HAppy Mûslimah
Статистикаአጫጭር ኢስላማዊ ታሪኮች ብቻ ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️ Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb
- Последний пост
- 23 июл.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 868
- 1/48двое суток
- 994
- 1/72трое суток
- 1 072
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከ ዝሙት አፅዱኝ… ~ • ማዒዝ ኢብኑ ማሊክ የሰው ልጅ ነውና ተሳሳተ፤ ሸይጧን አሸነፈውና ዝሙት ላይ ወደቀ። ወንጀሉን ማንም አላየበትም፤ ሌሊቱ ሰወረው፣ አላህም ነውሩን ሸፈነለት። ነገር ግን የማዒዝ ህሊና ሰላም ሊሰጠው አልቻለም። ምድሪቱ በሰፊው ጠበበችው። «እንዴት አላህን በዚህ ወንጀል እገናኘዋለሁ?» የሚለው ሀሳብ እንቅልፍ ነሳው። የማዒዝ ነፍስ መዳንን ፈለገች። ዱኒያ ላይ ተቀጥቶ አሊያም ነፅቶ ወደ አኼራ መሄድን መረጠ። እግሮቹ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂድ እየመሩት፣ ልቡ ግን በፍርሃት እና በተስፋ መሃል ትናወጥ ነበር። ማዒዝ ወደ ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ገባ። ከፊታቸው ቆመ። የውስጡን እሳት ለማብረድ እንዲህ ሲል ተማፀነ፡- «يَا رَسُولَ اللَّهِ طَهِّرْنِي» «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አፅዱኝ(ከ ወንጀል)» አላቸው። የእዝነቱ ነብይ ግን ማዒዝን ማጣት አልፈለጉም ነበር። ፊታቸውን አዞሩበት። አልሰሙ እንደሆነ በማስመሰል ወደ ቀኝ ፊታቸውን መለሱ። ማዒዝ ግን አልተወም። አሁንም በዚያ በኩል ሄዶ ደገመው። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) አሁንም ፊታቸውን አዞሩ። እንዲህም አሉት፡- «وَيْحَكَ! ارْجِعْ فَاسْتَغْفِرِ اللَّهَ وَتُبْ إِلَيْهِ» «ወዮልህ! ተመለስ (ሂድ)፤ አላህን ምህረት ጠይቅ፣ ወደርሱም ተመለስ።» አሉት። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) በሩን ከፈቱለት። በራሱና በፈጣሪው መሃል ይሁን፣ ተውበት ያድርግና ይተወው በሚል ስሜት አሰናበቱት። ማዒዝ ግን ወንጀሉ ውስጡን እየበላው ነው። ዝም ብሎ መሄድ አልቻለም። ለሶስተኛና ለአራተኛ ጊዜ ተመላለሰ። «ዝሙት ፈፅሚያለሁ »እያለ መሰከረ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ማጣራት ነበረባቸው። እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- «أَبِهِ جُنُونٌ؟» «እብደት አለበት እንዴ?» ሰዎችም «አይደለም ጤነኛ ነው» አሉ። አሁንም ጠየቁ፡- «أَشَرِبَ خَمْرًا؟» «ኸምር ጠጥቶ (ሰክሮ) ይሆን?» አንድ ሰዉ ተነስቶ አፉን አሸተተው፤ ምንም አልጠጣም። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) ግልፅ በሆነ የአረብኛ ቃል ወንጀሉን መፈፀሙን አረጋገጡ። ማዒዝም ምንም ሳይሸሽግ «አዎ!»አለ። ማዒዝ ራሱ በጠየቀው መሰረት ፍርዱ ተወሰነ። ወደ ቅጣት ቦታው ተወሰደ። ድንጋይ ሲወረወርበት ህመሙ ሲሰማው እንደማምለጥ አለ። ሆኖም የዱኒያው ቅጣት ተፈፀመና ማዒዝ ወደ አላህ ሄደ። ይህ ክስተት በሰዎች መካከል መነጋገሪያ ሆነ። አንዳንዶች በልበ ሙሉነት ስለ ማዒዝ ተውበት ሲያወሩ፣ ሁለት ሰዎች ግን በመሃከላቸው እንዲህ ተባባሉ፡-«ይህንን ሰው አያችሁት አይደል? አላህ ነውሩን ሸፍኖለት ነበር፤ እሱ ግን እንደ ውሻ በድንጋይ ተወግሮ እስኪገደል ድረስ ነፍሱን ከመወንጀል አልተወገደም።» አሉ። ነብዩ (ሰለሏሂ ዐለይሂ ወሰለም) የነዚያን ሰዎች ንግግር ሰሙ። ዝም ብለው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። መንገድ ላይ የሞተ አህያ (በክት) ተጥሎ አዩ። ያኔ እነዚያን ሰዎች ጠሩና እንዲህ አሉ፡- «كُلَا مِنْ جِيفَةِ هَذَا الْحِمَارِ» «ከዚህ የአህያ በክት ብሉ!» ሰዎቹ ደነገጡ። «አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ! ይህን ማን ይበላል?» አሉ። ነብዩም ልብን የሚሰብር ምላሽ ሰጡ፡- «ቅድም በወንድማችሁ ክብር ላይ የሰነዘራችሁት ቃል ከዚህ በክት ከመብላት ይበልጥ የከፋ (የቆሸሸ) ነው።» አሏቸው። ከዚያም ስለ ማዒዝ ታላቅ ተውበት ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- «لَقَدْ تَابَ تَوْبَةً لَوْ قُسِّمَتْ بَيْنَ سَبْعِينَ مِنْ أَهْلِ الْمَدِينَةِ لَوَسِعَتْهُمْ» «በ እርግጥም ለመዲና ነዋሪዎች ለ70 ሰዎች ቢከፋፈል ለሁሉም ይበቃቸው ነበር።» ብለው መሰከሩለት። @heppymuslim29
በአውስትራሊያ የሚኖር አንድ አዛውንት በሰላም ተኝተው ሳለ፣ የኢድ አል-ፊጥር የተክቢራ ድምፅ ከእንቅልፋቸው ይቀሰቅሳቸዋል። አዛውንቱ በድምፁ ተረብሸውና ተበሳጭተው፣ ድምፁን እንዲያጠፉ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ወደ መስጂዱ አመሩ። ▪️መስጂዱ እንደደረሱ ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው። የመስጂዱ ኢማምና የጀመዓው አባላት በታላቅ አክብሮትና ትህትና ተቀበሏቸው። እንዲህም አሏቸው፦ "ስላስቸገርንዎት በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን፤ ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳይደገም ቃል እንገባልዎታለን።" አዛውንቱ በዚህ መልካም አቀባበልና ትህትና ልባቸው ተነካ። ወዲያውኑ ስለ እምነቱ የበለጠ ለማወቅ ፈልገው ከኢማሙ ጋር ለመቀመጥ ጠየቁ። ኢማሙም ስለ እስልምና ምንነት፣ ስለ መቻቻል፣ በሁሉም ነቢያት ስለማመንና ወደፊት ስለሚከሰቱ ነገሮች አስቀድሞ ስለሚተነብየው የቁርዓን ተአምራት በሰፊው አስረዷቸው። ሽማግሌው በሰሙት ነገር እጅግ ተደንቀው እያለቀሱ እንዲህ አሉ። "እኔ አሁን የ85 ዓመት አዛውንት ነኝ፤ ወደ እስልምና ለመግባት ዕድሉ ያለኝ አይመስለኝም። *ኢማሙም ሲመልሱ፦ "ወደ እስልምና ለመግባት የቀረዎት አንድ ሰከንድ ቢሆን እንኳ፣ አላህ መሐሪና አዛኝ ስለሆነ ወንጀልዎን ይምርልዎታል።" አሏቸው። በመጨረሻም መጀመሪያ ቅሬታ ለማቅረብ የመጡት አዛውንት፣ በመልካም ስነ-ምግባር ተማርከው የእስልምናን እምነት ተቀበሉ። ሱብሃን አላህ!! ▪️ከአረብኛ ፅሁፍ የተወሰደ @heppymuslim29
ኸውለት ቢንት አል-አዝወር **** ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) በአንድ ወቅት ከሮማውያን ጋር በተደረገው ውጊያ የሙስሊሞችን ሰልፍ በማስተካከል ላይ ሳለ አንድ ሙሉ ሰውነቱን እና ፊቱን በአረንጓዴ ጨርቅ የተሸፈነ ተዋጊ ከሰልፉ ፊት ለፊት ተመለከተ፡፡ የሙስሊሞችንም ሰልፍ እየመራ የሮማውያኑን ጦር ከፍተኛ ጉዳት ያደርስበት ጀመር፡፡ ከሙስሊሞች ጦር ውስጥም የተሸፋፈነውን ሰው የሚያውቀው አንድም ሰው አልተገኝም፡፡ በውጊያው መሃልም ከሙጃሂድ ወንድሞቹ አይን ተሰወረ፡፡ ውጊያው ሲቀዘቅዝም ከሮማውያኑ መሃል በደም የተነከረ ሰይፉን ይዞ ወጣ፡፡ ራፊዕ ኢብን ኡመይራ (ረ.ዐ) በወቅቱ ከሙስሊሞች ጦር ጋር ነበር፡፡ ክስተቱንም እንዲህ ሲል ይተርካል፡- “በውጊያ ውስጥ እያለን የተሸፋፈነውን ሰው ጀብዱ ስንመለከት የጦር መሪያችን ኻሊድ ኢብን ወሊድ (ረ.ዐ) ፊቱን ሽፍኖ ገብቶ ይሆናል ብለን ገምተን ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ጀግና ጦርነቱ ሲቀዘቅዝ ከሮማውያን መሀል ሲወጣ ከቀኙ በኩል ኻሊድ ኢብን ወሊድን (ረ.ዐ) ተመለከትነው፡፡ ለኻሊድም (ረ.ዐ) “ይህ ከፊት ለፊትህ ሆኖ አስገራሚ የጀግና ውጊያ የሚዋጋው ሰው ማን ነው?” ብለን ጠየቅነው ኻሊድም (ረ.ዐ) “እኔም እንደናንተ ላውቀው አልቻልኩም” አለን፡፡ ውጊያውም እንደ አዲስ ሊጀመር ነው፡፡ ኻሊድም “የሙስሊም ጦር ሆይ! በጀግንነት ተዋጉ፣ ከእምነታቹሁም ላይ የጠላትን ወረራ ተከላከሉ” በማለት ሙስሊሞችን አበረታታ፡፡ የተሸፋፈነውም ሙጃሂድ ጦሩን ከፊት ለፊት ሆኖ መምራቱን እንደቀጠለ ነው፡፡ ውጊያውም ከተጀመረ በኋላ ወደ ጠላት ስብስብ ገስግሶ ስለሚገባ ሙጃሂድ ወንድሞቹ ከሰልፋቸው ውስጥ አይመለከቱትም ነበር፡፡ ጦርነቱም ሲጠናቀቅ ልብሶቹ በደም የተነከሩ ሆነው ወደ ሙስሊሞች ካምፕ መጣ፡፡ ኻሊድ እና ሙጃሂዶቹም “ለአላህ ስትል ፊትህን ግለጥና አሳየን” ብለው ተናዘዙት፡፡ እርሱ ግን ለንግግራቸው ቦታ ሳይሰጥ ጅርባውን ሰጥቷቸው ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከሰውዬው የሚታየው ሁኔታ ጉዳዩ አላህ ዘንድ ብቻ እንዲታወቅለት የፈለገ ይመስላል፡፡ ሙስሊም ተዋጊዎችም “አንተ የተሸፋፈንክ ሰው ሆይ! የጦር መሪህ እያዘዘህ ነው ፊትህን አሳየን” እያሉ ከየአቅጣጫ መጮህ ጀመሩ፡፡ ኻሊድም የሰውዬውን እምቢተኝነት በተመለከተ ጊዜ ከፊት ለፊት ቀደመው፡፡ “ወዮልህ! በተግባርህ የሰዎችን ትኩረት ሳብክ” በማለትም ደጋግሞ ጠየቀው፡፡ ጀግናው ሙጃሂድም የጥያቄው መደጋጋም ሲበዛበት “እስካሁን መልስ ያልሰጠሁህ ከአንተ ፊት ድምፄን ለማውጣት ሐያእ (ሀፍረት) ይዞኝ ነው፡፡ እኔም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፊታችንን ላልተፈቀደልን ወንዶች እንዳናሳይ ካስተማሩን የሙስሊም ሴቶች ውስጥ አንዷ ነኝ” ስትል በእንስታዊ ድምፅ መለሰችለት፡፡ ኻሊድም በጉዳዩ ተደንቆ “እሺ አላህ ይባርክሽና ስምሽን ንገሪን” ሲል ጠየቃት፡፡ “ኸውለት ቢንት አዝወር ነኝ” ብላ መንገዷን ቀጠለች፡፡ @heppymuslim29
ሸይኹ በሚያስተምርበት መስጂድ ውስጥ ሰዎች የሚሰጡትን ክብር እንድትመለከት ሚስቱን አስከትሎ ሄደ። በምላሷ ትወጋው ስለነበር አዛዋን ለማስቆም መሆኑ ነው።….. መስጂድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ ሲያስተምር ዋለ። እቤት ሲመለሱ ሃሳቧን ጠየቃት። «ሁሉም ሰው ዝም ብሎ በዒባዳ ተመስጦ ነበር። አንተ ብቻ ስትለፈልፍና ስትንቀለቀል ነበር።ሰዎች በተዋዱዕ መሬት ላይ ሲቀመጡ ጉረኛው አንተ ግን ከፍታ ቦታ ላይ ራስህን ቆልለህ ቆመሀል!»…ልክ ልኩን ነገረችዋ¡ @heppymuslim29
‹‹መሞትህ ነው›› አሉት ገጠሬውን። ‹‹ከዝያ የት ነኝ?›› ብሎ ጠየቀ። ‹‹እጌታህ ዘንድ›› ቢሉት... ‹‹ታድያ መልካም ሁላ ተሱ ዘንዳ ይገኝ የለ! ምን አስፈራኝ!›› #ተስፋ ‹‹ዱዓው ተቀባይ የሆነን ሰው ታውቃለህ›› ብለው ጠየቁት። ‹‹አላውቅም፤ ግና ዱዓን የሚቀበል ጌታ አውቃለሁ›› አላቸው። #እምነት ሰሓቢዩ ዘንዳ አንዱ መጥቶ ጠየቀ፦‹‹ቂያም ቀን ማን ነው ሞጋቻችን?›› ‹‹አላህ›› ሰሐቢዩ መለሰ። ‹‹እንግዲህ ድነናላ!›› ብሎት ሄደ። #ጥልቅ_ተስፋ ወጣቱ ሞት አፋፍ ላይ ሁኖ ሲያጣጥር እናት ታለቅሳለች፦‹‹እማ! የቂያም ለት ሂሳብ ተሳሳቢዬ አንች ብትሆኚስ፤ ምን ታደርጊኛለሽ? ›› ጠየቃት። ‹‹ስለማዝንልህ ይቅር እልሀለው !›› ‹‹ካንቺ በላይ ወደሚያዝንልኝ ጌታ እየሄድኩ ነው'ና አታልቅሺ›› #ፍቅር @heppymuslim29
ከኢሻ ሶላት ቡሀላ ወደ ቤቱ ተመለሰ ልጆቹም ተኝተው አየ፣ ለሚስቱም ልጆቹ ሰግደዋል? እንዴ ብሎ ጠየቃት እሷም፦ምግብ ስላልነበረ አባብዬቸው ተኙ አልሰገዱም እሱም፦ ቀስቅሻቸው አላት እሷም፦ የእገሌ አባት ሆይ …!!ከቀሰቀስኳቸው ከረሀብ የተነሳ ያለቅሳሉ የሚበላ ደሞ የለም! አለቺው እሱም፦ አድምጪኝ: ከኔ የሚጠበቀው እንዲሰግዱ ማዘዝ ነው…እርዚቃቸው ከኔ አይደለም ፣ቀስቅሻቸው እርዚቃቸው ከአላህ ነው ! አላህም እንዲህ ይላል (ቤተሰቦችህንም በስግደት እዘዝ ፣በእሷም ላይ ዘውትር ፅና ፣ሲሳይን አንጠይቅህም ፣እኛ እንሰጥሀለን ፣ መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቅቆቹ ናት ) እናቲቱም እጅ ሰጠችና ቀሰቀሰቻቸው ሰግደው እንደጨረሱም የቤታቸው በር ተንኳኳ ፣ ከዛም ሲከፍቱት ከከተማው አንድ ከበርቴ ከማእዱ ጣፋጭ ከሆነው ግማሹን ይዞ ቆሞ ነበር ፣ ሰውየውም ፦ ውሰድ ላንተ እና ለቤተሰቦችህ ነው አለው እሱም ፦እንዴት ሲለው ሰውየውም፦«አንድ ባለ ስልጣን እንግዳዬ ነበር ማእዱን ከመመገባችን በፊት ተጣላን እና ምግቡን ላይበላ ምሎ ሄደ » ምግቡንም ይዜ እንዲህ አልኩ "እግሬ ለቆመበት ሰው እሰጣለሁ ,በአላህ እምላለሁ አንተ ደጃፍ ስር እንጂ እግሬ አልቆመም ነበር ! በአላህ ይሁንብኝ ምን ወደዚህ ይዞኝ እንደመጣ አላውቅም "አለው !! 《 ጌታዬ ሆይ ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ ፣ከዘሮቼም አድርግ! ጌታችን ሆይ ፀሎቴንም ተቀበለኝ፤ 》 @heppymuslim29
ተራዊሕ አምሽተን ስንገባና ደክመን ስንወድቅ ዘጠኝ እና አሥር ሰዓት አካባቢ ገላን ከፍራሽ ማላቀቅ ትልቅ ጉልበት ይጠይቃል። ለሱሑር እንደመነሳት የሚከብድ ነገር የለም። በመሆኑም ብዙዎቻችን ያለ ሱሑር መፆምን በወደድን። ግና ሱናዉን አስበንና በረካዉን ለማግኘት ብለን እየታገልን እንነሳለን። ዐይናችን ሳንከፍት የምንበላ ሁሉ አለን። ከሱሑር በኋላ እስከ ሱብሒ ያለው ሰዓት አጭር ቢሆንም ለብዙዎቻችን ይረዝምብናል። ግና ከፊቱ ያለዉን የግዴታ ሶላት ሳይሰግዱ መተኛት ቁጭትን የሚያስከትል በመሆኑ እንቅልፋችንን እየታገልን በኢስቲግፋርና ቁርአን በመቅራት እንቆያለን ። ገና ለሱብሒ ሶላት እንደቆምን ከሶላቱ በኋላ ያለው ጣፋጭ እንቅልፍ ይታወሰናል። ያ እንቅልፍ ዱንያ ላይ ካሉ ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ መካከል ቀዳሚው ሳይሆን አይቀርም። ግና ከሱብሒ በኋላ መተኛት አይመከርም ። ሰዓቱ አላህን የማውሳትና የዱዓ ሰዓት በመሆኑ ወደ አላህ መቅረብንና በርሱ ዘንድ መወደድን አስበልጠው ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክርና ዱዓ እያደረጉ የሚቀመጡ ብርቱዎችንም አሉ። ኢማን ማለት ይህ ነው። የማይታየዉን የአላህ ቃልኪዳን እንደሚታይ አድርጎ ማመን። እኛ ከምንፈልገው በላይ አላህ የሚወደዉን ማስቀደም። ነፍሲያችን ከምትመርጠው አላህ የሚመርጠዉን መምረጥ። ጀነት ዉድ ናት ። ነፍሲያን መጫንን ፣ ፍላጎትን መጨቆንን ትጠይቃለች ። ጀነት ለነፍሲያ በሚከብዱ ነገሮች የተከበበች ናት። እንቅልፍ መቁረጥን፣ ድካምን መርታትን፣ ስንፍናን ማሸነፍን ፣የምንወደዉን አላህ በሚወደው መተካትን ትሻለች። አላህ ያበርታን። @heppymuslim29
ረመዷን ውስጥ የሚደረግ ዑምራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሐጅ ሲመለሱ ለኡሙ ሲናን (ረ.ዐ.) “ለምንድነው ከኔ ጋር ሐጅ ያላደረግሽው?” አሏት። “ባለቤቴ ሁለት ግመሎች ነበሩት። አንዱን ተሳፍሮ ሐጅ ሄደበት፤ ሁለተኛው ደግሞ አገልጋያችን ውሃ የሚያመላልስበት ነው፡፡” አለቻቸው። እንዲህ አሏት፡- “በረመዷን ውስጥ የምትደረግ ዑምራ ከኔ ጋር ሐጅ ማድረግን ትስተካከላለች። ” የሐጅ ምንዳን ትስተካከላለች ማለታቸው ነው። ነገር ግን ሰውዬው ሐጅ አደረገ ማለት አይደለም። አላህ ምንዳን የሚያነባብራቸው ጊዜያት አሉ። ልብ ብላችሁ ተጠቀሙባቸው። @heppymuslim29
የኢፍጧር ሰዓት እንዲህ በል! 👈ذَهَبَ الظَّمَأُ، وَابْتَلَّتِ العُرُوقُ، وَثَبَتَ الأجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ ➜ጥማት ተወገደ ➜የደም ሥሮች ረጠቡ ➜የአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳም ተረጋገጠ @heppymuslim29
ልጅ እያለሁ ነው ያው ልጅ እያለሁ ማለት በደምብ ልጅ እያለሁ...የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት መስጂድ ላይ ባለው ወከባ እና ርብርብ ብቻ የወሩን ክቡርነት ተረድተናል፤ እናም ይህ ክቡር ወር ከመግባቱ ቀናቶች ሲቀሩት ኡስታዛችን ሰብሰብ አደረገን እና ስለ ፆም ህግጋትን በልጅኛ አንደበት ያብራሩልን ጀመር "ማንኛውም የሚበላና የሚጠጣ ነገር ፆምን ያጠፋል እሺ፣ያው ረስታቹ ከበላችሁ ግን ችግር አይኖረውም" ውብ ፈገግታ እየቸሩን ስለ ወሩ በደምብ ያወጉና እኛም ስንናፍቀው ቀናቶች የአመታት ያህል እየረዘሙብንም ቢሆን ከወሩ ዘለቅን ረመዳን 1 ብሎ በተራዊህ ጅማሮውን አበሰረ ኢላሂ!! የዛን ግዜ ደስታ የሆነ ለየት ያለ ስሜት ነበረው። ተራዊሁ ተገባዶ ወደ መፆም አለፍን። ሱሁር እንዲያነሱኝ ባስጠነቀኳቸው መሰረት ሱህሬን ተመግቤ የፆመኛን ክብር በእጄው ያዝኩ (ፆመኛው እኔ) ቀኑን እንደምንም እስከ ዙህር እየተንገዳገድኩም ቢሆን ከፆምኩ ቡሀላ ዙህርን ከጓደኞቼ ጋር ሰግደን ከመውጣታችን ነው አንድ ሸንኮራ አዟሪ ባይናችን እልፍ ያለው እህእእ ሸንኳራ ግን ፆም ያጣፋል እንዴ፤ እርስ በእርስ አንሾካሾክን " አረ ኡስታዝ እኮ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነው ያሉት ሸንኮራ ደግሞ እንጨቱ ይተፋላ እንዴ!!!" አዎ አዎ ሁላችንም ተንጫጫን (የልጅነት ፈትዋ)እናሳ ተርበናል እኮ ያልፆመ ደግሞ ፍጡር ላይ የሚደርስበት መገለል ይታወቃል። ያለችንን 25፣50ም ሳንቲምን እያዎጣን ቁርስ ምሳችንን ለቀናት በሸንኮራ ያለ ከልካይ ፁመናል #ዝምታ ቢበዛም ጥቂቶች ትዝታቸውን አስቃኝተውናል የረመዳን ትዝታውን ያጋራንን የወንድማችንን ፅሁፍ አንካችሁ ብያለሁ!! ትዝታ! እና ረመዷን @heppymuslim29
👉 ተራዊሕ ላይ ቁርአን ይዞ መከታተል የሸይኽ ፈውዛን ፈትዋ ↙️ https://t.me/AbuImranAselefy/8443 ➲ ብዙ ሰዎች በተራዊሕ ሶላት ላይ ኢማሙ ሲያሰግድ ቁርኣን ይዘው ይከታተላሉ። ይህ ተግባር በሶላት ውስጥ አንድ ሰው ማድረግ ያለበትን ተግባሮች ይቃረናል። ➪ አንድ ሰው በሚሰግድ ጊዜ የቀኝ እጁን መዳፍ በግራ እጁ ሳአት ማሰሪያ ላይ ደርቦ ደረቱ ላይ ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ከሶላት ሱናዎች አንዱ ነው። እንደዚሁ በሚቆምበት ጊዜ ስጁድ የሚያደርግበትን ቦታ መመልከት አለበት ይህም ሱና ነው። ➧ ኢማሙ በሚቀራበት ጊዜ ማዳመጥ አለበት ይህም ዋጂብ ካልሆነ ሱና ነው። ሌላው ሶላት ላይ ሆኖ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም። ቁርኣን ይዞ የሚከታተል ሰው እነዚህን ሁሉ ሱናዎች ይቃረናል። ለእነዚህና ለመሳሰሉት ምክንያቶቸ አብዛኛዎች የኢስላም ሊቃውንቶች ይከለክላሉ። ምናልባት ቁርኣንን የሸመደደና ኢማሙ ቢሳሳት ሊመልስ የሚችል ከሌለ አንድ ሰው ከኋላው ቁርኣን ይዞ ይከታተለው ይላሉ። ➽ ከነጭራሹ ሶላቱ ባጢል ነው የሚሉም አሉ። በተቃራኒው ይቻላል ብለው አነስ ኢብኑ ማሊክ በሚያሰግድ ጊዜ ከኋላው አንድ ወጣት ቁርኣን ይዞ ከተሳሳተ ይመልሰው ነበር የሚሉ አሉ። ነገር ግን ሌሎች ዑለሞችም ሐፊዝ በሌለ ጊዚ አንድ ሰው ይከታተለው ያሉትም ለዚህ ነው ደሩራ ስለሆነ። ➾ ከዚህ ውጪ አሁን ባለው መልኩ በነብዩም ይሁን በሶሐቦች ዘመን አልተገኘም። በዚህ ዙሪያ ያሉትን የዑለሞች አቋም የሚከተለውን ይመስላል:– — ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ክልክል ነው ይላሉ። – ኢማሙ ማሊክ ይጠላል ይላሉ። – ኢማሙ አሕመድና ኢማሙ ሻፍዕይ ይቻላል ይላሉ። – ኢብኑ ሐዝም ሶላቱ ባጢል ነው ይላል። – ከዘመናች ዑለሞች ኢማሙ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሰይሚንና ሸይኽ አልባኒ ሱናን ስለሚቃረን ለደሩራ ካልሆነ አይቻልም ይላሉ። ➧ ከላይ ለተጠቀሱት ሙኻለፋዎች ምክንያት ለደሩራ ካልሆነ አይቻልም የሚለው አመዛኝ ነው። ዒባዳችንን ከሙኻለፋ መጠበቅ የኛ ድርሻ ነው። አላህ ለመልካሙ ይወፍቀን። @heppymuslim29
አቅጣጫችሁን የምትወስኑበት…ወኔያችሁን የምታድሱበት…ለአሏህ ብላችሁ ቆርጣችሁ የምትነሱበት…ከቁርዓን ጋር ትስስራችሁን የምታሳምሩበት… Turning point የሆነ ረመዳን ያድርግላችሁ REMEDAN MUBARAK. @heppymuslim29
ግርም ከሚሉኝ የሕይወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የዓኢሻ ነው፡፡ በስንት ዓመቷ አገባች በሚለው ላይ ዉዝግብ ስላለ ልለፈው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ﷺ ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡ ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያዉም በእጅጉ የምትቀናባቸዉን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው፣ ልጅ አልነበራትም፡፡የሚገርመው “ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ” ብላ ነቢዩን ወትዉታለች የሚል ሐዲሥ አልተገኘም፡፡ ልብ በሉልኝ። ከርሣቸው ህልፈት በኋላ 47 ዓመታትን ብቻዋን ነው የኖረችው፡፡ አዎ ብቻዋን። አላህ ለዓኢሻ ልጅ ያልሰጣት ስለሚጠላት ነው የሚል ይኖር ይሆን?? አላህ ምንን ለምን እንደዳደረገ የሚያውቅ ጌታ ነው፣ አንችን ባርያዉን አይጠላም እሺ። እናታችን ዓኢሻ አላህ ሱ.ወ ልጅ ስላልሰጣት መፈጠሯን አልጠላችም፣ በአምላኳም አላማረረችም። እምነቷን አልቀየረችም። 'የኔስ ተለየ' አላማረረችም። የሷ ባልሆነው ልጅ 'ኡሙ ዐብደላህ' ተብላ እየተጠራች ሙሉ ሕይወቷን በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሃድ አሳለፈች፡፡ ትላልቅ ሶሐቦች ከሷ ተምረዋል፣ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለብዙዎች ታስረዳ ነበር፡፡ ከዚህ ምን እንማራለን መሰለሽ ... ልጅ ስለጠፋ፣ ትዳር ስለጠፋ፣ ቤት ስለጠፋ፣ መኪና ስለጠፋ … ሕይወት አትቆምም ትቀጥላለች፡፡ @heppymuslim29
አንድ ወጣት አንድ ሸይኽ ዘንድ ደውሎ አንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ ያ ሸይኽ ጥያቄ ነበረኝ? ሸይኹ፦ መርሃባ መጠየቅ ትችላለህ። ወጣቱ፦ ሰለፎቻችን ከቁርዐን ጋር የነበራቸው ሁኔታ እንዴት ነበር? አብራሩልኝ ሸይኹ፦ በአሁን ዘመን ወጣቱ ከስልኩ ጋር እንደማይላቀቀው እነሱም ከቁርዐን ጋር አይላቀቁም ነበር። @heppymuslim29
ከኡሙ ደርዳእ ምክሮች - ኡሙ ደርዳእ ከበኒ ተሚም ጎሣ ለሆነ አቡ ሂዛር ለሚባል አንድ ታላቅ ሰው ‹የሂዛር አባት ሆይ ! በሞት አልጋ ላይ ያለ ሰው ምን እንደሚል ልንገርህን?› አለችው። ‹ምን ይላል ?› አላት። ‹እንዲህ ሲል የሚጣራ ይመስለኛል፡፡› አለችው፡፡ ‹ ጎረቤቶቼ ሆይ! የአስከሬኔ ተሸካሚዎች ሆይ! ይህች ዓለም እኔን እንዳታለለችኝ እናንተንም እንዳታታልላችሁ ። በኔ እንደተጫወተችብኝ በናንተም አትጫወትባችሁ። ቤተሰቦቼ ሆይ! ወንጀሌ ሁሉ ሸክሙ በኔ ላይ ነው። ከኔ ወንጀል ቅንጣት ታህል አትሸከሙም።› ኡሙ ደርዳእ ረ.ዐ አሁንም ትመክራለች። ድንገተኛውን እና ጥፍጥና ቆራጩን ሞት ታስታውሰናለች። ሰዎች የሞተን ሰው ገላ ሲሸከሙ ኃጢኣቱን አብረው አይሸከሙም፡፡ ቢሸከሙማ ኖሮ በተለይ የመጥፎ ሰው በድን እንዴት ይከብድ ነበር በአላህ!፡፡ ሰዎች አንድ የሞተን ሰው ቀደ መቃብር ሲሸከሙ ወንጀሉ የራሱ እዳ ነውና አብረው አይሸከሙም፡፡ ቢሸከሙማ ኖሮ በተለይ የእኩይ ሰው አስከሬን ስንቶችን ባጎበጠ ነበር፡፡ እንደሞተ ሰው የሚያሣዝን ማን አለ!፡፡ ለነፍሱ ለመሥራት እድል የለውም። መልካም ሥራዎቹን ለማብዛት ዕድሜ አይኖረውም፡፡ የቆይታ ጊዜው አብቅቷልና። የተሠጠውን እድሜ ጨርሷልና፡፡ የመልካምም ሆነ የመጥፎ ሥራ ባለቤት የሰው ልጅ ዱኒያን ሲሰናበት የጎደለበት ሆኖ ነው። መቆጨቱም የማይቀርና የግድ ነው። የመልካም ሥራ ባለቤት መሥራት የሚገባኝን ያህል አልሠራሁም ብሎ ይቆጫል። የመጥፎ ሥራ ባለቤት ደግሞ የገዛ መጥፎ ሥራው መልሦ እሾህ ሲሆንበት እጁን ይነክሣል። ኡሙ ደርዳእ የዋዛ ሴት አልነበረችም። መሞቷን በርግጠኝነት አወቀች። በመሆኑም በብዙ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ ከራሷ ጋር አውርታለች። መጨረሻዋንም አርቃ ለማየት ሞክራለች። እጣ ፈንታዋንም ፈርታለች። ስለሆነም ወደ መቃብር መንገድ የጀመሩ ሙታኖችን በሀሣብ ለማነጋገር አሠበች። እንዲህ የሚሏት ይመስላታል - የፈለጋችሁትን ያህል ብትኖሩ መሞታችሁ ግድ ነው። የቱን ያህል ብትሮጡ ሩጫችሁ ፌርማታ አለው። ፌርማታውም ወደ እውነተኛውና ቋሚው ዓለም መሸጋገሪያ ነው። ረጃጅም ጉዞዎች፣ አስፈሪ መሰናክሎችና አቀበቶች ከፊት ለፊታችሁ አሉ። ነገ ረጅም ጉዞ እንዳለበት ያወቀ ሰው ደግሞ ዛሬን በአንድ ልብ ማረፍ የለበትም። ለዚያኛው ሀገር መዘጋጀት ይኖርበታል። በቂ ስንቅም ያስፈልገዋል። ኡሙ ደርዳእ በእምቅ ቃላቶቿ ትመክራለች….. በዚህች ዓለም ጥቅም አትዘናጉ። ለአስፈሪው ቀን ስንቅ ያዙ። ከፊታችሁ ብዙዎች ቀድመዋችኋል፡፡ እናንተም ትሄዳላችሁ፡፡ የተቀሩትም ይከተሏችኋል። በፍፁም አትታለሉ። ዘላለም እንደሚኖር ሰው አትገንቡ። እድሜ ልክ እንደሚከርም ሰው አታከማቹ። ቋሚ አይደላችሁም ትሄዳላችሁ። የቀኑ ጨዋታችሁ ያልቃል። የለሊቱም እንቅልፋችሁ ያበቃል። ዛሬን ለአላህ ሱ.ወ ስገዱ፡፡ ካለፋችሁ በኋላ የሚሰግድላችሁ/ መልካም ሥራ የሚሠራላችሁ የለም። ዛሬውና ሞልታችሁ ሥሩ፤ ነገ የሚሞላላችሁ አታገኙም። ዛሬውኑ ፍጠኑ፤ ቆሞ የሚጠብቃችሁ አታገኙም። የመዘናጋትን ጥላ ከላያችሁ ላይ ግፈፉ። ያልሠራ ሰው በርትቶ ከሠራው ሊቀድም አይችልም። የሚራመደውም የሚሮጠውን ይቀድማል ተብሎ አይታሠብም። ይህች ዓለም አታታልላችሁ። ውድድሩን የሚያቋርጥ ሰነፍ ሰው ከመወዳደር አያዘናጋችሁ። ዛሬ ሥራ ነው ዉጤት የለም። ነገ ደግሞ ውጤት ነው ሥራ የለም። @heppymuslim29
"አስተውለህ ታውቃለህ ግን? "አስተውሎ ከጨረሰ በኋላ የሚጠይቀኝ ጥያቄ ነው .. " ምኑን?" " አጥብቀን የምንፈልጋቸው ነገራቶች እንደማይገኙ ?" " እኔንጃ ለምሳሌ ምን ምን ?" ቀለል የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያበዛ ቢሆንም መመለስ አልወድም.. የሚለውን ባደምጥ ምላሼን እዛ ውስጥ እንደማገኘው አውቃለው " ብዙ ጊዜ ቸኩለን አልያ ደግሞ በጣም ፈልገነው ያለ እቃ ከጠፋ ለማግኘት እንቸገራለን « አሁን በጣም ስለፈለኩት ነው'ጂ በቀላሉ አገኘው ነበር» እንላለን እና ይህ አጋጥሞህ አያውቅም ?" ሁሌ ቁልፍ እየጣልኩ የምንከራተተው ነገር ትዝ ብሎኝ ፈገግ አልኩ " አዎ ሁሉም ሰው ላይ ያለ ነገር ይመስለኛል" "አዎ ሁሉም በሚባል ደረጃ አሳልፎታል...እና ካስተዋልክ እንደዛ ላይ ታች የምንልባቸው እና መጮህ እስኪያሰኘን የሚያለፉን እቃዎች መጨረሻ ላይ ግን ግልፅ ቦታ ላይ ነው የምናገኛቸው " እዚ ሆኖ ነው የለፋነው ?" እንላለን ብዙ ጊዜ ...ለምን ይመስልሀል ?" "እኔንጃ ለምንድነው ?" " አላውቅም ግን ሲመስለኝ በዛ ሰዓት ማግኘት እንዳለብን እንጂ እንዴት ማግኘት እንዳለብን አናስብም ። ቦታ የተባለ ነገር ሁሉ እቃን ማስቀመጥ ስለሚችል ሁሉን ቦታ እናስሳለን ደሞም አይተነው ልናልፈው እንችላለንኮ...ግን በዛ ሰዓት የጠፋብን እቃ የት ሊቀመጥ ይችላል የሚለውን ብናስብ ብዙ ልፋት እናድን ነበር ...እና እኛ የሰው ልጆች አሁን የጠፋብን ነገር እነዚ ደስታ ፣ ሀሴት እና ፍቅር የምንላቸው ነገራቶች ናቸው ። ሁሉም ሰው ደግሞ አጥብቆ እየፈለጋቸው ነው ....ለምን አላገኘነውም ?" " እኔንጃ !" " ሁሉም ቦታ በችኮላ እየፈለግናቸው ይመስለኛል ! ሁሉም ሰው አድካሚ በሆነ ፍጥነት ነገራቶችን እያዘበራረቀ እየፈለገ ቢሆንም ሊያገኘው አልቻለም ቅድም እንዳልኩህ ማግኘት እንዳለብን እንጂ የት ማግኘት እንደምንችል አላወቅንም ። ሁሉም በሌሎች ተፅዕኖ እና ግፊት ሁሉንም መንገድ ቢጠቀምም ሊያገኛቸው አልቻለም ።" "እና የት እንፈልጋቸው ? እንዴት ?" " ቀላል ነው ! ወደውስጣችን ...ሰፊ ወደሆነው የራስ አለማችን እይታችንን ማዞር ነው ። ነፍሳችን ውስጥ ነው ሚስጥሩ ። " ልክ ይሁን ? እንጃ @heppymuslim29
አንድ ቀን አባቴ ለሁለታችን የሚሆን ምግብ አዘጋጀና በሁለት ሳህን ከፍሎ የምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። የተዘጋጀው ምግብ ፓስታ በእንቁላል ነበር። አባቴ ፓስታውን ሲያስቀምጠው በአንደኛው ሳህን ከፓስታው በተጨማሪ የተቀቀለ አንድ እንቁላል ከአናቱ አድርጎበታል። በሌላኛው ሳህን ግን ከፓስታው በላይ እንቁላል የሚባል ነገር የለበትም። ከዚያ አባቴ ወደ እኔ እየተመለከተ፣ “ልጄ! የትኛውን ትፈልጋለህ? አንዱን ሳህን ምረጥና አንሳ...” አለኝ። በጊዜው እንቁላል እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ ምግብ አልነበረም። ድህነቱ፣ ገንዘብ ማጣቱ በሁላችንም ቤት ጫን ያለ ስለነበረ አዲስ ዓመት ካልመጣ ወይም ዓመትባል ካልደረሰ በቀር እንቁላል መብላት ዘበት ነው። ታዲያ እኔ፣ አንዱን ሳህን መርጬ እንድወስድ አባቴ ሲጠይቀኝ ፈጥኜ እንቁላል ያለበትን ሳህን መረጥኩ። እንዴ ማን ይሞኛል? እንቁላል ተገኝቶ ነው? በሰዓቱ እንቁላል ያለበትን ሳህን ሳነሳ ቅንጣት ታህል አላመነታሁም ነበር። ደስ እያለኝ ፓስታ በእንቁላሌን መብላት ጀመርኩ። አባቴ ሁለተኛውን ሳህን አንስቶ መመገብ ሲጀምር ግን ዐይኔን ማመን አቃተኝ። አባቴ ከሚበላበት ሳህን ውስጥ ሁለት የተቀቀሉ እንቁላሎች በፓስታው ተሸፍነው ኖሯል። አቤት እንዴት እንደተናደድኩ! ቆጨኝ በጣም! ቸኩዬ በመወሰኔ ራሴን ወቀስኩት። ምናልባትም በሕይወት ዘመኔ እንደዚያ ቀን የተበሳጨሁበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ይኼን ጊዜ አባቴ እየሳቀ፣ “የእኔ ልጅ… ዐይኖችህ የሚያዩት ነገር ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ መቼም እንዳትረሳ! ደግሞ በሰዎች ላይ ብልጣብልጥ ለመሆን ስትሞክር ትጎዳለህ!!” አለኝ። @heppymuslim29
እኔ ግን እጠይቀዋለሁ . . ይህች ምኗ ደፋር፣ ምኗ ዐይናውጣ ናት አሏት ጠየቀችው ተብሎ መወራቱን ሲሰሙ፡፡ ‹እኔ እሞታታለሁ እንጂ አልጠይቀውም፡፡› አለች አንደኛዋ፡፡ ‹እኔ ግን እጠይቀዋለሁ› አልኳት ኮስተር ብዬ፡፡ ‹አዎ እኔ ግን ባንቺ ቦታ ቢሆን እጠይቀዋለሁ፡፡› አልኳት፡፡ ‹እንዴት?› አለች ማነሽ ብርቄ ነይማ እስቲ … ምን መሰለሽ … ጉዳዩ ቀልድ አይደለማ፣ ጉዳዩ የቁምነገር ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ የዲን ጉዳይ ነው፤ ጉዳዩ ዱንያ አኺራን የማሳካት ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ ኢስላማዊ ቤተሰብን የመመሥረት ጉዳይ ነው፡፡ በጉዳዩ ዉስጥ ከራስ እስከ ማኀበረሰብ አርቆ የማሰብ ዓላማ አለበት፡፡ ለዚህ ነው እፍረቴን ገፍፌ እጠይቀዋለሁ ያልኩሽ፡፡ እንዲሁም ጉዳዩ ሌላ ጉዳይም አለው፡፡ ጉዳዩ ከሚወዱት ጋር የመኖር ጉዳይ ነው፡፡ ከሚወዱት ጋር መኖር ደግሞ ፀጋ ነው፤ ከሚወዱት መውለድ ደግሞ ሌላ ፀጋ ነው፡፡ የወደዱትን ማግኘት እንዴት ደስ ይላል መሠላችሁ! ዱንያ ሁለቴ አይኖርባትም። አስቦኝ ይሆናል ብዬ ካሰብኩ፣ ሰው እንደሌለው ከገመትኩ፣ ለኔ ጥሩ አመለካከት እንዳለው ካስተዋልኩ፣ አብሮ የሚሄድ ቀለም አለን ብዬ ካሰላሰልኩ የምሬን ነው የምላችሁ ዐይኔን በጨው አጥቤ እጠይቀዋለሁ፡፡ እናንተ እፈሩ እንጂ እኔ አላፍርም፡፡ ‹የትዳር አጋሩ እንድትሆኚው ያሰበሽ ሰው አለ› ቢለኝ ‹አንተስ ለምን አትሆነኝም?› እለዋለሁ ኮስተር ብዬ፡፡ ‹እስቲ ሚስት ምናምን ፈልጊ› ካለኝ ‹ ሚስት እኮ በዙሪያችን ሞልቷል› እለዋለሁ😁፡፡ ታሞ እንጂ ፈርቶ የሞተ ማን አለ!፡፡ ማን ያውቃል ደፍሮ መጠየቅ አቃተው እንጂ እሱም አስቦኝ ይሆናል፡፡ : : ‹ አረ ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀርም!› አለች፡፡ ‹ ጥንቅር ብሎ ለምን ይቀራል?› አልኳት፡፡ ‹ ምን ይቀርብኛል?› አለች፡፡ ‹ ጥሩ ባል ሊቀር ይችላል፡፡ አላህን የሚፈራና የሚያመልክ ጥሩ ቤተሰብ ሊቀር ይችላላ አልኳት. እናም እጠይቀዋለሁ እንጋባ ማለት ቅሌት አይደለም መውረድም፣ መቅለልም መዋረድም አይደለም፣ ሐያእ ማጣትም አይደለም፡፡ ሐያእ ማለት ሐቅን መሸሽ ማለት አይደለም፡፡ መውደድም ወንጀል አይደለማ፡፡ መንፈሳዊ ሕይወቱ ከሳበኝ፣ ታማኝነቱ፣ ኢማኑና ለዲን ያለው ትጋቱ ከማረከኝ ለምን ብዬ ነው የማፍረው እጠይቀዋለሁ፡፡ ሐሳቤ መልካም ነውና፣ ዓላማዬ ትልቅ ነውና፣ የዉስጤን አምላኬ ያውቃልና እጠይቀዋለሁ ብጠይቀው ምንድነው ጥፋቴ!፡፡ ባማክረውና ጥቅሙ የጋራችን ነው ብለው የት ላይ ነው ክፋቴ!፡፡ እሱን በማሰቤ ምንድነው ኃጢኣቴ፡፡ አትጠይቁ የሚል አስተምህሮ አለ እንዴ!፡፡ ለሚጠቅም ነገር መሽቀዳደም ጠቃሚ አይደለም እንዴ! እናታችን ኸዲጃ ነቢዩን የመሰለ ታላቅ ሰው ከእጇ ያስገባችው ጠይቃ አይደለም እንዴ!! ሆ … . እጠይቀዋለሁ ስል ታዲያ ኩሽማንኩሹን አይደለም፡፡ ትኩረቴም ፊቱና ኪሱ አይደለም፡፡ ትኩረቴ ኢማኑና ዲኑ ነው፡፡ ትኩረቴ ስብእናውና ዓላማው ነው፡፡ የሚኮራውንና የሚያስወራውን አይደለም የምጠይቀው፡፡ ኋላ ላይ ‹ጠይቃኝ፣ ወትውታኝ፣ አቻኩላኝ፣ መቆም መቀመጥ ነስታኝ፣ መግባት መውጣት ከልክላኝ … እኮ ነው ያገባኋት› ብሎ ሊመፃደቅ ይችላል ብዬ የገመትኩትን አይደለም የምጠይቀው፡፡ ቁምነገር ያለውን፣ ለምን እንደጠየቅኩት ከኔ በላይ የሚገባውን ነው የምጠይቀው፡፡ ስንቱ ሐራም ፍለጋ ብሎ ከቦሌ እሰከ ጉለሌ እየሄደ አይደለም እንዴ! እኔሰ ለሐላሉ ምን አሳፈረኝ?፤ ቢሳካ መልካም ነው፣ ባይሳካም አይከፋኝም፡፡ እንቢ ተባልኩ ብዬም አልሸማቀቅም፡፡ የሆነው ሁሉ አላህ ያለው ነውና፡፡ ለወንጀል አይደለም የጠየቅኩት፡፡ ለዝሙት አይደለም ያሰብኩት እና አልፈራም አላፍርም …. እጠይቀዋለሁ። ‹ሆ … እናንተ ፀሃፊዎች እኮ እማታመጡት የለ› አለች እታለሜ ሀሳቡን ሳነሳባት ጊዜ አፍጥጣ እያየችኝ፡፡ . . እኔ ይሄን አልፃፍኩም🙄፡፡ ሀሳቡ ግን የኔም ነው፤ መስማማት ያለመስማማት ደግሞ የግል ጉዳይ ነው😊 @heppymuslim29
ወጣቶች እንደሚተናኮሏትና እንዳስቸገሯት በመናገር ለወንድሟ አቤት ያለችውን እህት! ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫ ወስዶ ለፊትና የማያጋልጥ ኢስላማዊ ልብስ ገዛላትና መልበስ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አሁንም ወጣቶቹ ያስቸግሩሻል? በማለት ጠየቃት። የእህቱ ምላሽ፤ "በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ልብስ ከገዛህልኝ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ያከብረኛል" የሚል ነበር። ወንድሟ ይህን ሲሰማ እንዲህ አላት « የሚፈታተን ልብስ በመልበስ አንቺ ነበርሽ ማለት ነው የምትለክፊያቸው። እነሱ ቢሆኑ ኖሮ የጨዋ ልብስ ከለበስሽ በኃላም ማስቸገራቸውን ይቀጥሉ ነበር»። [ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞ ﻷَِّﺯْﻭَاﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ ﻭَﻧِﺴَﺎءِ اﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦ ﺟَﻼَﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰٰ ﺃَﻥ ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼَ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ] الأحزاب 59 «አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» አል አህዛብ 59 @heppymuslim29
ሰውየው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃዉን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው " የምንወዳቸውን እና የምናከብራቸዉን ጎረቤቶቻችን አብረውን እንዲበሉ ሄደህ ጥራቸው ። ” ልጁ ወደ ጎዳና ወጥቶ እንዲህ ሲል መጮህ ጀመረ “እባካችሁ የአባቴ ቤት በእሳት ስለተያያዘ ለማጥፋት እርዱን ድረሱልን!" ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጥቂት ሰዎች መጡ ሌሎቹ የእርዳታ ጩኸቱን እንዳልሰሙ ሆነዉ ቀሩ ። የመጡ ሁሉ ግን በሉ ጠጡ ። ባየዉ ነገር የተደናገጠው አባት ወደ ልጁ ዞሮ እንዲህ አለ "የመጡትን ሰዎች እኔ አላውቃቸውም ከዚህ በፊትም አይቼአቸዉ አላውቅም ስለሆነም ወዳጆቻችን ቤተሰቦቻችን እና የሥራ ባልደረቦቻችን የት አሉ? " ልጁም " ከቤታቸው ወጥተዉ የመጡት ሰዎች ቤታችን ላይ የተነሳዉን እሳት ለማጥፋት ጩኸት ሰምተዉ ሊረዱን እንጂ በቤታችን የተዘጋጀውን ፓርቲ ሊካፈሉ አይደለም ። ግብዣችንና እንግዳ ተቀባይነታችን የሚገባዉ ለእነዚህ ዓይነቶቹ ነዉ" አለ። ሁሉም የምትወዷቸውና የምታከብሯቸዉ ሰዎች እውነተኛ ወዳጆቻችሁ ላይሆኑ ይችላሉ ። እውነተኛ ወዳጅ ማለት በተቸገራችሁና የነርሱ ድጋፍ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ፈጥነዉ ከጎን የሚገኙ ናቸው። @heppymuslim29