tgindex
ኢስላማዊ ግጥሞች الشعر الإسلامي لسيد أبو ذر

ኢስላማዊ ግጥሞች الشعر الإسلامي لسيد أبو ذر

Статистика

አድናቆትን ዝናን ስምን ፈልጌ ሳይሆን አሏህ በሰጠኝ እዉቅና ወንድምና እህቶቼን ለማገልገል አንድ ጊዜ ተፈጥሪያለዉ እናም ዱኒያ አኼራዬን እንዲያሳምርልኝ በዱዓ አግዙኝ ለማንኛዉም ጥያቄ 👇 👇 @seidabuzerbot

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 428
−2 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
256
21 постов
Вовлечённость
17,9%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
57
1/48двое суток
65
1/72трое суток
70

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በምድር የቱንም ያህል ተስፋ ብናደርግና የቱንም ያህል ጠንካራ ሠራተኞች ብንሆን ፍላጎታችን ሙሉ በሙሉ አይሳካም፡፡ አንዱ ሲሞላልን ሌላው ይጎልብናል፡፡ በአንዱ ደስ ሲለን በሌላው ይከፋናል፡፡ ከፊሉ ጋር ጥሩ ፍቅር ስናገኝ በሌላው እናጣለን፡፡ ህያው ፍቅርና የምሉዕነት ዓለም ያለው በጀነት ነው፡፡ ከፊሉ ከከፊሉ የተለየ ስሜት አይሰጠንም፡፡ በጎነትና ተድላ ወይም ፍቅርና መተሳሰብ የምናገኝበት ውብ የፍቅር ምሳሌ ማለት ጀነት ነው፡፡ ስለጀነት ስናስብ በቅርቢቱም ዓለም ሆነ በቀጣዩ የሕይወት ምዕራፍ ጥሩ ምሳሌ እናገኛለን፡፡ በምድር ለምንሰራቸው ሥራዎች ትክክለኝነት ጀነት ወሳኝ ፋይዳ አለው፡፡ ምን ማድረግና በምን መስክ ራሳችንን መወሰን እንዳለብን መንደርደሪያ ይሰጠናል፡፡ በምድር የሠራነውን ብንሠራ ፍላጎታችን በምሉዕነት አይሳካም፡፡ በሁሉም መስክ ስኬታማ መሆን አንችልም፡፡ አቅማችንም ሆነ እድሜያችን ሁሉ ለማዳረስ አይበቁም፡፡ ስለዚህ የተወሰኑ መንገዶችን እንመርጣለን፡፡ ምርጫችን ከግብ ሳይደርስ ልንሞትም እንችላለን፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ቅፅበት ሊመጣ የሚችለውን የሞት መዘዝ አስተውለን ግባችንን ለመቅረፅ ጀነትን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ታላቅ የፍቅርና ደስታ መሰረት መሆኗን ስናውቅ ከሞት በላይ የሚያሳስበን የምንሠራው ሥራ ፍሬያማነት ይኖረዋል፡፡ t.me/muselimnegn

  • የኔ እህት ቢረዝምም ቀን ያልፋል ፅልመት ይገፈፋል ካፀና ሰው ልቡን ይጨብጣል ግቡን መንገዳድ ሁሉ አይሰጥም ለውድቀት ከመድረስ አያግድ ቢረዝምም ርቀት የተጣለው ፍሬ ያፈራል ከፀና ጊዜ የጣለውን ጊዜ ያነሳልና ብቻ መታገስ ነው ሰማዩ እስኪጠራ ብቻ መታገስ ነው እስኪደርሰን ተራ እሩቅ ከመሰለን ከፍታ ላይ ወጥተን ቀን አለን ለመሳቅ እንባችንን  ረስተን ብቻ መታገስ ነው፤ ሀዘን ያጠላበት ገፃችን ይፈካል ጨለማ እጁን ሰጥቶ ብርሃን ይተካል ሁሉም ቀኑ ሲደርስ ይጨብጣል ህልሙን ፈገግ ይላል ያኔ ይረሳል ህመሙን ብቻ መታገስ ነው፤ ጊዜ ዳኛው ፈርዶ ተራው የኛ ሲሆን የለም የማይቻል አይኖርም የማይሆን ብቻ መታገስ ነው፤ የሚነፍሰው ነፋስ እንዳሻው ሳይወስደን ከጅምር መሰልቸት ቁልቁል ሳያወርደን መሳሳትን ሳንሸሽ ውድቀትን ሳንፈራ መጠበቅ ብቻ ነው እስኪደርሰን ተራ t.me/islamawigetem

  • ሕይወት በየቀኑ ፈተና ናት ዱንያ በየዕለቱ እንቅፋት አላት ለቀናት በፈተና ከርመን ያለፈው አልፏልና ብለን ዛሬ  ምንም እንዳልተፈጠረ አስበን ለብሰንና ተጣጥበን  በሰው መሀል ቀና ብለን እንሄዳለን ያለፈውን ለትምህርት ካልሆነ በስተቀር እንረሳለን እንደገና ሕይወትን እንደ አዲስ እንኖራለን፣ ሐምድ ማለት ይህ ነው ሰው ከፈጠረው አምላኩ ጋር ምስጋና እንጂ ቂም የለውም እረፉ የሚለውም እሱ ተነሱ የሚለውም እሱ ነው ቢኢዝኒላህ ዳግም እናብባለን ጀሊሉ ከፃፈው ዉጭ በዚህች ምድር ላይ እየሆነ ያለ ምንም ነገር የለም t.me/muselimnegn

  • ሱምያእ(sumyaa'e) የጂኖች አባት ምድር ከተፈጠረች በኋላ ለረዥም አመታት ምንም አይነት ፍጥረት በላይዋ ሳይኖርባት ከርማለች።አላህም ምድር ላይ የሚኖሩ እና እሱን የሚገዙ ፍጥረታትን መፍጠር ፈለገ'ና ሱምያእ(sumyaa'e) የተባለን የጂኖችን አባት ፈጠረው። በመቀጠልም አላህ ለ ሱምያእ፦"የፈለግከውን ተመኝ" አለው። ሱምያእም፦"እኛ ማንንም እንድናይ እና ማንም ደግሞ እኛን እንዳያየን አድርገን...፣ በምድር ላይም ሰውረን...፣እዛውንቶቻችንንም ወጣት አድርግ..." አለ። በሱምያእ ምኞት መሰረት አላህም ምኞቱን ሊያሳካለት ቃል ገባለት።ከዚያም አላህ ሱምያእን እና ልጆቹን(ጅኖችን) ለረዥም አመታት ምድርን በአምልኮ እንዲያጌጧት አደረጋቸው።(ምድር ላይ ለመጀመርያ ግዜ አላህን ያመለኩት ጅኖች ናቸው) ጅኖች ምድርን በከፍተኛ ፍጥነት እየተባዙ ከሞሏት በኋላም አላህ የለገሳቸውን ኒዒማ ወዲያ ብለው በምስጋና ፋንታ አላህን ያምፁ ጀመር ያ አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ መገዳደል...፣ደም መፋሰስ እና መሰል አመፆችን በማስፋፋት ምድሪቱን እጅጉን በከሏት። ይህን ግዜ አላህም በአመፅ የተበከለችውን ምድር ለማፅዳት እና አመፀኛ ጅኖችንም ለመቅጣት የመላዕክት ወታደሮችን ወደ ምድር ላከ። መላዕክቱም ልክ ምድር እንደወረዱም ምድር ላይ ያሉ ጅኖችን በመውረር ከፊሉን ከገደሉ በኋላ የተቀሩትን ከምድር ያባሯቸው ጀመር። ይሁን እንጂ ጂኖች ቢሸሹም አብዝሃኛው ክፍላቸው ተገድለው ነበር'ና፤ የተቀሩት ጥቂቶቹ ወደ ተለያዩ ደሴቶች...፣ ባህር ዳርቻዎች እና የተራራ ጫፎች ላይ በመሸሽ አመለጡ። በመጨረሻም መላዕክት በወረራው ትርምስ ውስጥ ኢብሊስን ያዙት'ና ወደ ሰማይ ይዘውት ወጡ። ያን ግዜ ኢብሊስ ጨቅላ ህፃን ነበር። ከመላዕክቱ ወረራ በኋላ ምድር እጅጉን ጭርታ ውስጥ ገብታለች።ጅኖቹም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አያሳዩም። በዚህ ሁኔታ ብዙ አመታትን ካሳለፉ በኋላ ከመላዕክቱ ጋር በምርኮ መልኩ ወደ ሰማይ የወጣው ኢብሊስም በአስደናቂ የመላዕክቶች አምልኮ እና በመለኮታዊ ስነስርአት ሰማይ ላይ አደገ። ኢብሊስ ከመላዕክት ጋር የሚያደርገውን ድንቅ አምልኮ አጠናክሮ በቀጠለ ግዜም አላህ ለኢብሊስ የሰማአ-ዱንያን (የምናየውን ሰማይ) ሀላፊነት እና ስልጣንን ሰጠው። ኢብሊስ በተሰጠው ስልጣን እጅጉን ተደስቶ እና መላዕክትን እንዳሻው እያዘዘ እጅግ ለረዥም አመታት አላህን ካመለከ በኋላ አላህ ምድር ላይ አደምን የምድር ምትክ አድርጎ መፍጠር መፈለጉን ሲሰማ ይከነክነው ጀመር። አላህ አደምን ፈጥሮት ካጠናቀቀ በኋላ መላዕክትን እንዲሰግዱ ሲያዛቸው ሁሉም ለአላህ ትዕዛዝ እና ለአደም ክብር ባጎበደዱም ግዜ ኢብሊስ በኩራት አሻፈረኝ ብሎ መቆምን መረጠ። አላህም ኢብሊስን ለአደም ያላጎበደደበትን ምክንያት ሲጠይቀው ምላሹ፦"እኔ ከሱ የተሻልኩ ስሆን እሱን ከአፈር ፈጥረኸዋል፤ እኔን ደግሞ ከእሳት" ብሎ መለሰለት። አላህም ኢብሊስን ከእዝነቱ ካባረረው በኋላም አደምን እና ሀዋን ባዘጋጀላቸው ጀነት ውስጥ አስገባቸው'ና በጀነት ውስጥ ያለውን ሁሉ ሀላል አድርጎ አንዲትን ቅጠል ብቻ እርም አደረገባቸው። ይህን ነገር ኢብሊስ በሰማ ግዜም ለዘመናት በልቡ ትቀጣጠል የነበረችው የምቀኝነት እሳት ወደ ተንኮል መራችው'ና አደምንም በማሳሳት ከራህመት ለማስባረር ወሰነ። ይሁን እንጂ በጀነት ዙሪያ የተሰለፉ መላዕክት ኢብሊስን ወደ ጀነት መግባት ይቅር'ና አከባቢውን እንዲጠጋ አልፈቀዱለትም ነበር። ኢብሊስ በመጨረሻም አንድ ጥሩ ሀሳብ አመነጨ'ና… ይቀጥላል ታሪኩ ትምህርት አዘል ስለሆነ ይከታተሉት ። t.me/muselimnegn

  • без подписи

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ወዳጆቼ እንዴትናችሁልኝ በዉስጥ መስመር የጥያቄ እና መልስ ዉድድር ቀረ እንዴ ብላችሁ ለምትጠይቁኝ ወንድም እህቶቼ ከነገ ቡኋላ የጥያቄ እና መልስ ዉድድሩን እንጀምራለን  በአላህ ፍቃድ እናንተ ብቻ add በማድረግ አግዙኝ ባረከላሁ ፊኩም

  • እናት እና ልጅ የክርክር ሸንጎ ላይ ቁመዋል። የዘመኑ ከሊፋ ዑመርም ረዐ ሸንጎውን ከመንበሩ ተቀምጦ እየመራ ነው። ልጅ፦‹‹ይህች እናቴ ናት›› ብሎ ይከራከራል። እናት፦‹‹ልጄ አይደለም›› ብላ ትሞግታለች። የችሎቱ መሪም፦‹‹ሁለታችሁም ማስረጃዎቻችሁን አቅርቡ›› ብሎ አዘዘ። ልጅ እናቱ ስልመሆኗ ሚያስረዳለት ማስረጃ አልነበረውም ና ምላሽ አጣ። እናት ልጇ አለመሆኑን ለማስመስከር ያመጣቻቸው ቤተሰቦቿ ልጇ አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ጭራሽ ያላገባች መሆኗንም አክለው በመመስከር ይህ ልጅ በሴቱቲ ለሚቀጥፍባት ቅጥፈት የጁን እንዲያገኝ ሸንጎው ላይ አመለከቱ። የሸንጎው ሹም ዑመርም ረዐ ልጁ ላይ የግርፋት ውሳኔ አስተላልፎበት ለገራፊዎች አሳልፎ ሰጠው። ገራፊዎቹም ልጁን ከሸንጎው አስወጥተው ወደ መግረፍያው ስፍራ ሲወስዱት ዐሊይ ረዐ ከመንገድ ላይ አገኛቸው። ገራፊዎቹንም አስቁሞ ምክንያት ሲጠይቃቸው የሸንጎውን ውሳኔ ነገሩት። ዐሊይም ረዐ ገራፊዎቹንም ተገራፊውንም ይዞ ወደ ሸንጎው በመመለስ ጉዳዩን እሱ ሊመረምረው ተሰየመ። ‹‹ልጅሽ ነው?›› ብሎ ጠየቃት። ‹‹ገና አላገባሁም›› አለች። ዐሊይም ወደ ልጁ በመዞር፦‹‹ሸንጎ ላይ እንደካደችህ፤ ሽንጎ ላይ ካዳት›› አለው። ልጁም፦‹‹አንተ የነቢ አጎት ልጅ ሆይ! ወላሂ ይህች እናቴ ናት›› ብሎ ተማፀነ። ዐሊይም፦‹‹እሷን ካዳት አልኩህ! እኔ አባት እሆንኃለሁ፤ ልጆቼ ሀሰን እና ሁሰይንም ወንድሞች ይሆኑኃል›› አለው። ልጁም፦‹‹ክጃታለሁ፤ እናቴ አይደለችም›› ብሎ በሸንጎው አወጀ። ዐሊይም ወደ ሴትዮዋ ቤተሰቦች ዞር ብሎ፦‹‹ውሳኔዬ በዚህች ሴት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል›› አላቸው። እነሱም፦‹‹ያንተ ውሳኔ በእኛም ላይ ተፈፃሚ ነው ››አሉት። ዐሊይም፦‹‹እንግዲህ ይህች ሴት ለዚህ ልጅ ባዳ መሆኗን በሸንጎው ባረጋገጥነው መሰረት ይህችን ሴት ለዚህ ልጅ ድረንለታል። ሸንጎው ምስካሪ ይሁነን›› ብሎ ለሴቱቲ እሚሆን መህር እንዲያመጣ አገልጋዩን አዘዘው። ከዝያም ዐሊይ ረዐ ከሸንጎው እንደተሰየመ ወደ ልጁ በመዞር፦‹‹በል ሙሽሪትህን ይዝህ ሂድ፤ ግና በዚህ ሰሞን የጫጉላ ወዝህን እንዳይ ተመልሰህ እንድትመጣ›› ብሎ ከሸንጎው አሰናበታቸው። ሴቲቱ ደነገጠች፦‹‹በአላህ! በአላህ! ይህማ እሳት ነው። ወላሂ ይህ ልጄ ነው›› ብላ የእምነት ቃሏን እዝያው በቆመችበት ሰጠች። ዐሊይ ግምቱ ልክ መሆኑን ሲያረጋግጥ ደስታ ተሰማው፦‹‹ታድያ ልጅሽን ለምን ካድሽ?››አላት። ‹‹ይህን ልጅ የወለድኩት ከባርያ ዘር ነበር፤ የዚህን ልጅ አባት ቤተሰቤ ያለ ፈቃዴ እንዳገባ አስገድዶኝ ነበር ያገባሁት።  ይህንን ልጅ እንደፀነስኩ እባቱ በጦርነት ሞተ። ከዝያ ልጄን ስገላገል ወደ ሌላ ቀዬ ልኬው እንዲያድግ አድርጌ ከፍ ሲልም ልጄ አለመሆኑን ካድኩ›› አለች። ‹‹እኔ እኮ ዐሊይ ነኝ በማንም ማልሸወድ!›› ብሎ ሸንጎውን በብልኃት አጠናቀቀው። ምንጭ፦ موارد الظمآن لدروس الزمان t.me/muselimnegn

  • без подписи

  • እንደምን ነህ አባቴ ! ርቀኸኝ ያለኸው በመራቅህ ነፍሴን እረፍት የነሳኸው ከተለየን ወድያ እንዴት ነው ያለኸው ከሄድክብኝ ወድያ ወዳዲሱ ቤትህ ካልለመድከው ስፍራ እኛው ካስገባንህ በብቸኝነቱ ቤት፤ ኑሮስ እንዴት ያዘህ? እኔ እንኳ ደኅና ነኝ ካንተ ከተለየሁ ትዝታህ እያለኝ ምንስ እሆናለሁ ከትዝታህ ገፆች እያገላበጥኩኝ እሱን በማብሰልሰል እስካሁን አለሁኝ ባይሆን አባትዬ! ህመሜ በርትቶ ጤናዬን እማጣው ቀን ያሰብኩህ አንተን በህልሜ ሳጣህ ነው አንተን ያጣሁ ለታ ህመሜ እንዳይጠና እባክህ አባቴ ምሽት ምሽቱ ላይ በህልሜ ተሎ ና! 😭 t.me/islamawigetem

  • ጌታዬ!!! የልቦናዬን ስብራት የእዝነትህ ፈውስ እንጂ ጠጋኝ የለውም። ለድህነቴ የብልፅግናህ ደግነት እንጂ መድህን የለውም። ኢላሂ!!! የተስፈኞች ተስፋ ጣሪያው አንተ ላይ አበቃ።የጠያቂዎች ውጥን ባንተ ተሳካ። አንተ የሳሊሖች ወዳጅ...! አንተ የተጣሪዎች ሰሚ...! አንተ የስጋት መከታ...! አንተ የከንቱዎች ተስፋ...! አንተ የአማፂያን አለኝታ...! አንተ የችግረኛ ደራሽ...! መተናነሴ እና መዋደቄ ላንተ ነው፤ ዝቅታዬም እፍረቴም ላንተ ነው። ከውዴታህ ጣዕም ካስጎነጨኻቸው ባሮችህ ቀላቅለኝ። ጌታዬ! ይኸው ከቸርነት በርህ ያመፀህን ራሴን በተውበት ካባ ሸፍኜው አቀርቅሬ ቆምያለሁ፣ ከቸርነትህ ልትለግሰኝም ከጅያለሁ፣ ከጠንካራው ገመድህም ይዣለሁ። ያ ረብ! ምላሱ የረዘመውን፤ ስራው ያጠረውን ባርያህን እዘንለት። ከልቅናህ ጥላ ስርም አስጠልለው። ኢላሂ! አንደበቶች የልዕላንህን የውዳሴ ጣርያ መድረስ ተሳናቸው፣ ምናቦች የልቅናህን ውበት ለመገመት አቅም አጠራቸው። ያ መውላይ! የፊትህን ፍካት ለማየት አይኖች ተስኗቸው ተሰበሩ፣ ለፍጥረት ስላንተ ምንነት እንዳያውቁ አለማወቅን መንገድ አደርግክላቸው። ያ ረባህ! ስላንተ በምናብ የሚቀረፁ የውዳሴ ቃላትን ናፍቆት በቋጠሩ የእንባ ብዕሮች መፃፍ ምንኛ ያረካል። ያ ኢላሂ! አንተ የጠፊዎች አዳኝ...! አንተ የምስኪኖች ረዳት...! አንተ የባይተዋሮች ምሽግ...! የሀፅያትን ጉድጓድ መሽጋ በምታዘጋጅልን የፈተና ሀገር አደራህን አሸክመህ አስቀመጥከን፤ በአታላይ ገመዷ አንጠልጥላን ስናምናት በክህደት ምላጯ ገመዷን በጥሳ አደራህን አስጣለችን። ያ መላዚ! ከምድሪቱ የክህደት ሴራዎች ሁሉ ባንተ እንጠበቃለን። ከአብለጭላጭ አታላይ ጌጦቿ ባንተ ብርሃን እንከለላለን። t.me/muselimnegn

  • ታላቃችን ናት ፊቷም ሕይወቷ ኮስተር ያለ ነው። ቁምነገር እና ታታሪነት የሞላበት። በሥራም፣ በትምህርትም፣ በዓላማዋ ጎበዝ ናት። እንደሞዴላችን ነው የምናያት ከኛ በፊት ነበር ትምህርት የጨረሰችው ከሆነ ድርጅት በቆንጆ ደሞዝ ተቀጠረች። አግቢ አልናት፣ ሳቀችብን። ትንሽ ቆይታ ባህር ማዶ ተሻገረች። አሁንም አግቢ አልናት። አፌዘችብን፣ በንቀት አየችን፣ ስለ ዓላማዋ ትላልቅ ነገሮችን ነገረችን። የእናት አባቷን ደስታ ሳታይ፣ ወንድም እህቶቿን ለቁምነገር ሳታበቃ ማግባት የሚባል ነገር እንደማይታሰብ ነገረችን። እኛ አገባን። ወለድን፤ ወላለድንም። ነገርናት። ዓላማ የሌለው ሰው አድርጋ ቆጠረችን። እንዳሰበችው ለወላጆቿ ቤት ሠራች፣ መኪናም ገዛችላቸው። ሐጅም አስደረገች። እሷ ግን ትንሽ ልሥራ እያለች ቆየች። ቤቱን እናቷ ሶስት ዓመት ኖረውበት ዱንያን ተሰናበቱ። ሐዘን የበዛባቸው አባትም ከሁለት ዓመት በኋላ ሚሽታቸውን ተከተሉ። አገር ገብታ አይደለም የነርሱን ደስታ ለማየት ሲሞቱና ሲቀበሩ ለመድረስ እንኳን አልታደለችም ። ኋላ ቆይታ ዙርያዋን አየች። እናት አባት አኺራ ሄደዋል። ወንድም እህት የውርስ ድርሻቸውን ይዘው ክደዋታል። ቆምብላ ዱንያን ከለሠች። ብቻዋን ቀርታለች። አሃ ብላ ራሷን አሰበች። ወደራሷ ተመለሠች። አገባች። በትዳር ሁለት ዓመት ቆየች። የሆነ ቀን ደወለችልኝ ። ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነበር። ደንግጨ ምነው አልኳት። ልጅ እንቢ አለኝ ዱዓእ አድርግልኝ አለችኝ ። 45 ዓመት ሆኗት ነበር ። ቆይ ይህችን ልሙላ እንዳለች ሳይሞላላት እናትም፣ አባትም፣ ዕድሜም፣ ሕይወትም አመለጣት። ወዳጆቼ እሷ አትሞላምና ዱንያን ለመኖር ነገ ከነገ ወዲያ አትበሉ ነገ በእጃችሁ የለምና ሕይወትን ዛሬውኑ ኑሩ። ዕድሜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ ። ሁሉም ነገር በጊዜው ያምራልና ነገሮችን በጊዜያቸው ከውኑ። ለናንተ ከናንተ በላይ የሚያስብላችሁ የለምና ለራሣችሁም አስቡ። t.me/muselimnegn

  • без подписи

  • ለብዙ ሺህ አመታት አለምን በሀያልነት ሲያሸብሩ ኑረዋል። የአለምን ግዛት ለሁለት ከፍለው የፈለጉትን የአለማችንን ክፍል ህዝቦች ረግጠው ለበርካታ ዘመናት ገዝተዋል። እነኚህ ሁለቱ ሀያላን ሀገራት በጦር አቅማቸው ተፎካክረው የአለምን የመሪነት ስልጣን ለመቀዳጀት ለ700 አመታት ከባባድ ጦርነቶችን በሁለቱ መካከል አካሂደዋል። ሮም እና ፐርሺያ የጦር አቅማቸው እጅግ የሰለጠነ እና ብዛታቸውም እልፍ አእላፍ ስለነበር ማናቸውም ሳይሸናነፉ 700 አመታትን ተፋልመዋል። ለ7 መቶ አመታት የዘለቀው 1,000 የጦርነት ግጥሚያ ማብቅያ ጠፍቶለት ሀገራቱን በስጋት እና ፉክክር አከባብሮ አቆማቸው። የነብይህ ሰሀባዎች ድንገት ባዶ እግራቸውን ከመካ በኢማን ወኔ ተሞልተው ወደነዚህ ሀያላን ግዛት ተጓዙ። ለ700 አመታት የቆየውን የጦርነት ፉክክር ወድያ ትተው በ4 አመታት ሁለቱንም ሀያላን ሀገራት አንበረከኳቸው። ምን ሆነ መሰለህ! ያለሜዳቸው እና ያለ አቅማቸው ለጦር የተጓዙት ስንቅ አልባ ሰሀባዎች በ15 ግጥምያዎች ብቻ ፐርሺያን ሲያንበረክኩ ፤ ሮምን ደግሞ በ9 ግጥምያዎች በቁጥጥር አውለዋቸዋል። ከሁሉም እሚገርመው በ 200,000 ዘመናዊ ሰራዊት የፀናን ስረወ መንግስት የረሱሉ ሰዐወ ደረሳዎች በ 15,000 ወታደር በ4 አመታት ብቻ መበታተናቸው ነው። ክብር አይገባቸውም'ን? t.me/muselimnegn

  • አንድ ሰውዬ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ መጣና “እገሊት ብዙ ትሰግዳለች፣ ትፆማለች፣ ትመፀውታለች፣ ነገር ግን በምላሷ ጎረቤቶቿን ታስቸግራለች፡፡” አላቸው። እርሣቸውም “እሷ የእሣት ናት።” አሉት። እንዲሁም “እገሊት ደግሞ ብዙም ሶላት፣ ፆም፣ ምፅዋት የላትም፣ ጎረቤቶቿንም በምላሷ አታስቸግርም፡፡” አሏቸው። “እሷ የጀነት ናት፡፡” አሉት።   ቁምነገሩ በኪስህ ቁርአን ይዘህ መዞር አይደለም። ቁምነገሩ በባህሪህ ላይ አንዲት የአላህ ቁርአን አንቀፅ ተንፀባርቃ መታየቷ ነው። ሲዋክ ሱና ነው። ነገር ግን የሰውን ሥጋ የምትበላ (ሰው የምታማ) ከሆነ ትርጉሙ ምንድነው? ሐዲሥ መሐፈዝ ደስ የሚል ነገር ነው። ነገር ግን በሰዎች መካከል ነገር ለማመላለስ የምትሄድ ከሆነ ምንም አልጠቀመህም፡፡ ሰዎችን እየለያየህና ቤተሰብ እየበተንክ የተፍሲር ኪታቦችን ብትሰበስብ ምንድነው ትርጉሙ? በሰው ገንዘብ ላይ እጅህ የረዘመ ሆኖ ሳለ ሱሪህ ቢያጥር ምን ፋይዳ አለው? ፊትሽ በኒቃብ ተሸፍኖ የሰውን ነውር እየገለጥሽ ብትውይ የቱ ላይ ነው ኢማንሽ? ለሥራ ኃላፊህ የሰው ሥም ስታነሳ እየዋልክ ሱና ፆም ላይ ብትዘወትር የቱ ላይ ነው ጿሚነትህ? አላህ (ሱ.ወ.) የአምልኮ ተግባራትን ይወዳል፤ ሰውን ማስቸገርን ግን ይጠላል፡፡ ሲበዛ ሞኝ ሰው ማለት የቂያማ ቀን ተራራ የሚያክሉ መልካም ነገሮችን ይዞ የሚመጣና ዱንያ ላይ ሰዎችን ሲያስቸግር በመኖሩ ምክንያት አንድ በአንድ መልካም ነገሩ (ምንዳው) የሚወሰድበት ነው። t.me/muselimnegn

  • ልቤ_ስማኝ💞 __ ለጅስሜ ፍትህ አዳይ ኑረትን ምታደርሰዉ በሌት በቀትር ሳትደክም ሕይወትህን ምትለኩሰዉ ,,,,,,,,, ግድ የለም ስከን አትክነፍ ከሮጡት ጋር አታሩጠኝ ,,,,,,, ለአፍታ ጆሮህን ሰተኸኝ እህህህ ,,, ብለ ብታደምጠኝ ___ #ልቤ_ስማኝ ጭላንጭል ብርሃን አይተህ ፅልመት ዉስጥ አትራመድ ,,,,,,,, ኑሓ በሌለበት መርከብ ላይ ብቻህን ከቶ አትነግድ በከንቱ መባዘን ትተህ ኢማን ሰንቀ አሻግረኝ ,,,,,, ከሰላም ደሴት ጥለኸኝ በጽዳል ከበህ አኑረኝ ____ #ተዉ_ልቤ_ስማኝ ትህትናዬን ኮልሰህ እንደ ልጅ ልሳሳ ለሰዉ ,,, ድንድን ጠባዬን አግራልኝ የህዋነቴን መልሰዉ ምንስ ክፉ ሆነዉ ብታይ እሾህ ጋሬጣ ከይቅር ባዮች መድበኝ ጠላቴን በምህረት ልቅጣ ___ ,,,,, #ልቤ_ስማኝ የእዝነት ጦርህን ይዘህ በመስጠት በጥሩነት ጀቡነኝ ለግሼ በደል ልመልስ በለጋሽነት አጅገኝ ባይኖረኝ ብጓደል እንኳ በተስፋህ ተስፋዬን አብራዉ ,,,,,, ኸይር እንደሞላልኝ አድርገ ምናቤን ምራዉ __ #ልቤ_ስማኝ ጽኑ ኩኑኔ ላይ ጥለኸኝ ከጻድቃን እንዳልሰለፍ በመለኮት ጮራ ምራኝ በርክሰት እንዳልጠለፍ ,,,,,, ግድ የለም አንዴ ተለመን ፍትህ የማታዛንፍ ደምን የምትረጭ ለጅስሜ እህህ ብለኸኝ ተመከር አይክሽፍም የእሩቁ ህልሜ t.me/islamawigetem

  • አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ እንዴት ነህ ሰይድ አቡዘር  ፁሁፎች ለእኔ ብርታቴ  ተስፋዬ መፅናኛዬ.......  ሳነብ ይቀለኛል  አሁን ላይ እየደከመኝ ነው የወንድም ዱዓ ያስፈገኛል በመልካም ዱዓህ አግዘኝ። የልብ ሐኪም እየመሰልኳቸዉ ፣ ኢማን ያለኝ እየመሰላቸው የዚህ ዓይነት መልዕክት በየቀኑ ያደርሱኛል ብዙዎች ማን ያልደከመው አለ ወዳጆቼ  ቆሜ ስሄድ ሰው መስያችሁ ነው!! ከመንገዱ ላለመውጣት የሞት ሞቴን የምንገዳገድ ደካማ ሚስኪን ነኝ። በመልዕክቶቼም አብረን እንበርታ ለማለት እንጂ ብርቱ ሆኜ አይደለም እየወደቅንም እየተነሳንም መቼም ይህችን የዱንያ ጉዞ እንጨርሳታለን መቼስ ጌታችን አላህም በመልካም ሁኔታ ይቀበለናል ኢንሻአላህ በርቱ፣ ጠንክሩ፣ አብሽሩ ከመጠንከር ዉጭ ምን አማራጭ አለን ወዳጆቼ t.me/muselimnegn

  • ቆይታ ከአላህ ጋር ምንኛ ያምራል! ከአላህ ጋር ለመገናኘት ቅድመ ቀጠሮ ሳያሻህ እና በወራዳነትህ ማንም ሳይከለክልህ በተረጋጋ ሁኔታ አግኝተህ ታወጋዋለህ። እሱ ቸር ነው። ከአላህ ጋር ስታወጋ ለወሬህ መርዘም እና ለቆይታህ ብዛት ይቅርታ አትጠይቀውም፤ ምክንያቱም ደጃፉ ሁሌም ላንተ ክፍት ነው በቆየህ ቁጥር እሱ ዘንድ ትወደዳለህ። አይሰለችህማ! ይወድኃል። ከአላህ ጋር ስታወራ የቃላትህ መጉደፍ እና የአገላለፅ ብቃት ባይኖርህ አያሳስብህ፤  ከምላስህ ቅልጥፍና ይልቅ የልብህን ትርታ ነው  በትኩረት የሚያዳምጥልህ። እሱ ያውቅኃላ! ከአላህ ጋር ስታወጋ አይኖችህ በእንባ ተሞልተው ድምፅህ በሲቃ ሲቆራረጥ ሀፍረት አይያዝህ፤ እሱ ዘንድ ድክመትህ እና ለቅሶህ ክብር ነው። መዋደቅህም ልቅናህ ነው። ይረዳኃላ! ህመምህን ስለሚያውቅ! ከአላህ ጋር ስትመሳጠር  ለማንም ማታወጋውን ገመናህን በሹክሹክታ ትነግረዋለህ። እንዴት እንዳመፅከው ስታወጋው እንኳ ማመንህ እንደማያስቀጣህ ትተማመናለህ። ቸር ነው፤ አንተም ታወቃለህ! በመጨረሻም በቆይታ ግዜህ አደራ ብለህ የነገርከውን ሀጃህን ሁሉ ከደጃፉ ትተህ ስትነሳ ጉዳይህ በጌታህ ቁጥጥር ስር ክትትል ይደረግልሓል። በባዶ አትነሳም። አይሳነውማ! ሰው ሆይ! ምንኛ ታደልክ! ጌታዬ ብለህ ስትጣራ፦‹‹አቤት ባርያዬ! አብሽር ባዶ አትመለስም። ሀጃህን እፈፅምልኃለሁ፣ አልያም እየወረደ ያለን በላእ እመክትልኃለሁ፣ አልያም ለችግርህ ቀን ምንዳ አድርጌ እክስኃለሁ። አብሽር ባርያዬ›› የሚል አክባሪ ጌታ አለህ። t.me/muselimnegn

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ወዳጆቼ እንዴትናችሁልኝ  ይህን ቻናል እንዴት አያችሁት ምን ላስተካክል ሀሳብ አስተያየታችሁን ጀባ በሉኝ

  • ከምኞቴ ባህር መርከቤን አሻገርኩ ወዳሉበት አገር መልህቄንም ጣልኩት የዘመናት ግቤን ላንቱ ለመናገር ( ምኞት ነዉ) እርሶ ባሉበት ሰልፍ ሁሌ ሚሰለፈዉ ይሄ ባለ ጉዱ እባባብ የነደፈዉ .... ሩሁን አስምጦ በኢማን ወንዝ ላይ ወርዉሮ የጣለሎት ገንዘብና ነፍሱን ለእርሶ የሰዋሎት እንዲያዉ ቢፈቅዱልኝ ሲዲቅ ልሁንሎት _____ ____ #ወይስ መሞትዎን አይደለም መታመሞ ሚያመዉ በመዳፎ ዱዓ ቀልቡን ያሰለመዉ ያአዉራጅ ገዢ ዑመርን አስመኘኝ ...... በምናቤ ባህር እንደዚ አስዋኘኝ ከጎኖ ለመቆም አንድ ሰይፍ ተዉሼ ሞቱ ያሉኝ ለታ ደም እምባ አልቅሼ ናፍቆቴን ልዳብስ ከፊትሁ ተክዤ እንዲህም አስባለዉ ___ የጥቁሮች ልዑል የአዛኑ ሰንደቅ ይህን ፅልመት አለም ...... በማህሌቱ ጸዳል ዘዉትር የሚያጠምቅ ስምሁን እየጠራ ባለ መልክ ልሳኑ በሃሴት የሚያድሰዉ ለልቡ ትርታ አንቱን የሚያደርሰዉ ወይስ ቢላል ልሁን ...ተነስ በሉኝና አዛን ልበል አሁን __ ለዚህም ካልታጨሁኝ ለዚያም ካልታደልኩኝ ጧኢፍ ልሂድና ከእግሮ እየፈሰሰዉን ደሙን እየጠረኩኝ ምነዉ ያነቢዬ አንቱን በዘየርኩኝ _____ እርቃኔን ልካለዉ ካለሁበት ቀዬ ከአድማሱ ይግፉኝ ልምጣ አንቱን ብዬ ያለሁበት ቦታ የትም ይሁን የትም ጉልበቴን ግን ለእርሶ መቼም አልሰስትም __ ዘዉትር ከጉያዎ በሆንኩኝ አዝማሪ እንደ ሐሳን ቅኔ በአንደበቴ ሰይፍ ጉብዝናን ቀማሪ የቅኔ አድባራት ለአንቱ ቢታደሙ ይሰለቡብኛል ለእርሶ ቃላት ሳስስ ከባድ ያልኩት ፊደል ይሰለብብኛል _____ የአቅሜን ይስጠኝ እንጂ ግዑዝ ሆኜም ልቅረብ ,,,,,,, ዋሻ ልሁንና ያ በሻሻ ገፆን በማጀቴ ልክበብ #ግድ_የለም ሰዎች ጥርብ ብለዉ አርቀዉ ቢገፉኝ ሚንበር ያርጉኝና ሁሌም ይደገፉኝ በአካል ባይቀናኝ በሀሳብ እመጣለሁ በአዱኒያ ቀለብ ከሰባዉ ገላዬ ፊዳ እልዎታለሁ t.me/islamawigetem

  • без подписи