ቴዲ tadi
Статистика- Последний пост
- 16 июн. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 63
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሩስያን ከቡድን 7 አባልነት ማስወጣት ስህተት ነበር - ዶናልድ ትራምፕ **** የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩስያን ከቡድን 7 አባልነት ማስወጣት ስህተት እንደነበረ የገለጹ ሲሆን ምን አልባት ሩስያ በቡድኑ ውስጥ ብትሆን ኑሮ የዩክሬን እና የሩስያን ጦርነት በጊዜ ለማስቆም ይቻል እንደነበር ጠቁመዋል። በካናዳ የተሰባሰቡት የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች ዋና ትኩረታቸው አለም ላይ ባሉ ውጥረቶች ላይ ሲሆን፤ በተለይም በዩክሬን እና በሩስያ የሚደረገው ጦርነት ከአጀንዳዎቹ መካከል ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምንም እንኳን ይህንን ሀሳብ ቢያጋሩም የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች በጥብቅ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል ነው የተባለው። ሩስያ ከቀድሞው ቡድን 8 ማዕቀፍ በፈረንጆቹ 2014 እንድትወጣ የተደረገች ሲሆን ምክንያቱም የዩክሬን አካል የነበረችውን ክሬሚያን በህገ ወጥ መንገድ በመቆጣጠሯ ነበር። ይህም የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ እንደሆነና ለዩክሬን ሉዓላዊነት ስጋት ነው የሚሉ ክሶችም እንደቀረቡበት ይገለፃል።
без подписи
без подписи
ኢራንን እወዳታለዉ ኢራን ለምትወስደዉ ለእያንዳንዱ እርምጃ ድጋፌን እሰጣለዉ💀 ኪምጆንግ💀
без подписи
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የስለላ ድርጅት (IRGC) ሃላፊ የሆኑት መሀመድ ካዚሚ እና ምክትላቸው ሀሰን ሞሃቅ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን ድርጅቱ አረጋግጧል።
без подписи
ካለፈው ከአርብ ጀምሮ ለሦስተኛ ቀን የቀጠለው የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት እየተባባሰ ነው። ዛሬ በሁለቱም ወገኖች ጥቃቶች እየተፈጸሙ ናቸው። በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦ - እስራኤል በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን መምታቷን ቀጥላለች፤ የእስራኤል የመከላከያ ኃይል እንዳለው በዛሬው ዕለት 250 ዒላማዎችን መትቷል። - የኢራን የመገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አስከ ቅዳሜ ዕኩለ ቀን ድረስ 128 ሰዎች ሲገደሉ 900 የሚደርሱት ደግሞ ተጎድተዋል። ከሟቾች መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል። በኢራን የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦ ° ኢራን ሌሊት ላይ በእስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃቶችን የፈጸመች ሲሆን፣ በዚህም 6 ሰዎች ከቴል አቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ባት ያም በምትባል ቦታ እንዲሁም 4ቱ በሰሜናዊቷ ታምራ ከተማ አጠቃላይ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የእስራኤል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ° ዛሬ እሁድ ከሰዓት በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል በማስወንጨፍ ጥቃት ሰንዝራለች። የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንዳለው አብዛኞቹ ሚሳዔሎች የከሸፉ ሲሆን፣ ጉዳት ስለመድረሱ የወጣ ዘገባ የለም። በሌላ በኩል ፤ እስራኤል እየወሰድች ባለው ጥቃት በኢራን በዋና ከተማ ቴህራን የሚገኘው የሳህራን ነዳጅ ማከማቻ መመታቱን የኢራን ነዳጅ ሚኒስቴር ገልጿል። የነዳጅ ማቀነባበሪያው በጥቃቱ የእሳት አደጋ ቢደርስበትም አሁን በስራ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
без подписи
без подписи
без подписи
❗️ሐይፋ የተሰኘው ወደብ ትልቁ የእስራኤል ወደብ ሲሆን በዚህ አከባቢ ከፍተኛ የፔትሮል ማከማቻና በርካታ የሰራዊቱ መሳሪያ ማምረቻ ኢንዲስትሪዎች የሚገኙበት ነው።ከምሽቱ ጥቃት በኃላ በስፍራው ከፍተኛ ጭስ ታይቷል።
без подписи
❗️እስራኤል በምስራቅ ኢራን በማሽሃድ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እስራኤልን ለማጥቃት ነዳጅ ሲሞላ የነበረ የጦር አውሮፕላን ላይ ጥቃት አድርሳለች። በዚህ የተነሳ በአካባቢው ከፍተኛ ጭስ ታይቷል።
без подписи
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ? ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ የምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ወትሮም በጠላትነት በዓይነ ቁራኛ የሚጠባበቁት ሲበረታም በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ የሚፋለሙት እስራኤል እና ኢራን ካለፈው ሐሙስ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም. ሌሊት አንስቶ እስራኤል በከፈተችው ጥቃት ወደ ለየለት ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው ዓለም ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ እና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በፈጸመችው ከባድ ጥቃት በርካታ የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ሲገደሉ፣የኒውክሌር ተቋማት እና ወታደራዊ መሠረተልማቶቿ ላይ ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ ኢራን በበኩሏ የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ በርካታ የእስራኤል ከተሞችን በሚሳዔሎች እና በድሮኖች አጥቅታለች። ከዚያ ዕለት በኋላ የእስራኤል ጥቃት የቀጠለ ሲሆን፣ የኢራንም የአጸፋ ምላሽ እንደቀጠለ ነው። እስራኤል ኢራን አውዳሚውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመታጠቅ ከጫፍ ደርሳለች ይህም በኅልውናዬ ላይ የተጋረጠ ስጋት ነው ስትል የምትከስ ሲሆን፣ ኢራንም በበኩሏ እስራኤል ሉአላዊነቷን እየተገፋች በመሆኗ እራሷን ከመከላከል ወደ ኋላ እንደማትል አሳውቃለች። በዚህም ምክንያት የሁለቱ አገራት ድንበር ዘለል መጠቃቃት ወደ አውዳሚው የኒውክሌር ጦርነት እንዳያመራ ዓለም ስጋት ውስጥ ገብቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት እና በርካታ አገራት እስራኤል እና ኢራን ወደተባባሰ ሁኔታ ከመግባት እንዲቆጠቡ ጥሪ ሲያርቡ፤ አንዳንድ አገራት ከእስራኤል መቆማቸውን ሲያመለክቱ ሌሎች ደግሞ የእስራኤልን ጥቃት አውግዘዋል። እስራኤል እና ኢራን ለዘመናት የዘለቀ ባላንጦች ናቸው። በሁለቱ አገራት መካከል የቆየው ከፍተኛ የጠላትነት ስሜት በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እንዲርቅ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል። ቴህራን ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ የምትሻትን እስራኤልን “ትንሿ ሰይጣን” ስትላት፣ አሜሪካንን ደግሞ “ትልቋ ሰይጣን” በማለት ለሁለቱም ያላትን ተመሳሳይ አመለካከት ስታንጸባርቅ ቆይታለች። ኢራን እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ከመፈጸም ይልቅ በገንዘብ እና በትጥቅ የምትደግፋቸውን ቡድኖች በመጠቀም በእጅ አዙር ጥቃት እንደምታስፈጽም ይነገራል።
без подписи
"ኢራን ከባድ ዋጋ ትከፍላለች "- ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለምታጠፋው ግድያ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለች ብለዋል። ቤንያሚን ኔታንያሁ በባት ያም ከተማ የኢራን ሚሳኤል የተመታውን የመኖሪያ አካባቢ በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት ፣ ኢራን ሆን ብላ በሰላማዊ ሰዎች፣ ህጻናት እና ሴቶች ላይ የፈፀመችው ግድያ ለህልውናችን ትልቅ ስጋት" መሆኑን ያሳያል። “የተገደሉትን ሀዘኔን እገልጻለሁ፣ ሀሳባችን ከሟች ቤተሰቦች ጋር ነው” ሲል ህዝቡ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድ አሳስቧል። በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር ኢራናውያን የሀገሪቱን የጦር መሳሪያ ማከማቻ ለቀው እንዲወጡ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ የቴህራን ነዋሪዎች አንቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል ። ለመገናኛ ብዙሃን አንድ ነዋሪ በሰጠው አስተያየት ፣ "አዎ፣ ማስጠንቀቂያውን ሰምቻለሁ ። ወታደራዊ ሰፈር መሆኑን ወይም አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?" ሲል ተናግሯል ። የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ በተመለከተ ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፤ የቴህራን ነዋሪዎች የእስራኤል ማስጠንቀቂያ የበለጠ ያሳስባቸዋል። ቴህራንን ለቅቄ መሄድ አልችልም።ይህን ከተማ ለቅቄ መሄድ አልችልም እዚህ ሩቅ ለመጓዝ አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦች ትቼ መሄድ አልችልም። ምን ማድረግ እችላለሁ፣ እዚያ ተቀምጬ እጠብቃለሁ ብሏል ። የኢራን ባለስልጣናት መላ አገሪቱ በወታደራዊ ስጋት ውስጥ አለመሆኗን እና ፤ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ አልተሰጣቸውም፣ ንግድ እና ህዝባዊ እንቅስቃሴ አልተገደበም ብለዋል ።
без подписи
без подписи