General Wingate Polytechnic college-Official channel
Статистикаራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን። የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 166
- 1/48двое суток
- 2 482
- 1/72трое суток
- 2 677
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ላይ! 🇪🇹🌍 PICE በASEB 2026 የTOP 5 የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ውስጥ መመረጡን በደስታ እንገልጻለን። ይህ የሽልማት ውድድር ብቻ አይደለም። ይህ የኢትዮጵያን የፈጠራ፣ የቴክኒክ ክህሎት፣ የሥራ ፈጠራ እና የምርታማነት አቅም ለአፍሪካ የምናሳይበት እድል ነው። 🗳️ ለPICE ድምጽዎን ይስጡ! 🙏 ይምረጡ 📲 ያጋሩ 👥 ጓደኞችዎን ያሳትፉ 🌍 የኢትዮጵያን ድምፅ በአፍሪካ ያሰሙ! አንድ ድምፅ። አንድ ድምጽ ማሰማት። አንድ የአፍሪካ ተፅዕኖ። 🇪🇹🌍 VOTE ON;- https://www.asebs.com/finalists/productivity-improvement-center-of-excellence-coworking-space
ሐሙስ:- ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ∙ም የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ድህረ-EASTRIP ፕሮጀክት ዘላቂነት የሚያረጋግጥ የምክክር መድረክ ተካሄደ!! የEASTRIP ፕሮጀክት መጠናቀቅን ተከትሎ የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል የሚያስችል የዘላቂነት ማስተር ፕላን ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ። በዚህ መድረክ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች፣ የኢንዱስትሪ ተወካዮች ተሳትፈዋል። የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተቋማት ከፕሮጀክት ጥገኝነት በመውጣት ራሳቸውን ችለው መቀጠል እንዲችሉና ከፕሮጀክት ድጋፍ ወደ መንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) የሚሸጋገርበትን ስልታዊ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል። በግምገማው ወቅት ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ኮሌጁ ራሱን ችሎ መቀጠል እንዲችል የውስጥ የገቢ አቅሙን የሚያሳድግበት ስልታዊ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን ሌሎች ኮሌጆችም የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን መልካም ተሞክሮ በመውሰድ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ መነቃቃት ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተመላክቷል። በአሁኑ ወቅት በአጋርነት ከጀነራል ዊንጌት ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት አሳይተው ወደ ሥራ የገቡ በርካታ አካላት መኖራቸውንና በቀጣይም አብረው ለመሥራት አቅደው በዝግጅት ላይ ያሉ በርካቶች መሆናቸው ተገልጿል። ከጋራ ውይይቱ በተጨማሪ በተካሄዱ ተናጠል ስብሰባዎች የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የኮሌጅ ዲኖች በግልና መንግሥት አጋርነት (PPP) አተገባበር ዙሪያ ትኩረት አድርገው የመከሩ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የአድቫይዘሪ ቦርድ አባላት በበኩላቸው የነበራቸውን የሥራ እንቅስቃሴና አፈፃፀም ገምግመው በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቱ ለሀገሪቱ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በማድነቅ በቀሪው የፕሮጀክት የሥራ ጊዜ የሚከናወኑ ተግባራት በግልጽ ዕቅድና መሪ አቅጣጫ እንዲመሩ በጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በተለይም በኮሌጆችና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ቅንጅትና ትስስር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ የቀረበ ሲሆን ውይይቱ የኮሌጆችን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ ትልቅ መሠረት የጣለ እንደነበር ተጠቁሟል። "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ማክሰኞ:- ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በድምቀት የተጠናቀቀው የጀነራል ዊንጌት የክረምት እግር ኳስ ውድድር ሻምፒዮን ሆነ! በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲካሄድ የቆየው የአሰልጣኞች የክረምት ስፖርታዊ የእግር ኳስ ውድድር እጅግ ማራኪ እና ፉክክር በታከለበት የፍፃሜ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተጠናቋል። በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የዋንጫ ጨዋታ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንትን ድንቅ ብቃት በማሳየት የዘንድሮው የዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል። ለፍፃሜው ደርሰው ዋንጫውን ለማንሳት የተፋለሙት አይሲቲ ዲፓርትመንት (Wingate Best) እና ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ያደረጉት ጨዋታ በእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ነበር። ከጨዋታው በፊት ለዋንጫው ሰፊ ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የአይሲቲ ዲፓርትመንት ተጫዋቾች የጨዋታ የበላይነት በመውሰድ የመጀመሪያውን ግብ ከመረብ ጋር ማዋሃድ ቢችሉም ኮንስትራክሽኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ አቻ የሚያደርጋቸውን ግብ አግኝተዋል። ከእረፍት መልስም ሁለቱም ቡድኖች በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ጨዋታ በማሳየት ተጨማሪ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። አይሲቲዎች በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ ወስደው ወደ ግብ ክልል በተደጋጋሚ በመድረስ ሙከራዎችን ቢያደርጉም የኮንስትራክሽኑን ግብ ጠባቂ ማለፍ እና ኳስ ከመረብ ማገናኘት አልተቻላቸውም። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ግብ ጠባቂ የሆነው ዘካሪያስ ገብሬ የዕለቱ ኮከብ በመሆን አድምቋል! ዘካሪያስ ሁለት የአይሲቲ ቅጣት ምቶችን ድንቅ በሆነ ብቃት አምክኖ ቡድኑን ታድጓል። አይሲቲዎች በበኩላቸው የተሰጣቸውን ኳሶች መከላከል ባለመቻላቸው ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በ2 የግብ ልዩነት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል። ከዋንጫው ጨዋታ አስቀድሞ የደረጃ ፍልሚያ የተካሄደ ሲሆን ጀነራል መካኒክስ /GM/ (Iron Man) ከአግሮ ቢዝነስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ጀነራል መካኒክስ ተጋጣሚውን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የ3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በውድድሩ መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁት ዲፓርትመንቶች ደማቅ የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተካሂዶ የዘንድሮው የክረምት እግር ኳስ ውድድር በስኬት ተጠናቋል። "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи