ ሽቦ (Binding wire) ተጣብቀዋል። በራፍት መሰረት ስራ ወቅት በሳይት ቁጥጥር ወቅት ሊረሱ የማይገባቸው ነጥቦች፦ 1. Chair Supports (የብረት ወንበሮች): በTop እና Bottom Mesh መካከል ያለውን ክፍተት በትክክል ለመጠበቅ በቂ የብረት ወንበሮች (Chairs) መጠቀም። 2. Concrete Covers (ስፔሰሮች): የከባድ መሰረት ስለሆነ ከታች እና ከጎን በቂ የኮንክሪት ከቨር (50mm - 75mm) መስጠት። 3. Rebar Spacing & Lapping: በብረቶች መካከል ያለው ክፍተት ለትልቅ ጠጠር/ኮንክሪት ማልፈያ በቂ መሆኑን እና የላፕ (Lapping) ቦታዎችን ማረጋገጥ። https://t.me/ethioengineers1
⚡️Cube Test (Compressive Strength Test) 1. Cube Test ምንድን ነው? ✅Cube Test ማለት የተጠናከረ ኮንክሪት የግፊት ጥንካሬ (Compressive Strength) ለመለካት የሚደረግ የላብራቶሪ ሙከራ ነው። 👉 Slump Test የሥራ ቀላልነትን ይለካል፤ 👉Cube Test ደግሞ የኮንክሪቱን ጥንካሬ ይለካል። https://t.me/ethioengineers1
#Rate #Analysis ምንድን ነው? ✅Rate Analysis ማለት የአንድ የግንባታ ሥራ (1 m³ Concrete፣ 1 m² Plastering፣ 1 m³ Masonry...) አንድ ዩኒት ለመስራት የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ፣ የሰራተኛ፣ የማሽን እና ሌሎች ወጪዎች በዝርዝር ማስላት ነው። #Rate Analysis የሚመልሰው ጥያቄ፦ "1 m³ Concrete ለመስራት ስንት ብር ያስፈልጋል?" https://t.me/ethioengineers1
Project Management Triangle የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በ3 ዋና ነገሮች ላይ ይመሰረታል፦ ✅Time (ጊዜ) ✅Cost (ወጪ) ✅Quality / Scope (ጥራት / የሥራ መጠን) 🙏ከእነዚህ አንዱ ከተቀየረ ሌሎቹም ይጎዳሉ። ለምሳሌ፦ ✅ጊዜን ብታሳጥር ወጪ ሊጨምር ይችላል። ✅ወጪን ብትቀንስ ጥራት ሊቀንስ ይችላል። https://t.me/ethioengineers1
🙏Stress ዓይነቶች 1. Tensile Stress (የመዘርጋት ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጎተት የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅የSteel Reinforcement ✅Steel Tie Rod 2. Compressive Stress (የመጨመቅ ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጨመቅ የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Column ✅Concrete Block ✅ኮንክሪት በCompression ውስጥ በጣም ጠንካራ ነው። 3. Shear Stress (የመንሸራተት ውጥረት) በሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ምክንያት ቁሱ ሊንሸራተት ሲሞክር የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Beam በSupport አቅራቢያ ✅✅Bolts Rivets https://t.me/ethioengineers1
Flexible Pavement Layers (1) Wearing Course 👉ይህ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ የሚጓዙበት ንብርብር ነው። ☆ስራው 👉መንሸራተትን መቀነስ 👉ውሃን መከላከል 👉ለስላሳ የመንገድ ገጽ መስጠት (2) Binder Course 👉Wearing Courseን ይደግፋል 👉የትራፊክ ጭነትን ወደ Base Course ያስተላልፋል (3) Base Course 👉የመንገዱ ዋና ጭነት ተሸካሚ ንብርብር 👉ከተመረጠ ድንጋይ (Crushed Aggregate) ይሠራል (4) Sub-base 👉Base Courseን ይደግፋል 👉ውሃን ያስወግዳል (Drainage) 👉የጭነት ስርጭትን ያሻሽላል (5) Subgrade 👉Subgrade የመንገዱ የተፈጥሮ አፈር ወይም የተጠናከረ አፈር ነው። 👉የSubgrade ጥራት የመንገዱን ዕድሜ በጣም ይወስናል። https://t.me/ethioengineers1
⚡️የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት ያውቃሉ? - የመንግሥት የግዥ መመሪያዎችም ሆኑ የዓለም አቀፍ አበዳሪዎች (እንደ የዓለም ባንክ ያሉ) ሕጎች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes) ወዲያውኑ ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት በግልፅ ያስገድዳሉ። ይሁን እንጂ በተግባር ግን ይህ ሲደረግ ብዙም አይታይም። - በመክፈቻው ላይ የተነበቡ ዋጋዎች፣ ቅናሾች እና የሲፒኦ ዝርዝሮች ተጫራቾች እንዲያውቁት በማድረግ ተጫራቾች የግዥ ሂደቱ ፍትሃዊ እና በሕግ መሠረት እየተመራ መሆኑን እንዲያምኑ ያደርጋል፤ ይህም ለወደፊቱ ተቋሙ የተሻሉና ተወዳዳሪ ዋጋዎችን እንዲያገኝ ይረዳል። - ግዥውን የሚፈፅመው ተቋም ይህን ካላደረገ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) እንዲላክላቸው መጠየቅ ይችላሉ https://t.me/ethioengineers1
⚡️በTender Evaluation የሚመረመሩ ነገሮች ✅የኮንትራክተሩ ልምድ ✅የፋይናንስ አቅም ✅የቴክኒክ ብቃት ✅የመሳሪያ አቅም ✅የባለሙያ ቡድን ✅የሥራ ፕሮግራም ✅የቀረበው ዋጋ https://t.me/ethioengineers1
⚡️Setting Out (ማስቀመጫ መስመሮች) ይህ በSurvey Engineer የሚሰራ ሥራ ነው። የሚደረጉ ሥራዎች ✅Benchmark ማረጋገጥ ✅Grid Line ማስቀመጥ ✅Building Corners ማስቀመጥ ✅Foundation Center Line ማስቀመጥ ⚡️መሣሪያዎች ✅Total Station ✅Level Machine ✅GPS (እንደ ፕሮጀክቱ አይነት) ⚡️ በSetting Out የሚፈጠር ስህተት በሙሉ ፕሮጀክቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፤ ስለዚህ በConsultant መረጋገጥ አለበት። https://t.me/ethioengineers1
✅Shrinkage እና Swell ⨳በተፈጥሮ አፈር ላይ እነዚህ ለውጦች ይከሰታሉ። 1.Swell 👉አፈር ሲቆፈር መጠኑ ይጨምራል። ምሳሌ 100 m³ የነበረ አፈር ከተቆፈረ በኋላ 120 m³ ሊሆን ይችላል። 2.Shrinkage 👉አፈሩ ተመልሶ ሲጠናከር መጠኑ ይቀንሳል። https://t.me/ethioengineers1
🙏Method Statement ምንድን ነው? ⚡️Method Statement (MS) ማለት አንድ ሥራ እንዴት፣ በምን መሣሪያ፣ በማን፣ በምን የጥራት እና የደህንነት ሂደት እንደሚሰራ የሚገልጽ የጽሑፍ ሰነድ ነው። ዓላማው ✅ሥራው በአንድ ወጥ ዘዴ እንዲሰራ ✅ጥራት (Quality) እንዲጠበቅ ✅ደህንነት (Safety) እንዲረጋገጥ ✅የውል መስፈርቶች እንዲከበሩ https://t.me/ethioengineers1
Lap Splice (የብረት መቀጠያ) ✅የብረት ፋብሪካዎች የሚያመርቱት ስታንዳርድ የብረት ርዝመት 12 ሜትር ነው። ስለዚህ ረጅም ህንፃዎች ወይም ቢሞች ላይ ብረትን መቀጠል (Lap) ግድ ይላል። ✅የመቀጠያ ርዝመት (Lap Length): እንደ ዲዛይኑ እና እንደ ኮንክሪቱ ግሬድ የሚወሰን ቢሆንም፣ በግምት አብዛኛውን ጊዜ በሀገራችን 50×Φ (ሃምሳ ሲባዛ በብረቱ ዲያሜትር) ይወሰዳል። ለምሳሌ፡ የ Φ16 ብረት መቀጠያ ርዝመት 50×16 mm=800 mm (80 cm) መሆን አለበት። ቦታ (Location): ✅Beam ላይ: ከፍተኛ የቴንሽን (Tension) ዞን ላይ ብረትን መቀጠል አይፈቀድም። ለምሳሌ በቢም ታችኛው ክፍል መሃል ላይ (Mid-span) እና በቢም ላይኛው ክፍል ድጋፍ (Support) አካባቢ ላፕ ማድረግ አይመከርም። ✅Staggering: ሁሉም መቀጠያዎች በአንድ መስመር ላይ ማረፍ የለባቸውም። አንዱ ከተቀጠለበት ቦታ ወጣ ብሎ ሌላው እንዲቀጠል (Staggered) መደረግ አለበት። https://t.me/ethioengineers1
🙏RFI (Request for Inspection) ምንድን ነው? 👉RFI ማለት ተቋራጩ (Contractor) አንድ ሥራ ተጠናቆ እንደሆነ በመግለጽ፣ አማካሪው (Consultant/Engineer) መጥቶ እንዲመረምረው የሚያቀርበው የምርመራ ጥያቄ ነው። 👉 እዚህ የተጠቀሰው RFI ማለት Request for Inspection ነው። በአንዳንድ ፕሮጀክቶች RFI ማለት Request for Information ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህ በፕሮጀክቱ የሰነድ ስርዓት ውስጥ ያለውን ፍቺ መከተል አስፈላጊ ነው። 2. RFI መቼ ይቀርባል? RFI የሚቀርበው ሥራው ከመሸፈኑ (Cover) ወይም ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከመሄዱ በፊት ነው። ለምሳሌ፦ ✅ Excavation ከተጠናቀቀ በኋላ ✅ Rebar ከተገጠመ በኋላ ✅ Formwork ከተጠናቀቀ በኋላ ✅ Concrete Casting ከመጀመሩ በፊት ✅ Waterproofing ከመሸፈኑ በፊት 3. RFI የሚያካትተው ✅RFI Number ✅Project Name ✅Location ✅Activity Description ✅Drawing Number ✅Specification Reference ✅Inspection Date ✅Contractor Signature ✅Consultant Decision https://t.me/ethioengineers1
🙏በኢትዮጵያ የሚጠቀሙ የጨረታ ዓይነቶች 1. Open Tender (ክፍት ጨረታ) ✅ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟላ ተቋራጭ መወዳደር ይችላል። 2. Restricted Tender (ውስን ጨረታ) ✅የተመረጡ ተቋራጮች ብቻ ይሳተፋሉ። 3. Direct Procurement (ቀጥታ ግዥ) ✅በሕግ በተፈቀዱ ልዩ ሁኔታዎች ብቻ ይፈጸማል። https://t.me/ethioengineers1
✅IPC የሚያዘጋጁት ማን ነው? 👉Site Engineer – የተሰራውን ሥራ ይለካል። 👉Quantity Surveyor (QS) – IPC ያዘጋጃል። 👉QA/QC Engineer – የጥራት ሰነዶችን ያረጋግጣል። 👉Resident Engineer / Consultant – ያረጋግጣል እና ያፀድቃል። 👉Employer – ክፍያውን ይፈጽማል። https://t.me/ethioengineers1
🙏ለSite Engineer ወርቃማ ምክሮች ✅ሁልጊዜ ውሉን ያንብቡ። ✅የሚፈጠር ማንኛውም ለውጥ በጽሑፍ ያስመዝግቡ። ✅Site Diary በየቀኑ ይሙሉ። ✅ፎቶ ማስረጃዎችን ያስቀምጡ። ✅ማንኛውንም የውል ጉዳይ በቃል ሳይሆን በደብዳቤ ያረጋግጡ። https://t.me/ethioengineers1
⚡️በኢትዮጵያ የሚታዩ የContract Management ስህተቶች ❌ Variation በጽሑፍ ሳይፀድቅ ሥራ መጀመር ❌ Daily Records አለመያዝ ❌ EOT በሰዓቱ አለመጠየቅ ❌ Site Instructions አለመመዝገብ ❌ ሰነዶችን በአግባቡ አለማስቀመጥ https://t.me/ethioengineers1