ጉባኤ ቅዱሳን መንፈሳዊ ማህበር ቻናል✝️🙏💐🤝
Статистикаሰላም ይህ ቻናል ቅዱስ ወንጌል ለመማር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ያሉ አባቶችና ወጣቶች የተከፈተ ማህበር ነው ስለዚህ ቅዱስ ወንጌ ለመማር ፍላጎቱና ጥማቱ ያለው ማንኛውም ወደ ቻናላችን መቀላቀል ይችላል #እንኳን_ደና_መጣችሁ🙏💐 ቅዱስ ቃሉን በመማር ሕይዎትወን ይለውጡ #Join_አርገዉ_የተዘጋጁትን_ትምህርቶች_ያንብቡ_ይማሩ ይጠቀሙ ለወዳጅዎ ያካፍሉ ዘመንዎት በክርስቶስ ስም ይባረክ✝️🙌🙏
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 14
- Всего постов
- 43
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 85
- 1/48двое суток
- 97
- 1/72трое суток
- 105
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ኦ ክርስቶስ ኦ ክርስስ ኦ አምላክ ብሩህ ነህ/፪/ ልቦናዬን አብራው በጥዑም ቃልህ/፪/ ❴አዝ❵ የታቦር ደመና ክርስቶስ የሲና ልምላሜ ክርስቶስ ምነው ሙሴን በሆንኩ ክርስቶስ እንዳይህ ቀድሜ ክርስቶስ የዮርዳኖስ ውሃ ክርስቶስ በላዬ ሲፈላ ክርስቶስ የሐንስን በሆንኩ እንዳይህ በተድላ ❴አዝ❵ ነበልባል ሐመልማል ክርስቶስ ተዋህዶ ሲና ክርስቶስ ሙሴ ከሩቅ ሆኖ ክርስቶስ ተመልክቷልና ክርስቶስ በቀረበ ጌዜም ክርስቶስ ነገሩን ሲረዳ ክርስቶስ ለእሥራኤል ሾምከው ሁሉ እንዳይጎዳ ❴አዝ❵ ሙሴ በበትሩ ክርስቶስ ኤርትራን ሲመታ ክርስቶስ ተሻገሩ እሥራኤል ክርስቶስ በብዙ ደስታ ክርስቶስ ያልተደሰቱማ ክርስቶስ የፈርኦን ሠራዊት ክርስቶስ እየተሰጠሙ ቀሩ ወደ ኀላ ❴አዝ❵ ትንቢቱ ጸደቀ ክርስቶስ የኢሳይያስ ክርስቶስ ድንግልም ወለደች ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ ምነው ባደረገኝ ክርስቶስ እንደ ሰሎሜ ክርስቶስ ጌታዬ ሲወለድ ለማመስገን ቆሜ ❴አዝ❵ ሐዋርያት ሁሉ ክርስቶስ ዞረው ያስተማሩት ክርስቶስ ወንጌልህ ብርሃን ነው ክርስቶስ የዓለም መድሃኒት ክርስቶስ ዮሐንስ እንዳለው ክርስቶስ ጥምቀት ለንሰሐ ክርስቶስ እጠመቀዋለሁ የጎንህን ውሃ ❴አዝ❵ ሚካኤል በቀኝህ ክርስቶስ ገብርኤል በግራ ክርስቶስ ቅውማን የሆኑት ክርስቶስ ሁሉም በየተራ ክርስቶስ ሱራፌል ኪሩቤል ክርስቶስ ዐይናቸው የበዛ ክርስቶስ ያመሰግኑሃል አንተን የዓለም ቤዛ ኦ ክርስስ ኦ አምላክ ብሩህ ነህ/፪/ ልቦናዬን አብራው በጥዑም ቃልህ ዘማሪ ታዴዎስ ግርማ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan
ታቦር_አበራ ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና አነቃን ለምስጋና አዝ ሙሴም የቀደመው ሰዉ ኤልያስ ኃይለኛው ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል አዝ ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቸሃለሁ አሁን የሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ አርሙኒየም ደስ አለው ስሳራን ስለመታ አዝ እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ የዳዊት ልጆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ ብልኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ አዝ ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው አዝ የረዳኸው ይናገራል ያሰበከው በሕይወቱ አቤነዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ በደስታየም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ ከነጋር አልቅሰሃ አሳዝኖህ ሀዘኔ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ሆያ_ሆዬ_ሆ ሆያ ሆዬ ሆ/4/ እዛማዶ ምን ይታየሀል ታቦር ተራራ አብርሃን ለብሶአል ጌታ ቀሚሱ ያንፀባርቃል በክብር ውበት በግርማ ቁሟል ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ ጴጥሮስ በግርማው እጅግ ደንግጦ መሬት ወደቀ ራሱን ስቶ ኤልያስ ሙሴ መጡ ከፊቱ የእግዚአብሔር ልጅ ኑ ተመልከቱ ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ አብ በሰማያት ድምጹን አሰማ ልጁ ነን እንበል እሱን እንስማ በፍቅሩ ብርሃን እንዲያደምቀን እንቅረብ ፊቱ ስሙን አውቀን ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ በደብረ ጽዮን ህዝቡን ይጠራል በዚህ በግርማው ዳግም ይመጣል ከሙሴ ጋራ ከኤሊያስ ያቆመን በቀኙ እኛንም በ ነፍስን ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ የሙሴ ጌታ ሙሴ ነው ሲሉ እነ ኤልያስ ነብይ እያሉ አይሁድ ብስቱ ቢዋሹበት ኤልያስ ሙሴ መሰከሩለት ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ ጴጥሮስ በግርማው እጅግ ደንግጦ መሬት ወደቀ ራሱን ስቶ ኤልያስ ሙሴ መጡ ከፊቱ የእግዚአብሔር ልጅ ኑ ተመልከቱ ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አዝ የአመት ክብራችን ከጥንት የመጣ የቡሄ ለታ ችቦ ሲወጣ ከእማምዬ ቤት ሙልሙሉ ይምጣ ሆያሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ/4/ አመት አውዳአመት ድገምና አመት ድገምና /2/ የአባብዬን ቤት ድገምና አመት ድገምና ሰላም ይሙላበት ድገምና አመት ድገምና የእማምዬን ቤት ድገምና አመት ድገምና ፍቅር ይሙላበት ድገምና አመት ድገምና ክብር በንስሀ ክብር በጸሎተ የኔአባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ሀሁ ብዬ ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ ባአቦጊዳ አፌን የፈታዉብሽ በመልክተ መንፈሴ ተደሰተ በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ [፪] ተዋህዳ ...እህ ሀይማኖቴ ...እህ የእውቀት ምንጭ ...እህ መሰረቴ ....እህ አለኝ ትዝታ ከዛፉ ስር የኛ የኔታ ዱላ በትር [፪] ሀሁ ብዬ ስጮህ.......ሀ ድምፄን እያሰማው....ሁ አንዶን ቃል ስገርፋት..ሂ የኔታን አስቆጣ........ ሃ ሀ ማለት እግዚ ነው...ሄ እያሉ ሲቀኙ ...........ህ የኔታን አንደበት .......ሆ ማር ይንጠፍጠፍበት..ሆ አቦጊዳ ብዬ መልክተን ሳልወጣ የኔታ ደከሙ እንቅልፋቸው መጣ [፪] ፊደል ገበታዬ......ሀ ግዕዝ ጥያት ከመሬት ....ሁ ካብ አቧራዬን ማቡነን...ሂ ሳልስ ያዝኩኝ መላፋት....ሃ ሃራብ ሲነቁ የኔታ ..........ሄ ሀምስ ወስደው ከቀደሙ...ህ ሳድስ ልምጯን አንስተዎ...ሆ ሳብ ቁጣ ቃል አሰሙ.....ሀ ግዕዝ ተማሪና ውሻ ሁል ጊዜ አይስማሙ እስከ እድሜ ልካቸው አሉ እንደተዳሙ [፪] አቆፉዳ አንግቦ ሀ ደበሎዉን ለብሶ ሁ በእንተ ስሞ ሲል ሂ ድምፁን አለስልሶ ሃ አንዲት እፍኝ ጥሬ ሄ ለቁራሽ እንጀራ ህ ውሻ ሲያባርረው ሆ አያለው መከራ ሀ አለኝ ትዝታ ቅኔ ቤት በእንተ ስሟ ለ ማርያም ማለት [፪] የዜማው መለኪያ ህ ጭረት ምልክቱ ሆ እዝል እና ግዕዝ ህ ቅናቱ ድፋቱ ሀ ሳቢዘር ጥሬ ዘር ሄ ደሞም ቅኔ ቤት ህ አገባብ ሚስጢሩ ሆ ሰባት ስምንት ቤት ሆ አለኝ ትዝታ ከመቅደሱ ለሊቱን ሙሉ ማወደሱ [፪] መፃፉን ዘርግቶ ሀ ለጉባዬ ዉሎ ሆ ቅኔ ዜማ አጥንቶ ሄ ስምአኒ ብሎ ሀ ተፈስሂ እያልኩ ሄ እሱን ስደረድር ህ ሳዜመው ይነጋል ሆ ቅኔ ስደረድር ሆ አለኝ ትዝታ ከጎጀዬ ተሰቅላ ቆፋዳዬ [፪] ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan
ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው ብርሃን ከበበው አሸብርቋል ረጅሙ ተራራ ክብሩ ሲያበራ ክብሩ ሲያበራ..... ጴጥሮስና ያዕቆብ ደግሞ ዮሐንስን ዩዟቸው ተጓዘ የወረጣቸውን በፊታቸው ሳለ ድንገት ተለወጠ ኢየሱስ ሲያበረ ልባቸው ቀለጠ ክብሩ ሲያበራ.... ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ታዯቸው ጴጥሮስ በተመስጦ ዳስ እንስራ አላቸው ፍቅሩን የቀመሰ አይመኝም ሌላ ክርስቶስ ነውና እውነተኛ ተድላ ክብሩ ሲያበራ.... በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነውና ስለመዳናችሁ ስሙት በጽሞና ብሎ ሲመሰክር የሰማይ ንጉሱ ከኢየሱስ በቀር አላዩም ሲነሱ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ቡሄ በሉ | የደብረ ታቦር ዝማሬ መተናል በዓመቱ ኧረ እንደምን ሰነበቱ/2/ አደረሰን ለዓመቱ በከሃሊነቱ አደረሰን ለእለቱ በከሃሊነቱ ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆ የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር ሆ የተገለፀው ሆ ልብሱ እንደ ብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ የኛማ ጌታ ሆ የዓለም ብርሀን ነው ሆ ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን አዝ ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ አምላክም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ የመጣው እርሱ ሆ ፍቅር ስቦት ሆ ዓለምን ሊያድን ሆ በመስቀል ሞት ሆ በተዋሕዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደ ማርያም ነው ሆ ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን አዝ ታቦር አርሞንዔም ሆ ብርሀን የታያችሁ ሆ ቅዱሳን ተራሮች ሆ እንኳን ደስ አላችሁ ሆ ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ አባቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ እናቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ ተከምሯል እንደ ኩበት ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ/2/ አዝ ተገለጠ------------ሆ በታቦር ላይ---------ሆ ብርሐኑን-------------ሆ ለእኛ ሊያሳይ---------ሆ የምሥራች--------------ሆ እልል በሉ---------------ሆ ለሁሉ አባት-------------ሆ ለአዳኙ-------------------ሆ በሥምኽም ደሥ አላቸው ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/ አዝ........... ጽልመት ጠፍቶ------------ሆ ብርሐን ሆነ-----------------ሆ በክርስቶስ------------------ሆ ተከወነ----------------------ሆ ያን ጨለማ------------------ሆ በአንተ አልፈናል-------------ሆ አምላክ ክበር-----------------ሆ ውብ ሆነናል------------------ሆ በሥምኽም ደሥ አላቸው ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/ አዝ............ ጴጥሮስ ያዕቆብ----------ሆ ዮሐንስ----------------------ሆ ሙሴ ኤልያስ---------------ሆ ኢየሱስ---------------------ሆ ተመርጠው ነው------------ሆ ለሥደት---------------------ሆ ይኽን ክብር------------------ሆ ለማየት---------------------ሆ በሥምኽም ደሥ አላቸው ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/ አዝ........... ለእኛ በእዚኽ-------------ሆ ብንኖር----------------------ሆ መልካም ነበር-------------ሆ ያውም ክብር---------------ሆ ሦስት ዳስ-------------------ሆ እንስራና---------------------ሆ በእዚኽ እንኑር---------------ሆ በምሥጋና-------------------ሆ በሥምኽም ደሥ አላቸው ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/ አዝ.......... ተገለጠ------------ሆ በታቦር ላይ---------ሆ ብርሐኑን-------------ሆ ለእኛ ሊያሳይ-------ሆ የምሥራች------------ሆ እልል በሉ-------------ሆ ለሁሉ አባት------------ሆ ለአዳኙ-------------------ሆ በሥምኽም ደሥ አላቸው ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው/2/ ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት መዝሙር ዘማሪ ብርሃኑ ተፈራ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ታቦር አርሞንኤም ብርሐን ታየባቸው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
በብርሃን ደመና ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የታቦሩ ብርሃን በኢትዮጵያ ላይ ያብራ በጎቹ ይቆዩ ከእረኞቹ ጋራ ብርሃን ይዘው ይውጡ ቅዱሳን በጋራ የአብ ድምጽ ይሰማ በነጎድጓድ ግርማ ለሐዋርያቱ በግብጽ የገለጠ የሚወደው ልጁን ለመድህን ሰጠ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በጅራፍ ግርፋት ሕይወት የሰጠን በሠለሥቱ ምስጢር በአንድነት ጉንጉን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በቀራንዮ ላይ በአምስት ችንካር ቆመ ማየ ገቦ ፈሶ የአዳም ዘር ታከመ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሰላም ትዕግሥት ስጣት ለውዲቷ አገሬ ማስተዋልን ጥበብን ለሙሴው መምህሬ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ውረጅ ድንግል በብርሃን ደመና ንዒ ድንግል ከክርስቶስ ጋራ አዝ= = = = = በጥበብ ሃሳብ ላይ እንዳልነበር ገዝፎ ምን ያለው ነቀዝ ነው ጥቁር ሆኖ ቀፎ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ባዶነቱን አይቶ ለታላቅ ንጉሥ ሰው ንግሥቲቱን ሰጥቶ ቀፎውን በማር ሞላው ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የዶኪማስ ጓዳ ሆኗል ልቦናችን በአንቺ ልብ ይቀናል ማርያም እናታችን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ተነሱ ለጸሎት ይበለን አዳም ሰላም ለሁላችሁ ድምጽን አሰማን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ አውጣን ከዚህ ዘመን ከጥፋት ሀሳብ አገሬን አሻግራት ወደ ከነዓን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ተሰአለኒ አምላክ ተለመነኝ አምላክ ሆይ ስማ ህዝብሕን አደራ አዝ= = = = = በተዋህዶ የጸናች ኢትዮጵያ አገሬ የአዳም ርስቱ የክብሩ ጅማሬ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ⭐️ ኮከብ የቆጠሩ ቀኗን የቀመሩ አበው ሊቃውንቱ ጥበብን መርምሩ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሞትን ድል የነሱ ጻድቃን የወጡብሽ ስውራን ቅዱሳን የሚጸልዩብሽ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ግለጭው ክብርሽን ትውልድ ይመርምርሽ እንቆቅልሽ ስትይ ምን አውቅ እንዳይልሽ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ውረጅ ድንግል በብርሃን ደመና ንዒ ድንግል ከክርስቶስ ጋራ አዝ= = = = = ወአንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ ሕብስት ዘወረደ እም ሰማያት ስቡህ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ በጸሎተ ሐሙስ ጽዋ ሕብስትን ሰጠ የዘላለም ሕይወት ምሳሌን ገለጠ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ የአብርሃም ባራኪ መልከጼዴቅ ካህን የጽዋውን ስርዓት ምስጢሩን ይተንትን ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ሕብስቱን በመሶብ ጽዋ በማሰሮ ታላቅ ምስጢር አለው ካየነው በአንክሮ ቡሄ ቡሄ በሉ የአዳም ልጆች ሁሉ ጴጥሮስ ሙሴ - - ኧኸ ኤልያስ - -ኧኸ ያዕቆብ - - ኧኸ ዮሐንስ - - ኧኸ በወንጌሉ - - ኧኸ እንዳየነው - - ኧኸ ተገልጸዋል - - ኧኸ በተራራው - - ኧኸ ከጌታ ጋር - - ኧኸ ከአምላካቸው - - ኧኸ በብርሃኑ - - ኧኸ ተመስጠው - - ኧኸ ከርሞ ሰላም - - ኧኸ አድርሰን - - ኧኸ ለንስሐ - - ኧኸ አብቅቶን - - ኧኸ ትንሽ ትልቅ - - ኧኸ ሴት ወንዱን - - ኧኸ ፍቅር ሰላም - - ኧኸ አድለን - - ኧኸ ለአገራችን - - ኧኸ ኢትዮጵያ ኧኸ ፍቅር ስጣት - - ኧኸ ሃሌ ሉያ - - ኧኸ ሐዘን ስደት - - ኧኸ አገር ለቆ - - ኧኸ መለያየትን - - ኧኸ አርቆ - - ኧኸ ይስጠን ፍቅር - - ኧኸ ይስጠን ምሕረት - - ኧኸ ዛሬም ነገም - - ኧኸ የሁሉ አባት - - ኧኸ(፪) ዓመት ዓመት - - ኧኸ አድርሰን - - ኧኸ(፫) አገር ሰላም - - ኧኸ አርግልን - - ኧኸ ዓመት ዓመት - - ኧኸ አድርሰን - - ኧኸ(፫) አድርሰን - - - ኧኸ(፮) መዝሙር ዘማሪ እስጢፋኖስ ሳህሌ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
በብርሀን ደመና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
🥖ሃሌ ሉያ🥖 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 🥯ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4) 🥯ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ 🥯ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ 🥯መስማቱንማ ሰምቼ ነበር 🥯ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ 🥯ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር 🥯ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ 🥯እናቴ ሆይ.............ሆ🥖 🥯ይህን ባየሻ ..........ሆ🥖 🥯በቁርማ ዳቦ ........ሆ🥖 🥯ሲጥለኝ ውሻ........ሆ🥖 🥯ደጓ ጫማዋን ......ሆ🥖 🥯አውልቃዋለች.......ሆ🥖 🥯ውሃ ሲጠማ........ሆ🥖 🥯አጠጥታዋለች......ሆ🥖 🥯የስዋ ውዳሴ ......ሆ🥖 🥯ሆኖኛል ውይን ....ሆ🥖 🥯ዘሬም ብዘምር ....ሆ🥖 🥯እኖራለሁኝ .........ሆ🥖 🥯ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) 🥯በእምነት እንውጣ .ሆ🥖 🥯ከተራራው ላይ......ሆ🥖 🥯ይታይ ብርሃኑ........ሆ🥖 🥯ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ🥖 🥯ሙሴን እንጠይቅ...ሆ🥖 🥯የጥንቱን ነገር .......ሆ🥖 🥯ምን እንደሚለው ...ሆ🥖 🥯ጌታን ሲያናግር......ሆ🥖 🥯ድምጹን እንስማ ....ሆ🥖 🥯እንደ ትሁትነቱ.......ሆ🥖 🥯እንቀበለው ..........ሆ🥖 🥯እኛም በትሩን .......ሆ🥖 🥯ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2) 🥯ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) 🥯ተራራውማ ..........ሆ🥖 🥯ነውና አምሳል.......ሆ🥖 🥯ለቤተ ክርስቲያን...ሆ🥖 🥯መንበረ ልዑል......ሆ🥖 🥯ወጥተን እንጠይቅ.ሆ🥖 🥯ኤልያስን ............ሆ🥖 🥯እንድንዳስሰው.....ሆ🥖 🥯ጸጓራር ክንዱን......ሆ🥖 🥯ሰማይ በትለጉም...ሆ🥖 🥯ባህር ቢከፍል.......ሆ🥖 🥯እሳት ብታወርድ.....ሆ🥖 🥯ጠላትም ቢርድ......ሆ🥖 🥯በሰረገላ ..............ሆ🥖 🥯የተነጠከው...........ሆ🥖 🥯ይህ ሁሉ ክብር ......ሆ🥖 🥯በማን ስልጣን ነው...ሆ🥖 🥯ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4) 🥯የእመብርሃን .........ሆ🥖 🥯የምዬ ልጅ............ሆ🥖 🥯ተጥሎ ላይቀር ......ሆ🥖 🥯ተረስቶ ደጅ............ሆ🥖 🥯ሰአሊ ለነ ..............ሆ🥖 🥯ባለበት አፉ............ሆ🥖 🥯የጭንቁን እለት.......ሆ🥖 🥯ተሰብሮ ሰልፉ.........ሆ🥖 🥯እንዳባቶቹ .............ሆ🥖 🥯ቅኔን ተቀኘ.............ሆ🥖 🥯ድንግል ስትረዳው....ሆ🥖 🥯አይኑ ስላየ..............ሆ🥖 🥯ተፈስሂ ደብረ ታቦር (2) 🥯ተፈስሂ አርሙኒየም (2) 🥯ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር 🥯ተፈስሂ አርሙንየም 🥯ሙሴ ስላለ .......... ሆ🥖 🥯መና ያውርዳል.......ሆ🥖 🥯ቅዱስ ኤልያስ.......ሆ🥖 🥯ስጋ ያመጣል........ሆ🥖 🥯ዮሃንስንም...........ሆ 🥖 🥯ጌታ ይወዳል........ሆ🥖 🥯መድኃኒታችን.......ሆ🥖 🥯ፈውስ ይሆነናል....ሆ🥖 🥯በዚህ እንድንኖር ..ሆ🥖 🥯ዳሱን ጥለናል .....ሆ🥖 🥯ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4) 🥯አባቴም ቤት..........ሆ🥖 🥯አለኝ ለከት............ሆ🥖 🥯እናቴም ቤት .........ሆ🥖 🥯አለኝ ለከት...,........ሆ🥖 🥯ፍልሰታ ስትሆን.... ሆ🥖 🥯የቆምኩባት..........ሆ🥖 🥯በድብረ ታቦር ...... ሆ🥖 🥯ያጌጥኩባት.........ሆ🥖 🥯ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2)🥯 🥯ተቀኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2) 🥯አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና"🥖 🥯ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"🥖 🥯ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና"🥖 🥯የማምዬ ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"🥖 🥯ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና"🥖 🥯ነሩ በሀይማኖት 🥯ጽኑ በጸሎት🥖 🥯በተዋህዶ ቤት(4)🥖 🥯የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን"🥖 🥯አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን"🥖 🥯ከስጋ ወደሙ "በእምነት" ያድላችሁ "አሜን"🥖 🥯ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት" ያብዛላችሁ "አሜን"🥖 🥯ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ "አሜን"/2/🥖 🥯እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
ሀሌ ሉያ አንተ ሰው ሆይ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
без подписи
☎️ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን ይጫኑ /Start ╭━━━━━━━╮ ┃ ● ══ ▪ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃███████┃ ┃ 🔘 ┃ ╰━━━━━━━╯
እንኳን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ለፅንሰት በአል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን🙏 ነሐሴ_7 ጽንሰታ_ለማርያም ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው። ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች። በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። (ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ)
ፍልሰታ ለማርያም ❤️🙏 አጠር ያለ ታሪክ ነው ስለ እመቤታችን እርገት
ዘመን ተሻጋሪው የጽጌረዳ መዝሙር ሁሌም የማይሰለች መዝሙር❤❤❤❤❤
https://youtu.be/i15FvSbE4EY?si=X-k65pI6RiaVDIrs
ዘመዳችን ማርያም ዘመዳችን ማርያም ከዳዊት ዘር የሆንሽ አምላክን በስጋ በማህፀን ወሰንሽ የመመኪያችን ዘውድ የክብር አክሊላችን ልጅሽን ታቅፈሽ አይተናል በዓይናችን አዝ ባንቺ ድልድይነት የመጣው ወደኛ በጎቹ የገደሉት ነው መልካም እረኛ በጠበብ ደረትሽ ፈቅዶ ተወሰነ ፋሲካችን ታርዶ ዓለም በእርሱ ዳነ አዝ ሠረገላው እሳት ሰማይ ዙፋኑ ነው በስጋ ተገልጦ በእቅፍሽ ያየነው ካንቺ በፊት ይሁን እንዲሁም በኃላ አልተሰማ አልታየ ይህ ተአምር ከሌላ አዝ በነፃ ጠጥተን የህይወትን ውሃ ልምላሜ ሸፍኖን ወጣን ከበረሃ ባንቺ ስለሆነው ይገባል አንክሮ ጨው ያገኘንብሽ የኤልሳዕ ማሰሮ አዝ ዘመዳችን ድንግል ነውር የሌለብሽ የእምነት ምሳሌ ፀጋን የሞላብሽ ንጉሥ ውበትሽን አየና ወደደው ከሰማያት ስቦ ፍቅር አወረደው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE 👇👇👇 @gubaekidusan @gubaekidusan @gubaekidusan 👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
без подписи