tgindex
የአዲስ ኪዳን ካህናት

የአዲስ ኪዳን ካህናት

Статистика

" እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:6) ✔የዚህ ቻናል አላማ #የጸጋውን_ወንጌል ለአለሙ ሁሉ ማወጅ ነው ፡፡ ለአስተያየት: @samidaba @sofiblessed ✆✆ ☞ +251941982842

Последний пост
17 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 126
−2 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
179
21 постов
Вовлечённость
15,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 17 июн.149из tewoderosdemelash

    እነዚህን መጻሕፍት ስታዲየም የሚገኘው መሠረተ ክርስቶስ መጻሕፍት መደብር ማግኘት ይቻላል

  • 13 июн.1611из tewoderosdemelash

    እኛ እጅ ገብቷል፤ በቅርቡ እናንተም ጋር ይደርሳል

  • 11 июн.148из tewoderosdemelash

    без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 27 мая207из tewoderosdemelash

    без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 19 мая216из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 18 мая198из tewoderosdemelash

    እንዲህ ያለ ነገር የሚታየው አዝማሪ ዘንድ ነው፤ አዝማሪ አንዱን ባመሰገነበት ግጥምና ዜማ ሌላውን የሚያወድስ ለአንዱ የተቀኘውን ቅኔ ለሌላው የሚጠቀም እወደድ ባይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ለጌታ የቀረበ ዝማሬ መዘመር ለጌታ ብቻ የሚገባውን ውዳሴ ማጋራት ነው፡፡ ይህም ደግሞ ኀጢአት ነው፡፡ ስለዚህ ኀጢአት ላለመሥራት በኦርቶዶክሳውያን የቀረቡና ዝማሬ የሚል ስም የተሰጣቸውን ዜማቸው ከቤታችን በማራቅ እውነተኛ አምልኮ ያላቸውን ዝማሬዎች ወደመስማት ፊታችንን እንመልስ፡፡ https://t.me/tewoderosdemelash/1283

  • 18 мая177из tewoderosdemelash

    የኦርቶዶክስን መዝሙር መስማትና መዘመር ኀጢአት ነው! የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት መዝሙር የሚለውን ሲተረጕም፤ ‹‹ልዩ ልዩ ስልትና ቃና ባለው ድምፅ የሚዜም፣ በዜማ መሣሪያ የሚቀርብ መንፈሳዊ ማኅሌት›› መሆኑን ይነግረንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ሦስት ጥቅሶችን ለማስረጃነት ያቀርባል፤ የመጀመሪያው፤ ዘጸአት 15÷20-21 ላይ የሚገኘውና የሚከተለው ነው፤ ‹‹የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዘፈን በኋላዋ ወጡ። ማርያምም እየዘመረች መለሰችላቸው። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና #ለእግዚአብሔር #ዘምሩ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ››፡፡ ምንባቡ በግልጽ የሚያሳየው ዝማሬ የሚቀርበው ለእግዚአብሔር መሆኑን ነው፤ ይሄን ደግሞ በቀጣዩ ምንባብ እናጸናዋለን፡፡ ሁለተኛው፤ ኤፌሶን 5÷19 ላይ የተጻፈውና የሚከተለው ነው፤ ‹‹በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ #ለጌታ #በልባችሁ #ተቀኙና #ዘምሩ››፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መዝሙር፣ ዝማሬ እና መንፈሳዊ ቅኔ ሊቀርብ የሚገባው ለጌታ መሆኑን በግልጽ ጽፏል፡፡ በርግጥም ከአምላካችን ውጪ መዝሙር ዝማሬ እና መንፈሳዊ ቅኔ ሊቀርብለት የሚገባ አካል ማን አለ? ሦስተኛው፤ ቈላስያስ 3÷16 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈው ነው፤ ‹‹በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ #ለእግዚአብሔር #ዘምሩ››፡፡ ጳውሎስ አሁንም በድጋሚ ዝማሬና መንፈሳዊ ቅኔ ለአምላካችን ብቻ የሚገባ መሆኑን በመጻፍ ከእርሱ ውጪ ለማንም ሰው እንዳናጋራ እያሳሰበን ነው፡፡ ምናልባት አንድ ሰው መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 1 ላይ የተጻፈውን አንሥቶ ከእግዚአብሔር ውጪ ለአንድ ሰው የተዘመረ መዝሙር አለ ለማለት ይሞክር ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ምዕራፍ ላይ እየቀረበ ያለው በክፉዎች ምክር አለመሄድ፣ በኃጢአተኞች መንገድ አለመቆምና በዋዘኞችም ወንበር አለመቀመጥ ምን ዓይነት ሰው እንደሆነና ምን ምን እንደሚያገኝ የሚናገር ምንባብ እንጂ አንድን ሰው ለይቶ እያመሰገነ ያለ አይደለም፡፡ በክፉዎች ምክር ላልሄደው የቀረበ መዝሙር ነው ከተባለ መዝሙሩ እየቀረበ ያለው ለቀጣዩም አካል ነው ማለት ነው? ‹‹ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው። ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም። እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች››፡፡ ከምንባቡ መረዳት እንደሚቻለው ሁለት አካላት አሉ፤ አንደኛው ቀደም ሲል የቀረበውና ‹‹በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ›› ተብሎ የተገለጸው ነው፡፡ የአንድምታ መተርጕማን ለቊጥር 1 ካስቀመጡት ትርጓሜዎች ውስጥ ‹‹በረሲዓን ምክር ፀንቶ ያልኖረ ሰው ንዑድ ክቡር ነው›› የሚለው ይገኝበታል፡፡ ‹‹ረሲዓን›› ምንድን ነው? የሚለውን ደግሞ በሚከተለው መንገድ አስቀምጦታል፤ ‹‹ረሲዓን የሚላቸው እንጨት ጠርበው ደንጊያ አለዝበው የሚያመልኩ ናቸው›› (ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ መዝሙረ ዳዊት ንባቡና ትሯሜው በአንድምታ (2005) የምዘሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድን አንድምታ ትርጓሜ ይመልከቱ)፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ክፉ ተብሎ የተገለጸው ነው፡፡ ክፉዎች እንዲህ አይደሉም በሚል ቀደም ሲል ከተጠቀሰው የተለዩና በርግጥም ክፉዎች መሆናቸውን የሚጠቊም ነው፡፡ መጨረሻቸውም መጥፎ መሆኑን ለማሳየት ‹‹የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች›› በማለት ምንባቡ ሐሳቡን የሚዘጋ መሆኑንም ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ለሁለቱም የቀረበ መዝሙር ነው ማለት ነው? እንደሱ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይልቁንስ ምንባቡ የሚናገረው ‹‹የጻድቃንና የኃጥኣን ትርጓሜ›› መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው (የ2000 ዕትም ሰማንያ አሐዱ)፡፡ ሌላው እንደመከራከረያ የሚቀርበው ‹‹ሴቶችም፦ ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ እያሉ እየተቀባበሉ ይዘፍኑ ነበር›› የሚለው ምንባብ ነው (1ኛ ሳሙኤል 18÷7)፡፡ ሰዎቻችን ይሄን ይጠቅሱና ለዳዊት ተዘምሯል ይላሉ፡፡ በርግጥ ግን ሴቶቹ ለዳዊት የዘፈኑት ቅዱስ ነው ብለው ነው? ‹‹አዎ›› የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሰው ካለ ምንም እንኳ የዳዊት ግዳይ ቊጥር ከፍ ያለ ቢሆንም ለሳኦልም ተዘፍኗልና እግዚአብሔርን በመበደሉ ምክንያት የተቀጣውን፣ ዳዊትን ለመግደል ብዙ የለፋውን የመጀመሪያውን የእስራኤል ንጉሥ ‹‹ቅዱስ ሳኦል›› ማለት ይገባቸዋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ምንባብ ላይ የሆነው ከድል የተመለሰን ሰው በደስታና በሆታ መቀበል ነው፡፡ ይሄንም አንድ ቊጥር ብቻ ከፍ በማለት መረዳት ይቻላል፤ ‹‹እንዲህም ሆነ፤ #ዳዊት #ፍልስጥኤማዊውን #ገድሎ #በተመለሰ #ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው #ንጉሡን #ሳኦልን #ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ››፡፡ ሴቶቹ አታሞ ይዘው የወጡበት ምክንያት ዳዊት ቅዱስ ስለሆነና ለእርሱ መዘመር ስለሚገባ ሳይሆን ‹‹ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ›› በማለት ጉዳዩ የድል አድራጊነት (የጀግንነት) እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሐሳቡን የተሻለ ግልጽ ሲያደርገው ‹‹ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ›› ይለዋል፡፡ እንዲህ ያለው ልማድ በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ ያለ ልማድ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይሄ ብቸኛ ምንባብ አይደለም፡፡ በዚሁ መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ምንባብ እናገኛለን፤ ‹‹ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ። #የእስራኤልና #የይሁዳ #ሰዎች #ተነሥተው #እልል #አሉ›› (1ኛ ሳሙኤል 17÷51-52)፡፡ ከመጽሐፈ ሳሙኤል ወጣ ስንል የሚከተለውን ምንባብ እናገኛለን፤ ‹‹ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሀያ ከተሞችን በታላቅ አገዳደል መታቸው። የአሞንም ልጆች በእስራኤል ልጆች ፊት ተዋረዱ። ዮፍታሄም ወደ ቤቱ ወደ ምጽጳ መጣ፥ እነሆም #ልጁ #ከበሮ #ይዛ #እየዘፈነች #ልትገናኘው #ወጣች፤ ለእርሱም አንዲት ብቻ ነበረች፤ ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም›› (መጽሐፈ መሳፍንት 11÷33-34)፡፡ የዮፍታሄ ብቸኛ ልጅ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች የወጣችው በድል በመመለሱ በደስታና በሆታ ልትቀበለው ነው፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ‹‹ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ›› የሚለውም ለድል አድራጊ የቀረበ ዘፈን እንጂ ለቅዱሳን ዝማሬ ይገባል በሚል ለመከራከሪያ የሚቀርብ ምንባብ አይደለም፡፡ ዝማሬ ለእግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት። አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ›› (መዝሙረ ዳዊት 32÷2-3) በማለት ልንዘምር የሚገባው ለእግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያስተምራል፡፡ ከእርሱ ውጪ ለየትኛው ፍጡር ዝማሬ እንድናቀርብ የሚያስተምር ምንባብ የለም፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ዘማርያን እንደ ዐሥራት ከዐሥር አንድ ለጌታ በመስጠት ዘጠኙን የተለያዩ ፍጡራንን ከማመስግን ጀምረው አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የዘመሯቸው መዝሙሮች በብዛት አሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ለጌታ የተዘመሩትን በቤታችን እየመረጥን እንሰማ ነበር፡፡ ነገር ግን ዘማሪያኑ ማን ናቸው? የሚለው ሲነሣ ጌታን ባመሰገኑበት ፍጡርን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ በአንዱ ግጥምና ዜማ ፍጡርና ፈጣሪን የሚያመሰገኑ ናቸው፡፡

  • 17 мая131из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 15 мая171из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 10 мая160из tewoderosdemelash

    በቀሌን ከእርሱ አልተውም https://t.me/tewoderosdemelash/1279

  • 7 мая202из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 5 мая217из tewoderosdemelash

    ድርሳነ ኢያቄም ወሐና # 5 ሔዋን ትሰግድልሻለች ስግደት አምልኮ ከምንፈፅምባቸው ውስጥ አንዱ ነው። ሰይጣንም ይህን ስለሚያውቅ ከሰዎች ለመውሰድ የሚቋምጠው ስግደትን ነው። ለሰይጣንም ሆነ ለእግዚአብሔር ስግደትን በጣም ትኩረት የተደረገበት ነገር መሆኑን የምናስተውለው እግዚአብሔር በስግደት ጉዳይ ላይ ድርድር የሌለው ሰይጣን ደግሞ በተለያዩ መልኮችና ሁኔታዎች ስግደትን ለራሱ ለማድረግ የሚፈልግ መሆኑን ሰናይ ነው። ቀደም ሲል እግዚአብሔርን ሲያመልክ የነበረው ሰሎሞን እግዚአብሔር ያዘነበት ልቡ ወደ ጣኦት በማዘንበሉ ነው። ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ሰሎሞን <ልቡን አዘነበሉት... የሲዶናውያንን አምላክ... ተከተለ... መስገጃ ሠራ> እንጂ አመለከ የሚል የለም። ምነው ታዲያ እግዚአብሔር አዘነበት(1ነገ 11፥1-10)? ከዚህም ሌላ ምናሴ፣ ሮብዓም፣ ኤዶምያስ... የመስገጃ ዐፀድ መስራታቸው ተጽፏል። የመስገጃ አፀዱ የአምልኮት መፈጸሚያ በመሆኑ እግዚአብሔር በጣም አዝኗል (2ነገ 21፥3። 2ዜና 11፥15፤ 21፥11)። እግዚአብሔር ደስ የተሰኘባቸው ነገሥታት ሲንግሡ ደግሞ የመስገጃ አፀዶችን መስበርና ማፍረስ አንዱ ሥራቸው ነበር (2ነገ 18፥4፤ 23፥8: 15: 19፤ 2ዜና 14፥3)። ሰይጣን ክርስቶስን ሊፈተን በመጣ ጊዜ ካቀረባቸው ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ <ብትሰግድልኝ> የሚል ነበር። ሰይጣን <ብታመልከኝ> አላለም። የሰይጣን ጥያቄ አንዲት ስግደት ነበር። ኢየሱስም <ለጌታ ለአምላክህ ስገድ ተብሎ ተጽፏል> የሚል ስግደት ለድርድር እንደማይቀርብ የሚያሳይ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠው። ምንም እንኳን በሰይጣን ንግግር ውስጥ <ስገድልኝ> እንጂ <አምልከኝ> የሚል ባይኖርም ክርስቶስ ሲመልስለት <እርሱንም ብቻ አምልክ> በማለት ስግደት እና አምልኮ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸውን አሳይቷል። ስግደት ማለት ለሰገድክለት አካል አንተ የበታች እሱ የበላይ አንተ ተገዢ እርሱ ገዢ አንተ አምላኪ እሱ አምላክ መሆናችሁን በተግባር የምትገልፅበት መንገድ ነው። የድርሳነ ኢያቄም ወሐና አዘጋጆች እግዚአብሔር ስግደት ላይ ያለውን ጠንካራ አቋም እያወቁ ሊሰገድለትና ሊመለክ የሚገባው ሁሉን ቻዩ አምላክ ብቻ መሆኑ እየገባቸው እርሱን ለማስቆጣት በሚመስል ሁኔታ ፍጡር ለፍጡር እንዲሰግድ ሲመክሩና ሲያበረታቱ ይታያሉ። አስገራሚው ነገር ከዚህ ቀደም ለማርያም (ክርስቶስን ስለወለደች) እና ከክርስቶስ መምጣት በኋላ ለተነሱ ቅዱሳን ነበር ስግደት ይሰገዳል የሚባለው ሲሰገድም የሚታየው። አሁን ግን ለሐና (ማርያምን ስለወለደች) ስግደት ይገባታል ይባል ተጀምሯል። ምነው የሐናስ እናት ሐናን ስለ ወለደች ለምን አይሰገድላትም? ሌላው አስገራሚው ነገር ለሐና የምትሰግድላት ሔዋን መሆኗ ነው። ምናልባት እንዲህ የተባለው ከሔዋን ጀምሮ እስከ ጌታ መምጣት ድረስ ያሉ የሰው ዘሮች በሙሉ ለሐና ይሰግዳሉ ለማለት ይሆንን? ሐሳቡ ይህ ነው:- <እርሷም ያንቺን መምጣት ትጠባበቃለች። በልጅሽ ልጅ /በክርስቶስ/ ትንሳኤ ስታገኝ ትሰግድልሻለች> (ዘሰኑይ ቁ 23 ገጽ 19)። ይህ ሁሉ ግን እግዚአብሔርን ለማስቆጣት ሰይጣን የዘረጋው ወጥመድ እንጂ ከእግዚአብሔር ሌላ ስግደት የሚገባው አንዳች እንኳ ፍጡር እንደሌለ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ሊሆን ይገባል። ምክንያቱም ራሱ እግዚአብሔር አምላካችን < በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ> (ዘፀ 20፥4-5) ብሏል። በርግጥም ከእርሱ ውጪ ሊሰገድለት የሚገባ ማን ይኖር ይሆን? https://t.me/tewoderosdemelash/1276

  • 30 апр.148из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 29 апр.184из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 29 апр.126из tewoderosdemelash

    без подписи

  • 28 апр.130из tewoderosdemelash

    без подписи