tgindex
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR

Статистика
Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
18:46
Постов за неделю
0
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 106
+3 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 745
28 постов
Вовлечённость
82,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 28
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
841
1/48двое суток
963
1/72трое суток
1 039

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ለሚመለከተው ሁሉ ___ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዋትስአፕ አድራሻ (WhatsApp Account) በሌሎች አካላት የተጠለፈ ስለሆነ ምንም ዓይነት መልእክት ቢደርሳችሁ የብፁዕነታቸው መልእከት አለመሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

  • 25 июл.1 3002

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл.1 2952

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл.1 26032

    видео или голосовое, без подписи

  • 25 июл.1 13542

    ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! "ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።" (መዝሙር ፻፪፥፮) ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት። በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው። መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን! በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው። በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ። በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  • 16 июл.8 2301411

    ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሓላፊ/ሊቀ ጳጳስ እና የደቡብ ኦሞና አሪ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንኳን ለ፱ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላም አደረሰዎ! ቡራኬዎ አይለየን!

  • 10 июл.1 7716

    https://youtu.be/nRwTpWlUPSQ?si=e9eHkgrluGoSgIJE

  • 8 июл.2 05422

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 914

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 9457

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 79883

    የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) መልእክት _____ ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር። ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ (መዝ 118፥26) ከሁሉ አስቀድመን የ2018 ዓ.ም ተመራቂ ደቀመዛሙርት ሁላችሁም ከመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብና ቤታሰቦቻችሁ ጋር እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ የትምህርት ዘመናችሁን ስታጠናቅቁ የምናከብረው የምርቃት መርሐ ግብር የመማራችሁን ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት፣ በትዕግሥት እና በብርታት ያለፋችሁበትን ጉዞ ነው። የተወደዳችሁ ተመራቂ ደቀ መዛሙርት በሁሉም ፈተናና ችግር ውስጥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነበር፤ ዛሬም ወደዚህ የክብር ቀን አድርሷችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ። በክርስትና ሃይማኖት ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ሲገባ፣ እውነተኛ ስኬት በዲግሪ ወይም በስም ብቻ እንደማይለካ አስታውሱ። በፍቅር፣ በትሕትና፣ በታማኝነት እና በአገልግሎት የምታመጡት የሕይወት ለውጥ ከሁሉም የላቀ ነው። በፊታችሁ ያለው መንገድ የማይታወቅ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጀመረው ቅዱሳን ሐዋርያት እና ሐዋርያውያን አበው የተከተሉት፣ አበው ቅዱሳን ያስቀጠሉት እስከ ምጽአተ ክርስቶስ የሚቀጥል የሕይወት መንገድ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። “እኔ መንገድ እና እውነት፣ ሕይወትም ነኝ” (ዮሐ 14፥6) በማለት ያስተማረን አምላክ የጉዟችሁ መነሻና መድረሻ፣ የድካማችሁ ብርታት፣ የሃይማኖታችሁ ጽናት፣ ኃይልና ጉልበት መሆኑን እንድታስታውሱ አሳስባችኋለሁ። እርሱ ራሱ “እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ (28፥19) በማለት አብሮን እንደሚሠራ የገባውን ቃል ኪዳን እያሰባችሁ በእርሱ ያለውን ተስፋ፣ ጥንካሬ እና ዓላማ ዘወትር አስታውሱ። ያገኛችሁትን እውነትና ዕውቀት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለምታገለግሉታና ለተላካችሁበት ማኅበረሰብ ጥቅም አድርጉት። በምትሄዱበት ሁሉ “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች” (ማቴ10፥16) በመሆን የብርሃን እና የተስፋ ምሳሌ ሁኑ። የአገልግሎት ጉዞ ከፍታና ዝቅታ፣ አድካሚና አሰልቺ፣ እንደመሆኑ መጠን ሊከተላችሁ ሳይሆን እንድትከተሉት የሚያባብላችሁ፣ እንድታሳምኑት ሳይሆን ምርኮኛ ሊያደርጋችሁ የሚፈልግ ዓለም ከፊታችሁ ይጠብቃችኋል። እናንተ የክርስቶስ ወንጌል መልእክተኞች በመሆናችሁ ከዓለም የተለዩ የሰማያዊው መንግሥተ እግዚአሔር አምባሳደሮች ናችሁ እንጂ የብልጭልጩና ታይቶ የሚጠፋው የዚህ ዓለም ምርኮኞችና ቅጥረኞች አይደላችሁም። በምትሔዱበት ሁሉ የላከቻችሁን የእናት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ጠብቃችሁ አስጠብቁ። በጥበብ ተመሩ። በፍቅርም አገልግሉ። ያገኛችሁት እውነትና ዕውቀት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች በረከት እንዲሆን በጥበብ አድርሱ። የምትጓዙበት መንገድ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ መፈተናችሁ ከምትጠብቁት አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከማትጠብቁት፣ ይረዱናል፣ ይረዱናል ከምትሏቸውም በኩል ይሆናልና ተስፋ አትቁረጡ። ከክረምት ቀጥሎ በጋ፣ ከጨላማ በኋላ ብርሃን፣ ከመከራ ባሻገር ደስታ እንደሚመጣ የታወቀ ነው። በመልካም አገልጋዮች ዘንድም ከብዙ ድካም በኋላ ዘላለማዊ እረፍት እንዳለ እናምናለን። መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ (2ኛ ጴጥ 1፥10) እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እግዚአብሔር በእናንተ መታመን የጀመረውን መልካም ሥራ ይፈጽማልና በእምነት በፊታችሁ ያለውን ሩጫ ሩጡ። በእግዚአብሔር ታመኑ፣ በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ በበጎ ጥበብ የተሞሉ ናቸው። ቤተክርስቲያናችን ዕውቀት ያላቸውን ብቻ ሳይሆን፣ ርኅራኄ፣ ታማኝነት እና ፍቅር ያላቸውን ሰዎች ትፈልጋለች። ስለዚህ በሕይወታችሁ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የአባትነት ብርሃን ይታይባችሁ። ለመራራው ዓለም ማጣፋጫ፣ ሥጋዊው ዓለም ላደከመቻቸው ብርታት፣ ለቆሰሉና ለታመሙ ሐኪም፣ ግራ ለገባቸው መፍትሔ ልትሆኑ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ዛሬ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ለቅድስት ቤተክርስቲያን በቅድስት ቤተክርስቲያን መረቅናችሁ። በየትምህርት መርሐግብራችሁ ላለፉት የትምህርት ዓመታት ያስተማረቻችሁ፣ ለዚህ መዐርግም ያበቃቻችሁ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእናንት በሁሉም ዘርፍ ብዙ ትጠብቃለች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ የመማርንና የማገልግልን ምንነት አስረግጦ እንደነገረን “የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም ዐውቃለሁ መብዛትንም ዐውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊል 4፡1-13) እንዳለ በትምህርት ቆይታችሁ ዐውቀናል ስትሉ አለማወቅን አላወቅንም ስትሉ ጥበብን፣ በድካማችሁ ብርታትን ተምራችኋል፡፡ አሁን ደግሞ የበለጠው የኑሮና የሕይወት ትምህርት ቤት ከፊታችሁ አለ። በመኖርና በማገልግል የምትማሩበት፤ በቃል የሰማችሁትን በተግባር የምታዩበትና የምታሳዩበት፤ በጽሑፍ ያነበባችሁትን በአደባባይ የምትመሰክሩበት አዲሱና ቀጣዩን ትምህርት ቤት እንደጀመራችሁ ዕወቁ፡፡ በዚህ የሕይወትና አገልግሎት መስክ ችግር የምትፈቱ እንጂ ችግር የምታወሩ እንዳትሆኑ። ፈተናንን ምታሸንፉ እንጂ የፈተና ምክንያት ተደርጋችሁ እንዳትቆጠሩ። የሰውን ሸክም የምትሸከሙ እንጂ ሸክም እንዳትሆኑ። የጠበበውን የምታሰፉ፣ የተቆለፈውን የምትከፍቱ፣የተጣመመውን የምታቀኑ፣ የደፈረሰውን የምታጠሩ የጨለመውን የምታበሩ፣ አልጫውን የምታፍጡ እንድትሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአደራ ጋር ወደ ችግረኛው ዓለም ከዛሬ ጀምሮ ልካችኋለች፡፡ ታማኝ መልእክተኛ ለመሆን ያብቃችሁ። ውድ ተመራቂ ደቀመዛሙርት! ዛሬ ከታላቁ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ስንመርቃችሁ ትምህርት በቃችሁ እያልን እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። ይኽ የምረቃታሁ ዕለት በአንድ በኩል ለተቀደሰው አገልግሎት የጥሪ መጀመሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የነገረ መለኮት ትምህርት ተምረው የማይጨርሱት እንደመሆኑ ወደ ሌላው የትምህርት መንገድ መሻገሪያችሁ እንደሆነ ልብ በሉ። ከዚህ ተቋም የምትወጡት ዕውቀትን በአእምሮአችሁ ብቻ ሳይሆን፣ ጥሪን በልባችሁ ተሸክማችሁ ነው። እንደሚታወቀው ትምህርተ እግዚአብሔር (ቴዎሎጂ) የመጻሕፍት ንባብ ትምህርት ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔርን እውነት፣ ፍቅር እና ለሰው ልጆች ያለውን ዓላማ የምንረዳበትና መንፈሳዊ ሕይወትን የምናዳበርበት፣ አእምሮን የምንገነባበት መንገድ ነው። ስለዚህ ወደ አገልግሎት፣ ስትሰማሩ ወይም ወደ ትምህርትና ሌላ ጥናት ስትገቡ፣ ዓለም የሚፈልገውን ብቻ የምትናገሩ ሳይሆን ዓለም እናንተ የምትናገሩትን የሚሰማ የቃሉ ታማኝ አገልጋዮች እንድትሆኑ ነው። ሕይወታችሁ ከቃላችሁ በላይ ይስበክ። በትሕትና፣ በቅንነት፣ በፍቅር እና በመንፈሳዊ ወኔ ተመላለሱ። እግዚአብሔር በጥበብ፣ በሰላም እና በበረከት ይምራችሁ። አባ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የደበብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሰኔ 27፤2018 ዓ.ም

  • 4 июл.1 911

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 672

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 430

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 191

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 168

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 июл.1 8804

    ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ ሥጦታ ተበረከተላቸው ___ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ደቀ መዛሙርቱን በሚያስመርቅበት ወቅት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ገበታው የወርቅ ቅብ የሆነ የቅዳሴ መጽሐፍ ተበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ሓላፊ በራሳቸው እንዲሁም በሚዲያው በኩል የተለያዩ ሥጦታዎችን ሠጥተዋል። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት