tgindex
ኢማን መልቲሚዲያ

ኢማን መልቲሚዲያ

Статистика

<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >> ሱረቱል ዐስር፦(1፥3) 👇👇👇 @deva_1st https://telega.io/c/sineislam

Последний пост
27 окт.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
18 092
−37 за 3 дн.
Сутки
−21
−0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 438
23 постов
Вовлечённость
35,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 27 окт.5 003518

    📝 ተጠንቀቅ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ اللَّهَ يُعَذِّبُ الَّذِينَ يُعَذِّبُونَ النّاسَ في الدُّنْيا.﴾ “አላህ እነዛን በዱኒያ ላይ ሰዎችን ያለአግባብ ይቀጡ የነበሩትን አላህ በአኼራ ላይ ይቀጣቸዋል።” 🌱 ሙስሊም ዘግበውታል: 2613 @sineislam @sineislam

  • 7 сент. 2025 г.12,5 тыс644

    በዚህ ሰዓት የሚሰማቹ ፍርሃት ሁሌም አላህን መፍራትና መታዘዝ እንዳለብን ያሳየናል ያጀመዓ አይመስላቹም!?

  • видео или голосовое, без подписи

  • 7 сент. 2025 г.10,1 тыс195

    ያጀመዓ በዱዓ ተበራቱ🤲

  • #ፈገግታ_ሱና_ነው። ባል ሚስቱ ጋ ተጣልቶ ሚስት ቤተሰቧ ጋ ትሆናለች : ባል ፦ደወለ : ሚስት፦ ሄሎ : ባል፦ነይ ተመለሽ ቤትሽ ? : ሚስት ፦መጀመሪያ ይሄን አድርግልኝ፤  ብርጭቆ አለህ : ባል ፦ አዎ አለ : ሚስት፦ሂድና አምጣ : ባል፦አመጣው ? : ሚስት፦ ወርውረህ ስበርው! : ባል፦ወረወርኩት? : ሚስት ፦እንደ በፊቱ መመለስ ትችላላህ? : ባል፦ፕላስቲክ ስለሆን አልተሰበረም : ሚስት፦ይስበርክ አልልም ናና ውስደኝ በር ላይ ቁጭ ብያለው። በባል እና ሚስት ፀብ አትግቡ። ለማለት ነውስ። @sineislam

  • ቻናል ለምትፈልጉ 👇 Price 400👉 @kurulus_osman_eth1 Price 650👉 @kurulusosmanethiopia1 Price 450👉 @selahadin_eyyubi Price 350👉 @Halal_promotion25 Dm👇 @deva_1st

  • 🖋እንደዉ በጥሞና ላደመጠዉ ለቀልብ ሰላም ይሰጣል አቅልን ከጭንቀት ይገላግላል።ፊደላቱ የተደረደሩበት መንገድ አጂብ ያሰኛሉ እያንዳነዱ አንቀፅ ድንቅ ተዓምርን አዝሏል፤እንደዉ ጥመት ካልሆነ እርሱን ማስተባበል ከቶ አይቻልም #ቁርዐን አላህ አንብበዉ ካስተነተኑት አስተንትነዉም ከተጠቀሙበት ያድርገን አሚን🤲 @sineislam @sineislam

  • ምስጋና ሊመራህ ሲሻ ባላሰብከዉ ወቅት በሻዉ መንገድ ነዉ:: ግደለኝ እያልከዉ የህይወት አይነት ያዘንብብሀል:: መመራትህ በችግር ዉስጥ ሲሆን ደግሞ ልኖር ነዉ ስትል 10 ሞት ይመጣል:: አይጥላህ ብቻ እንጂ:  መንገድህ ለቅጣት አይሁን እንጂ ባሪያን የማንሳትን ጥበብ ያሳይሀል::ፈጥሮ የተወ ጌታ በጭራሽም የለንም::ጌታዬ ጥራት ይገባህ 🩵 ووجدك ضالا فهدى [ Adh-Dhuha :7]   የሳትክም ሆነህ አገኘህ: መራህም        [አል-ዱሀ:7] @sineislam @sineislam

  • የመስጂድ ስርዕቶች ❶ መስጂድ ከመምጣት በፊት ነጭ ሽንኩርት ከመመገብ መቆጠብ ❷ ሴት ልጅ ሽቶ ከመቀባት መቆጠብ ❸ ወደ መስጂድ ሲኬድ በእርጋታ መራመድ ❹ ወደ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመጅዕል ፊቀልቢ ኑራ ወፊ ሊሳኒ ኑራ ወፊ ሰምዒ ኑራ ወፊ በሰሪ ኑራ ወሚን ፈውቂ ኑራ ወሚን ታህቲ ኑራ ወአን የሚኒ ኑራ ወአን ሺማሊ ኑራ ወሚን አማሚ ኑራ ወሚን ኸልፊ ኑራ ወአእዚምሊ ኑራ ”)ማለት ❺ መስጂድ ሲገባ ቀኝ እግርን ማስቀደም ❻ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊ ሙሀመድ አላሁመፍታህሊ አብዋበ ራህመቲክ ”)ማለት ❼ ሁለት ረከዕ (ተህየተል መስጂድ) መስገድ ❽ መስጂድ ውስጥ ከመትፋት መጠንቀቅ ❾ መስጂድ ውስጥ ድምፅን ዝቅ ማድረግ ❿ መስጂድ ውስጥ ከመሸጥና ከመግዛት መቆጠብ ❶❶ መስጂድ ውስጥ የጠፋን ነገር አፋልጉኝ ከማለት መጠንቀቅ ❶❷ አዛን ከተደረገ በሆላ ከመስጂድ አለመውጣት ❶❸ ከመስጂድ ሲወጣ ግራ እግርን ማስቀደም ❶❹ ከመስጂድ ሲወጣ ይህን ዚክር (“አላሁመ ዒኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ”)ማለት @sineislam @sineislam

  • በጥቅሉ የጁሙዓ ኹጥባ የጁመዓን ሶላት ተቀባይነት ያለው ከሚያሰኙ መስፈርቶች መሀል አንዱ ነው። ከአሏህ ዲን ምልክቶች (ሸዓኢር) መሀልም ይመደባል። ለዲኑ ምልክቶች ደግሞ የተለየ አክብሮትና ዕውቅና መስጠት ተገቢ ነው። በመሆኑም ሰጋጆች በልባቸውም ሆነ በአካላቸው ወደ ኹጥባው ማተኮር አለባቸው። በሌላ ነገር መጠመድ የለባቸውም። መብላት፣ መጠጣት፣ ጨዋታ፣ ቁርኣን ማንበብም ሆነ በማንኛውም ነገር መጫወት የለባቸውም። በኹጥባ መሀል መተኛትም ሆነ መናገር አይገባም። ምክንያቱም የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በዚህ መሰል ነገሮች ዙሪያ ያስተላለፉት ጥቅል መመሪያ አለ፡- “ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ባለበት ጓደኛህን ዝም በል ካልከው በእርግጥ አበላሸህ!” ያበላሸ ሰው ደግሞ የጁመዓው ምንዳ ጎዶሎ ይሆናል። ነገርግን ጁመዓው ከነጭራሹ ይፈርሳል አይባልም። ምክንያቱም ይች ጁሙዓ ከሰውየው ጫንቃ ላይ የጁመዓን ግዴታ እንደምታነሳለት ስምምነት አለ። አሏህ የተሻለ ያውቃል!

  • ⓻👉ድምፅን ከፍ አድርጎ ሶላት እና ሰላምታን በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ማውረድ በዚህ ጊዜ የሚገባው ድምፅን ዝግ ማድረግ ነው። አል-ኪሳኢይ ኹጥባውን ማድመጥ በነብዩ ላይ ሶለዋት ከማውረድ ይበልጣል ብለዋል። ስለዚህ ኹጥባ ላይ ስማቸው ሲሰማ ኹጥባውን ማድመጥ እንጂ በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ አይገባም። ምክንያቱም በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት የማውረድን ቱሩፋት በማንኛውም ወቅት ሊያገኘው ይችላል። ኹጥባውን የማድመጥን ቱሩፋት ግን መቼም አያገኘውም። ኹጥባው በዚያ ወቅት ነው የሚገደበው። ስለዚህ  ኹጥባውን ማድመጥ ይበልጣል። ከአቡ ዩሱፍ እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል፡- “የርሳቸውን ሥም ሲሰማ ድምፁን ዝግ በማድረግ ሶለዋት ያውርድ። ምክንያቱም ይህ ኹጥባውን ከማድመጥ አያግደውም። በመሆኑም ሁለቱንም ቱሩፋቶች በአንዴ ያገኛል።” (በዳኢዑ-ስ-ሶናኢዕ፤ ቅፅ፤ ገፅ 38)።

  • ⓺👉በትከሻ ላይ መራመድ ከዐብዱሏህ ቢን ቡስር በተዘገበው ሐዲስ ላይ እንዲህ የሚል ተገኝቷል፡- “አንድ ሰው የሰዎችን ትከሻ በጁመዐ ቀን እየተራመደ መጣ። የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ኹጥባ እያደረጉ ነበር። ከዚያም የአሏህ ነብይ፡- اجلس آذيت وآنيت “ተቀመጥ! ሰው እራስህ ዘግይተህ ሰዎችን አስቸገርክ!” አሉት። ሸውካኒይ እንዲህ ይላሉ፡- “የዒልም ሰዎች የሰዎችን ትከሻ መራመድ የሚሰጠውን ብይን አስመልክቶ የተለያዩ ሐሳቦች አሏቸው። ቲርሙዚይ የዒልም ሰዎችን ሃሳብ እያስረዱ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑለሞች በጁሙዐ ቀን የሰዎች ትከሻ መራመድን ጠልተዋል። ጥላቻቸውንም አጠንክረውታል።” አቡሐሚድ “ተዕሊቅ” የተሰኘው መፅሃፋቸው ላይ ከሻፊዒዮች እንደዘገቡት የሰዎችን ትከሻ መራመድን በግልፅ ሐራም ብለውታል። ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፡- “ትክክለኛውና የተመረጠው ሃሳብ ሐራም መሆኑ ነው። ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሶሒሕ ሐዲሶች መጥተዋል። የኢማም አሕመድ ተከታዮች ግን ይጠላል በማለት ተብቃቅተዋል።” (ነይሉል-አውጣር፤ ቅፅ 5 ገፅ 345)።

  • ⓹👉መብላትና መጠጣት ኢብኑል ሁማም አል-ሐነፊይ እንዲህ ብለዋል፡- “በኹጥባ ወቅት በመልካም ማዘዝ፣ ተስቢሕ፣ መብላት፣ መጠጣት እና መፃፍን የመሰሉ ነገሮች ሐራም ናቸው። ያስነጠሰን ሰው ማስደሰት እና ሰላምታን መመለስ ደግሞ የተጠላ ነው።” (ፈትሑል-ቀዲር፤ ቅፅ 3 ገፅ 239)። ኢማም ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፡- “ሰዎች ኹጥባ ሲያዳምጡ ፊታቸውን ወደ ኹጥባ እድራጊው ቢያዞሩ ይወደድላቸዋል። በሌላ ነገር መጠመድ የለባቸውም። እንደውም ብዙ ባልደረቦቻችን (ሻፊዒዮች) ውሃን ለጣዕሙ ብሎ መጠጣት ይጠላል ብለዋል። ለጥም ከሆነ ግን ኹጥባ ለሚያደርው ሰውም ሆነ ለአድማጮቹ መጠጣት ይፈቀድላቸዋል። ይህ የእኛ መዝሃብ ነው።” ኢብኑል-ሙንዚር እንዲህ ብለዋል፡- “ጧውስ፣ ሙጃሂድ እና ሻፊዒይ ውሃ መጠጣት ፈቅደዋል። ማሊክ፣ አል-አውዛዒይ እና አሕመድ ግን ከልክለዋል። አል-አውዛዒይ እንደውም ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ውሃ መጠጣት ጁሙዓን ያፈርሳል ብለዋል።” ኢብኑል-ሙንዚር ግን ውሃ መጠጣት የሚፈቅደውን ሃሳብ መርጠዋል። “ለሚከለክሉት ሰዎች የሚሆን መረጃ አላውቅም።” ይላሉ።” (አል-መጅሙዕ፤ ቅፅ 4 ገፅ 529)። ኢብኑል-ሙፍሊሕ አል-ሐንበሊይ እንዲህ ብለዋል፡- “በኹጥባ ጊዜ ውሃ መጠጣት እና መጫወት ኹጥባን ለሚሰማው ሰው ይጠላል። የማይሰማው ሰው ከሆነ ግን አይጠላም። ይህንን ኢማም አሕመድ በግልፅ አስፍረውታል። ነገርግን ጥሙ ከጠናበት መጠጣት ይፈቀዳል ተብሏል።” (አል-መብዲዕ ሸርሑል-ሙቅሪዕ፤ ቅፅ 2 ገፅ 395)።

  • ⓸👉በኹጥባ መሀል መተኛት ይህ ድርጊት አሳዛኝ ነው። ሰጋጆች በኹጥባ መሀል ሊተኙ አይገባም። መተኛት ኹጥባው ከተደነገገበት ዋና ዓላማ ጋር ይጋጫል። ኹጥባ የተደነገገው ሰዎች እንዲያዳምጡት ነው። ደግሞም የተኛው ሰው ውዱእ ሊፈርስ ይችላል። የተኛን ሰው በድርጊት መቀስቀስ ይቻላል። በንግግር መቀስቀስ ግን አይፈቀድም። የተኛን ሰው በድርጊት መቀስቀስ ከሚፈቀድባቸው ምክንያቶች መሀል ማሊክ “አል-ሙወጧእ” ላይ ከናፊዕ- ዐብዱላህ ቢን ዑመርን ዋቢ በማድረግ- እንደዘገቡት፡- “ኢብኑ ዑመር ሁለት ሰዎች ኢማሙ በጁሙዐ ቀን ኹጥባ እያደረገ እያለ ሲያወሩ ተመለከቷቸውና በጠጠር መቷቸው። ዝም በሉ ለማለት።” (አል-መውጧእ፤ ቅፅ 1 ገፅ 300) ። አል-ሐፊዝ ኢብኑ ዐብዱል-በር እንዲህ ይላሉ፡- “ዘገባው የዚህ መሰል ድርጊቶችን እንዴት መቃወም እንደሚገባ ይጠቁማል። ንግግር በማይፈቀድበት ቦታ ላይ በንግግር መቃወም የለበትም።” (አል-ኢስቲዝካር፤ ቅፅ 5 ገፅ 63።) ሼኽ ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ብለዋል፡- “የሚያወራን ሰው ከተመለከተ በንግግር አያስቆመውም። ምክንያቱም የአሏህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ እያለ ጓደኛህን ዝም በል ካልከው በእርግጥ አበላሸህ።” ነገርግን ሰውየውን በምልክት ማስቆም ይችላል። ይህ አሕመድ በግልፅ ያስቀመጡት ነው። እጁን አፉ ላይ ጭኖ ማመልከት ወይም በምልክት ማስረዳት እንጂ በንግግር መከልከል እንደሌለበት ከሚያምኑ ዑለሞች መሀል ዘይድ ቢን ሰውሐን፣ ዐብዱራሕማን ቢን አቢ ለይላ፣ ሰውሪይ፣ አውዛዒይ እና ኢብኑል-ሙንዚር ይገኙበታል። በምልክት ማስረዳትን ኢማም ጣዉስ ጠልተውታል። ነገርግን ለኛ የሚሆን ማስረጃ አለን። እርሱም ሰውየው የአሏህ መልእክተኛ ዘንድ ሰውየው መጥቶ “ቂያማ መች ነው?” ብሎ በጠየቃቸው ቀን የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባሉበት ሰዎች በምልክት ዝም እንዲል ማዘዛቸው ነው። በተጨማሪም ንግግር በሚያፈርሳት ሶላት ውስጥ እንኳን ምልክት ተፈቅዷል። ስለዚህ በይበልጥ በኹጥባ ወቅት የተፈቀደ ነው ማለት ነው።” (አል-ሙግኒ፤ ቅፅ 2 ገፅ 165)።

  • ⓷👉ሰላምታን መጀመርም ሆነ መመለስ፣ ያስነጠሰን ሰው ማስደሰት፣ በሙስበሐ ተስቢህ ማድረግ፣ ቁርዓን መቅራት፣ ማንኛውንም መፅሀፍ ወይም ጋዜጣ ማንበብ… ወዘተ። እነዚህ ሁሉ የጁመዓን ኹጥባ የሚያዳምጥ ሰው ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ ተግባራት ናቸው። ምክንያቱነም እነዚህ ተግባራት በኹጥባ ጊዜ ከታዘዝንበት በጥሞና ከማድመጥ ጋር ይጋጫሉ። በሐዲስ ውስጥም እንዲህ ተብሏል፡- إذا قلت لصاحبك يوم الجمعة أنصت والإمام يخطب فقد لغوت “ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ጓደኛህን ዝም በል ካልከው በእርግጥም አበላሸህ።” ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል። ኢብኑ ዐቢዲን እንዲህ ይላሉ፡- “በሶላት ውስጥ እርም የተደረጉ ነገሮች በሙሉ በኹጥባ ወቅትም ሐራም ናቸው። መብላት፣ መጠጣት፣ መናገር- ተስቢህም ቢሆን-፣ ሰላምታ መመለስ ወይም በበጎ ማዘዝ ሁሉም ሐራም ነው።” (ሐሺየቱ ኢብኑ ዐቢዲን፤ ቅፅ 4 ገፅ 196)።

  • ⓶👉በኹጥባ ወቅት በምንም ነገር መጫወጥ የተከለከለ ነው ከአቡሁረይራ በተገኘው ሐዲስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- ‏ ‏من مسَّ الحصا فقد لغا‏ ‌‏ “ጠጠርን የዳበሰ በርግጥም አበላሸ!” ሙስሊም ዘግበውታል። ኢማም ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “በኹጥባ ወቅት ጠጠርን መነካካትም ሆነ በሌላ ነገር መጫወትን ይህ ሐዲስ ይከለክላል። ቀልብንም ሆነ አካልን ወደ ኹጥባው ማዞር እንደሚገባ ያስረዳል።” (ሸርሑ ሶሒሕ ሙስሊም፤ ቅፅ 6 ገፅ 147)። አል-ዐደዊይ አል-ማሊኪይ እንዲህ ይላሉ፡- “በጥቅሉ በኹጥባ ወቅት ዝም የማለትን ግዴታነት የሚጋፋ ማንኛውንም ድርጊት መፈፀም ኹጥባውን በማይሰማ ሰው ላይም እንኳን ሐራም ነው። በመብላት በመጠጣት ወይም አንድን ነገር በማንቀሳቀስ ምክንያት ድምፅ መፍጠር- ለምሳሌ ወረቀት ማንኮሻኮሽ፣ በር መክፈት እና ሙስበሐ መቁጠር ወይም የመፅሀፍ ገጾችን ማንቀሳቀስ ሐራም ነው።” (ሐሺየቱል-ዐደዊያ፤ ቅፅ 3 ገፅ 165)።

  • ይህን በዚህ መልኩ ከተገነዘብን ሰጋጆች የጁመዓ ኹጥባን በጥሞና ማድመጥ ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ከኹጥባው ከሚያዘናጋ ምንም አይነት ድርጊትም መቆጠብ አለባቸው። መረጋጋት እና መስከን ግዴታቸው ነው። ኹጥባውን አድምጠው ከርሱ መጠቀምም አለባቸው። ሰጋጆች በኹጥባ ወቅት መተግበር የሌለባቸው ነገሮችን ከዚህ በማስከተል እንዘረዝራለን፡- ንግግር፡- ከአቡሁረይራ በተዘገበው ሐዲስ የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡- إذا قلت لصاحبك يوم الجمعة أنصت والإمام يخطب فقد لغوت “ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ እያለ ገዋደኛህን ዝም በል ካልክ በርግጥ አበላሸህ!” ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል። አብዛኞቹ የፊቅህ ልሂቃን በጁመዐ ኹጥባዎች መሀል መናገር ሐራም ነው ብለዋል። አል-ሐፊዝ ኢብኑ ዐብዲል-በር እንዲህ ይላሉ፡- “የተለያዩ ከተማዎች የፊቅህ ልሂቃን በጁመዐ ኹጥባ መሀል መናገር ሐራም መሆኑን ይስማማሉ።” (አል-ኢስቲዝካር፤ ቅፅ 5 ገፅ 43)። “አበላሸህ” የሚለው ቃል ትርጉም የሚያበላሽ ሥራ ሰራህ ማለት መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህም መሰረት አንዳንድ ዑለሞች “የጁመዓህ ቱሩፋትን አበላሸህ!” ማለት ነው ብለዋል። ሌሎች ደግሞ፡- “ምንዳህን አጣህ” ማለት ነው ብለዋል። ሌሎች ደግሞ “ጁመዓ ዙሁር ሆነብህ” ማለት ነው ብለዋል። ሌሎች ትርጓሜዎችም ከተለያዩ ዑለሞች ተገኝተዋል።” (ዑምደቱል-ቃሪ›፤ ቅፅ 6 ገፅ 239)። አል-ሐፊዝ ኢብኑ ረጀብ አል-ሐንበሊይ እንዲህ ብለዋል፡- “ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ሐዲስ ውስጥ በኹጥባ ወቅት የሚናገሩ ሰዎችን ዝም በሉ ማለት በራሱ የጁመዐውን ምንዳ ማበላሸት መሆኑን እየተናገሩ ነው። በመልካም ማዘዝና ከክፋት መከልክል ከመሆኑ ጋር ማለት ነው። ስለዚህ ኹጥባውን ከማድመጥ የሚያግድ ማንኛውም ንግግር ክልክል ነው ማለት ነው። ምንዳን እንደ ማበላሸትም ይቆጠራል።” (ፈትሑል-ባሪ፤ ቅፅ 6 ገፅ 228) ከአቡዘር እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል፡- “በጁመዐ ቀን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኹጥባ እያደረጉ ሳለ ወደ መስጂድ ገባሁ። ከዚያም ለኡበይ ኢብኑ ከዕብ ቀረብ ብዬ ተቀመጥኩኝ። የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ሰረቱል “በራኣህ” የምትሰኘዋን ምዕራፍ አነበቡ። ከዚያም “ይች ምዕራፍ መቼ ነው የወረደችው?” ብዬ ጠየኩት። ኡበይ ገላመጠኝ፤ አላነገረኝም። የአሏህ መልእክተኛ ሶላት ሰግደው ሲያገባድዱ ኡበይን “ስጠይቅህ አላነገርከኝም፤ ገላመጥከኝ!” አልኩት። ኡበይም “ካበላሸኸው ውጭ ከሶላትህ ምንም የለህም!” አለኝ። እኔም ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄድኩና “የአሏህ ነብይ ሆይ እርሶ ሱረቱ “በራኣን” ሲያነቡ እኔ ከኡበይ አጠገብ ነበርኩኝ።  ይች ሱራ መቼ ወረደች ብዬም ጠየኩት። ነገርግን ገላመጠኝ፤ አላናገረኝም። ከዚያም “ካበላሸኸው ውጭ ከሶላትህ ምንም የለህም!” አለኝ።” አልኳቸው። የአላህ መልእክተኛም “ኡበይ እውነት ተናግሯል!” አሉኝ።” ኢብኑ ኹዘይማ ዘግበውታል።

  • ጥያቄ:– በጁመዓ ኹጥባ ወቅት የሚፈቀዱና የማይፈቀዱ ነገሮች ምንድን ናቸው❓ መልስ:- የጁመዓ ኹጥባዎች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸው አያከራክርም። አሏህ እንዲህ ይላል፡- يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡” (አል-ጁምዓ 62፤9) ኢማም አል-ቁርጡቢይ ይህን አንቀፅ ሲተነትኑ “አሏህን ወደ ማስታወስ” የሚለው ሐረግ ላይ እንዲህ ብለዋል፡- “(አሏህን ማስታወስ) እዚህ ቦታ ሶላት ነው። ኹጥባ እና ምክሮች ማለት ነው የሚልም አለ። ይህንን ያሉት ሰዒድ ቢን ጁበይር ናቸው።” ኢብኑል-ዐረቢይ እንዲህ ብለዋል፡- “በማንኛውም መልኩ የጁመዓ ተግባራት በሙሉ ዋጂብ ናቸው ቀዳሚው ኹጥባ ነው። ከዑለሞቻችን ከዐብዱል-መሊክ ኢብኑ ማጂሹን በስተቀር ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተጉዘዋል። እርሳቸው ብቻ ሱና ነው ብለዋል። ግዴታ መሆኑን የሚያመላክተው መረጃ ወቅቱ ከገባ በኋላ መገበያየት ሐራም መሆኑን የተመረኮዘ ነው። ኹጥባ ሱና ቢሆን ኖሮ የተፈቀደን ነገር እርም አያድግም ነበር። “አሏህን ወደ ማስታወስ” የሚለው ሐረግ የሚያመላክተው ሶላትን ነው ብንል እንኳን ኹጥባው ከሶላቱ ጋር ይደመራል። አንድ ባሪያ በተግባሩ አሏህን ሊያወሳ ይችላል።” (ተፍሲር አል-ቁርጡቢይ፤ ቅፅ 18፤ ገፅ 10) ብዙ ዑለሞች ኹጥባን የጁሙዓ ሶላት ተቀባይነት እንዲኖረው መሟላት ከሚገባቸው መስፈርቶች መሀል መቁጠራቸው የጁሙዐን ኹጥባን አሳሳቢነት ያስረዳል። ሸይኽ ኢብኑ ቁዳማ አል-መቅዲሲይ እንዲህ ይላሉ፡- “ኹጥባ ማድረግ የጁሙዓ ሶላት መስፈርት ነው። ያለ ኹጥባ የጁመዐ ሶላት ውድቅ ነው። ይህ ዐጧእ፣ ቀታዳ፣ ሰውሪይ፣ ሻፊዒይ፣ ኢስሃቅ፣ አቡሰውር እና አስሐቡር-ራዕይ ያሉት ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሐሰን ውጭ እነርሱን የነቀፈ ሰው መኖሩን አናውቅም። ሐሰን ግን “ኢማሙ ኹጥባ ቢያደርግም ባያደርግም ጁመዓቸው ይሆንላቸዋል።” ብለዋል። ምክንያቱም የጁሙዐ ሶላት እንደዒድ ሶላት ናት። ስለዚህ ልክ  እንደ ዒዱል-አድሐ ሶላት ኹጥባ መኖሩ መስፈርት አይሆንም። ነገርግን “አሏህን ወደ ማስታወስ” የሚለው የአሏህ ንግግር እኛን ይደግፋል። እዚህ ቦታ ላይ “አሏህን ወደ ማስታወስ” የሚለው ኹጥባን ነው። በተጨማሪም የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወት ዘመናቸው የጁመዓን ኹጥባ ትተው አለማወቃቸው ይህንን ሃሳብ ያጠናክርልናል። እርሳቸው፡- ‌‏صلوا كما رأيتمونى أصلي‏ “እንደምሰግደው አይታችሁ ስገዱ።” ብለዋል። ከኢብኑ ዑመር እንደተዘገበውም “የጁሙዓ ሶላት ያጠረችው ለኹጥባው ተብሎ ነው።” ይህን ንግግር ሙስሊም ከዐዒሻ ዘግቦታል።” (አል-ሙግኒ፤ ቅፅ 2 ገፅ 224; አል-መጅሙዕ፤ ቅፅ 4 ገፅ 514; እና በዳኢዑስ-ሶናኢዕ ቅፅ 1 ገፅ 693)። የጁመዐ ኹጥባን አሳሳቢነት ከሚጠቁሙ መረጃዎች መሀል ተጠቃሽ የሚሆነው መላኢካዎች እርሱን ለማድመጥ መሰብሰባቸው ነው። ከአቡሁረይራ እንደተዘገበው፡- “የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ፡- من اغتسل يوم الجمعة غسل الجنابة ثم راح فكأنما قرَّبَ بدنة- أي ناقة – ومن راح في الساعة الثانية فكأنما قرَّبَ بقرة، ومن راح في الساعة الثالثة فكأنما قرَّبَ كبشاً أقرن، ومن راح في الساعة الرابعة فكأنما قرَّبَ دجاجة، ومن راح في الساعة الخامسة فكأنما قرَّبَ بيضةً، فإذا خرج الإمام حضرت الملائكة يستمعون الذكر “የጁሙዐ ቀን የጀናባ ትጥበት ታጥቦ ወደ መስጂድ የወጣ ሰው የግመል ሶደቃ እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ሰዓት ላይ የሔደ ደግሞ ልክ ከብት እንዳቀረበ ነው። በሦስተኛው ሰዓት ላይ የወጣ ቀንዳም ሙክት እንዳቀረበ ነው። በአራተኛው ሰዓት የወጣ ደግሞ ዶሮ እንዳቀረበ ነው። በአምስተኛው ሰዓት የወጣ እንቁላል እንዳቀረበ ነው። ኢማሙ ኹጥባ ለማድረግ ከወጣ መላኢካዎች ተግሳፁን ለማስማት ይሰበሰባሉ።” ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

  • በሰላሳ አመቴ ወሊድ የተባለ ወጣት የትዳር ጥያቄ አቀረበልኝ ። በጣም ውብና አማላይ የሚባል ወጣት ነበር ። ሁሉ ነገሩን ወድጄ አንድ ነውር ብቻ ነበር ያገኘሁበት ። ወሊድ ከኔ በፊት ሌላ ሰው አግብቶ ነበር ። በዚያም ትዳር የወለደው አንድ ልጅ አለው።ሚስቱ ህፃኑን በወለደችበት ሰዓት ነበር ያረፈችው። ከሚስቱ ያላለቀ ፍቅር ያለው ወሊድ በእናቱ ግፊት እኔን ለማግባት ወሰነ። እኔም ከጥቂት አመታት በኃላ ከመንደሩ ሰው የሚወረውርብኝን የ"ለምን አታገባም?" ጥያቄ ለመመለስ አገባሁት። በሰርጋችን ምሽት መጀመሪያ አደራ ያለኝ:-"አሏህ ላንቺ መልካም እንዲያረግልሽ ከሻሽ ለሁሳም መልካም ሁኚ።" ይህ ነበር አደራው ። ሁሳም ካለፈ ትዳሩ ያፈራው ልጁ ነው። ከተጋባን ከአንድ አመት በኃላ ጨረቃ የመሰለ ልጅን አላህ ሰጠኝ። ነገር ግን ልጄ  ከልብ ህመም ጋር ነበር አብሮ የተወለደው ። በዚህም የተነሳ ለባለቤቴ እሰጠው የነበረውን ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ለህመምተኛው ልጄ መስጠት ጀመርኩ ። ይህም በመካከላችን ክፍተትን ፈጥሮ እኔ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ ። ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ወሊድ በመኪና አደገ ደረሰበት። አደጋው ከባደ ስለነበር የመትረፍ አድል እንደሌለው ያወቀው ወሊድ በብዙ ነገራት አደራ አለኝ ። የመጨረሻው አደራ ግን "አሏህ መልካም እንዲሰራልሽ ከፈለግሽ ለሂሳም በጎ አድርጊ። እሱ አሁን አባቱንም ማጣቱ ነው።" የሚል ነበር። ይህን ካለ ብዙም ሳይቆይ ወሊድ ጥሎኝ ሄደ። ፍቅሩን በምላስ ብዙ ጊዜ ባይገልፅም እጅግ አዛኝ፣ምግባረሰናይና ርሁሩህ ነበር። ከዚህ ወዲህ  የባሌን አደራ ለመጠበቅ ነብሴን አሳልፌ ሰጠሁ። ቤተሰቦቼ ሁሳምን ለህፃናት ማሳደጊያ አንድሰጥ ቢወተውቱኝም አሻፈረኝ ብዬ እንደልጄ አድርጌ አሳደግኩት።ችግሩን፣ናፍቆቱን ሃሳቡን ሁሉ በጫንቃዬ ተሸክሜ አሳደግኩት። በሌላ በኩል የኔው ልጅም ከህመሙ ጋር እየተታገለ አስራ አምስት አመታትን ከቆየ ወዲያ እስከ ወዲያኛው አሸለበ።ከሁሳም ውጭ አጫዋችም ሆነ አፅናኝ የሌለኝ ብቸኛ ሆኜ ቀረሁ። ታዲያ ሁሳምም አድጎ ተመረቀልኝ። በተመረቀልኝም ቀን በሁሉም ፊት ዝቅ ብሎ እግሬን ስሞ ስጦታን አበረከተልኝ። በህይወቱ አንድም ቀን "ጀነቴ" ብሎኝ አንጂ ጠርቶኝ አያውቅም። የኔን መተኛት ሳያረጋግጥ ወደመተኛ ክፍሉም ገብቶ አይተኛም። ይህ ልጄ ትናንት የራሱን ሆስፒታል ገምብቶ አስመረቀ።በሁሉም ፊትም አንድ ቃል ገባ።በሳምንት ጁሙዓ እለት ሁሉም ሰው በነፃ ህክምና አንዲያገኝ እንደሚያደርግ ቃል ገባ።ይህም ለወንድሙ ሰደቃ እንዲሆን በመሻት እንደሆነም ገለፀ። ሳራህ አል-ዓቃሪ Umer Yasin Yusuf 🙏 @sineislam @sineislam

  • 🌻 ዒድ ሙባረክ 💐 እንኳን ለ1446ኛው ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሰን። 🌸 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 人  ★* 。 • ˚* ˚ 🌙 .  (_ _) * ዒድ * ★ . ┃口┃ *     mubark     * . ┃口┃★ *   ***.    .  *˛• . ┃口┃★   * •★ 。•˛˚˛* . ┃口┃ •˛˚˛*   人  •˛˚  *        . ┃口┃     .-:'''"''''"''.-.      . ┃口┃  (_(_(_()_)_)_)            ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃ . ┃.   ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃ .  三_三三三三三 🌷አላህ መልካም ሥራችንን ሁሉ ይቀበለን!  ጥፋታችንንም ይቅር ይበለን። የደስታ የሰላም እና የተባረከ ዒድ ይሁንልን!! 🌼 ዒድኩም ሙባረክ እንኳን አደረሳቹ🥰 @sineislam