- Последний пост
- 13 мар.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ውድ በ2017ዓ.ም በኬፕለርና በተባባሪ ኮሌጆቹ በ GEP ፕሮግራም ሰልጥናችሁ የተመረቃችሁ በተለይም በአካውንቲንግ ፡ አይሲቲና ማርኬቲንግ ተመርቃችሁስራ ያላገኛችሁ ተመራቂዎች ፡ እፎይ የሞግዚት እና የቤት አያያዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በኦፕሬሽን ኦፊሰር ፡ በሶሻል ሚዲያና በስራትስስር የስራ ዘርፎች ላይ አወዳድሮ ተመራቂዎችን መቅጠር ስለሚፈልግ ፍላጎት ያላችሁ በ0973409940 ወይም 0973405540ላይ በመደወል መረጃውን ከኬፕለር እንዳገኛችሁ በመግለጽ ለፈተና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የስራ ቦታ መገናኘ ደራርቱሞል አጠገብ
без подписи
ውድ በ2017 ዓ.ም ብቻ በኬፕለርና በተባባሪ ኮሌጆቹ ትብብር በ GEP ፕሮግራም ሰልጥናችሁ የተመረቃችሁና እስካሁን ስራ ያላገኛችሁ ተመራቂዎች ኬፕለር በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ቢሮዎች ውስጥ ለሚሸጡ ዲኮደሮች የሽያጭ ኮንትራት ስራ ከታስክ ሞቢ ጋር ስላመቻቸ በተለይም ስራ ለማግኘት አስቸጋሪ በሆኑት ፊልዶች የተመረቃችሁ ተማሪዎች እንድትመዘገቡ አመቻችተናል፡፡ ስለስራው ማብራሪያ 1) ደሞዝ ፡ በወር 7680 እና ተጨማሪ ኮሚሽን 2) ፆታ ፡ ሴት 3) የምዝገባ ቀን ፡ ህዳር24 እና 25 ጠዋት 2018 ዓ.ም ብቻ 4) የምዝገባ ሂደት ፡ ከስርበተቀመጠው ስልክ ደውሎ መመዝገብና ሲጠሩ ዝግጁ ሆኖ መገኘት 5) የስራ ቦታ ፡ በተለያዩ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከሎች
ውድ በኬፕለርና በተባባሪ ኮሌጆች በ GEP ፕሮግራም ሰልጥናችሁ በማንፋክቸር: በኢዱስተሪ ማሽን ኮነትሮል: በኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ፊልድ የተመረቃችሁና በተልይም ሴት ተመራቂዎች ሄንከን ኢትዮጵያ በማሽን ኦፕሬቲንግ እና ፓኬጅ ዘርፍ የስራ እድል አመቻችቷል:: በመሆኑም በእድሉ ለመጠቀም የምትፈልጉ ተመራቂዎች ለመመዝገብ በተዝጋጀው ሊንክ ውስጥ በመግባት በቀጥታ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን ፡፡https://docs.google.com/forms/d/1W6JLDOLrcdycv_iANIn3SR3a_ZrBpy5P2rprVDGn4Tc/edit
የ2017 ስራ ዓውደ ርዕይ አንድ ቀን ብቻ ቀረው። ዝግጁ ናችሁ? ለማስታወስ ያህል የሚከትሉትን ነገሮች ማድረጋችሁን አረጋግጡ! -Resume ሰርታችሁ ጥቂት ኮፒዎችን ፕሪንት አድርጋችሁ/QR ኮድ አውርዳችሁ በስልካችሁ መያዛችሁን። -ይህንን ሊንክ ተጠቅማችሁ መመዝገባ። -ለስራ ቦታ ተገቢ የሆነ ልብስ ማዘጋጀታችሁን ። -ራሳችሁን ለቀጣሪዎችና ለተለያዩ ግለሰቦች ለማስተዋወቅ መዘጋጀታችሁን/Personal Pitch።
የ2016 የስራ ዓውደ ርዕይ 40 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች በላይ እና 300 በላይ በተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተመረቁ የፖሊቴክኒክ ተመራቂዎች የተሳተፉበት ነበር። ዘንድሮ 60 አካባቢ ቀጣሪ ድርጅቶች እና 1200 በላይ ተመራቂ ተማሪዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚታሰበው የስራ ዓውደ ረእይ ማክሰኞ ነሃሴ 20 2017 በ አዲሳአበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይካሄዳል። ትሳተፉ ዘንድ ተጋብዛችኋል። መልካም ዕድል!
без подписи
ለስራ ዓውደ ርዕዩ እንዲረዳችሁ ይህንን ቪዲዮ እንድትመለከቱ ጋብዘናችኋል። መልካም ዝግጅት!
ራስን ለቀጣሪዎችና ለተለያዩ ግለሰቦች ማስተዋወቅ የሚያስችሉ 4 ጥቆማዎች 1.ራስን ማስተዋወቅ፣ ስም ከነ አባት እና አግባብ ያለው ሰላምታ:: 2.የሙያ ብቃትን ማጋራት፣ ያለንን የትምህርት ዝግጅት ሙያዊ ክህሎቶች እና የስራ ልምድ ጠቅለለ ባለ መልኩ መናገር ሲሆን ከምናናግረው ሰው/ድርጅት ተወካይ ዓላማና ተግባር ጋር ማገናኘት ብሎም ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማተኮርና አጽዖት መስጠት ያስፈልጋል። 3.ፍላጎትን በግልጽ ማሳወቅ፣ እያናገረን ካለው ሰው ምን እንደምንፈልግ/እንደምንጠብቅ መግለጽ።ይህም ያሰባችሁት ወይም የፈለጋችሁት የስራ ዕድል፡ ምክር፡ ትብብር፡ወይም የስር ላይ ልምምድና ወዘተ መሆኑን መግለጽና ማስረዳትን ያካትታል። 4.ቀጣይ የቤት ስራ ላይ መስማማት፣ ምን እንደምትጠብቁና ምን እንደሚጠቀምባችሁ በመስማማት መጨረስ ይህም የስልክ ፡ የአካል፡ ወይም የኢሜይል ክትትል ማድረግን ያካትታል።
ለስራ ዓውደረዕይ የሚሆን የ CV አዘገጃጀት መመሪያ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ!
በስራ ቦታ ላይ ያሉ ግንኙነቶችን ውጤታማ ማድረግ እንዴት ይቻላል? -ቀለል ያለ የእጅ ሰላምታ መስጠት። -የሰዎችን ማዕረግና ስልጣን በመጠቀም መጥራት። -ለታላላቆችና የሃላፊነት ቦታ ላሉ ሰዎች ጎንበስ በማለት ሰላምታ መስጠት። -ሰላምታ ለመጨረስ አለመቸኮል በተጨማሪ የግል የስራ የቤተሰብ ጉዳዮችንም መጠየቅ። -ቢዝነስ ካርድ ሲሰጣችሁም ሆነ ስትሰጡ በቀኝ እጃችሁ ወይም በሁለት እጃችሁ ቢሆን ይመረጣል። -በእርጋታ እና በአክብሮት መናገር። -የተብራሩና ገላጭ ቃላትን መጠቀም እንዲሁም የሌሎችን የቋንቋ ዘይቤና አነጋገር ማክበር ። የስራ አውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን ለማወቅ ይህንን ሊንክ ይጫኑ!
ውድ የGEP የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች፤ ነሃሴ 20,2017 ዓ.ም የሚካሄደው የስራ ዓውደ ርዕይ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል። ከ50 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች እናንተን ለማግኘት ይመጣሉ። በስራ ዓውደ ርዕይው ላይ የሚገኙትን ድርጅቶች ለማወቅ ይህንን ሊንክ(https://shorturl.at/N34sz) ይጫኑ። ስራ እንዴትና የት መፈለግ ይቻላል? .የስራ ማስታወቂያ በማንበብ፥ ይህም ጋዜጦች፣የስራ ዌብ ሳይቶች፣ማስታወቂያ ሰሌዳዎችን ያካትታል፡ የድርጅቶች ድረ ገጾች፥ ልትሰሩባቸው ፍላጎት ያላችሁ ድርጅቶች ድረ ገጾች በመጎብኘት በግልና በቤተሰብ በምናቃቸው ሰዎች፥ ቤትሰብን ጨምሮ ባቅራቢያችን ያሉ ሰዎችን ማናገር እንዲሁም ማማከር የተለያዩ የስራ ዕድሎችንና ጠቃሚ ምክሮችን ያስገኛሉ የሰዎች ጥቆማዎች፥ አሰልጣኞቻችሁ፡ የስራ ላይ ልምምድ አብረዋችሁ የሰሩ ሰዎች፣ ጓደኞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች የስራ ጥቆማዎች እንዲሰጧችሁ መጠየቅና መጠቀም የስራ ዓውደ ርዕዮችን አየፈለጉ መሳተፍ፥ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ለመገናኘት ብሎም ስራ ለማመልከት እድል ይፈጥራል የGEP ዓውደ ርዕይ የነገ ሳምንት ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል። ተዘጋጁ!
без подписи
ውድ በኬፐለር ሰልጥናችሁ ለባለፉት አምስት አመታት ከንፋስስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተመረቃችሁ የቀድሞና የዚህ አመት ሰልጣኞች ብቻ የኮሌጃችሁ የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ማህበር እንዲመሰረት ያግዝ ዘንድ ከስር ባስቀመጥነው የጎግል ፎርም ሊንክ በመግባት መረጃ እንድትሞሉ የማህበሩ አባል እንድትሆኑ በማክበር እንጠይቃለን፡፡ https://forms.gle/QaS5A19YADfck53P7
без подписи
“ ለሦስት አሸናፊዎች እስከ 20 ሺሕ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል ” - ሄፈን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ 500 ወጣቶችን የሚያሳትፍ፣ ሦስት አሸናፊዎችን እስከ 20 ሺሕ ዶላር የሚያሸልም የግብርና ቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ሄፈር ኢትዮጵያ ገለጸ። ውድድሩ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን፣ የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል፣ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ፈጠራ አቅም ለማጎልበት ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ከዛሬ (ግንቦት 13/2017 ዓ/ም) ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአዩቲ ድረገጽ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ድርጅቱ ጠቁሟል። የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን በየትኛውም ክልል ያሉና የግብርና ቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ የማቅረብ አቅሙ ያላቸው ወጣቶች መሳተፍ እንደሚችሉም አዘጋጆቹ አብራርተዋል። ሽልማቱን የሚያገኙት እነማን ናቸው ? ከሚቀርቡት 500 የፈጠራ ውጤቶች መካከል በጣም የተሻሉ ተብለው የሚመረጡ ሦስት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የሽልማቱ አሸናፊዎች ይሆናሉ። በዚህም ፦ - አንደኛው አሸናፊ 10 ሺሕ ዶላር - ለሁለተኛ አሸናፊ 6, 500 ዶላር - ሦስተኛው አሸናፊ ደግሞ 3, 500 ዶላር ይሸለማሉ ተብሏል። ውድድሩን አሸናፊዎችስ በተዋረድ እንዴት ይለያሉ ? ይቀርባሉ ተብለው ከሚጠበቁት 500 ገደማ የግብርና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች መካከል 30ዎቹ ልምድ ባላቸው ዳኞች ተገምግመው ይመረጣሉ። 30 የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችም ተወዳድረው የሚያሸንፉ 10 የፈጠራዎች ባለቤቶች ለአምስት ቀናት ስልጠና ይወስዳሉ። 10 የሚሆኑት ደግሞ ለመጨረሻ ውድድር ቀረበው ሦስቱ አሸናፊዎች ይመረጣሉ። ኦንላይን መመዝገቢያው https://ayute-ethiopia.et መሆኑ ተጠቁሟል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Job Title: Machin Operator III Job Type: On-site - Permanent (Full-time) Work Location: Addis Ababa, Ethiopia Salary/Compensation: Monthly Deadline: May 17th, 2025 Description: Duties: - Make sure that the machine and environment is clean and safe for operation. - Make sure the raw material is as per the company standard. - Precautions, protects and preserves ... [view details below] __________________ Repi Soap & Detergent PLC Verified Company ✅ 18 Jobs Posted __________________ From: afriworket.com | @freelanceethbot | @freelance_ethio | @afriworkamharic
ሰላም👋 የTVET ወይም የ Kepler ተመራቂዎች, የፊታችን ዓርብ እና ቅዳሜ ማለትም (ሚያዚያ 3, 2017 እና ሚያዚያ 4, 2017) ከ 94 በላይ የሥራ ቅጥር ፍላጎት ያላቸው Company (ድርጅቶች)( የTVET ተመራቂ የሆኑ ወጣቶችን ለመቅጠር) የሚገኙበት Job fair(የሥራ አውደሪ) ስለተዘጋጀ :- Job fair ላይ ለመሳተፍ የQR Code registeration ግዴታ ስለሆነ መሳተፍ የምትፈልጉ ልጆች ከላይ በቀረበላችሁ ሊንክ እንድትመዘገቡ በአክብሮት ልናሳስባችሁ እንወዳለን:: ማሳሰቢያ:- ይህንን QR Code ያላገኘ ተመራቂ Job Fair ላይ መሳተፍ አይችልም/አትችልም::
без подписи
የስራ አውደ ርዕይ ማስታወቂያ ውድ በ2016 ዓ.ም በኬፕለርና በተባባሪ ኮሌጆቹ ሰልጥናችሁ የተመረቃችሁ እስካሁን ስራ ያላገኛችሁ ሰልጣኞች፡ ደረጃከደንቦስኮ ጋር በመተባበር ሚያዝያ 3 እና 4 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ አውደ ርዕይ በሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ ከ70 ያላነሱ የተለያዩ ቀጣሪዎች ይገኛሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በአውደ ርዕዩ ላይ ለመሳተፍ ደረጃ ባዘጋጀው ገለጻና አጭር ስልጠና ላይመገኘት የግድ መሆኑን እያሳወቅን ለዚሁ ይረዳ ዘንድ ሶፍት ኮፒ ሲቪና የስራ ማመልከቻ አዘጋጅታችሁ ነገ መጋቢት 30 ቀን 017ዓም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ በተግባረ ዕድ ኮሌጅ ግቢ እንድትገኙ ናሳውቃለን፡፡ እንደማሳሰቢያ ነገ ስልጠናውን ያልተሳተፈና ያልተመዘገበ ማንኛውም ተመራቂ ስራ አውደ ርዕዩ ላይ መገኘት እንደማይችል በማወቅ ስራ ላላገኙ ጓደኞቻችሁ ይህንን መልዕክትእንድታስተላልፉና ከሌላ ኮሌጅ የምትመጡ መታወቂያ እንድትይዙ እናሳውቃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ፡ የተግባረ ዕድ ኮሌጅ የስራ ትስስር ቢሮ ሃላፊ አቶ ታከለ ደጀኔን በ 0916830056 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::