ኢትዮጲክ -Ethiopique
СтатистикаLocal News for the DMV area Ethiopians and Eritreans.
- Последний пост
- 00:22
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 23
- Всего постов
- 93
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 590
- 1/48двое суток
- 676
- 1/72трое суток
- 729
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በነገው የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ ላይ ሐሙስ ስላከበርነው የቢውልት ሂር ዊዝ ኢትዮጲክ ተጨማሪ መረጃዎች፤ በመጪው ዊኬንድ በዲሲ ናሽናል ሞል አካባቢ ስለሚኖረው የመኪና ውድድርና የሚዘጉ መንገዶች፤ ስለ ዲ ኤም ቪ አካባቢ ባክ ቱ ስኩል መረጃዎችና የሹፌሮችን መረጃ ስጡኝ አልሰጥህም የፌደራል መንግስትና የስቴቶች እሰጥ አገባ በትራክ ድራይቨሮች (የሲ ዲ ኤል አሽከርካሪዎችን መረጃዎች) በሚመለክት ... ሜሪላንድ፤ ዲሲና ቨርጂንያን ጨምሮ የፌደራል መንግስትን ፍርድ ቤት ያቆሙበት ሌላኛው ጉዳይ ሆኗል። ይህን ሁሉ በነገው ዲጂታል ጋዜጣችን ይመዝገቡና በቀጥታ በኢሜይልዎ ይደርስዎታል። - https://mailchi.mp/eef309e2301b/ixe7m6uotn
ማስታወቂያ -- አመታዊው የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ ... የቤተሰብ መዝናኛ 🗓️ - ሴፕቴምበር 6 - 2026 📍- ዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ - ቬተራንስ ፕላዛ ሙሉ ቀን አዘጋጅ - የኢትዮጵያውያን ኮሚውኒቲ በሜሪላንድ
አይስ (ICE) ሙሉ በሙሉ ይፍረስ ወይስ ማሻሻያ ይደረግበት? በዲሞክራቶች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳው አከራካሪው ውሳኔ እና የድንበር ጉዳዮች ኃላፊ ቶም ሆማን "አደገኛ መዘዝ ያስከትላል" ሲሉ የሰጡትን ጠንካራ ምላሽ ያካተተውን ሙሉ ዘገባ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ። ዝርዝሩ 👇🏾 https://ethiopique.com/democrats-disagree-over-abolishing-or-reforming-ice-dnc-meeting/
የዲሲ ነዋሪ ከሆኑ ከኦገስት 23 በፊት ሊንኩን ተጭነው ያመልክቱ https://direc.to/oACG
የታዳጊዎች እግር ኳስ ተሰጥኦዎችንና ማህበረሰቡን በአንድነት ያሰባሰበው «የኢትዮጵያ ወጣቶች አንድነት ዋንጫ 2026» ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ቀጥሏል። ስለ ውድድሩ ዝርዝር ሁኔታ እና የተካተቱትን መርሃ ግብሮች ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ።👇🏾 https://ethiopique.com/greatest-haile-soccer-academy/
ማስታወቂያ.....በዲ ኤም ቪ አካባቢ ያሉ አንዳንድ ከተማዎች እስከ 50ሺህ ዶላር ለቤት መግዣ እንደሚሰጡ ያውቃሉ?... የዛሬ ከሰዓት ፕሮግራማችሁን ከመዓዛ ጋር አድርጉ... ትማሩበታላችሁ.. በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ቤት ልግዛ ቢሉ እርስዎን በገንዘብ የሚደግፉ ፕሮግራሞች የተኞቹ እንደሆኑና እንዴት ማመልከት እንደምትችሉ ታሳውቃችኋለች። ሊንኩን ተጭነው ይሳተፉ። -- በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ያሉና ለቤት ገዢዎች የሚሰጡ ግራንቶች፤ የክሎዚንግ ኮስት አሲስታንስና የመሳሰሉትን በሚመለከት የመማሪያና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም። - ኦገስት 15 ከሰዓት 4pm ጀምሮ -በመአዛ ኤሮም ሊንኩን ተጭነው ይመዝገቡ - https://us06web.zoom.us/meeting/register/XdoloLyQRG-uIBUlTXgOBg#/registration
ማስታወቂያ -- የኢትዮጵያ አዲስ አመት ክብረበዓል ከሞንጎምሪ ኮሌጅ We would love for you to join us as we celebrate the Ethiopian New Year with a wonderful day of culture, community, and connection! 📅 Saturday, August 29, 2026 ⏰ 11:00 a.m.–3:00 p.m. Bring your family and friends and enjoy an afternoon filled with: 🎶 Live Ethiopian cultural music and entertainment 🛍️ Ethiopian cultural vendors 📚 Montgomery College Workforce Development and Continuing Education (WDCE) and EOC information tables ☕ Traditional Ethiopian coffee ceremony 🤝 Community resource tables and cultural exhibits 🎉 Family-friendly activities and opportunities to connect and network Whether you are reconnecting with your culture, discovering something new, or exploring educational and workforce opportunities at Montgomery College, there will be something for everyone!
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የማህበረሰብ ኃብት ግንባታ ፕሮግራማችንን የማስጀመሪያ ስራ ትላንት በ ኤም ኤንድ ቲ ባንክ ኤክስኪውቲቭ ቢሮ አንድ ብለን ጀምረናል። ዝርዝሩን በቅርብ ይዘን እንመለሳለን። በዚህ ፕሮግራም ላይ በዋናነት የተንሸራሸረው ኃሳብ ሰዎች እንዴት በቡድን ሆነው አንድን አላማ ማሳካት እንደሚችሉ፤ እና ይህንን አላማ ለማሳካትም ምን አይነት ድጋፎች እንዳሉ በፕሮግራሙ ላይ ተጋብዘው ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡን የተለያዩ ባለሞያዎች እውቀታቸውን አጋርተውናል። በዚህ አጋጣሚ በፕሮግራሙ የታደሙትንና ባለሞያዎቹን እንዲሁም ይህ ፕሮግራም እውን እንዲሆን በገንዘብም በቴክኒካል ድጋፍም ያገዙንን ድርጅቶችና የስራ ባልደረቦቻችንን ከልብ እናመሰግናለን።
ማስታወቂያ ጆንስ ሆፕኪንስ የነርሲንግ ትምህርት ቤት (Johns Hopkins School of Nursing) በውጭ አገር የተወለዱ ስደተኛ ሴቶች ስለ ቢሼፕ (BSHAPE) የምርምር ጥናት የበለጠ እንዲማሩ እየጋበዘ ይገኛል። ዕድሜዎ 18 ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ፣ የማንኛውም ዘር ወይም ዜግነት ያላቸው በውጭ አገር የተወለዱ ስደተኛ ሴት ከሆኑ፣ ደጋግመው ለሚከሰቱ አስጨናቂ የሕይወት ተሞክሮዎች ተጋልጠው የሚያውቁ ከሆነ፣ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ ከኢንተርኔት ጋር መጠቀም የሚችሉ ከሆኑ ለዚህ ጥናት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ፦ https://nursing.jhu.edu/bshape/bshape-about-the-research-study/ ለጥያቄዎች በ 443 203 8628 ይደውሉ ወይም በ bshape@jhu.edu ኢሜይል ያድርጉ።
የትምህርት ዘመኑ ሲቃረብ በዲኤምቪ ዙሪያ በትምህርት ቤት ዞኖች አዳዲስ የፍጥነት ካሜራዎችና ጥብቅ የቁጥጥር ሕጎች እየተተገበሩ ነው። በአርሊንግተን፣ ሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ዲ.ሲ. ያሉትን የቅጣት መጠኖች እና የሕግ ልዩነቶች በማወቅ ከድንገተኛ ቅጣቶች ይጠበቁ! ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ። 👇🏾 https://ethiopique.com/dmv-school-zone-speed-cameras-2026/
የኢትዮጵያውያኗ የቆዳ ውጤቶች ብራንድ ሰገን ሌዘር ክራፍትስ (SEGEN Leather Crafts) ስምንተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን «ዘ ሰገን ኢቮሉሽን» በተሰኘ ልዩ የቦርሳ ፋሽን ትርኢት በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ሊያከብር ነው። ከማገገም የተጀመረው እና አሁን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እያደገ ያለው የዚህ ብራንድ ጉዞ እና የዝግጅቱን ሙሉ መረጃ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ! https://ethiopique.com/segen-leather-crafts-eight-years-evolution-arlington/