መዓዛ ሠናይ
Статистика☞ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እንወቅ ☞እንረዳ ☞እንማማር ♥♥♥♥♥♥ ለበለጠ መረጃ @Tadi16 ላይ ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን፡፡
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 146
- 1/48двое суток
- 167
- 1/72трое суток
- 180
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬ በትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25)፣ 2024 ዓ. እ.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ። ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሜዳልያ (Medal of St. Ephrem the Syrian) የተባለውን በክብር አበርክታለታለች። እነዚያን ወርቅ የሆኑ አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚወጉ የማር ኤፍሬምን ድርሳናት ከውጭ (በሃይማኖት) ሆኖ መተርጎሙ ሁሌ ያሳዝነኝ ነበር። ታምሞ ግን የሚድንበትን መድኃኒት ተሸክሞ እንደሚቸገር ምስኪን ሰው አድርጌም አስበው ነበር። ድርሳናቱ መቼ ነው ወደሚድንበት መርከብ እየመሩ የሚያስገቡት ብዬ ብዙ ጊዜ እጠይቅ ነበር። ያለፈው ቅዳሜ ግን ይህን ኀዘን የሚሽር የምሥራች ሰማሁ። ለካስ ቅዱሱ የቀጠረለት ቀን ነበር?! ይኸው የኤፍሬም ቀለም የበላውን (ያቃጠለውን) ምሁር ከኦርቶዶክሳዊው ካህን ስር በትሕትና በርከክ ብሎ አየሁት። ይህ መመለስ የቅዱሱ ምልጃ እና በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ያለቀሱ የብዙ የዋሃን ምእመናን እንባ ውጤት ነው። የአበው ድርሳን አሁንም በሥራ ላይ ነው!!! ዲያቆን አቤል ካሣሁካሣሁን
"ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሐሳብህ ላይ ሐሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።" ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!' መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡ 'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው። (ዲያቆን አቤል ካሳሁን)
без подписи
#ቅድስት_ሥላሴ (#ሐምሌ_7) ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! ( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ፔጅ)
"በማዕበል መሀል እንዳለች ታንኳ ልብህ በጭንቀት ስትናወጥ፣ ማዕበሉን ጸጥ ማድረግ ወደሚችለው ወደ ክርስቶስ ፊት ቅረብ። ጭንቀትህ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ግን ከዚያ ይበልጣል። እርሱ ስለ አንተ የሚያስብ አባት ነውና ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ አትጨነቅ፤ የዛሬን ቀን የሰጠህ አምላክ የነገውንም ማዕበል በጥበቡ ያሳልፈዋል። ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው ሁሉንም ነገር በራሳችን አቅም ለመወጣት ስንሞክር ነው፤ ነገር ግን ሸክምህን በጸሎት ወደ እርሱ ስትጥለው፣ እርሱ በልብህ ውስጥ ሰላምን ያሳድራል። ቅዱሳን ሐዋርያት በዓለም ሳሉ ብዙ መከራና ጭንቀት ገጥሟቸዋል፤ ነገር ግን ልባቸው አልፈራም፤ ምክንያቱም ከእነርሱ ጋር ያለው ጌታ ከዓለም ሁሉ እንደሚበልጥ ያውቁ ነበርና። አንተም ዛሬ ሸክምህን ለእርሱ ስጥ፤ እርሱ ደግሞ ዕረፍትን ይሰጥሃል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
без подписи
በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡ ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡ በዚያም ዕለት በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡ በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!
ወዳጆቼ ሆይ! መከራን በመቀበላችን ክፉ ደረሰብን ብለን አንመረር፤ ነገር ግን ኃጢአትን በፈጸምን ወቅት መከራ እንደመጣብን እንቁጠር፡፡ ይህ ነው መራሩ መከራ፡፡ እኛ ግን በዚህም ምድር ኑሮአችንን በቅንጦት እያሳለፍን የሚመጣውን ዓለም ሕይወት ለመስበክ አንሻም፡፡ እንዳውም በሚመጣው ዓለም የምንኖረው እንዲህ ዓይነት ሕይወት እንደሆነ እናስተምራለን፡፡ ሕሊናችን እንዴት በኃጢአት እንደተጨማለቀ እስቲ ቆም ብለን እናስብ ፡፡ ይህ ከሌሎች ቅጣቶች ይልቅ እጅግ ከባዱ ቅጣት አይደለምን? መከራን መቀበል በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ ክፉ ነገር ኃጢአት መሥራት ነው - አዎን! እጅግ መራራው መከራ ኃጢአት መሥራት ነው! ኃጢአት ከመሥራታችን የተነሣ በወዲያኛው ዓለም የሚያገኘንስ ይቅርና በዚህም ዓለም የሚገኘን መከራ መራራ ነውና በእውነት ያለ ሐሰት መከራ የሚባለው ኃጢአት መሥራት ነው ብዬ እነግርሃለሁ፡፡ ስለዚህም እነዚህን ነገሮች መፈጸም አንድ ሰውን ኃጢአተኛ የሚያሰኙት ከሆነ መከራ አለበት ማለት ነው፡፡ መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይሆን ተሳዳቢው መሆኑን መረዳት ይቻለናል (ምክንያቱም ተሳዳቢው ኃጢአት እየሠራ ስለሆነ)፡፡ አንተ 'እርሱ ልጄን ሞኝ ብሎ ተሳድቦታል' ልትል ትችላለህ፤ ነገር ግን አንተ ለስድቡ አጸፌታውን በመመለስ በበደል እርሱን አትምሰለው፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ስለ መከራና ስለ እግዚአብሔር ጥበቃ" ባስተማረበት ድርሳኑ)
#ለወላጆች #ይነበብ "ልጅህን በሚገባ ካሳደግኸው አንተም ትከበራለህ፤ እርሱም ለራሱና ለቤተክርስቲያን ኩራት ይሆናል፤ እግዚአብሔርም በእናንተ ምክንያት ይከበራል። ልጅህን ችላ ካልኸው ግን አንተም ትዋረዳለህ፤ በእርሱ ጥፋት ምክንያት እግዚአብሔር ይሰደባል፤ ማኅበረሰቡም በክፉ ጠባዩ ይጎዳል። ልጆችህን ስታሳድግ ራስህን እንደ አንድ ታላቅ ቀራፂ ቁጠር። አንድ ቀራፂ ድንቅ ምስልን ለመፍጠር በድንጋዩ ላይ እንደሚተጋ፣ አንተም በልጅህ ነፍስ ላይ የክርስቶስን መልክ ለመሳል ትጋ። ከመጀመሪያው ጀምረህ ክፉ ሐሳቦች በልቡ ውስጥ ሥር እንዳይሰዱ፣ የማይረቡና ቆሻሻ ቃላትም ከአንደበቱ እንዳይወጡ በንቃት ጠብቀው። ለልጅህ ምድራዊ ሀብትን ለማከማቸት አትጨነቅ፤ ይልቁንም መንፈሳዊ ጥበብንና ትሕትናን እንዲያተርፍ አስተምረው። ለልጅህ እውነተኛውን ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባርን ካወረስከው፣ ይህ ከማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በላይ በምድርም በሰማይም ለዘላለም ይከተለዋል። አንተ በሕይወት እያለህም ሆነ ካለፍክ በኋላ ልጅህ በመልካም መንገድ ከሄደ፣ አንተም የክብሩ ተካፋይ ትሆናለህ። ልጅህን በሕፃንነቱ በሥርዓት ካላነፅኸው፣ ነፍሱ ከጠነከረች በኋላ ሥርዓት ለማስያዝ ብትሞክር ይከብድሃል። ለጋው ተክል ገና ሳይጠነክር እንደፈለጉት እንደሚታጠፍ ሁሉ፣ ሕፃንም በልጅነቱ ለበጎ ሥራ በቀላሉ ይታጠፋል። አንዴ ከደረቀና ከጠነከረ በኋላ ግን ለማጠፍ ብትሞክር ይሰበራል እንጂ አይታጠፍም። ስለዚህ የልጅህን ነፍስ ገና በለጋነቱ በእግዚአብሔር ቃል ቀጥቅጠህ አቅናው።" (ምንጭ፡- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ልጆች ክርስቲያናዊ አስተዳደግ ካስተማረው ትምህርት የተወሰደ)
ባለህ ተደሰት በዚህ ዓለም ላይ ትልቁ ፍልስፍና ፣ ትልቁ ጥበብ፣ ትልቁ እምነት “እንደ ፈቃድህ” ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደዚህ ዓለም መጥተናል፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ዓለም እንሄዳለን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ገዥ ነው። ፈቃድህ ይሁን ባንልም ፈቃዱ ይሆናል። ፈቃዱ ይሁን በማለት ግን ሕይወት ጥያቄ ሳይሆን መልስ እንድትሆን ያደርጋል። ትልቅ ፍልስፍና ራስን መጣል አይደለም፣ ራስን መጣል ስንፍና ነው። ፈላስፎች ከምድር ጀምረው በምድር ይጨርሳሉ። ያለ ክርስቶስም ለዚህ ዓለም ስለሚሞቱ ትንሣኤ የላቸውም። ዓለም ከንቱ ናት ቢሉም ብርቱ በሆነው በክርስቶስ ግን አልቀየሩአትም። ትልቅ ፍልስፍና የሕይወቴን መግቢያና መውጫ ለያዘው እግዚአብሔር መንገድ መልቀቅ ነው። ያለ ፈቃዴ መጥቼ ያለ ፈቃዴ በምሞትበት ዓለም ላይ ፈቃድህ ይሁን ማለት ምቹ ትራስ እንጂ የድንጋይ መደገፊያ አይደለም። ትልቅ ጥበብም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅና ማክበር ነው። ጥበብ እውቀትን የምንኖርበት ተግባራዊነት፣ እሾሁን ሳይሆን ጽጌረዳውን የምናይበት መነጽር ነው። “የማይጋፉትን ግንብ ዞረው ያልፉታል” እንዲሉ የማንጋፋውን ፈቃድ መቀበል ከመጋጨት ያድናል። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ ቀጥሎ ከሰው ጋር ሳይሆን ከራሱ ጋር ይጋጫል። ከራሱ ጋር የተጋጨም ከሰው ጋር ሰላም የለውም። ትልቁ እምነትም ተአምራት ማድረግ ሳይሆን “ፈቃድህ ይሁን” ብሎ ማረፍ ነው። ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተሰጠን ነገር እንደሌለ ያለ ፈቃዱም የሚወሰድብን ነገር የለም። ይህች ዓለም ጉድለትዋ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን አዳም በስደት ከመጣባት ጊዜ አንሥቶ ነው። ለምለም እንድታበቅል የተፈጠረችው እሾህ አሜኬላ ሲበቅልባት፣ እየደሙና እያደሙ መኖር ሲበዛባት፣ አንዱ ላንዱ ዕረፍት መሆን ትቶ ሐፍረት ሲሆንባት ዓለም ከንቱ ነው እንላለን። ዛሬ የጀመረ የመሰለን ክስተትም ኃጢአትም የለም። የሚሆነው ሲሆን የነበረ ነው። “ደንቆሮ የሰማ ቀን ያብዳል” እንዲሉ አላዋቂ ዛሬ ሲሰማ ያ ነገር ዛሬ የጀመረ ይመስለዋል። ልቅሶ ላልሰማው ሰው ሁልጊዜ አዲስ ነው። ሰውዬው ሚስቱ በሞተች ባመቱ የሰማ ሰው መጥቶ ሲያለቅስ “እኔ ረስቻታለሁ አንተ እስካሁን ታስባታለህ” አለ ይባላል። ፍላጎታችንን በውል መረዳት በማንችልበት ዓለም ላይ ነን። ትላንት የምንፈልገውና ዛሬ የምንፈልገው እርስ በርሱ የሚቃረን ነው። በምኞት ስንሰጥ ኖረን ስናገኝ ስስታም ነን። ሁሉም ነገር ቢሟላ ዓለም ዓለም መሆንዋ ይቀር ነበር። “ብልህ ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል” እንዲሉ የመጣውን መቀበል ያልመጣውን ለመጠበቅ ኃይል ነው። ብዙ ሰው ከፍላጎቱ ውጭ የተማረ፣ የሚሠራ ፣ የሚኖር ሊሆን ይችላል። የሚወደውን ነገር ያገኘ ጥቂት ነው። ዕለት ዕለት የምንሸከመው መስቀል የማንወደውን ነገር መታገሥ ነው። ደስታን ማሳደድ በበዛበት በዛሬው ዘመን፣ ደስታ ላግኝ እንጂ በየትም በኩል ይምጣ በሚባልበት በእኛ ዓለም፣ በቆሻሻ ውኃም ቢሆን እሳትን ማጥፋት ይቻላል ተብሎ ከእውነት ስሜት በሚከበርበት ምድር የሚወዱትን ማጣት ብርቱ ነገር ነው። በዚህ ምድር ላይ የምንኖረው ግን የምንወደውን ስላገኘን ብቻ ሳይሆን በማንወደው ነገር ውስጥም ትዕግሥትን ለመለማመድ ነው። እንደ እኛ አሳብ በዚህ አገር፣ በዚህ ኑሮ ውስጥ አልነበርንም። ከመረጥነው የተመረጠልን ይሻላልና ደስ ሊለን ይገባል። የትም ቢሄዱ ሰማይና አፈር አንድ ነው። የትም ቢሄዱ ምግብ የሚባል ነገር አናገኘም፣ የምግብ ልዋጭ እንጂ እግዚአብሔር ብቻ እንግዳ ደስታ ነው። የምንወደው ወዳጃችን፣ የመከራችን ጓድ ዛሬ በቅርበትም በሕይወትም ላይኖር ይችላል። ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ይሻላልና ያገኘነውን መውደድ ያስፈልጋል። ሰው የሚኖረው ወዳጁ ያለበት ሳይሆን እንጀራው ያለበት ነው። እየተዋደድን ከብዙ ወዳጆቻችን ጋር በእንጀራና በሞት ምክንያት ተለያይተናል። ዛሬ ያሉት ወዳጆቻችን እንደ ቀድሞዎቹ ላይሆኑልን ይችላሉ። ፍቅር እየቀነሰ ባለበት ዘመን ባለመጥፋቱ ማመስገን ይገባናል። ከመልካምና ከክፉ ማነጻጸር በድሎት ዘመን ነው። በክፉ ዘመን ከክፉ የተሻለው ክፉ ይመረጣል። የምንወደውን ትምህርት እየተማርን ላይሆን ይችላል። ሰው ግን የሚኖረው በትምህርቱ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚሰጠው ዕድል ነውና መከፋትና ማዘን አይገባም። የትምህርት አንካሳ የለውምና ሁሉን መማር መልካም ነው። በምንወደው ሥራ ላይ ላንሆን እንችላለን፣ የምንወደው ጋ ለመድረስ ያገኘነውን መውደድ መሰላል ነው። የምንወደውን ማግኘት አለመቻላችን የሚያናድድ ሳይሆን ሰው መሆናችንን የሚያስረግጥ ነው። ሰው ማለት አቅሙ የተወሰነ ፍጡር ነውና። እኛ የምንወደው ባይገኝም እግዚአብሔር ይሁን ያለው ግን አልቀረም። በገጠመን ዕድል ሳይሆን በመረጥነው ክፉ እንጠየቃለን። እነዚያ ነገሮች ባይሆኑ መልካም ነበር። ፈቃዳችን ሳይሆን በሆኑት ነገሮች ግን ጸጸት ሊሰማን አይገባም። ከንቱ ጸጸት ተመጻቂነት ነውና። የዛሬ አለመቻል የነገ መቻል ነው። አለመቻልን እንደ መቻል ስንቀበለው የምንችልበት ቀን ይመጣል። ትንሣኤ ያለው ትንሣኤ ውስጥ ሳይሆን ውድቀት ውስጥ ነው። በጠለቀችው ፀሐይ ሳይሆን በወጡት ጨረቃና በፈኩት ከዋክብት አመስግን። ጨለማ ባይመጣ ከዋክብት አይታዩም ነበር ፣ ክፉ ቀኖችም ሰዎችን ያሳውቁሃል። በእጃችን ያለው ትንሽ ነገር፣ የማንወደው ቢሆንም ደስ ይበለን። የምንወደው እየቀረበ ይመጣል። ምስጋና ጨለማን ብርሃን፣ መንፈሳዊ ደስታም ጉብኝትን ያመጣል። ባንወደውም ወደ ሞት የምንጓዝ ነንና የምወደው ቀረብኝ ብለን መከፋት አይገባንም። የምንወደውን ብናገኝም ሞት አይቀርም። በሥላሴ ማመን ግን ከሲኦል ሞት ያድናል። የምትወዱትን ስላላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
የቀጠለ.... "እንግዲህ ሚስትህ ውበት ቢጎድላት እንኳ አትናቃት። ስማኝ፤ ከሰውነቱ ክፍል አንዱ ቢታመም አካሉን የሚጥል ማነው? ማንም! ይልቁንም ያንን የታመመውን የአካል ክፍሉን ይበልጥ ይንከባከበዋል እንጂ። ሚስትህም አካልህ ናትና ድክመት ቢኖርባት በፍቅር አክማት። ባል ሆይ! ሚስትህን ስትመክራት በታላቅ ርኅራኄ ይሁን። አትጩህባት፤ ይልቁንም በፍቅር ቃላት አቅርባት። 'ውዴ ሆይ! እኔና አንቺ አንድ አካል ነን፤ ሕይወታችንም አንዲት ናት። አንቺን ማስከፋት ራሴን እንደ መጉዳት ነው' በላት። እንዲህ ያለ ቃል ከብረት ይልቅ የጸናን ልብ ያቀልጣል። ሚስትም ባሏን ስታከብር 'እንደ ባሪያ' ሳይሆን 'እንደ አካል' ይሁን። አካል ለራስ እንደሚታዘዝ፣ አንቺም ለባልሽ ታዘዢ። ነገር ግን ባል ሆይ! ሚስትህ እንድትታዘዝልህ ከፈለግህ፣ መጀመሪያ አንተ ራስህን ለእርሷ አሳልፈህ ስጥ። ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የወደዳት ገና ጠላት ሳለች ነው፤ አንተም ሚስትህ ብታስቀይምህ እንኳ በፍቅር መልሳት። በቤታችሁ ውስጥ ግብዣ ስታደርጉ ምስኪኖችንና ድሆችን ጥሩ። ክርስቶስ በድሆች አምሳያ ወደ ቤታችሁ ይገባል። በሰርጋችሁም ሆነ በቤታችሁ ግብዣ ላይ ዘፋኞችንና ተላላዎችን አታስገቡ። ይልቁንም መንፈሳዊ መዝሙር ይዘመር። መጽሐፍ ቅዱስን አብራችሁ አንብቡ፤ ባል ያነበበውን ለሚስቱ ያብራራላት። ልጆቻችሁን ስታሳድጉ በንብረትና በሀብት ላይ አታተኩሩ። ይልቁንም ነፍሳቸውን በምግባር እነጹ። ለልጅህ የምትተወው ትልቁ ርስት እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እንዲህ ስታደርጉ ቤታችሁ የምድር መንግሥተ ሰማያት ይሆናል። ሰይጣን ሰላም ባለበት ቤት መቆም አይችልም። እርስ በእርሳችሁ የምትዋደዱ ከሆነ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ይኖራል፤ እርሱ ባለበት ደግሞ ምንም ዓይነት ክፋት አይደርስባችሁም። ባል ሆይ! ከሚስትህ ውጪ ያለ ውበት ሁሉ ላንተ የሞተ ይሁን። በሌላ ሴት ላይ ዓይንህን ስታሳርፍ የገዛ አካልህን እየቆረጥክ እንደሆነ እወቅ። በልብህም እንዲህ በል፦ 'ከሚስቴ በላይ የምትሆን፣ ከእርሷም የምትበልጥ ማንም የለችም።' ታማኝነት ለትዳር መሠረት ነው፤ መሠረቱ ሲናጋ ቤቱ መፍረሱ አይቀሬ ነው። አንቺም ሚስት ሆይ! ለባልሽ ያለሽ ታማኝነት በሥጋ ብቻ ሳይሆን በሐሳብም ጭምር ይሁን። ባልሽን ከሌሎች ጋር በማወዳደር አታቃልዪው፤ ይልቁንም ላንቺ የተሰጠሽን የጸጋ ስጦታ አድርገሽ ተቀበዪው። በመካከላችሁ ስለሚደረግ ጸሎትም ስሙ፤ ባልና ሚስት አብረው ሲጸልዩ ጸሎታቸው ኃይል አለው። አብራችሁ ተንበርከኩ፣ አብራችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ። በጸሎታችሁ ጊዜ፦ 'ጌታ ሆይ! እርስ በእርሳችን እንድንዋደድና እስከ መጨረሻው በአንድነት እንድንጸና እርዳን' ብላችሁ ለምኑ። ጸሎት ባለበት ቤት ቁጣ የለም፤ ጸሎት ባለበት ቤት ዝሙትና ክህደት ቦታ የላቸውም። ባል ሆይ! ሚስትህን በምታይበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠህን ረዳት እንደሆነች አስብ። እርስ በእርሳችሁ የምትረዳዱት ለምድራዊ ኑሮ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ሕይወት ጭምር ነው። አንዱ ሲደክም ሌላው ያበርታው፤ አንዱ ሲሳሳት ሌላው በገርነት ይመልሰው። በመጨረሻም የምመክራችሁ ይህ ነው፦ በምድር ላይ ስትኖሩ እንደ እንግዶች መሆናችሁን አትርሱ። እውነተኛው ቤታችሁ በሰማይ ነው። እዚህ በፍቅርና በአንድነት ከኖራችሁ፣ ነገ በክርስቶስ ፊት በታላቅ ደስታ ትቆማላችሁ። ያን ጊዜ ሞት የማይለየው፣ ድካም የማይሰማው የዘላለም አንድነት ይኖራችኋል። እግዚአብሔር ቤታችሁን በሰላም ይባርክ፤ ጸጋውና በረከቱም ከሁላችሁ ጋር ይሁን።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የኤፌሶን ምዕራፍ ፭ ትርጓሜ ድርሳን 20)
#አባታችን_ሆይ_እንደፈቃድህ_ይሁን ብዙ ሰው "ያሰብኩት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ ያም ብቻ አይደለም "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን የሚያማርርም አለ። "እርሱ ይሰጠኛል" ሳይሆን "እኔ አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ ላይ የነበረውን ነገር እንደነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ወዳጄ መጀመሪያ ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸውና? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይክና? ባላማከርከው ነገር ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ? ምናልባት በተለያዩ ጉዳዬች በሥራ ፣ በትምህርት ፣ በህመም ምክንያት በተቻኮልክበትና ጊዜ ባጣህበት ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል። ስለዚህ እንደ ፈቃድህ ይሁን በለው።
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!! 𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!! 𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0
ጾሙስ አበቃ.....? (#በአባ_ገብረ_ኪዳን) ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል! አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ? የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ! ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ! የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!! 𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!! 𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!! 𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0 https://t.me/addlist/kPdI_k-RelVkMWM0
#ምጽዋት "ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈጣሪ ለመቅረብ እንደ ምጽዋት ክሂል የሚሰጥ የለም። ከሥራም ወገን ወድዶ ሰጥቶ እንደመቸገር በልቡና ኅድዓት (ፀጥታ ፣ ዕረፍት ፣ ሠላም) የሚያደርግ የለም። ሰጥተኽ መጽውተኽ አጥተኽ 'አላዋቂ' ቢሉኽ ይሻልኻል። ጨብጠኽ ይዘኽ አስተዳደር ዐዋቂ ከሚሉኽ።. . . ኅብስቱን ከውሃ ጣለው ብሎ ተናግሯልና። ከውሃ የጣሉት እንዳይመለስ ፣ 'ይ 'ሰጠኛል' ብለኽ አትስጥ ሲል ነው። አንድም ኀብስቱን ከእግዚአብሔር ፊት አኑረው ሲል ነው። በፍጻሜ ዘመንኽ ዋጋኽን ታገኛለኽ። ባለጸጋውን ለይተኽ ለድኻ አትስጥ። 'ይኽ ይገባዋል ይኽ አይገባውም' አትበል። አላ ኩሉ ሰብእ ይኩኑ ዕሩያነ በኅቤከ -በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለኽ መጽውት እንጂ! አስተካክለኽ በመስጠትኽ ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለኽ። ምንም የበቁ ባይኾኑ ነፍስ በመብል በመጠጥ ምክንያት ወደ ክቡር እግዚአብሔር ትሳባለችና! በምጽዋት ጊዜ 'ይኽ አይሁዲዊ ነው። ይኽ ከሀዲ ነው' አትበል። 'ይኽ ነፍሰ ገዳይ ነው' አትበል። ይልቁንስ ብታስታውለው ወንድምኽ ነው እንጂ። አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ።ከበጎው ነገር ወገን ለሰው ያደረግኽ እንደኾነ መክፈልን አትውደድ።. . . መጽውተኽ ብትቸገር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ቸርነት ከትካዝ ሥጋዊ ትድናለኽ! ከኹሉ በላይ ትኾናለኽ! ሰው ኹሉ ለገንዘቡ ሲገዛ እሱ ለእግዚአብሔር ይገዛልና። . . . 'በዝናም ያበቀለው በፀሓይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው' ብለኽ ምጽዋትኽን በትሕትና መጽውት። ጻድቃን በሚከብሩበት ጊዜ ይቅርታን ታገኛለኽ" (ምንጭ፦ ከመጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ) አንቀጽ ፩ ፣ ምዕ.፲፪፣ ገጽ ፳፩ - ፳፫)