tgindex
Ethiopian Architecture and Urbanism

Ethiopian Architecture and Urbanism

Статистика

It is a platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry inside Ethiopia. It will also include similar issues from across the world.

Последний пост
21:12
Последнее чтение
11:52
Постов за неделю
10
Всего постов
35
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
15 461
−2 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 975
28 постов
Вовлечённость
12,8%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 35
Упоминаний
6
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 623
1/48двое суток
1 859
1/72трое суток
2 006

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 21:121 11438

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 11337

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 10938

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 05738

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 05838

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 06038

    видео или голосовое, без подписи

  • 21:121 0523538

    የገዳ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ንድፍ ውድድር (ሁለገብ ሕንፃ) ​የአንደኛ  ደረጃ አሸናፊ ​ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ​ነዳፊ ፦ ሲጎር ኮንሰልት - አርክቴክቸር + ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ​የገዳ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት - “ባሊ፦ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር” ​በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሚገነባው የገዳ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ንድፍ ፣ በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚከናወነውን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ወይም ባሊን መሠረት ያደረገ ነው። ይህ የኪነህንጻ ጽንሰ-ሐሳብ፤ የአንድነት፣ የቀጣይነት፣ የኃላፊነት፣ የትብብር እና የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እሴቶችን ወደ ዘመናዊ የሕንፃ ጥበብ ይዘት የለወጠ ነው። • ​የሕንፃው ውጫዊ ገጽታ (Façade)፦ ሁለቱ አባ ገዳዎች በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የገዳውን ዘንግ ሲቀባበሉ የሚያሳየውን የእጆች እንቅስቃሴ በምሳሌያዊ ሁኔታ ይወክላል። • ​አምስቱ ቀጥታ የፊት ገጽታ ስብስቦች፦ አምስቱን የገዳ ፓርቲዎች (ሉባ) ይወክላሉ። • ​ማዕከላዊ የኦዳ ጥላ (Odaa Canopy)፦ የኦዳ ዛፍን እንደ ሕዝብ መሰብሰቢያ እና የኅብረተሰብ መገናኛ ማዕከልነት ያሳያል። • ​ወደ ውስጥ ገብ ብሎ የተሠራው ማዕከላዊ መስመር፦ የገዳውን ዘንግ በመወከል ቀጣይነትን እና የጋራ ኃላፊነትን ይገልጻል። • ​የሕንፃው መግቢያ፦ ከኦዳ ዛፍ ሥሮች መነሻነት የተወሰደ ሲሆን፣ ይህም መሪነትን፣ ማንነትን እና ልማትን ከጠንካራ የማኅበረሰብ መሠረት ጋር ያገናኛል። ​ኪነህንጻው  የባህል፣ የማንነት እና የጋራ ኃላፊነት ማንጸባረቂያ ሆኗል። ​የቦታው ስፋት፦ 6,579 ካሬ ሜትር በቴወድሮስ ገብረጻድቅ በኩል @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 13 авг.1 768134

    የመጀመርያው ድልድይ አዲስ አበባ። በ፲፱ነኛው (19ኛው) ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ድልድይ የተሠራው በእንጨት ሲሆን የሰጠውም ጥቅም አጭር ነው። እንዲሁም የመጀመሪያው የድንጋይ ድልድይ የተሠራው በ፲፱፻፪ (1902) በራሺያዊ ኢንጅነር ሲሆን ኢንጅነሩም ድልድዩን የሠራው አንድ ጓዳኛቸውን የቀበና ወንዝ ስለወሰደው በዚህ ሳቢያ በምኒልክ ሆስፒታልና በራሺያ ቆንስል መካከል በሚገኘው የቀበና ወንዝ ላይ የድንጋይ ድልድይ ተሠራ። ሁለተኛው የድንጋይ ድልድይ የራስ መኮንን ድልድይ ሲሆን የመጠሪያ ስያሜ ያገኘው ከተሠራበት ጊዜ አንስቶ ነው። (አዲስ አበባ ፲፰፻፸፱-፲፱፻፸፱ ኅዳር 1979 አዲስ አበባ ) በ ዘሪሁን ጉልቴ በኩል @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 12 авг.2 301144

    “አዳዲስ ሀሳቦች አሮጌ ሕንፃዎችን መጠቀም አለባቸው” እውቋ የከተማ ንድፈ ሀሳብ አመንጪ ጄን ጄኮብስ ከተሞች በቀላሉ የሕንፃዎችና የመንገዶች ስብስብ ብቻ ሳይሆኑ፤ በሰዎች፣ በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች፣ በስብጥርና ቀደም ሲል በነበሩ የታሪክ ሁነቶች ቅርፅ የሚይዙ ሕያውና እየተለወጡ የሚሄዱ ቦታዎች መሆናቸውን አሳስባናለች። “አዳዲስ ሀሳቦች አሮጌ ሕንፃዎችን መጠቀም አለባቸው” የሚለው እምነቷ፣ ነባሩ የከተማ ቅርፅና መዋቅር ለልማት እንደ ማደናቀፊያ ሳይሆን ፈጠራን፣ መላመድንና ቀጣይነትን ለማምጣት እንደ ጥሩ እድል እንድናየው ያደፋፍረናል። ​ታላላቅ ከተሞች የሚገነቡት በቅርሥ ጥበቃና በለውጥ (በሽግግር) መካከል በሚደረግ ሚዛን ነው። እንደ ህንጻ ነዳፊዎችና የከተማ ነዳፊዎች፣ ፍጹም የሆነ አዲስ ገጽታ ለማምጣት ስንል የከተማዋን ውስብስብ ተፈጥሮ ማጥፋት የለብንም፤ ይልቁንም ቀደም ሲል በጥሩ ሁኔታ እየሰራ ካለው ነገር መማር፣ መሻሻል ያለበትን ማሻሻልና አዳዲስ ሀሳቦች አሁን ባለው የከተማዋ ማንነትና ባህሪ ውስጥ እንዲያድጉ መፍቀድ አለብን። ከተማ እድገት እያሳየች መሄድ አለባት እንጂ መተካት የለባትም። ጽሁፍ። በ ቴዎድሮስ ገብረጻድቅ ( ህንጻ እና ከተማ ነዳፊ እንዲሁም መምህር) @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 12 авг.1 83064

    በ ጣልያን ወረራ ወቅት በአዲስ አበባ የነበሩት የጤና ተቋማት። (ከ1929-1933 ) ሃገራችን በፋሽስት ወረራ እጅ በወደቀችበት ወቅት አዲስ አበባ ውስጥ ቀደም ሲል ተቋቁመው የነበሩ የጤና ድርጅቶች ለወራሪዎቹ ለኢጣሊያውያን እንደሚስማሙ ሆነው ተደራጁ፤ ኢትዮጵያውያን ግን "በሽታ" እንዳያስተላልፉ የሚገለገሉባቸው ጥቂት የጤና ድርጅቶች ተዘጋጁላቸው። በዚሁ መሰረት 1. የቤተ ሳይዳ ሆስፒታል "ቪክቶሪያ አማኑኤል" የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ከ300-400 አልጋ እንዲይዝ ሆኖ ተደራጀ። 2. የምኒሊክ ሆስፒታል “ዲገሌ ኢብሩዜ" ተብሎ ለሁለት በመክፈልም አንዱ ወገን 700 አልጋ እንዲይዝ ሆኖ ለኢጣልያኖች በሌላም አካባቢ ከ150 አልጋ በላይ ሊይዝ የሚችለው 500 አልጋ ተዘርግቶበት ለኢትዮጵያውያን ተመደበ። 3. የዘውዲቱ ሆስፒታል "ማተርኒቲ ኢንፋኒሲያ" ተብሎ ለእናቶችና ሕፃናት ብቻ አገልግሎት ዋለ። ከነዚህ ነባር ሆስፒታሎች ሌላም በተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ሆስፒታሎች ተከፍተዋል፤ እነሱም አንደኛው የእቴጌ መነን ት/ቤት ይባል የነበረው 300 አልጋ እንዲይዝ ተደርጎ ለወታደሮቻቸው ሆስፒታል ሲሆን፤ ሁለተኛውም የራስ ሙሉጌታ ቤት ከ250 እስከ 350 አልጋ ያለው "ኤዊጂዝ" የሚል ስም አግኝቶ ለእነሱው ሠራተኞች ሆስፒታል ሆነ፤ ለሕፃናት መታከሚያ ደግሞ በኢጣልያን ኩንስሌት ግቢ ውስጥ በግራዚያኒ እናት ስም የተሰየመ ሆስፒታል ተቋቋመ። በክሊኒክ ደረጃም በ1929 እና በ1930 በተለይም የዓይን በሽታ ወደ ጣሊያኖች እንዳይሰራጭ ለዓይን ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች በብዛት ተቋቋመው ነበር፤ ኋላም በ1931 ለኢትዮጵያውያን መኖሪያ በተከለለው አካባቢ ማለትም በጉለሌ የፕሬስፒቴሪያንን ሆስፒታል ከ60- 80 አልጋ እንዲይዝ ተደርጎ “ኦሰፔዳሎ ፕርኮኝ ኢኖሩቢል እንጀኔ” የሚል ስም ተሰጥቶት ለኢትዮጵያውያን መታከሚያ ተመደበ። የአማኑኤል ሆስፒታል ከ80-120 እንዲይዝ ሆኖ እንደዚሁ ለኢትዮጵያውያን አገልግሎት ዋለ። ምንጭ:- አዲስ አበባ ፲፰፻፸፱-፲፱፻፸፱ ኅዳር 1979 አዲስ አበባ በ ዘሪሁን ጉልቴ በኩል። @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 8 авг.2 521

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.2 22785

    የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ወደ ሙሉ ትግበራ ሊገባ መሆነ ተገለፀ ነሐሴ 01/2018ዓ.ም አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ያወጣው በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህንፃዎች ከፍታ፣ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና የህዝብ ቁጥር እድገት ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና የህይወትና ንብረት ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብና መመሪያው ላይ ለህብረተሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው የሚሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ደንቡን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሐመድ በመግለጫቸው እንደተናገሩት የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ፣ ቁጥጥር ፣ ፍተሽና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 163/2017 የከተማችንን ህብረተሰብ ህይወትና ንብረት ከአደጋ ስጋት ለመጠበቅ የወጣ ደንብና መመሪያ ነው። የደንቡ ዋና ዓላማ በከተማዋ ውስጥ አደጋ እንዳይደርስ አስቀድሞ መከላከል እንደሆነ ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም አደጋ ከደረሰ በኋላ ይደረግ የነበረውን የመከላከል ተግባር ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ ወደ መከላከል ያሸጋገረ አሰራር መሆኑን አብራርተዋል። ኮምሽነር አህመድ አያይዘውም መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ መሆኑን በመጠቆም፣ ተቋሙ በከተማዋ የሚገኙ ተቋማትን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ የፍተሻና ቁጥጥር ስራ በማካሄድ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርቲፋይድ) የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በደንቡ መሠረት ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንፃ፣ የንግድ ተቋም ወይም አደገኛ ንጥረ ነገሮችን የሚያከማች ድርጅት በየዓመቱ ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ደህንነት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የመያዝ እና የማደስ ግዴታ ተጥሎበታል። ተቋማትና የህንፃ ባለቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የውሃ መቅጃ ሀይድራንት (Hydrant)፣ የእሳት ማጥፊያ ሲሊንደሮች፣ የጭስ ማወቂያዎችና የስፕሪንክለር ስርዓት የመገጠም እንዲሁም በህንፃ ዲዛይኖቻቸው ውስጥ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ መንገዶችን የማካተት ግዴታ አለባቸው። የተጣሉ የደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ በሚገኙና ህጉን በሚጥሱ አካላት ላይ እንደ ጥፋቱ ደረጃ ከብር 10,000.00 እስከ ብር 100,000.00 የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት የሚጣል ሲሆን፣ በተጨማሪም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላስተካከሉ ተቋማት የንግድና ስራ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ የሚደረግ ይሆናል። ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡ ምንጭ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 8 авг.1 5513

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.1 71067

    በኢትዮጵያ የሊፍት ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈረመ በኢትዮጵያ በአሳንሰር ወይም በሊፍት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚታየውን የአገልግሎት እና የጥገና ክፍተት ወደተሻለ ደረጃ ለማሻገር የሚያስችል የጋራ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የተፈራረሙት ሀገር በቀሉ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሞናጎ ኢሊቬተር እና የቱርኩ ኬ. አር. ሲ ኢሊቬተር ኩባንያ ናቸው። ላለፉት አምስት ዓመታት አብረው ሲሰሩ የቆዩት ሞናጎ እና ኬ. አር .ሲ ኢሊቬተር ኩባንያዎች፤ አሁን ላይ ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር በኢትዮጵያ የሊፍት ማምረቻ ፋብሪካ በጋራ ለመገንባት ተስማምተዋል። የሞናጎ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ኢሳያስ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ በሀገሪቱ የሊፍት ቴክኖሎጂ ላይ የሚታዩ መሰረታዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል። በተለይም ቀደም ሲል በግዢ እና በጨረታ ሂደት የሚገጠሙ ሊፍቶች ከሽያጭ በኋላ በቂ የጥገና አገልግሎት እና የስፔር ፓርት አቅርቦት ባለማግኘታቸው ምክንያት ስራ የማቆም ችግር ይገጥማቸው እንደነበር ጠቁመዋል። አዲሱ አጋርነት ይህንን ክፍተት በመሙላት የቅርብ ክትትል፣ የጥገና እና የስፔር ፓርት አቅርቦትን አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል። በስምምነቱ መሰረት የመንግስት የመሬት አቅርቦት ድጋፍን በመጠቀም የሚገነባው ይህ ፋብሪካ፤ የቱርኩን የላቀ ማሽነሪ እና ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን በመስጠት ዘላቂ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ ታቅዷል። ይህ የጋራ ኢንቨስትመንት ምርቱን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ማምረት ሲጀምር፤ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን፣በህንፃዎች ላይ የሚገጥሙ የአሳንሰር ስራ ማቆም ችግሮችን ለማስወገድ እና በዘርፉ አዲስ የኢንዱስትሪ ደረጃን ለመፍጠር ሚና እንደሚጫወት ተመልክቷል። ምንጭ። Ethio FM 107.8 @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 7 авг.2 236175

    ሚዛን እና ምጣኔ (scale & proportion) ናይል ሶርስ ህንጻ፣ ቦሌ መንገድ በ ዘለቀ በላይ የተነደፈ አዲስ አበባ ዘለቀ በላይ ሚዛን እና ምጣኔን ባልተለመደ ሁኔታ በመነካካት የእይታ ውጥረትን እየፈጠረ ህንጻዎቹ ለእይታ ሳቢ እንዲሆኑ ማድረግ የቻለ በሳል ህንጻ ነዳፊ ነው። የህንጻው አካላትን ልኬት ለመረዳት የግዴታ ሚዛን ሰጪ ሰዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሚያስፈልጉት ሲሆን፣ ባልተለመደ መልኩም የህንጻው አካላት ምጣኔ ከለመድናቸው የህንጻ አካላቶች ይለያሉ። በዘለቀ ህንጻዎች ላይ የተለመዱት የወለል ክፍልፋዮች አለመኖራቸው፣ ክፍተቶች እርሱ በፈለገው መልኩ ወለልን ሳይጠብቁ በመከፈታቸው ፣ የህንጻ እካላቶች ያልተለመዱ ልኬቶች  መያዛቸው፣ እንዲሁም በውስጣዊ ንድፉ ላይ ወለልን ሳይጠብቁ የሚዘረጉ ተዳፋታዊ መተላለፊያዎች ለዚህ የሚዛን እና ምጣኔ ውጥረት አስተዋጽኦ አድርገዋል። ይህን የሚዛን እና ምጣኔ ውጥረት በሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ላይ እንዴት ይገልጸው ይሆን? ዘለቀ የሰማይ ጠቀስ ህንጻ እስከአሁን በይፋ አላበረከተም። እሱ የነደፈው እና አሁን በሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ላይ የሚገኘው ሰማይ ጠቀሱ የኦሮሚያ ኦንሹራንስ ህንጻ ይሄንን ውጥረት ያሳየን ይሆን? ጽሁፍ እና ምስል። ዳዊት በንቲ @ethiopianarchitectureandurbanism

  • 6 авг.1 8942

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.2 10772

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.2 4882

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.2 2772

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.2 1412

    видео или голосовое, без подписи