tgindex
KAWGMS

Kegn. Andarge W/Giorgis Memorial School Official Telegram Channel

Последний пост
28 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
2 398
+1 за сутки
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 828
20 постов
Вовлечённость
159,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
975
1/48двое суток
1 117
1/72трое суток
1 205

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 28 июл.1 1001

    መጠይቁን ለመሙላት የሚያገለግል መመሪያ

  • KAWGMS pinned «📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 ለወላጆች/አሳዳጊዎች እና ተማሪዎች በሙሉ፤ ት/ቤቱ የመማር-ማስተማር ሂደቱን፣ የአገልግሎት አሰጣጡን እና አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ላይ ያለውን ጠንካራ ጎን ይበልጥ ለማጠናከር እና ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚያስችል የአስተያየት መጠይቅ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት ሊንኮች አማካይነት አስተያየት እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ 1) ለወላጆች (@kawgmparentBot)…»

  • 28 июл.1 2246

    📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌 ለወላጆች/አሳዳጊዎች እና ተማሪዎች በሙሉ፤ ት/ቤቱ የመማር-ማስተማር ሂደቱን፣ የአገልግሎት አሰጣጡን እና አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ላይ ያለውን ጠንካራ ጎን ይበልጥ ለማጠናከር እና ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚያስችል የአስተያየት መጠይቅ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት ሊንኮች አማካይነት አስተያየት እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ 1) ለወላጆች (@kawgmparentBot) 2) ለተማሪዎች (@kawgmstudentBot) 3) ማንኛውንም አስተያየት ለመስጠት (@kawgmcommentBot) ማስታወሻ፦ ሊንኩን ከመረጡ በኃላ መጠይቁን ለመጀመር Start የሚለውን ይጫኑ። ይህን መጠይቅ ለመሙላት ከ 5-10 ደቂቃ ያህል ብቻ የሚወስድ ሲሆን፣ ስም መጻፍ አያስፈልግም። ለትብብራችሁ እና ለምትሰጡን አስተያየት አስቀድመን ከልብ እናመሰግናለን! 📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

  • 29 июн.2 7213из wwwAddisAbabaeducationbureau

    የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ ሰኔ 23 ይጀምራል። (ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም )የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። ለፈተናው በድምሩ 563,501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306,456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,045 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው። አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል። ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (Admission Card)፣ የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም። ፈተናው በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ፣ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባር እና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

  • 29 июн.2 103из wwwAddisAbabaeducationbureau

    አያይዘውም የዘንድሮው ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላል ብለው ለተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ ለትምህርት ቤቶችና መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል:: ተማሪዎች ውጤታችሁን የማስፈንጠሪያዉን በመጫን መመልከት ትችላላችሁ https://aa.ministry.et/#/result ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 29 июн.2 080из wwwAddisAbabaeducationbureau

    በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዘገቡ፡፡ (ሰኔ 22/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ውጤቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝና ከዚህ አኳያ ባለፉት አመታት በከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የታየውን ውጤት በመመልከት ዘንድሮ በ2018 የትምህርት ዘመን የተመዘገበዉን የላቀ ውጤት በማነጻጸር የትምህርት ማህበረሰቡ በትምህርት ልማት ስራዉ ላይ የተከናወኑ ተግባራት ያስመዘገቡትን ውጤት እንዲያውቅና ለቀጣይ ጉልበት በመሆንና የፉክክር መንፈስን በመፍጠር ሀገር የሚገነባ ትውልድ የመፍጠሩ ስራ ግቡን እንዲመታ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል:: የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ አንዱ አመላካች የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ውጤት መሆኑን የገለፁት ዶክተር ዘላለም 95.85% ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት በማምጣት ማለፋቸውን ተናግረው ለውጤቱ መመዝገብ የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ስራዉ ልዩ ትኩረት መስጠቱ ፣ የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉ ፣ የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተደንፎ በትኩረት መሰራት መቻሉ ፣ የመማሪያና የማስተማሪያ ግብዓቶች መቅረባቸው እንዲሁም ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ተጠቃሽ መሆናቸውን አብራርተዋል:: አያይዘውም የዘንድሮው ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት

  • 16 июн.2 82034

    ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ጉዳዩ፤ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን መሀከል የሚዘዋወር አደገኛ/የተሳሳተ/ ሀሳብ ስለቀረበላቸው፣ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ስለመታደግ ይሆናል፤   በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ በኦንላይን ተፈታኝ ተማሪዎች ዘንድ እየተሰራጨ ያለውን፣ ‹‹በኦንላይን (CBT) የፈተና ኮምፒዩተር ላይ የአንድን ተማሪ መልስ ሴቭ አድርጎ፣ በሌላ ተማሪ አካውንት ገብቶ መፈተን ይቻላል›› የሚለው ወሬ ለከፍተኛ አደጋ እራስን የሚያጋልጥ ነው። ይህ ድርጊት በኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ አንቀፅ 11 መሠረት በሕግ የሚያስቀጣ፣ እንዲሁም የፈተና ውጤትን ሙሉ በሙሉ የሚያሰርዝ ከባድ ጥፋት ነው።   ዘመናዊው የኮምፒዩተር ፈተና ማስፈተኛ አፕሊኬሽን (CBT) ማጭበርበሮችን በቀላሉ የሚከታተልባቸው 4 ዋና ዋና የቴክኖሎጂ መንገዶች፦   1)  ዲጂታል አሻራ (Digital Footprint)፦ ሲስተሙ የተፈተነበትን ኮምፒዩተር ልዩ መለያ (MAC Address) እና የራውተሩን IP አድራሻ ይመዘግባል። ሁለት የተለያዩ አካውንቶች በአንድ ኮምፒዩተር ላይ ከተጠቀሙ በቀላሉ ይለያል። 2)  የጊዜ ስታምፕ እና የሥራ እንቅስቃሴ ሎግ፦ ፈተናው የተጀመረበትን፣ የተጠናቀቀበትንና የተላከበትን ሰዓት በትክክል ይመዘግባል። ተማሪዎች ባልተለመደ ፍጥነት ወይም ተመሳሳይ የጊዜ ቅደም ተከተል (Pattern) ሲያጠናቅቁ ሲስተሙ ጥቆማ ይሰጣል። 3)  ባዮሜትሪክስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፦ የኮምፒዩተሩ ዌብካሜራ የፊት ገጽታን በማንበብ ተፈታኙ በትክክል የተመዘገበው ተማሪ መሆኑን እና በፈተናው ወቅት ከስክሪኑ ፊት መኖሩን በAI ረዳትነት ያረጋግጣል። 4)  የመልስ አመላለስ ትንተና፦ ኩረጃን የሚከላከሉ አልጎሪዝሞች የመልሶችን መመሳሰል እና ያልተለመዱ የምላሽ ጊዜዎችን በመለየት የኩረጃ ምልክት (Flag) ያሳያሉ።   ይህ ዓይነቱ ማጭበርበር በወንጀል የሚያስጠይቅ፣ ውጤትን የሚያሰርዝ እና በተማሪዎች ስነ-ልቦና ላይ አሉታዊ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ፣ ተማሪዎች በራሳቸው ጥረት ብቻ አጥንተው እንዲፈተኑ ትምህርት ቤቱ አጥብቆ ያሳስባል።   ወላጆችም ልጆቻቸው በራሳቸው ተማምነው እንዲሰሩ እና እንዲያልፉ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ እንድሰጡ ጥሪ እናቀርባለን።   ትምህርት ቤቱ፣

  • 16 апр.4 39021

    የስብሰባ ጥሪ ስለመሠረዝ ውድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች የ2018 ዓም አገር አቀፍ ፈተና (በተለምዶ ማትሪክ) ግንቦት 3 ቀን ይጀምራል የተባለው ወደ ሰኔ ወር መዛወሩ ትናንት ይፋ ተደርጓል። ት/ቤታችንም የፈተና ጣቢያ አንዲሆን የተወሰነው  ቀርቷል። በመሆኑም ተማሪዎቻችን ፈተናውን የሚፈተኑት በአቅራቢያችን በሚገኝ ሱመያ ት/ቤት መሆኑም ተረጋግጧል። ነገር ግን ት/ቤታችን 58 ኮምፒዩተሮች ማቅረብ እንዳለበት ታዟል። ስለዚህ ወላጆች ልጆቻችሁ በለመዷቸው/የራሳቸው/ ላፕቶፖች ቢፈተኑ ተጠቃሚ ይሆናሉ። መብራት እንኳን ቢቋረጥ በላፕቶፕ ከተፈተኑ ያለእንከን ፈተናውን መጨረስ ይችላሉ። በዴስክቶፕ ከተፈተኑ ግን ጀነሬተር እስኪነሳ እንዲሁም ኮምፒዩተሮቹ እስኪጀምሩ ድረስ የሚባክነው ጊዜ ተፈታኞቹ ላይ የሚያስከትለው ሳይኮሎጂካል ጫና ስለሚኖር ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትላል። ስለዚህ ወላጆች በራሳቸው ላፕቶፕ እንዲፈተኑ ተባበሯቸውም አበረታቷቸውም።            በተረፈ  ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ  8 ቀን ከቀኑ በ 11:00 ሰዓት ት/ቤቱ የጠራው ስብሰባ መሠረዙን እናሳውቃለን።                                          ት/ቤቱ

  • 14 апр.4 53045

    የስብሰባ ጥሪ ውድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች የ2018 ዓም አገር አቀፍ ፈተና (በተለምዶ ማትሪክ) ግንቦት 3 ቀን እንደሚጀምር ታውቋል። ት/ቤታችንም የፈተና ጣቢያ መሆኑ ተነግሮናል። በመሆኑም የቀረው ጊዜ በጣም አጭር ስለሆነ በዚህ ፈተና እና ዝግጅት ዙሪያ ተቀራርቦ መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ሐሙስ ሚያዝያ  8 ቀን ከቀኑ በ 11:00 ሰዓት ት/ቤቱ ቤተ-መፃሕፍት እንድትገኙ በአክብሮት ጠርተናችኋል። አደራ ተገኙ፣ ጊዜ የለም !!                                          ት/ቤቱ

  • 2 апр.4 6707из wwwAddisAbabaeducationbureau

    12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸው የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ ሆኑ። (መጋቢት 24/2018 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሠረት ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዝኛ ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው። ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል። የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት ላይ ያተኩራል። ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

  • 30 мар.5 9906

    ለ ቀአወጊመ ተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች ሠላም ለሁላችሁም፤ ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ ከያዝነው መጋቢት ወር ጀምሮ በዘመቻ በሰፊው በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። በቀኛ አንዳርጌ ወ/ጊዮርጊስ ት/ቤት በኩልም የማሰባሰብ ሥራ ለመጀመር በወ/ሮ ሙሉሰው ሙንዬ እና አቶ መስፍን ኃይሉ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000753353139 ለዚሁ ዓላማ አካውንት የተከፈተ እና በራሪ ወረቀቶች የተላኩላችሁ መሆኑ ይታወሳል፤  ሆኖም ሁኔታዎች ተጣርተው ት/ቤቱ በይፋ እስኪያሳውቃችሁ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም መጠን ያለው ገንዘብ በዚህ ሂሳብ ቁጥር እንዳታስገቡ ት/ቤቱ ያሳስባል።                                              ት/ቤቱ

  • без подписи

  • 9 янв.7 2908

    የስብሰባ ጥሪ ስለመሰረዝ ውድ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች፣ የአንደኛ ሴሜስተር ትምህርትን አስመልክቶ በመማር ማስተማር ሂደት፣ በተማሪዎች የፈተና ውጤት፣ በዲሲፕሊን ግድፈት እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ት/ቤታችን ከወላጆች ጋር ተገናኝቶ ለመመካከር ለእሁድ ጥር 3 ቀን 2018 ዓም በ 3:00 ሰዓት በትቤቱ አዳራሽ ስብሰባ መጠራቱ ይታወሳል፣ ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ከጥር 4 እስከ 6  የማትሪክ ሞዴል ፈተና እንዲፈተኑ በአ.አ ት/ ቢሮ ታህሳስ 30 ቀን ስለታዘዘ ቅዳሜና እሁድ ለፈተና ዝግጅት የሚውሉ ቀናት በመሆናቸው ምክንያት እሁድ ጥር 3 ቀን ተጠርቶ የነበረው ስብሰባ መሰረዙን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።                                            ት/ቤቱ

  • 2 янв.7 0619

    የስብሰባ ጥሪ ውድ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች፣ የዘንድሮ አንደኛ ሴሜስተር ትምህርትን አስመልክቶ በመማር ማስተማር ሂደት፣ በተማሪዎች የፈተና ውጤት፣ በዲሲፕሊን ግድፈት እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ት/ቤታችን ከወላጆች ጋር ተገናኝቶ መመካከር አስፈላጊ እና ተጠባቂ በመሆኑ እሁድ ጥር 3 ቀን 2018 ዓም በ 3:00 ሰዓት በትቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርታችኋል።                                            ት/ቤቱ

  • 19 дек.7 8535

    ውድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች፣ መንግስት የ2018 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና (ማትሪክ) ተፈታኝ ተማሪዎች የፋይዳ ቁጥር የግድ ሊኖራቸው ይገባል ባለው መሠረት የፋይዳ ቁጥራቸው (National ID FIN number) ለሰኞ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓም ተማሪዎቹ ይዘው እንዲመጡ አስታውሱልን። አደራ! አደራ! አደራ! ቀአወጊመ   ት/ቤት

  • 2 дек.8 61018

    ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች፣ ሰኞ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓም በአገር አቀፍ ደረጃ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታስቦ ይውላል። መንግስት የዕለቱን አከባበር አስመልክቶ መመርያ ያወጣ ሲሆን በዚህ ቀን ተማሪዎች ጠዋት ሲማሩ ውለው ከምሳ በኋላ በጥያቄ እና መልስ ውድድር ሲያሳልፉ መምህራንም በፓናል ውይይት ቀኑን አስበው ይውላሉ። ከዚህ ውጪ ሌላ ዝግጅት ወይም የዴይ አከባበር ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን መመሪያው ይገልፃል። ይህ በእንዲህ እያለ በቀአወጊመ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አነሳሽነት ሌሎቹንም ተማሪዎች በአካተተ መልክ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በሌላ ቀን ከልቸር ዴይ በሚል ስያሜ ለማክበር ልብስ መግዣ ወይም በትምህርት ቀን ከት/ቤት ቀርተው ሌላ ቦታ ለማከበር ወይም ቀኑን ለማክበር ባሰቡት ቀን መኪና ለመከራየት ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል። በመሆኑም  ተማሪዎች ት/ቤት ግቢ ውስጥ እናከብራለን ሲሉ እኛ ደግሞ አይቻልም ብለን ስንከለክል አለመግባባት እንዳይፈጠር ወላጆች ከወዲሁ አንድም የተከለከለ ድርጊት መሆኑን እንድታስረዱልን እና ከት/ቤት በማንኛውም ቀን እንዳይቀሩ ተከታትላችሁ እንድትልኩ፣ ሁለትም ገንዘብ ባለመስጠት እንድትተባበሩን ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።                                                 ት/ቤቱ